Thursday, November 19, 2015

ወያኔ ዛፍ እና አፋሮች:.ወያኔ ዛፍ


አፋሮች ይህን ዛፍ የሚያውቁት ወያኔ አካባቢውን ከተቆጣጠረ በኋላ ነው። ዛሬ ይህ ዛፍ ሌሎች ሃገር በቀል ዛፎችን እየገፋ የአፋር ክልልን ማጥለቅለቁ እና ለቁጥጥርም አዳጋች መሆኑ ይነገራል። አፋሮች ዛፉን ‘ወያኔ ዛፍ’ ይሉታል።ይህዛፉ አፋር ክልልን ተሻግሮ ሌሎችንም እንዲህ እያዳረሰ ወይም እንዲዳረስ እየተደረገ ነው። ወያኔ ዛፍ ግንዱ ሳይቀር ትልልቅ እሾህ ያለበት ዛፍ ሲሆን ቅጠሉን ግመልም ሆነ ሌሎች እንስሳት አይበሉትም። ይህን ዛፍ የአካባቢው ሰዎች ለከሰል ስራ አገልግሎት ቢያውሉትም ከሰሉ ግን እስከዚህም እንደሆን ሰምቻለሁ።
እውነቱን ለመናገር ወያኔ ዛፍ ያምራል። ይህም ሆኖ ዛፉ በስሙ እንዲሆን ያልፈለገው ወያኔ ግን የግብርና ባለሙያዎቹን እያሰማራ የዛፉ ስም ‘ደርጊ ሃራ’ ነው ማስባል ከጀምረ ቆይቷል። አፋሮች እና ዛፉ በሚበዛበት አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦች ግን ይህን ዛፍ እና ወያኔን የምናውቀው በተመሳሳይ ወቅት ስለሆነ የደርግ ሳይሆን “የወያኔ ዛፍ ነው!” ማለቱን እንደቀጠሉ ነው። የሚገርመው ማህበረሰቡን አስተምረው ስሙን እንዲያስቀይሩ ደሞዝ ከሚከፈላቸው አንዱ የግብርና ባለሙያ እራሱ በማህበረሰቡ ተቀይሮ ‘ይህ የወያኔ ዛፍ ይባላል።’ ብሎ ለብዙ ጊዜ በስም የማውቀውን ዛፍ ትናንት በአካል አስተዋውቆኛል። ለማታውቁት ደግሞ እኔም የወያኔን ዛፍ ይሄው አስተዋወቅኋችሁ።

No comments:

Post a Comment