Thursday, April 30, 2015

ምርጥ የህዝብ ልጅ ይሄ ነው ለህዝብ መስራት ማለት ፤ ለሚወደሰት ሲከፋ ከጎኑ መቆም ትልቅ ዋጋ ነው!!!! ጌታ ያክ...

በጣም-አስደንጋጭ-

ETHIOPIAN Revolution : የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው እስማኤል ዳውድ መታሰሩ ተሰማ

ETHIOPIAN Revolution : የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው እስማኤል ዳውድ መታሰሩ ተሰማ: የአንድነት ፓርቲ አባል እና የሚሊየኖች ድምፅ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ ትላንትና ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ለእስር መዳረጉን ወላጅ እናቱ አስታወ ቁ፡፡ እስማኤል፣ ከ...

የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው እስማኤል ዳውድ መታሰሩ ተሰማ


የአንድነት ፓርቲ አባል እና የሚሊየኖች ድምፅ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ ትላንትና ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ለእስር መዳረጉን ወላጅ እናቱ አስታወቁ፡፡
እስማኤል፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል የለበሱ ሰዎች ቤቱ በመምጣት ‹‹ቃል ሰጥተህ ትመለሰላህ›› በማለት ከቤቱ ወደ አራዳ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱት በኋላ ‹‹ቃሉን ሰጥቶም ቢሆን መለቀቅም እንደማይችል አስታውቀውት ወደ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወሩን›› ወላጅ እናቱ ገልፀዋል። በትላንትናው እለትም ከአራዳ ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ተደውሎላቸው ችሎት መድሃኒያለም አካባቢ ወደሚገኘው ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወሩን እንደተገለፀላቸው አስረድተዋል።
እስማኤል፣ በዛሬው እለት ፒያሳ በሚገኘው አራዳ ፍርድ ቤት ከረፋዱ 5፡30 የቀረበ ሲሆን በችሎቱ የተሰየመችው ዳኛ ‹‹በአራት ቀን ውስጥ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለክስ የሚያበቃ በቂ ማስረጃ ካለው ፍርድቤት እንዲያቀርበው አለበለዚያ ግን በነጻ እንዲያሰናብተው›› ትእዛዝ አስተላልፋለች፡፡ ወላጅ እናቱን በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገ ላነሳሁላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹ከረቡዕ ሰልፋ ላይ በመገኘቱ ምክንያት እንደሆነና ከእሱም ሌላ ሁለት ጓደኞቹ ለእስር መዳረጋቸውን›› ገልፀዋል፡፡
ፖሊስ በረቡዕ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ተቃውሟቸውን በመንግስት ላይ የገለፁ ወጣቶችን ከቤታቸው እያደነ በማሰር ላይ እንደሚገኝ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ መንግስት በበኩሉ በረቡዕ ሰላማዊ ሰልፋ ላይ ለተነሳው ግጭት ሰማያዊ ፓርቲና ህገ-ወጥ ሲል የሰየመውንና በቀድሞ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ ይመራ የነበረውን የአንድነት ፓርቲ አባላትነትን ተጠያቂ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ስድስት አባሎቹ እንደታሰሩ ያስታወቀ ሲሆን ‹‹ህገ-ወጡ›› አንድነት በመባል በመንግስት የሚጠራውና በቀድሞ የፓርቲው ፕሬዝዳንት በላይ ፍቃዱ ይመራ ከነበረው አንድነት ውስጥ ለእስር የተዳረጉት ቁጥራቸው ሶስት ደርሷል፡፡ አቶ እስማኤል ዳውድ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና የፓርቂው የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ዳዊት አስራደ ከረቡዕ ሰልፋ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ እስማኤል ዳውድ፣ በትእግስቱ አወሉ በሚመራውና በበዙዎች ዘንድ ህገ-ወጡ አንድነት በመባል በሚታወቀው የፓርቲው አባላት አማካኝነት ስም የማጥፋት ክስ ተመስርቶበት ለሀያ ቀናት ታስሮ በዋስ መለቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በታሠሩ ጋዜጠኞች ብዛት በአፍሪካ አንደኛ ነች!!!


Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
ኢትዮጵያ እሥር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን፤ ቪየትናም ደግሞ የኢንተርኔት ፀሐፊዋን ወይም ብሎገሯን ታ ፎንግ ታንን እንዲለቅቁ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ናቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህንን የመንግሥታቸውን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በዚህ ሣምንት እያወጣቸው ባሉ ተከታታይ የፕሬስ መግለጫዎች በዓለም ዙሪያ በየእሥር ቤቱ ያሉ ጋዜጠኞችን በየቀኑ እያነሣ ይገኛል፡፡
በዚህ “FREE THE PRESS” ወይም “ፕሬስን ነፃ አውጡ” በሚለው ዘመቻው የዛሬው የመሥሪያ ቤቱ መግለጫ ካተኮረባቸው ሁለት ጋዜጠኞች አንዷና ቀዳሚዋ የቀድሞ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ መምህር ኢትዮጵያዊቱ ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ነች፡፡
በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት በተመሠረተባት ክሥ ጥር 10/2004 ዓ.ም ተፈርዶባት እስከዛሬ ወኅኒ ቤት እንደምትገኝ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ጠቁመዋል፡፡ “… ርዕዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ በተመሠረቱባቸው ክሦች ምክንያት ከታሠሩ 18 ጋዜጠኞች አንዷ ስትሆን ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያ በአህጉሩ ብዙ ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚዋ እንድትሆን አድርጓታል …” ብለዋል፡፡
ርዕዮት የመንግሥቱን ፖሊሲዎች የሚተቹ ፅሁፎችን በጋዜጣ በማውጣቷ ምክንያት በሰኔ 2003 ዓ.ም ተይዛ የሽብር ፈጠራ ክሥ ከተመሠረተባት በኋላ የ14 ዓመት እሥራት ተፈርዶባት እንደነበረ ያስታወሱት ራትካ የእሥራት ዘመኗ ወደ አምስት ዓመት ዝቅ እንዲል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በነሐሴ 2004 ዓ.ም መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ ክሡ ሙሉ በሙሉ እንዲሠረዝላት በተከታታይ ያቀረበቻቸው የይግባኝ አቤቱታዎች ውድቅ መደረጋቸውንም ራትኮ አመልክተዋል፡፡
“… ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት መብቷን ተግባራዊ በማድረጓ ብቻ ታሥራ የምትገኘውን ርዕዮትን እንዲፈታ ለመንግሥቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን – ያሉት ራትኮ – መንግሥቱ ፀረ-ሽብር አዋጁን ሃሣብን በነፃነት የመለዋወጥን ተግባር ለመጠምዘዝ ጉዳይ ከመጠቀም እንዲቆጠብም እናሳስባለን …” ብለዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጄፍ ራትኮ በመቀጠልም በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር የ2013 ዓ.ም ጀብዱ ፈፃሚ ሴቶች ዓለምአቀፍ ሽልማት ያሸነፈችውና የቪየትናምን መንግሥትና ኮምዩኒስት ፓርቲውን የሚተቹ ፅሁፎችን ኢንተርኔት ላይ በማውጣቷ የአሥር ዓመት እሥራት ተፈርዶባት ወኅኒ የምትገኘው ታ ፎንግ ታንን የቪየትናም መንግሥት በአፋጣኝ እንዲለቅቅ መንግሥታቸው እንደሚያሳስብ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ:- ቪኦኤ አምሀሪክ

ኢትዮጵያ በየአመቱ በርካታ ወጣቶች ጥለዋት ከሚሰደዱ ሀገሮች ዋነኛዋ እንደሆነች የታወቀ ነው

ለወጣቶቹ መሰደድ ደግሞ ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ አልጄዚራ በድረ-ገጹ ባወጣው ፅሁፍ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በማለፍ ለኢትዮጵያውያኑ መሰደድ በዋነኛነት የሚነሱ ምክንያቶችን ዘርዝሯል
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በኢኮኖሚ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገሮች መካከልም ስሟ የሚጠራ ቢሆንም ዜጎቿ ግን መሰደድን አላቆሙም በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ በሚመርጡት ህገወጥ ስደት ብዙዎች እየሞቱ ይገኛሉ
በከተሞች አካባቢ አጥጋቢ የስራ እድል አለመኖሩ, በአብዛኛው የሚሰሩ ስራዎች የዜጎችን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የሚችል አለመሆኑ, በየጊዜው የኑሮ ውድነት እየጨመረ መምጣቱ እና ሌሎች ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ
አልጄዚራ ባወጣው ፅሁፍ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በፖለቲካ ሁኔታ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው አነስተኛ የሚባል አይደለም ለዚህም እንደማጣቀሻ ጥሩ የስራ እድል የሚያገኙ ዜጎች ከመንግስት የፖለቲካ ሁኔታ ጋር ቅርበት ያላቸው መሆናቸው ይነገራል
ሁላችንም እንደምናውዘቀው በዜጎች ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ በግልፅ የሚታይ እውነታ ነው ነገር ግን ለሚደርሰው ጥፋት በዋነኛነት ተጠያቂ ሊሆን የሚችለውን አካል ለእያንዳንዳችን ግንዛቤ እንተወውና በሁላችንም ዘንድ ምን መፍትሄ ማምጣት ይቻላል?
ማን ምን ቢያደርግ ይሻላል ትላላችሁ? በኩራት ታሪክ እየጠቀስን ብቻ የሀገርን ገፅታ መለወጥ እንችላለን?
የኛ ሀገራዊነት ስሜት ስፖርታዊና ስፖርታዊ ባልሆኑ ውድድሮች ላይ ብቻ የሚንፀባረቅ አይመስላችሁም?
የእናንተ ሀሳብ ምንድነው?

ኢትዮጵያ በታሠሩ ጋዜጠኞች ብዛት በአፍሪካ አንደኛ ነች!!!



Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
ኢትዮጵያ እሥር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን፤ ቪየትናም ደግሞ የኢንተርኔት ፀሐፊዋን ወይም ብሎገሯን ታ ፎንግ ታንን እንዲለቅቁ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ናቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህንን የመንግሥታቸውን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በዚህ ሣምንት እያወጣቸው ባሉ ተከታታይ የፕሬስ መግለጫዎች በዓለም ዙሪያ በየእሥር ቤቱ ያሉ ጋዜጠኞችን በየቀኑ እያነሣ ይገኛል፡፡
በዚህ “FREE THE PRESS” ወይም “ፕሬስን ነፃ አውጡ” በሚለው ዘመቻው የዛሬው የመሥሪያ ቤቱ መግለጫ ካተኮረባቸው ሁለት ጋዜጠኞች አንዷና ቀዳሚዋ የቀድሞ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ መምህር ኢትዮጵያዊቱ ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ነች፡፡
በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት በተመሠረተባት ክሥ ጥር 10/2004 ዓ.ም ተፈርዶባት እስከዛሬ ወኅኒ ቤት እንደምትገኝ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ጠቁመዋል፡፡ “… ርዕዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ በተመሠረቱባቸው ክሦች ምክንያት ከታሠሩ 18 ጋዜጠኞች አንዷ ስትሆን ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያ በአህጉሩ ብዙ ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚዋ እንድትሆን አድርጓታል …” ብለዋል፡፡
ርዕዮት የመንግሥቱን ፖሊሲዎች የሚተቹ ፅሁፎችን በጋዜጣ በማውጣቷ ምክንያት በሰኔ 2003 ዓ.ም ተይዛ የሽብር ፈጠራ ክሥ ከተመሠረተባት በኋላ የ14 ዓመት እሥራት ተፈርዶባት እንደነበረ ያስታወሱት ራትካ የእሥራት ዘመኗ ወደ አምስት ዓመት ዝቅ እንዲል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በነሐሴ 2004 ዓ.ም መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ ክሡ ሙሉ በሙሉ እንዲሠረዝላት በተከታታይ ያቀረበቻቸው የይግባኝ አቤቱታዎች ውድቅ መደረጋቸውንም ራትኮ አመልክተዋል፡፡
“… ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት መብቷን ተግባራዊ በማድረጓ ብቻ ታሥራ የምትገኘውን ርዕዮትን እንዲፈታ ለመንግሥቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን – ያሉት ራትኮ – መንግሥቱ ፀረ-ሽብር አዋጁን ሃሣብን በነፃነት የመለዋወጥን ተግባር ለመጠምዘዝ ጉዳይ ከመጠቀም እንዲቆጠብም እናሳስባለን …” ብለዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጄፍ ራትኮ በመቀጠልም በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር የ2013 ዓ.ም ጀብዱ ፈፃሚ ሴቶች ዓለምአቀፍ ሽልማት ያሸነፈችውና የቪየትናምን መንግሥትና ኮምዩኒስት ፓርቲውን የሚተቹ ፅሁፎችን ኢንተርኔት ላይ በማውጣቷ የአሥር ዓመት እሥራት ተፈርዶባት ወኅኒ የምትገኘው ታ ፎንግ ታንን የቪየትናም መንግሥት በአፋጣኝ እንዲለቅቅ መንግሥታቸው እንደሚያሳስብ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ:- ቪኦኤ አምሀሪክ

ኢትዮጵያ በየአመቱ በርካታ ወጣቶች ጥለዋት ከሚሰደዱ ሀገሮች ዋነኛዋ እንደሆነች የታወቀ ነው


ለወጣቶቹ መሰደድ ደግሞ ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ አልጄዚራ በድረ-ገጹ ባወጣው ፅሁፍ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በማለፍ ለኢትዮጵያውያኑ መሰደድ በዋነኛነት የሚነሱ ምክንያቶችን ዘርዝሯል
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በኢኮኖሚ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገሮች መካከልም ስሟ የሚጠራ ቢሆንም ዜጎቿ ግን መሰደድን አላቆሙም በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ በሚመርጡት ህገወጥ ስደት ብዙዎች እየሞቱ ይገኛሉ
በከተሞች አካባቢ አጥጋቢ የስራ እድል አለመኖሩ, በአብዛኛው የሚሰሩ ስራዎች የዜጎችን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የሚችል አለመሆኑ, በየጊዜው የኑሮ ውድነት እየጨመረ መምጣቱ እና ሌሎች ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ
አልጄዚራ ባወጣው ፅሁፍ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በፖለቲካ ሁኔታ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው አነስተኛ የሚባል አይደለም ለዚህም እንደማጣቀሻ ጥሩ የስራ እድል የሚያገኙ ዜጎች ከመንግስት የፖለቲካ ሁኔታ ጋር ቅርበት ያላቸው መሆናቸው ይነገራል
ሁላችንም እንደምናውዘቀው በዜጎች ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ በግልፅ የሚታይ እውነታ ነው ነገር ግን ለሚደርሰው ጥፋት በዋነኛነት ተጠያቂ ሊሆን የሚችለውን አካል ለእያንዳንዳችን ግንዛቤ እንተወውና በሁላችንም ዘንድ ምን መፍትሄ ማምጣት ይቻላል?
ማን ምን ቢያደርግ ይሻላል ትላላችሁ? በኩራት ታሪክ እየጠቀስን ብቻ የሀገርን ገፅታ መለወጥ እንችላለን?
የኛ ሀገራዊነት ስሜት ስፖርታዊና ስፖርታዊ ባልሆኑ ውድድሮች ላይ ብቻ የሚንፀባረቅ አይመስላችሁም?
የእናንተ ሀሳብ ምንድነው?

Wednesday, April 29, 2015

Ethiopian music 2015 Jacky Gosee HAQ

የወያኔ ደህንነቶች ሰማያዊ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ ከለከሉ


የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች፣ ካድሬዎችና ፖሊሶች ሰማያዊ ፓርቲ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ እንደከለከሉ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሲቀሰቅስ ቆይቶ ወደ አዋሳ ያቀናውን የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዋሳ ሲደርስ እንዳይቀሰቅስ እንደተከለከለ የገለጹት አቶ ስለሽ ደህንነቶች የመኪናውን ባለቤት በማስፈራራት በእጅ አዙር ቅስቀሳችንን በማስቆም ከተማው እንድንወጣ ጫና እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ‹‹አዋሳ ውስጥ መቀስቀስ አትችሉም፡፡ ከተማውን ለቃችሁ ውጡ፡፡ ለቃችሁ ካልወጣችሁ መኪናውን ለ10 ቀን እናስረዋለን፡፡ 10 ሺህ ብርም እንቀጣችኋለን›› እያሉ የመኪናውን ባለቤትና ቀስቃሾቹን እያዋከቡ እንደሚገኙ የቅስቀሳው ተሳታፊዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ደህንነቶች፣ ፖሊሶችና ካድሬዎች እያደረጉት ባለው ወከባም የመኪና ላይ ቅስቀሳው ለጊዜው እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ልብሴን እንዳወልቅ ከታዘዝኩ በኋላ ራቁቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፖርት እንድሰራ እገደድ ነበር›› ትላለች የዞን ዘጠኟ ማህሌት ፋንታሁን፡፡


ጋሻው መርሻ .
ፈቃዱ የተባለ በአሁኑ ሰዓት ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪ የነበረ ወጣት ማዕከላዊ በተባለ ማጎሪያ ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ራቁቱን እንዲቆም ይደረግ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ‹‹ወንድ መርማሪዎች ፊት ለፊት ራቁቴን ስቆም ሀፍረት እንደሚሰማኝ የተረዱት መርማሪዎች ይድነቅህ ብለው ሴት መርማሪዎች ፊት ከ3 ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እርቃኔን እንድቆም እገደድ ነበር›› ይላል ፈቃዱ በወቅቱ ስለነበረው ነገር ሲያስረዳ፡፡ እንደ ፈቃዱ ምስክርነት ከሆነ ሴት መርማርዎቹ ፈቃዱን ፊት ለፊታቸው አስቁመው ጌም ይጫዎታሉ፡፡ ይሳሳቃሉ፡፡ ‹‹እኔን ራቁቴን ከሶስት ሰዓት በላይ እስቁመው ደብድበው ይሸኙኛል›› ይላል የሕሊና እስረኛው ፈቃዱ፡፡
በተመሳሳይ ‹‹ልብሴን እንዳወልቅ ከታዘዝኩ በኋላ ራቁቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፖርት እንድሰራ እገደድ ነበር›› ትላለች የዞን ዘጠኟ ማህሌት ፋንታሁን፡፡ ኤዶም ካሳዬም ተመሳሳይ ቶርቸር እንደተፈጸመባት ትናገራለች፡፡ መቸም ይህን ያክል በደል በወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽሙ ሰዎች አንዳች ችግር ሳይኖርባቸው አይቀርም፡፡ ወንዶቹ ሴት አግብው ሴቶቹም ወንድ አግብተው ይኖራሉ፡፡ ወንድም ሆነ ሴት ልጆች አሏቸው፡፡ ታዲያ እንዴት ሴት ልጅ አቅፎ የሚያድር ገላ በሴት እህቶቻችን ላይ እንዲህ አይነት ብልግና ለመፈጸም ምን አስጨከናቸው? ወንድ ልጅ ደረት ላይ ተለጥፋ የምታድር ሴትስ ብትሆን እንዲህ አይነት ለአዕምሮ የሚከብድ ነገር ለማድረግ ጭካኔውን ከየት ተማረችው? ሀገራችንስ ወዴት እያመራች ነው? በእውነት እንደ ዜጋ ያሳዝናል፡፡ እንደ ሀገር ሲያስቡት ደግሞ ያሸማቅቃል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሴትን ልጅ እርቃኗን አስቁሞ ከመመርመር የወረደ ነገር ምን አለ፡፡ እንደ ሀገር ምን አይነት የሞራል ዝቅጠት ውስጥ እንደገባን አይነተኛ ማሳያ መስሎ ይሰማኛል፡፡
የተከበረውን የሰው ልጅ ገላ እርቃን እንዲሆን አድርጎ መደሰት ምንድን ነው ትርፉ? ቂም በቀልን ለልጅ ልጆቻችን ከማውረስ በቀር፡፡ እነዚህ ልጆች ለሀገራቸው ነግ ተጨንቀው፤ የመንግስት ዝርክርክ አሰራሮችን ለማስተካከል በልጅ አዕምሯቸው የመሰላቸውን ነገር ስለጻፉ፤ ስህተት ነው ብለው ያሰቡትን ነገር ስለተቹ ይህን ሁሉ ግፍ በአካላቸው ላይ መፈጸም ምን አመጣው፡፡
እኛ ውጭ ያለነው እስረኞችስ ብንሆን ይህን ነገር ለማቆም ምን አደረግን ብዬ ስጠይቅ ምንም የሚል መልስ አገኛለሁ፡፡ በቃ ቁመን ስንጠብቅ የእኛም ተራ ይደርስና እርቃናችን እንድንቆም ይደረጋል፡፡ ያኔ እንደ አዲስ ነገር ይወራል መልሶ በሳምንቱ ይረሳል፡፡ ይህ የክፋት አዙሪት እንዲቆም የበኩላችን አስተዋጽኦ ማድረግ የግድ ይኖርብናል፡፡ ያለ በለዚያ ግን አዙሪቱ እኛ ጋር መድረሱ አይቀርም፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ አካሄዱ


በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ ሲያካሂዱ መሰንበታቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣እንደምንጮቻችን መረጃ።- የብ.አ.ዴ.ን. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዝያ 6 እና 7 2007 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የአካባቢያችን ደህንንትና ሰላም ምን ይመስላል? የዚህ ክልል አለመረጋጋት ምክንያቱ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲከራከሩ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው። በተለይ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት በመንግስታችን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሊያደርግ ሰራዊቱን በሁመራና አካባቢው ላይ አስጠግቷል በሚል ፍርሃት የወለደው ስብሰባ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
እኒህ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው። መንግስት በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ሊወስድ ስለሆነ በክልላችን ስለድርጅቱ የሆነ መረጃ ያመጣ ሰው ለማበረታቻ የሚሆን ሽልማት ይሰጠዋል በማለት ህብረተሰቡን በማታለል ስራ ላይ ተጠምደው እንደሰነበቱ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣

Friday, April 24, 2015

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን ማራካሱን ቀጥሎበታል

ሳም ቮድ ሶን አንዳርጋቸው's photo.
ማምሻውን ፖሊሶችና ፌድራል ፖሊሶች ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ጉዳት የደረሰባቸው  ገለጹ
ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን በማርከስ ከዚህ ቀደም በገዳማት በመስጅዶች ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት በጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድረስ በመዝለቅ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውን በቦታው ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው  ገልጸዋል፡፡
በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከሚስቱ ጋር እንደነበር የገለጸው ወጣቱ ፖሊሶቹ ሴት ወንድ ሳይሉ ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑት ምእምናን ላይ ድብደባ እንደፈጸሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቤተክርስቲያኑ የነበሩትን አማኞች በከደበደቡ በሁላ በየክፍለ ከተማቸው በመለየት በመኪና ጭነው እንደወሰዷቸው በድጋሚ እንደደበደቧቸው ተናግረዋል;፡
በመጨረሻም ፎቶ አንስተው አሻራ ተቀብለው ከምሽቱ 5፤45 እንደለቀቋቸው  ገልጸዋል፡፡ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት አክብሪያለሁ እያለ የእምነት ተቋማትን ክብር ጭምር በመዳፈር የዚህ አይነት አስነዋሪ ድርጊት በመፈጸማቸው ማዘናቸውን ምእምናኑ ገልጸዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ


የተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።
ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።
የዘመኑ ጥቂት የህወሓት ቱጃሮች ፎቆችን እየገነቡ በነሱ መጥገብ እኛ እንድናገሳላቸው ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡ፣ መታረዙ፣ መደህየቱ እውነት ነው፤ ሆኖም ግን “ተራብኩ”፣ “ታረዝኩ”፣ “ደኸየሁ” ብሎ መናገር አይችልም። እውነት መናገር ያስቀጣል፣ ያስወነጅላል። በፍርደ ገምድል ችሎት እውነት መናገር “ሽብርተኛ” ያስብላል። እስር ቤቶችን የተሞሉት ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃናትና ለእኩልነት በቆሙ ሰዎች አይደለምን?
በአይ ሲስ ያሳረደን ማነው? መልሱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው። እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የደረሰብን ውርደት የትም ብንሄድ የምናመልጠው አልሆነም። በአገር ውስጥ የደረሰብንን ውርደት ለማምለጥ ስንሰደድ ውርደት ተከትሎን ይመጣል።
ወገኖቼ፤ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሊኖረን አይችልም። ዛሬ የመሸሻ ጊዜ አይደለም። አገራችንን ከወያኔ ነጥቀን፤ በአገራችን ኮርተን በሰላም መኖር እንሻለን። ይህ መብታችን ነው። አገራችን የኛ ነች። አገራችን የጥቂት ወያኔዎች መፈንጫ አይደለችም።
ወገኔ፤ ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም በአርበኖች ግንቦት 7 ስም የማደርግልህ ጥሪ አድምጠኝ። በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ልዩነት ሳታደርግ ዛሬ በአንድነት እንደተሳህ አንድነትህን እንደጠበቅህ ቀጥል። አንድነትህን ለመሸርሸር ወያኔ የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፤ ለወያኔ ዱለታ ጆሮህን አትስጥ። የወያኔ አገዛዝ እንዲያበቃ በአንድነት ተነስ። ዛሬ የጀመርከው ትግል እዳር ሳይደርስ እረፍት የለንም።
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር በመጣመር የአገር አድን ኃይል የመገንባት ሥራውን እያጠናቀቀ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት ሳንከፋፈል፤ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባካተተ ስብስብ ውስጥ አብረን ህወሓትን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የአንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ነው። የትግሉም የአገሪቷም ባለቤት አንተ ነህ። ስለሆነም ተነስ! “እንቢኝ” በል። ዘርፈ ብዙ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ወያኔን አዳክም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በትግልህ ፍሬ የአገርህ ባለቤት ሁን።
የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። የደረሰብንን ብሔራዊ ውርደት እያያችሁ፤ እሮሮዓችን እየሰማችሁ በሕዝብ ላይ መተኮስ በራሳችሁ ጭንቅላት ላይ መተኮስ ማለት መሆኑን ለደቂቃ እንኳን አትዘንጉ። ይልቁኑ ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የወጣትነት የፈጠራ ችሎቻችሁ መፈተኛው አሁን ነው። ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ መመሪያ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ። እያሰላችሁ፣ እያጠናችሁ፣ እያደባችሁ፣ ወያኔን ታገሉ።
የታፈረች፣ የተከበረችና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።
ብርሀኑ ነጋ
የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር
ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም
11150143_678342725645299_5875406239496253050_n

በስቶክሆልም የመድኃኒዓለም ቤ/ክ በሊቢያ ለተገደሉ ወገኖቻችን ጸሎት ምሕላ ተደረገ


Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. April 22, 2015)፡- ዛሬ ማምሻውን ከ12 ሰዓት (18፡00) ጀምሮ ለሁለት ሰዓታት በስቶክሆልም በደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በሊቢያ ለተገደሉት ወገኖቻችን በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የምስራቅ አፍሪካና የአውሮጳ ሊቀጳጳስ የተመራ ሥርዓተ ጸሎት ተደረገ። በርካቶች ሲያለቅሱ ነበር።
በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በግፍ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሞት ያስደነገጣቸው ከ300 በላይ ምዕመናን የተገኙ ሲሆን፣ የእስልምና እምነት እና የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተከታዮች በአንድነት ተሰባስበው ተገኝተዋል።
በስቶክሆልም መድኃኒዓለም ቤ/ክ በሊቢያ ለተገደሉ ወገኖቻችን ጸሎት ላይ የተገኙ ምዕመናን
ከሥርዓተ ጸሎቱ ፍጻሜ በኋላ አቶ ታምራት አዳሙ የሰበካ ጉባዔው ሰብሳቢ የሞቱት ወገኖቻችንን በማስመልከት ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም በእነዚህ ወገኖቻችን ላይ ካራ መዝዘው ግድያ የፈፀሙ ኃይሎች የማንንም እምነት ተከታይ እንደማይወክሉ ገልጠዋል። “ለዚህም ምሳሌ ሊሆን የሚችለው የሙስሊም እምነት ተከታዮች ሳይቀሩ በአሁን ሰዓት በዚህች ቤተክርስቲያን መገኘታቸው ነው” ብለዋል።
ከዚህ በመቀጠል ወገኖቻችንን በማሰብ በደብሩ መዘምራን ኀዘናዊ መዝሙር ቀርቦ፣ ከመካነ ኢየሱስ የመጡት ቄስ ዮናስ ቤተክርስቲያኒቱን በመወከል ለምዕመናኑ ትምህርት ሰጥተዋል። በትምህርታቸውም “የሌላው መከራ ለእናንተም እንዲሆን አድርጉ” የሚል የመጽሐፍ ቃል በመጥቀስ አስተምረዋል።
በስቶክሆልም መድኃኒዓለም ቤ/ክ በሊቢያ ለተገደሉ ወገኖቻችን ጸሎት ላይ የተገኙ ምዕመናን
አቶ ሶፊያን የእስልምና ዕምነትን በመወከል ትምህርታዊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ከተገደሉት ውስጥ አንዱ ሙስሊም መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ የእስልምና ተከታይ ወገኖቹ ላይ ካራ እንዲመዝ ተጠይቆ እምቢ በማለቱ ከክርስቲያን ወገኖቹ ጋር አንድ ላይ እንደተገደለ ገልጠዋል። በማጠቃለያቸውም ለዚህ ሁሉ አስከፊ መከራና ስደት የተዳረግነው አንድነት ስለጎደለን መሆኑን በመጥቀስ፤ ከዚህ በኋላ በኃይማኖት፣ በዘር፣ … ሳንከፋፈል አንድነታችንን አጠናክረን መጓዝ ይገባናል ብለዋል። ኢትዮጵያዊው የወገኖቹን ኀዘን ለመወጣት በጋራ በመሰባሰቡ ምስጋና አቅርበዋል። ይህ ጭካኔ በእስልምና ስም የተሰራ ደባ እንጂ የእስልምና ኃይማኖትን እንደማይወክል ገልጠዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አስቀድመው የተናገሩትን የእስልምና እና የመካነ ኢየሱስ ኃይማኖት ተወካዮችን መርቀው፣ የተናገሩት ከእውነት ያልራቀ መሆኑን ገልጠዋል። “የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስል ጊዜ ይመጣል” የሚለውን የመጽሐፍ ቃል በመጥቀስ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል። የተሻለ ሠይጣን ተባርሮ፣ የከፋ ሠይጣን ሊቢያ ውስጥ እንደመጣ ጠቅሰው፤ የወገኖቻችን ሞት፣ ሞት ሳይሆን ሰማዕትነት እንደሆነ አስተምረዋል። ይህም የሁለተኛው ዘመን ቃል እንደተፈጸመ ይቆጠራል ብለዋል። ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ሰማዕታት ይህን በመሰለ አሟሟት እንደሞቱ አስታውሰዋል።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በምስጢር እንደሚጠብቃት ገልጠው፣ “አሁንም እግዚአብሔር በምስጢር ይጠብቀን! ለችግራችንም እግዚአብሔር አምላክ መፍትሄ ይስጠን! የወገኖቻችንን ነፍስ ይማርልን! በቅርቡም ከሲኖዶስ ትልቅ ውሳኔ ይተላለፋል” በማለት ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል።
በስቶክሆልም በደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን
150422-stockholm-medhanialem-01

Tuesday, April 21, 2015

ከታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ለኢትዮጵያውያን የተላለፈ መልእክት


ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ ሀገራት በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ እና የሌላ ሀገር ተወላጅነት ባላቸዉ ንፁሀን ዜጉች ላይ በተፈፀመዉ አሰቃቄ የግድያ ወንጀል አዝነን ሳናበቃ ፦ ዛሬ ደግሞ በሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን እጅግ አሳዛኝ ፤ አረመኔያዊ ተግባር ስይና ስንሰማ የተሰማኝን ሐዘን ለመግለፅ ቃላትም ሆነ ቋንቋ ያጥረኛል።
እንኳን የኔ በሚሉት የራስ ወገን ይቅርና ክቡር በሆነዉ የትኛዉም የሰዉ ልጅ ፍጡር ላይ እንዲህ አይነቱ ፍፁም ርሕራሔ የሌለዉ ኢሰብአዊ ተግባር ሲፈፀም ማየትም ሆነ መስማት የሚፈጥረዉን ጥልቅና መሪር የሀዘን ስሜት ለመረዳት ወገን ሆኖ መገኘት ብቻ ሳይሆን ሰዉ ሆኖ መፈጠር ይበቃል።
እንደ ሰዉ ሰዉ በመሆኔ ብቻ ሳይሆን በተለይ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ በወገኖቼ ላይ የተፈፀመዉ ድርጊት አሳዝኖኛል አስቆጥቶኛልም።
ከመቼዉም ጊዜ በበለጠም እኛ ኢትዮጵያዊያን ማንኛዉም አይነት ልዮነት ሳይወስነን በግፍ ለተጠቁት ወጉኖቻችን በአንድነት ቆመን ወገናዊነታችንን የምናሳይበት ወቅት አሁን ነዉ።
የኛ አለመግባባትና አንድ አለመሆን እንዲህ ላለው መጠቃት አሳልፎ ሲሰጠን ዛሬ አዲስ ባይሆንም መደጋገሙ እና ተጠናክሮ መቀጠሉ ግን እዚህ ጋር ይበቃል ልንል ይገባል።
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን መንካት የእሳት ዘንግ መጨበጥ እንደሆነ የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነትን ጨምሮ በዘመናት የቀደመ ታሪክ የታየና ወደፊትም የሚቀጥል የመሆኑ ሐቅ ከአለት የፀና ነዉ። ይህም ቃል ኪዳን በልኡል እግዚአብሔር የታተመ የማይቀየር ቃል ነዉ።
ላስተዋለዉ
የምስራቹ ደጅ ላይ ሲደረስ ይህ የጣሩ ድምጽ ጅማሬ ስለሆነ የኢትዮጵያ ብርሀን ዓለምን ሊሞላ የተጣሏትም፤ ያዋረዷትም ፈፅመዉ ሊከደኑ እጅግ ጊዜዉ ቀርቧልና አይዟቹሁ ፅኑ ። ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ አንድነታችን ሊጠናከር የሚገባበትም ጊዜ አሁን ነዉ።
በመጨረሻም በግፍ የተገደሉትን ንፁሀን ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዛአብሔር በቀኝ መንግስቱ እንዲያሳርፍ እየተማፀንኩ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላዉ ኢትዮጵያን ወገኖች መፅናናትን እመኛለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
ፍቅር ያሸንፋል11173345_1421576574825777_553275562926316751_n

ሰበር ዜና ህዝብ በወያኔ ላይ በአዲስ አበባ ተቃውሞውን እያሰማ ነው

ሰበር ዜና
አሁን የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው ከተማ ውስጥ ማን እንደበተነው ያልታወቀ ነገ የስራ ማቆም አድማ እና ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ወረቀት ተበትኗል! በየታክሲውና ከተማ ውስጥም መነጋገሪያ እንደሆነ ታውቋል።
ፖሊስ ሰልፈኛው ወደ ሜክሲኮ እንዳይሄድ ለማገት ቢጥርም ህዝቡ ግን አንቆምም ብሎዋል
ሰልፉ አዲስ አበባን ሲዞር ሊውል ነው!
አሁን ሰልፈኛው ወደ ከቄራ ወደ ሜክሲኮ እየዞረ ነው!
ፖሊስ ምንም ማድረግ ስላልቻለ ሰልፉ በሞተር እየተመራ ነው፡፡ በርካቶች በስሜት፣ በቁጭት እየተቀላቀሉት ነው፡፡ መፈክሮች፣ ለቅሶ፣ መዝሙር፣ ጩኸት እየተሰማ ነው!
አሁንም በርካታ እናቶች፣ ወጣቶችና ሌሎችም እያለቀሱ ሰልፉን እየተቀላቀሉ ነው! የሰልፈኛው ቁጥር እየተበራከተ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው! የኢህአዴግ ናቸው የተባሉ ነገሮች ሁሉ እየተቀዳደዱ ነው!
መንግስት የሌለው ኢትዮጵያ ብቻ ነው
አዲስ አበባ ህዝቡ ያለአንዳች ቀስቃሽ ለሰማዕታቱ ሀዘኑን ለመንግስት ቸልተኝነት ተቃውሞውን እየገለፀ ነው።
በጉልህ ተፅፈው ከሚታዩት መፈክሮች ውስጥ ”ሉዓላዊነት ማለት የትም ቦታ ያሉትን ዜጎቻችንን መብት ማስከበር ነው”11173407_959193090780198_3490740387873963160_n 11150143_678342725645299_5875406239496253050_n 1908198_824771097630671_3394828389672125741_n 11173407_959193090780198_3490740387873963160_n

Monday, April 20, 2015

ESAT Breaking News Ethiopians in Libya speak to ESAT April 19, 2015 | ESATTUBE

ESAT Breaking News Ethiopians in Libya speak to ESAT April 19, 2015 | ESATTUBE

በግፍ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን በተመለከተ የአርበኖች ግንቦት 7 መግለጫ


ሀያ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደርሷል። ይህ አሰቃቂ መርዶ ልብን የሚሰብር ነው። አይ ሲስ በጥንት በጭለማ ዘመን እንኳን ባልነበረ ጭካኔ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን በማረድ የሚደሰት፤ በሰው ዘር ሁሉ ላይ የመጣ አውሬ መሆኑን ነብዩ መሐመድ አትድረሱባቸው ያሏቸውንም ኢትዮጵያዊያንን ጭምር በማረድ አረጋገጧል። ይህ አሰቃቂ ተግባር ምንም ዓይነት አመክኖ ሊቀርብለት የማይችል አረመኔዓዊ የሽብር ጥቃት ነው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል። ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አይ ሲስን በጥብቅ እንዲያወግዙ፤ በአመቻቸው መንገዶች ሁሉ እንዲታገሉት አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።
በዚህ አጋጣሚ የአይሲስን የሽብር ተግባራት ከእስልምና እምነት ጋር ማያያዝ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ፤ ብዙሃን ሙስሊሞች የአይሲስና መሰል ቡድኖችን አካሄድ የሚቃመው መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ማስገንዘብ ይሻል። ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር ተዋደውና ተፋቅረው የኖሩና እየኖሩ ያሉ ሲሆን የሁለቱ ሀይማኖቶች ተከታዮች ተደጋግፎ መኖር ለሀገራችን ህልውና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ነው።
በያዝነው ሣምንት በወገኖቻችን ላይ እልቂት ሲደርስ የሊቢያ ብቸኛ ክስተት አይደለም። በደቡብ አፍሪቃ ወገኖታችን ከነሕይወታቸው በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፤ በስለት ተዘልዝለዋል፤ ንብረታቸውን ተዘርፈዋል። በዛሬው ዕለት 700 ዜጎች የሜዲተራኒያን ባህር በጀልባዎች ሲሻገሩ መስመጣቸው ተሰምቷል። በየመን ደግሞ በርካታ ወገኖታችን በጦርነት እሳት ውስጥ እየተማገዱ ናቸው።
ኢትዮጵያዊያን በአገራችን የሰፈነውን የነፃነት እጦት፣ የፍትህ መጓደልና የኑሮ መክበድ ሸሽተን በሄድነት አገር ሁሉ የሚጠብቀን አሰቃቂ ሞትና ውርደት ሆኗል። ኢትዮጵያ ለኑሮ ያልተመቸችን በህወሓት አገዛዝ ብሉሽነት መሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህንን ብልሹ አገዛዝ አስወግደን በምንወዳት አገራችን ተከብረን መኖር እንችላለን። ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም።
አርበኖች ግንቦት 7: የኢትዮጵያዊያን መከራ እንዲያበቃ ስደት ይብቃ ይላል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባሌውና እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ አሊያም የሥራ ቦታውና መኖርያው ሳይለቅ በሕዝባዊ እምቢተኝነት በተደራጀ መንገድ የህወሓትን አገዛዝን ይታገል። በሕዝባዊ አመጽና በሕዝባዊ እምቢተኝነት የህወሓት ፋሽስቶችን አስወግደን በአገራችን በነፃነትና በክብር እንድንኖር ሀይማኖትም ሆነ የዘር ሀረግ ሳይለየን በጋራ እንታገል የሚል ጥሪ ያቀርባል።
ዘላለማዊ ክብርና እረፍት ለግፍ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን11150143_678342725645299_5875406239496253050_n

የምናዝነው ስንት ሰው ሲሞት ነው? በዲያቆን ዳንሄል ክብረት


በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡
ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?
ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም ይሂዱ በአውሮፕላን ተሳፍረው፤ መጀመሪያ ሰዎች፣ ቀጥሎም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸውና ኀዘን ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ክብር አንዱ በሞቱ ጊዜ የክብር ልቅሶና ኀዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአካባቢያቸው ላለመራቅ፣ ከራቁም ለመመለስ ከሚሰጧቸው ምክንያቶች አንዱ ‹በክብር ዐርፎ በክብር መቀበርን፣ የክብር የኀዘን ሥነ ሥርዓትን ማግኘትን› ነው፡፡
ካገሬ እንዳወጣህ አገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ፤
እንኳን የሚቀብረው የሚያዝንለት አጣ
ምን ወግ ማረግ ያያል ካገሩ የወጣ፤
የሚሉት ለዚህ ነበረ፡፡
የመንግሥት አካላት ለምን ይኼንን ለመዘንጋት እንደፈለጉ አልገባኝም፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቃጠሎና ግድያ ሲመጣ የሀገራችን ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ብቅ ብለው ‹‹በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ነገር ከልብ እናዝናለን፣ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር ተነጋግረን አስፈላጊውን እናደርጋለን፤ ተመሳሳይ ችግር ለወደፊቱ እንዳይከሰትም አንሠራለን› ዓይነት ሰውነት ያለበት መግለጫ ጠብቄ ነበር፡፡ የለም፡፡ ሲሆን በሀገራችን የልቅሶ ሥነ ሥርዓት መሠረት፡፡ አሁን ደግሞ ዓለም ያወቀው አሸባሪ ‹አይ ሲስ› ኢትዮጵያውያኑን በክርስትና እምነታቸው ብቻ ሲሠዋቸው የተሰጠው መግለጫ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጥ፣ እንኳን ሰው እንስሳ የሞተብን የማያስመስል ሆነ፡፡ ከማጣራቱም ከምኑም በፊትኮ ስሜቱ ይቀድማል፡፡፡ አዝናችኋል ወይ? ስትሰሙና ስታዩ ምን ተሰማችሁ? የአሜሪካ መንግሥት እንደዚያ ዓይነት መግለጫ ሲያወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ያንን ነው ወይ መስማት ያለብን? ለመሆኑ መሪዎቻችን ኀዘናቸውን የሚገልጡት ምን ስንሆን ነው? ለምንድን ነው ሁሉም ነገር ፖለቲካ የሚሆነው?
ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?
መንፈሳዊ መሪዎችስ የት ናቸው? አንዳንዶቹ ውጭ ሀገር መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ሲሆን ይህንን ሲሰሙ አቋርጦ መምጣት፤ ካልሆነም ባሉበት ሆኖ አባታዊ ኀዘንን መግለጥና በእምነቱ የሚገባውን ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሲኖዶሱስ ምን እየሠራ ነው? አልሰማም ይሆን? ዛሬ ጠዋት ቢያንስ በአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት መደረግ አልነበረበትም? ባፈው ካይሮ ሄዳችሁ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው ያያችሁት? በጎቹ እረኛ የላቸውም ማለት ነው? አባቶች የሚያዝኑት ምን ሲገጥማቸው ነው? እረኛው የሚያለቅሰው ስንት በጎች ሲታረዱ ነው?
ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሩን በዝምታ የምታልፈው ከሆነ እኛ እንደ ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ቀኖና እነዚህን በክርስትናቸው ምክንያት የተሠው ክርስቲያኖች ‹ሰማዕታተ ሊቢያ› ልንላቸው ይገባል፡፡ የሰማዕትነታቸውንም በዓል ማክበር አለብን፡፡ በስንክሳሩ ማስገባት ባንችል ታሪካቸው በኅዳጉ ማስፈር አለብን፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ በሚገባ የተማሩም ይሁኑ ያልተማሩ፣ ከመካከላቸው የማያምኑም እንኳን ቢኖሩ የተገደሉበት ምክንያት ክርስትና ነውና ሰማዕታት ናቸው፡፡ ያውም ‹ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት›፡፡ በስንክሳሩ እንደምናነበው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የክርስቲያኖች መንደርና ቤተ ክርስቲያን እየተወረረ ክርስቲያኖቹ ሲሠው ገና ያልተጠመቁት፣ ነገሩ ያልገባቸው፣ ክርስትናን ለመቀበል ያልወሰኑት ሁሉ አብረው ተሠውተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን የተሠውበት ምክንያት ክርስትና በመሆኑ ሁሉንም ሰማዕታት ብላቸዋለች፡፡ የእነዚህም ክብር እንዲሁ ነው፡፡
እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡ አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡
11036900_1650669808485924_1661000344523026471_n

በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር


senakriem1
ክንፉ አሰፋ
“አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ…ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር… በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። … በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።” ይላል አንድ የ 11 አመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት።
አስሩን ህጻናት በአንድ መኪና(ትራክ) ውጽጥ አጭቆ ነበር ወደ ሞሉ የወሰዳቸው። የያዘው መኪና ከአራት ሰው በላይ መጫን አይችልም። እመንገድ ላይ ፖሊስ እንዳያያቸው “ሁላችሁም ጎንበስ በሉ።” ይላቸው እንደነበርም ህጻናቱ አጫውተውኛል።
እነዚህ ሕጻናት ሀገሪቱ የምትመካባቸው የነገ ሳይንቲስቶችዋ ናቸው። ከአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ከፍተኛ፤ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ታዳጊዎች። በነዚህ ታዳጊዎች እና በወላጆቻቸው ላይ የደረሰው በደል እጅግ ብዙ ነው። ታሪኩ አንድ አሳዛኝ ፊልም ይወጣዋል። ወላጆቹ አሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ደውለው ይህ በደል ለህዝብ ይፋ እንዲሆንላቸው ቢጠይቁም የራዲዮ ጣብያው ጉዳዩን ባልታወቀ ምክንያት አፍኖታል። ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጻፉት የአቤቱታ ደብዳቤም ምላሽ ተነፍገዋል። ጉዳዩ ለሚመለከተው ክፍል ሁሉ አቤት ብለዋል። ሰሚ ግን አላገኙም።
senakriem-mekonnen
ይህንን በደል የፈጸመው ግለሰብ ከአዲስ አበባ እንዲሸሽ ተደርጎ በዚያው በዋሽንግተን ዲሲ በአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር ቤት መሽጓል። በአሜሪካ የመኖርያ ፈቃድ የለውም። የባንክ ሂሳብ ግን አውጥቶ ገንዘቡን እዚያው አከማችቷል።
የትንግርታዊው “ዶክተር” ሳሙኤል ዘሚካኤልን የሽወዳ ስልት ገና ከአእምሯችን ሳናወጣ፤ ሌሎች የእሱ ደቀ መዝሙሮች ብቅ እያሉ ነው። ስልታቸውን ይቀይሩ እንጂ የሁሉም ቁጭ በሉዎች አላማ አንድ ነው – ህዝብን ማታለል። አንዳንዶቹ ለሽወዳቸው ረቀቅ ያለ ዘዴ ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ ዘርካካ በመሆን የዋሁን ህዝብ በዘረፋ ተያይዘውታል።
ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አጭበርባሪ የረቀቀ ስልት ባይጠቀምም ለሌብነቱ የተለየ መንገድ ይዞ ነው ብቅ ያለው። ሰናክሪም መኮንን ይባላል። ይህ ሰው የገዥው ፓርቲ አባል በመሆኑ ለዝርፊያው ምቹ መንገድ እንደፈጠረለት ይነገራል።
የሰናክሬም መኮንን አንድ አዲስ ፕሮጀክት ነደፈ። ከመላው ትምህርት ቤቶች በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን አወዳድሮ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ታዳጊዎችን አሜሪካ በመውሰድ ሂውስተን ቴክሳስ የሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ማስጎብኘት። ከዚህም ሌላ የላቀ ውጤት ላመጡ ህጻናት የላፕቶፕ እና የአይፓድ ልዩ ሽልማት እሰጣለሁ ብሎ ቃል ይገባል። በየትምህርት ቤቱ እየዞረ የትምህርት ቤቶቹን እና ልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም አላማውን አስፈጸመ። ወጪውን ሁሉ የሚሸፍኑ ስፖንሰሮች አገኘ። አዲካ ትራቭል፣ ኦሮሚያ ባንክ እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ የህጻናቱን ወጪ በሙሉ የሚሸፍን በቂ የሆነ ስፖንሰር ተገኘ።
macdonalds
ሰናክሬም የስፖንሰሩን ድጋፍ እና የአስሩን ህጻናት ፓስፖርት ይዞ አሜሪካ ኤምባሲ ለቪዛ ሄደ። በቂ የስፖንሰር ድጋፍ ስለነበረው ያለምንም ችግር የልጆቹን ቪዛ አገኘ።
ጫወታው እዚህ ላይ ነው የሚጀምረው። ስፖንሰሩን እና ቪዛውን በእጁ ካስገባ በኋላ የህጻናቱን ቤተሰቦች በተናጥል እየጠራ እያንዳንዳቸው የህጻናቱን የትራንስፖርት እና የመስተንግዶ ወጪ እንዲሸፍኑ ጠየቃቸው። ሰውየው በቂ በጀት ከስፖንሰሮች እንዳገኘ በወላጆቹ ይታወቃል። በመጀመርያ የገባውን ቃል አጥፎ ወላጆቹ የልጆቻቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ መጠየቁ ለሁሉም እንግዳ ሆነባቸው። ሁሉም አንከፍልም ሲሉ መለሱለት።
ሰናክሬም ግን አጭር መልስ ሰጣቸው። “ወጪውን የማትሸፍኑ ከሆነ እድሉል ሌሎች ልጆች እሰጠዋለሁ።” ሲል የባሰ መርዶ አመጣባቸው።
ወላጆች አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ። በአንድ በኩል ልጆቻቸው ወደ ሂውስተን ለመሄድ ተነሳስተዋል። የልጆቻቸውን ስሜት መጠበቅ ግድ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሰው እያጭበረበራቸው መሆኑን አውቀውታል። ከብዙ ማንገራገር በኋላ ግን ገሚሱ ወላጅ የአውሮፕላን ትኬት፣ የአምስት ኮከብ ሆቴል፣ የመስተንግዶ እና የኮቴ ከፍሎ ልጆቹን ወደ አሜሪካ ላከ። ሰናክሬም ከውጭ ሃገር ከተቀበለው ዶላር ውጭ ወላጆቹ የከፈሉት ገንዘብ በድምሩ አንድ ሚሊዮን ብር ይጠጋል።
ይህንን ወጪ መክፈል ያየልቻሉ ህጻናትን ተሰረዙ። የነሱ እድል ሌሎች ጥሩ ውጤት የሌላቸው ግን ገንዘብ ላላቸው ወላጆች ተሸጠ። ዘረፋው በዚህ መልኩ ተፈጸመ። አስሩ ህጻናትም ወደ አሜሪካ ተጓዙ።
ወደ ዋና ድራማው ደግሞ ልውሰዳችሁ። አሜሪካ ዋሽንግተን እንደገቡ ለአንድ ቀን ብቻ በማሪዮት ሆቴል ቆይታ ያደርጋሉ። በነጋታው ሁሉም በአንድ ትራክ ተጭነው እዚህ ግባ የማይባል ማረፍያ ውስጥ በቡድን በቡድን ታጎሩ።
የጉዞው ዋና አላማ በሂውስተን የሚገኘውን የናሳ ጠፈር ምርምር ተቋም መጎብኘት ነበር። እሱን እርሱት ብሏቸዋል ሰናክሬም። ለግዜው ወላጆችን ማታለያ አስሩንም በቡድን ፎቶ አነሳቸው። የናሳን ማስክ በፎቶሾፕ እያስገባ አለበሳቸው። ናሳ የሄዱም አስመሰላቸው። ፎቶውንም በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ለጠፈው።
አሁን ልጆቹም ስለናሳው ጉዳይ አያስቡም። ከወላጆቻቸው ተነጥለው ወጥተው በአንድ ሃላፊነት በጎደለው ሰው እጅ ላይ ወድቀዋል። በአንድ ክፍል ወስጥ ተቆልፎባቸው ይውሉና ለተወሰነ ሰዓት በገበያ አዳራሽ ውስጥ ይለቀቃሉ። በአሜሪካን ሃገር በርሃብና ጥማት እየተሰቃዩ ነው። ረሃብ ጸንቶባቸው ሆስፒታልም የገቡ አሉ።
ወላጆቹ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ*፣ “ሰናክሬም ከእያንዳንዱ ወላጅ የአምስት ኮከብ ሆቴል ሂሳብ ተቀብሎ ሳለ ህጻናቱ ግን ተገቢውን የሆቴል አገልግሎት አላገኙም። ሴቶቹ የማይታወቁ ሰዎች ቤት እንዲያርፉ መደረጉ እና ወንዶቹ ደግሞ በቡድን በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲያድሩ አድርጓል።” ብለዋል።
ምግብን በተመለከተ ተገቢውን ምግብ ሳይመገቡ ለረሃብና ለህመም መዳረጋቸውና ከዚህም የተነሳ በምግብ ማጣት ጉዳት ሆስፒታል መግባታቸው፤ የተወሰኑት ከአቶ ሰናክሬም ተወስደው ወደ ዘመድ ቤት እንዳረፉ በደብዳቤው ላይ ተገልጿል። በመጀመርያዎቹ ቀናት ማክዶናልድ እየወሰደ ይመግባቸው እንደነበር ልጆቹ ተናግረዋል። ከዚያ በኋላ ነው የረሳቸው።
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ደግሞ እነዚህን በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በዋሽንግተን ዲሲ ለልመና መጠቀሙ ነው። “ከሄዱበት አላማ ውጪ በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በየቤተክርስትያኑ እያዞረ ‘ለችግረኛ የሚሆን’ በማለት ኩፖን በማሸጥ አሰማርቷቸውም ነበር።” ይላል ደብዳቤው። ልጆቹን በዚህ መልኩ በልመና በማሰማራት በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሰበሰበ ህጻናቱ ይናገራሉ። በተለይ ዋሽንግተን ዲሲ ያለው ወንጌላዊ ቤተ-ክርስትያን ህጻናቱ በጉባኤው ፊት ቆመው የልመናውን ኩፖን እንዲያሳዩና እንዲሸጡ አድርጓቸዋል። ይህ የሆነው የቤተ-ክርስቲያኗን ፓስተር ሃንፍሬይን በማታለል ነው።
ሕጻናቱ በዚህ መልኩ ተንገላትተው ግን ለመጡበት አላማ ምንም ነገር ሳያደርጉ ሊመለሱ ነው። በአካባቢው ያሉ የቤተሰብ አባላት አንድ ሃሳብ አመጡ። ኢትዮጵያዊው ጠረፍ ሳይንቲስት የሆኑትን ዶ/ር ብሩክ ላቀውን በጉዳዩ አማከሩዋቸው። ዶ/ር ብሩክም ፈቃደኛ ሆኑ። በወላጆች ትውውቅ የመጡት እኚህ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ህጻናቱ ካረፉበት ስፍራ ድረስ በምሄድ ስለ ናሳ አስረዷቸው።
ህጻናቱም ይህችን እውቀት ይዘው፤ ናሳን በቴለቭዥን እንኳን ሳይመለከቱ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። የሰናክሬም የናሳ ጉዞ ፕሮጀክትም በዚህ ላይ ተጠናቀቀ። ገቢው አጓጊ ነውና ሰናክሬም አሁንም ሌላ ዙር ሊሰራ ማሰቡ አልቀረም።
የህጻናቱ ቤተሰቦች ግን በመሰባሰብ የጋራ አቋም ላይ ደርሰዋል። ያላግባብ የተወሰደባቸው ገንዘብም እንዲመለስ ጠይቀዋል። ሰናክሬም ግን ሸሽቶ አሜሪካ መሽጓል።
ይህ መረጃ እንደደረሰኝ ሰናክሬም መኮንን በኢሜል አግኝቼው ነበር። ጉዳዩን እልባት እንዲሰጥ፤ የሰዎቹንም ገንዘብ እንዲመልስ በተደጋጋሚ ጠየቅኩት። ይህ ከልሆነ ታሪኩን ለህዝብ ይፋ እንደማደርገውም ነግሬው ነበር። ይህ ጉዳይ ሜድያ ላይ ከወጣ ታዋቂ እንደሚያደርገው ተናግሮ አሾፈብኝ።
ይህንን የማደርገው ለሌሎች ወላጆች ትምህርት እንዲሆን ነው። ጉዳዩን ለበርካታ የሜዲያ አካላት ማሳወቄም ግድ ነው። ለጥንቱ ወዳጄ ሰይፉ ፋንታሁንም የህጻናቱን በደል ነግሬው ነበር። ህጻናቱን አነጋግሯቸዋል። ጉዳዩን በቅርቡ እንደሚያቀርበው ነግሮኛል።

Thursday, April 16, 2015

ለወራት በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ የቆየው የኮምቦልቻው ወጣት ዘሪሁን ገሰሰ ተለቀቀ.


የጀስቲስ (ዘሪሁን) አድናቂ
የካቲት 13 ቀን ከአዲስ አበባ ወደ ኮምቦልቻ በመጓዝ ላይ ሳለ ሸዋሮቢት ከተማ ላይ ከተሳፈረበት አውቶብስ ላይ በመንግስት ታፍኖ የተወሰደው የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የኮምቦልቻ የህዝብ ግንኙነትና የወጣቶች ጉዳይ ሀላፊ እንዲሁም የሚሊየኖች ድምፅ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የነበረው በአሁኑ ሰዓት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ዘሪሁን ገሠሠ ከወራት አፈና በኋላ ሰኞ በ 28/07 / 07 ምሽት ላይ ተለቋል. ወጣት ዘሪሁን ገሠሠ እጅግ ጠንካራ ፖለቲካዊ አቋም ያለውና ሀገር ወዳድ ሰላማዊ ታጋይ የነበረ ሲሆን በሰላማዊ ትግሉ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችና በአካባቢው ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በስርአቱ የሚፈፀሙ በደሎችን በማህበራዊ ድህረ-ገፆችና የሚዲያ አ ውታሮች በመፃፍ በማጋለጡ ሁኔታው ያልተመቸው አንባገነናዊው መንግስት ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግበት ቆይቶ በህገወጥ መንገድ አፍኖት እንደቆየ ለማወቅ ተችሏል. ምንም እንኳ ወጣት ዘሪሁን ዝርዝር መረጃዎችን በፓርቲው በኩል ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግና ውስን መረጃዎችን ብቻ የሰጠ ቢሆንም ከአሁን በፊት ሲገለገልባቸው የነበሩት የፌስቡክ አካውንትና ፔጆች እንዲሁም ዌብሳይቶችና የኢሜይል አካውንቶቹ በህገ-ወጥ መንገድ ከተለቀቀ በኋላም በመንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ አልሸሸገም.
ወጣት ዘሪሁን ገሠሠን ያነጋገሩት ምንጮቻችን እንደገለፁት << ወጣት ዘሪሁን ገሠሠ ከፍተኛ ጥበቃና ምርመራ እየተደረገበት ባላታወቀ ድብቅ እስር ቤት እንደቆየና በቆይታውም የሀሰት ውንጀላን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈፀመበት ያረጋገጠ ሲሆን አጠቃላይ ሁኔታውንና መንግስት በተለይ በሰማያዊ ፓርቲ ብሎም በሰላማዊ ታጋዮች ላይ ለመፈፀም እየተዘጋጀበት ስላለው የሀሰት ውንጀላ ሁኔታና ዝርዝር መረጃዎችን ለፓርቲው አሳውቆ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት ተናግሯል. ከዚሁ ጋር አያይዞም በወጣቱ ሰላማዊ ታጋይ መታሰር ከፍተኛ ቁጭት በማሳደርና ህገወጡን መንግስታዊ አፈና በማጋለጥ; በማውገዝ ከፍተኛ ተፅእኖ ሲያሳድሩ የነበሩ የሚዲያ ተቋማት; እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ-ገፃች መረጃዎችን ለህዝብ ሲያደርሱ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን; ድርጊቱን በቀጥታ በማውገዝ ለማስፈታት ጥረት ያደረጉ የውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶችና በአጠቃላይ የህገ-ወጡን መንግስት ሽፍታዊ ተግባር በማውገዝ ስሜታቸውን ለገለፁ ዜጎች ብሎም የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የትግል አጋሮቹ ከፍተኛ ምስጋናውን እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል. ወጣት ታጋይ ዘሪሁን ገሠሠ ለቀድሞው አንድነት ፓርቲ እጩ የነበረ ሲሆን ፓርቲው መፍረሱን ተከትሎ ለተለጣፊዎቹ እውቅና አልሰጥም በማለት ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል ለተወካዮች ም / ቤት እጩ የነበረ መሆኑና በአሁኑ ሰዓት እራሳቸውን << >> አንድነት ብለው የሚጠሩት የመንግስት ተለጣፊዎቹ << የእነ ትግስቱ ቡድን >> እና የምርጫ ቦርድ የተለመደ ተባባሪነት በተወሰደ ፖለቲካዊ ውሳኔ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በጣሰ መልኩ ከእጩነት መሰረዙ አይዘነጋም.Kattani Katti their image.

በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአየር ሃይል የበረራ አስተማሪዎች ታሰሩ


ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች  ያስተላለፉትን ድንገተኛ ትእዛዝ ተከትሎ በፌደራል ፖሊስ አባላት የእጅ ስልኮችና የኢሜል አካውንቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ፣ የተቃዋሚ መሪ ፎቶዎችን፣ አገራዊ ሙዚቃዎችንና ማንኛውም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ከኢንተርኔት አውርደው በስልካቸው ላይ ያስቀመጡ ፖሊሶች ተይዘው የተወሰኑት ማእከላዊ ሲገቡ፣ የተወሰኑት ደግሞ ጃንሜዳ አካባቢ በሚገኝ እስር ቤት መታሰራቸውን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል።
በድንገት የተደረገውን ፍተሻ ተከትሎ በአጠቃላይ ከ120 ያላነሱ ፌደራል ፖሊስ አባላት ሲታሰሩ፣ በፍተሻው በቀጥታ የተቃዋሚ መሪዎች ፎቶዎች ወይም ፖለቲካ ነክ የያዙ ጽሁፎች የተገኙባቸው 37 የሚሆኑ ፖሊሶች ማእከላዊ ተወስደው ታስረዋል።
ከ80 በላይ የሚሆኑት ደግሞ አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮች አሉ በሚል ለተጨማሪ ምርመራ ጃን ሜዳ አካባቢ በሚገኝ ማቆያ እንዲታሰሩ ተደርጓል።
የፌደራል ፖሊስ አዛዦች የሚሰጡትን ትእዛዝ ላለመቀበል ያንገራግራሉ ተብለው አስቀድመው በተለዩ ፖሊሶች ላይ ደግሞ ክትትሉ መጨመሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በዚህም መሰረት በአርማጭሆና ሰሜን ጎንደር የጸረ ሽብር ግብረሃይል ሃላፊዎች የሆኑት ኢንስፔክተር ስንታየሁ፣ ሳጅን አበበ እና ም/ል ሳጅን ብርሃኑ ተይዘው ወደ ማእከላዊ ተወስደዋል።
በእስር ላይ የሚገኙት የግንቦት7 ዋና ጻሃፊ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ግራፍ በብዙ ወታደሮች ሞባይል ስልኮች ላይ መገኘቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
ከድምጻውያን ደግሞ የቴዲ አፍሮ፣ የብርሃኑ ተዘራና የፋሲል ደሞዝ ሙዚቃዎችን ከኢንተርኔት አውርዶ ማዳመጥ ኢህአዴግን እንደመክዳት እያስቆጠረ ነው ተብሏል።
በተመሳሳይ ዜና  ድሬዳዋ ውስጥ በበረራ አስተማሪነት ይሰሩ የነበሩ ሁለት መኮንኖች ሰሞኑን ተይዘው ማእከላዊ መታሰራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ስማቸውን እስካሁን ለማወቅ ባይቻልም፣ አብራሪዎቹ ቀድም ብሎ ከታሰሩት 4 አብራሪዎች ጋር ግንኙነት ነበራችሁ ተብለው መታሰራቸው ታውቋል።
የኤም 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር የበረራ አስተማሪ የነበረው የሻለቃ አክሊሉ መዘነ ወንድም ሰይፉ መዘነም ማእከላዊ ታስሮ በመሰቃየት ላይ ነው። የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የአመራር አባል የነበረው መሳይ ትኩም ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት ነው።
ገዢው ፓርቲ በደህንት ተቋማት ላይ ያለው ጥርጣሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ እያለ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ ተጨማሪ ፍተሻዎች፣ ድንገተኛ ግምገማዎችና እስሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገልጻሉ።
የጥርጣሬው መነሻ ምን እንደሆነ በውል ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጅ ስራቸውን እየለቀቁ የሚጠፉ የፌደራል ፖሊሶች ቁጥር መጨመር ስርአቱን ስጋት ላይ ሳይጥለው እንደማይቀር ምንጮች  ይገልጻሉ።ethiopian-airforce

በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ ነው


ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ አፍሪካዋ የቱሪስት ከተማ የደርባን ተወላጆች_የውጭ አገር ዜጎች ከአገራቸው እንዲወጡ ለማስገደድ በወሰዱት ጥቃት 3 ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አጇንስፍራንስፕሬስዘግቧል።
ኢትዮጵያዊያኑ ሱቆቻቸው ውስጥ እንዳለ በጋስ በተሞላ ቦንብ መቃጠላቸውን አንዳንዶች ተደብድበው መሞታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በደርባንና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጭንቅ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ ደግሞ አንድ ኢትዮጵያዊ አገራችን ችግር ላይ ነች፣ አገር የለንም የት እንደምሄድም አላውቅም ብሎአል።
የአሁኑ ተቃውሞ የዙሉ ባህላዊ ንጉስ ጎድ ዊል ዝዌልቲኒ የውጭ አገር ዜጎች ሻንጣዎቻቸውን ሸከፍው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ነው። የፕሬዚዳንት ዙማ ልጅ በበኩሉ ” የውጭ አገር ዜጎች አገሪቱን በረጅም ጊዜ ሊቆጣጠሩዋት ይችላሉ” በሚል የሰጠው መግለጫ ለግጭቱ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል።  ማላዊ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ በማውጣት የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።11129923_821879477919833_1647963852543383279_n

Wednesday, April 15, 2015

8 የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ሊያገሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ


በወላይታ ዞን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ያቀረቡ 8 የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዞኑ እየደረሰባቸው የሚገኘው አፈና እና በደል መፍትሄ ካልተሰጠው ራሳቸውን ከመጭው ግንቦት 2007 ዓ.ም ምርጫ ራሳቸውን ሊያገሉ እንደሚችሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ፣ ለምርጫ ቦርድና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ባስገቡት ደብዳቤ አስጠንቅቀዋል፡፡
ከመጭው ምርጫ ራሳቸውን ሊያገልሉ እንደሚችሉ ያስጠነቀቁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰማያዊ፣ የኢትዮጵያ ፍትሕና ዴሞክራሲ ሃይሎች ግንባር (ኢፍዴሃግ)፣ የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወሕዴግ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ናቸው፡፡
ማስጠንቀቂያውን ያቀረቡት ፓርቲዎች ለምርጫ ምቹ የሆነ አጋጣሚ እንዳለ በሚዲያ የሚገለፀው ትክክል እንዳልሆነ፣ ያለ ገደብ መብት የሰጠው ገዥው ፓርቲ ሰሆን በእነሱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና እና በደል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡ ፓርቲዎቹ አክለውም ምህዳሩ እጅግ የጠበበ መሆኑን በየጊዜው አቤቱታቸውን ለምርጫ ክልሎችና ለጋራ ምክርቤት ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙና በአባላቶቻቸው ላይ የሚፈፀመው በደል ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
‹‹የወረዳና የዞን የምርጫ አስተባባሪዎች የገዥውን ፓርቲ ድምጽ ከመስማት በስተቀር ምንም አይነት ውሳኔ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡›› ያሉት ፓርቲዎች በዚህም ምክንያት ምህዳሩ እጅግ መጥበቡንና ከችግር ላይ ችግር እየተደራረበ በመምጣቱ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን በደብዳቤው ገልጸዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለደቡብ ክልል ምርጫ ቦርድና ሌሎችም አገራቀፍና የክልሉ ተቋማት በላኩት ደብዳቤ
Semayawi Party- Ethiopia's photo.
Semayawi Party- Ethiopia's photo.Semayawi Party- Ethiopia's photo.

በኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ እየጨመረ ነው


ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ባለፉት አምስት አመታት ተግባራዊ ባደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረት ምርቶችን ውደ ውጭ በመላክ በያመቱ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በአምስቱ አመታት ውስጥ ያሳካው ሩቡን ያክል መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል።national bank of ethiopia
መንግስት በያመቱ ከኤክስፖርት ከ2 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን እስከ 3 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ ሲንቀሳቀስ ቢቆይም፣ በአምስት አምት ውስጥ ያገኘው አጠቃላይ ገቢ ከ3 ቢሊዮን ዶላር ያልበለጠ ነው። በተቃራኒው መንግስት በአምስት አመቱ ውስጥ ወደ አገር ውስጥ ያስገባው ገቢ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን፣ በአምስት አመቱ መጨረሻ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከፍ ብሎአል።
የወጪ ንግድ ገቢው ዝቅተኛ መሆን በአንድ በኩል የ5 አመቱ የልማት እቅድ ህዝቡን ሆን ብሎ ለማደናገር በምኞት ላይ ተመስርቶ የታቀደ መሆኑን ሲያመላክት፣ በሌላ በኩል ደግሞ እቅዱን ያወጡ ሰዎች ችሎታውና ብቃቱ የሌላቸው መሆኑን ኢኮኖሚስቶች ይናገራሉ።
የንግድ ሚዛን ጉድለቱ መስፋት የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ማባባሱንም ኢኮኖሚስቶች ይናገራሉ። ለጊዜው መንግስት እዳዎቹን ለመክፈል ከአይ ኤም ኤፍና ከሌሎች አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር ቢችልም፣ እዳው እየሰፋ ሲሄድ ለመከፍል የሚቸገርበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ኢኮኖሚስቶች ይገልጻሉ።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች በውጭ ምንዛሬ እጥረት የሚቸገሩትም በዚሁ የተነሳ መሆኑን ኢኮኖሚስቶች ይገልጻሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት 5 አመታት አገሪቱ ወደ ውጭ ልካ ካገኘቸው አጠቃላይ ገቢ ይልቅ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ አመት ብቻ ወደ አገራቸው ከሚልኩት ጋር እኩል መሆኑ ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአገሪቱ ኢኮኖሚ መሰረት መሆናቸውን ያሳያል። ባለፉት 5 አመታት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ12 -15 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገራቸው ልከዋል።