የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች፣ ካድሬዎችና ፖሊሶች ሰማያዊ ፓርቲ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ እንደከለከሉ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሲቀሰቅስ ቆይቶ ወደ አዋሳ ያቀናውን የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዋሳ ሲደርስ እንዳይቀሰቅስ እንደተከለከለ የገለጹት አቶ ስለሽ ደህንነቶች የመኪናውን ባለቤት በማስፈራራት በእጅ አዙር ቅስቀሳችንን በማስቆም ከተማው እንድንወጣ ጫና እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ‹‹አዋሳ ውስጥ መቀስቀስ አትችሉም፡፡ ከተማውን ለቃችሁ ውጡ፡፡ ለቃችሁ ካልወጣችሁ መኪናውን ለ10 ቀን እናስረዋለን፡፡ 10 ሺህ ብርም እንቀጣችኋለን›› እያሉ የመኪናውን ባለቤትና ቀስቃሾቹን እያዋከቡ እንደሚገኙ የቅስቀሳው ተሳታፊዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ደህንነቶች፣ ፖሊሶችና ካድሬዎች እያደረጉት ባለው ወከባም የመኪና ላይ ቅስቀሳው ለጊዜው እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment