Monday, November 30, 2015

ለሱዳን ሊሰጥ የታሰበው መሬት ጉዳይ አሁንም አወዛጋቢነቱን ቀጥሏል



በዳግማዊ አፄ ምንሊክ ዘመን በወቅቱ የሱዳን ቅኝ ገዢ የነበረችው የእንግሊዝ ተወላጅ የሆነው ጉዌን የተባለግለሰብ ያለማንም ፈቃድ የሱዳንን ካርታ አዘጋጅቶ ለእንግሊዝ መንግሥት ያቀረበ ሲሆን የእንግሊዝ ነገሥታቶች በካርታው ዙሪያ ከኢትዮጵያው ንጉሥ አጤ ምንሊክ ጋር ሳይስማሙ በመቅረታቸው የእንግሊዝ ፍላጎት ሳይሳካ ቀረ ሆኖም ጊዜ እና ዘመን ሲጠብቁ የኖሩት የሱዳን መሪዎች ፀሎታቸው ሰምሮ ኮትኩተው ያሳደጉት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ የቆመ ሕወሐት የተባለ መንግስት አገኙ ጫካ እያሉ እኔ የትግራይ ገዢ እንጂ የተቀረው የኢትዮጵያ መሬትን ጉዳይ እንደፈለጋችሁ በሚሉ ምክንያቶች ስምምነቶች ላይ የተፈራረሙ በመሆኑ ሕወሐት ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ ይህ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ቀን ሲጠብቁ ኖረው ዛሬ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ደርሰዋል።
ለሱዳን የሚሰጠው መሬት ከጎንደር ተነስቶ ኦሮሚያን ቆርሶ የጋምቤላ ምድር ድረስ የሚደርስ ሲሆን ርዝመቱ እስከ1600 ኪሎ ሜትር ይደርሳል ይህም ማለት ምን አልባት ከአዲስ አበባ ዳሕላክ ወደብ የሚደርስ መሬትን ያህል እኩሌታ ማለት ነው
ይህ የሚሰጠው መሬት ወደኢትዮጵያ ድንበር ከ47 እስከ 50 ኪሎ ሜትር የሚገባ መሆኑም ታውቋል ሌላው አስደንጋጩ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩት አጤ ቴዎድሮስ የተማሩበት ማህበረ ሥላሴ የተሠኘው ገዳምም በድንበር ማካለሉ ስምምነት ምክንያት የሱዳን አካል የሚሆን ሲሆን አፄ ዮሐንስ ከሱዳን ማህዲስቶች ጋር ጦርነት ላይ በነበሩበት ወቅት የተሰዉበት ሞፈር ውሃ የተሰኘው ታሪካዊ ቦታም አብሮ ለሱዳን የሚሰጥ ይሆናል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሚያ እና የጋምቤላ ተወላጅ የሆኑ በድንበሩ ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸውን እንዲለውጡ ወይም አካባቢውን ለቀው ሊሰደዱ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው።
ከዚህ ቀደም እንዳልኩት የሕወሐት መሪዎች ትልቁ ችግራቸው ለሱዳን ተላልፎ የሚሰጠው መሬት የአማራና የኦሮሞ እንጂ የኛ አይደለም የሚል የዘረኝነት ልክፍት ውስጥ መግባታቸው ነው።
የህወሐት መሪዎች ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት ጉዳይ የተፈራረሙት እኛ ሳንሆን የቀድሞ የኢትዮጵያ ገዢዎች ናቸው ይሉናል ማስረጃ ግን አያቀርቡም ማስረጃ አቅርቡልንና እንመናቹህ
ወዳጆቼ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ በኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ከሕወሐት መሪዎች ውጭ ድንበሩን ለሱዳን ለመስጠት የተስማማ የኢትዮጵያ ገዢ የለም ሌላው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የምሆንላቹህ ዝም ብለን ከተቀመጥን በቅርቡ መሬት ለሱዳን ይሰጣል ያኔ ማፈር የሚኖርበት ሕወሐት ሣይሆን እኛ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን ነን።

No comments:

Post a Comment