Wednesday, November 4, 2015

ወያኔ እስካለ የመልካም አስተዳደር ችግር በኢትዮጵያ ይቀረፋል የሚል እምነት የለኝም

ምክንያቱም ድርጅቱ፡-– መሰረቱ በውሸት፣ በሌብነት እና አጠቃላይ በሙስና የተዘፈቀ ስለሆነ
-በዘረኝነት ላይ የተንጠለጠለ እከክልኝ ልከክልህ አካሄድ የህልውናው መሰረት ስለሆአባላቱም ሆኑ አመራሩ በትምህርትም ሆነ 
-በእውቀት ብቃታቸው እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ ሰዎች የተመሰረተ እና የሚመራ በመሆኑ
-አባላቱም ሆኑ አመራሩ ከህግ የበላይነት ይልቅ ለዕለት ጉርስ እና ርካሽ ስልጣን ሲባል እያንዳንዳቸው ከህግ ይለቅ የበላይ አካላቸውን ፍላጎት ለማሟላት እና ለማስደሰት የሚሰሩ በመሆኑ
-በተለይ በየ እርከኑ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ከእውቀት እና ጥሩ ስነምግባር የፀዱ በመሆናቸው
-አባላቱን የሚያደራጀውና የሚመለምለው የፖለቲካ ፕሮገራሙንም ሆነ ፖሊሲውን አስተዋውቆና ተቀባይነት አግኝቶ ሳይሆን ከሆድ ባልዘለለ ርካሽ ጥቅማጥቅም መደለያ አሊያም የጉልበት ማስፈራሪያ በመሆኑ
-ከህወሓት ጥቂት የአመራሩ አስኳሎች በስተቀር አመራሩም ሆኑ አባላቱ የሚያምኑበትን እና ህግን የተከተለ አሰራር ለመከተል የራስ መተማመን የሌላቸው በመሆኑ
-ምንም እንኳ ብሔር/ጎሳ ላይ የተንጠለጠለ የስልጣን መሸሸጊያ ከማድረግ በስተቀር ለየትኛውም ጎሳም ሆነ ብሔር አሊያም አጠቃላይ ህዝብ ጠቅምና መብት ዋጋ የማይሰጥ በመሆኑ
-ስለሚከተለው ርዕዮተ ዓለም የጠራ እና ትክክለኛ ምንነት፣ ግብና ዓላማ መደናገር ውስጥ ያለ በመሆኑ
-በሀገሪቱ ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ተቋም፣ ደህንነት፣ ሲቪክ ተቋማትና ነፃ ፕሬስ ስለሌለ
-የሀገርን እና ህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝባዊ አመኔታ እና ውክልና ኖሮት የተመረጠ ስላልሆነ ከሰሞኑን የነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተራ ፐሮፖጋንዳ በዘለለ በኢትዮጵያ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር ይቀረፋል ማለት ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ነው ሚሆነው፡፡ ስለዚህ በሀገሪቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሊቀረፍ የሚችለው ራሱ ኢህአዴግ ስልጣን ሲለቅ አሊያም ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ ላይ መቅረፍ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment