Thursday, April 30, 2015

ኢትዮጵያ በታሠሩ ጋዜጠኞች ብዛት በአፍሪካ አንደኛ ነች!!!


Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
ኢትዮጵያ እሥር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን፤ ቪየትናም ደግሞ የኢንተርኔት ፀሐፊዋን ወይም ብሎገሯን ታ ፎንግ ታንን እንዲለቅቁ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ናቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህንን የመንግሥታቸውን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በዚህ ሣምንት እያወጣቸው ባሉ ተከታታይ የፕሬስ መግለጫዎች በዓለም ዙሪያ በየእሥር ቤቱ ያሉ ጋዜጠኞችን በየቀኑ እያነሣ ይገኛል፡፡
በዚህ “FREE THE PRESS” ወይም “ፕሬስን ነፃ አውጡ” በሚለው ዘመቻው የዛሬው የመሥሪያ ቤቱ መግለጫ ካተኮረባቸው ሁለት ጋዜጠኞች አንዷና ቀዳሚዋ የቀድሞ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ መምህር ኢትዮጵያዊቱ ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ነች፡፡
በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት በተመሠረተባት ክሥ ጥር 10/2004 ዓ.ም ተፈርዶባት እስከዛሬ ወኅኒ ቤት እንደምትገኝ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ጠቁመዋል፡፡ “… ርዕዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ በተመሠረቱባቸው ክሦች ምክንያት ከታሠሩ 18 ጋዜጠኞች አንዷ ስትሆን ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያ በአህጉሩ ብዙ ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚዋ እንድትሆን አድርጓታል …” ብለዋል፡፡
ርዕዮት የመንግሥቱን ፖሊሲዎች የሚተቹ ፅሁፎችን በጋዜጣ በማውጣቷ ምክንያት በሰኔ 2003 ዓ.ም ተይዛ የሽብር ፈጠራ ክሥ ከተመሠረተባት በኋላ የ14 ዓመት እሥራት ተፈርዶባት እንደነበረ ያስታወሱት ራትካ የእሥራት ዘመኗ ወደ አምስት ዓመት ዝቅ እንዲል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በነሐሴ 2004 ዓ.ም መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ ክሡ ሙሉ በሙሉ እንዲሠረዝላት በተከታታይ ያቀረበቻቸው የይግባኝ አቤቱታዎች ውድቅ መደረጋቸውንም ራትኮ አመልክተዋል፡፡
“… ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት መብቷን ተግባራዊ በማድረጓ ብቻ ታሥራ የምትገኘውን ርዕዮትን እንዲፈታ ለመንግሥቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን – ያሉት ራትኮ – መንግሥቱ ፀረ-ሽብር አዋጁን ሃሣብን በነፃነት የመለዋወጥን ተግባር ለመጠምዘዝ ጉዳይ ከመጠቀም እንዲቆጠብም እናሳስባለን …” ብለዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጄፍ ራትኮ በመቀጠልም በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር የ2013 ዓ.ም ጀብዱ ፈፃሚ ሴቶች ዓለምአቀፍ ሽልማት ያሸነፈችውና የቪየትናምን መንግሥትና ኮምዩኒስት ፓርቲውን የሚተቹ ፅሁፎችን ኢንተርኔት ላይ በማውጣቷ የአሥር ዓመት እሥራት ተፈርዶባት ወኅኒ የምትገኘው ታ ፎንግ ታንን የቪየትናም መንግሥት በአፋጣኝ እንዲለቅቅ መንግሥታቸው እንደሚያሳስብ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ:- ቪኦኤ አምሀሪክ

ኢትዮጵያ በየአመቱ በርካታ ወጣቶች ጥለዋት ከሚሰደዱ ሀገሮች ዋነኛዋ እንደሆነች የታወቀ ነው

ለወጣቶቹ መሰደድ ደግሞ ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ አልጄዚራ በድረ-ገጹ ባወጣው ፅሁፍ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በማለፍ ለኢትዮጵያውያኑ መሰደድ በዋነኛነት የሚነሱ ምክንያቶችን ዘርዝሯል
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በኢኮኖሚ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገሮች መካከልም ስሟ የሚጠራ ቢሆንም ዜጎቿ ግን መሰደድን አላቆሙም በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ በሚመርጡት ህገወጥ ስደት ብዙዎች እየሞቱ ይገኛሉ
በከተሞች አካባቢ አጥጋቢ የስራ እድል አለመኖሩ, በአብዛኛው የሚሰሩ ስራዎች የዜጎችን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የሚችል አለመሆኑ, በየጊዜው የኑሮ ውድነት እየጨመረ መምጣቱ እና ሌሎች ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ
አልጄዚራ ባወጣው ፅሁፍ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በፖለቲካ ሁኔታ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው አነስተኛ የሚባል አይደለም ለዚህም እንደማጣቀሻ ጥሩ የስራ እድል የሚያገኙ ዜጎች ከመንግስት የፖለቲካ ሁኔታ ጋር ቅርበት ያላቸው መሆናቸው ይነገራል
ሁላችንም እንደምናውዘቀው በዜጎች ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ በግልፅ የሚታይ እውነታ ነው ነገር ግን ለሚደርሰው ጥፋት በዋነኛነት ተጠያቂ ሊሆን የሚችለውን አካል ለእያንዳንዳችን ግንዛቤ እንተወውና በሁላችንም ዘንድ ምን መፍትሄ ማምጣት ይቻላል?
ማን ምን ቢያደርግ ይሻላል ትላላችሁ? በኩራት ታሪክ እየጠቀስን ብቻ የሀገርን ገፅታ መለወጥ እንችላለን?
የኛ ሀገራዊነት ስሜት ስፖርታዊና ስፖርታዊ ባልሆኑ ውድድሮች ላይ ብቻ የሚንፀባረቅ አይመስላችሁም?
የእናንተ ሀሳብ ምንድነው?

No comments:

Post a Comment