ያልታደለው የጭልጋ ነዋሪ በወያኔና በኩሊዎች እየታመሰ ይገኛል፡፡ ከጥቅምት 20 ቀን በፊት የወያኔ ኩሊዎች ሌሊቱን ጀምሮ በአማራና በቅማንት መካከል ያለውን ሰላም ለማኮላሸት ‹‹ማተብ የሌለው ሀይማኖት መጣብህ፤ ሀይማኖት የሚያስቀይርህ መጣ፤ ልኩን አሳየው፤….ወዘተ. ›› የሚሉ የጠብ አጫሪ መልእክቶች ያሉበት ወረቀት ሌሊት፣ ሌሊት እየተበተነ ያድራል፡፡ ይህንንም በመቃወም የጭልጋ ወረዳ የኹሉም ት/ ቤቶች ተማሪዎች ተቃውሞ በመውጣት ሲገልጹ መሳሪያ ያነገቡ ወሮበሎች በመደብደብ፤ በማንገላታት፤ በማሰር፤…ልዩ ልዩ ግፎችን እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ እስር ቤቶች ጠበው በየግለሰብ ቤት ተከራይተው እያሰቃዩአቸው ይገኛሉ፡፡
በርካታ ሰዎች በስጋት ይገኛሉ፤ በርሃ ገብተው የተሸሸጉም ብዙ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል በዳባት ወረዳ 12 ቀበሌዎች ‹ግብር አንከፍልም›› በማለታቸው ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ሲኖሩ 2 ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል፡፡
አወን ወያኔ ከሃዲ በርካታ አወናባጅና እርስ በርስ የሚያባሉ ሰዎችን ለእንደዚህ ‹አላማ› ቀጥሮ እያሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ወያኔ ቀጥሮ ከሚያሰራቸው ሰዎች ውስጥ adam getaneh በሚል የፌስ ቡክ አካውንት የሚጠቀም ሙሉአዳም ጌታነህ የሚባል ሰው በላ አካይስት ገንዘብ ተመድቦለት ጎንደርና ጎጃምን፤ ወሎና ጎንደርን፣ አማራንና ኦሮሞን፤ክርስቲያንና እስላሙን፤….ወዘተ. ለማጣላት በተለያዩ ቦታወች እየተዘዋወረ ተልእኮ ተሰጥቶት ወረቀት የሚበትን፣ ወሬ የሚነዛ፣ ከፍተኛ ቅስቀሳ የሚያደርግ የሰይጣን ውላጅ ነው፡፡ምስሉ ይኸው
ጎበዝ ከምንም በላይ አንድነታችንን አጠናክረን ወያኔንና ጀሌዎችን መፋለም ግድ ነው፡፡ በምንም መልኩ ‹የከፋፍለህ ግዛውን› ዓላማ ማስፈጸም ድርብ ክህደት ነው፡፡ለዚህ በምንም በር መክፈት የለብንም! ቆርጠን በኅብረት ክንድ ወያኔንና ጄሌዎች ላይ እንረባረብ!!!
ርትእ- ንጽሮት
አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment