Monday, November 30, 2015

በሀረማያ ዩኒቨርስቲ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን የተቃወሙ ስልፈኞች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ።


በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዳይሆን የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ከነበሩ የኦሮሚያ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የፊዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ወደ ዪኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በመግባት ሶስት ተማሪዎችን መግደላቸውንና ብዙዎችን ማቁሰላቸው እየተሰማ ነው ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወልቃይት ቀፍታ በራሪ ፅሁፎችን በተሳካ ሁኔታ ለህዝቡ አሰራጭቷል፡፡


የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወልቃይት ቀፍታ፣ አድ ኸርዲ፣ አፀ ሐርማዝ፣ አድ ፀፀርና በሌሎችም ትንንሽ ከተሞች በመዘዋወር ለሁለት ተከታታይ ሌሊቶች በራሪ ፅሁፎችን በተሳካ ሁኔታ ለህዝቡ አሰራጭቷል፡፡
የአረበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት አርብ ሌሊት በወልቃይት ቀፍታና አድኸርዲ የድርጅቱ ዓላማና የትግል ጥሪ የታተመባቸውን ወረቀቶች በገፍ ለህዝቡ አድርሷል፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአፀ ኸርማዝና አድ ፀፀር በራሪ ፅሁፎችን ለህዝቡ የበተነው አሁን ያለፈው ቅዳሜ ሌሊት ነበር፡፡
በራሪ ፅሁፎቹ “እኛ አርበኞች ግንቦት 7 ነን!” የሚል ርዕስ አላቸው፤ “…እኛ ለነፃነትና ለፍትህ የቆምን፤ ለእኩልነትና ለአንድነት የተጋን፤ ለህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት እየደማንና እየሞትን የምንገኝ፤ የህዝብ ጭቆና እና ምሬት የወለደን አርበኞች ግንቦት 7 ነን…” የሚል ሀሳብም ይገኝበታል፡፡
በአራቱ ትንንሽ ከተሞችና በሌሎች መንደሮች በበራሪ ፅሑፎች መበተን በእጅጉ የተደናገጠውና የተረበሸው የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል በአካባቢው እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የህወሓት መከላከያ ሰራዊት የጦር አዛዦች በጥልቅ የጭንቅ ባህር ውስጥ ሰጥመው ሰራዊቱን ከበረሃ በረሃ እያንከራተቱት ነው፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወደ አይቀሬው ህወሓትን የመደምሰስ የመጨረሻ ፍልሚያ ሜዳ በፍጥነት እየተራመደ በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ ሀወሓትም እንዲሁ ወደ ተማሰው መቃበሩ በፍጥነት እያመራ ነው፡፡

ለሱዳን ሊሰጥ የታሰበው መሬት ጉዳይ አሁንም አወዛጋቢነቱን ቀጥሏል



በዳግማዊ አፄ ምንሊክ ዘመን በወቅቱ የሱዳን ቅኝ ገዢ የነበረችው የእንግሊዝ ተወላጅ የሆነው ጉዌን የተባለግለሰብ ያለማንም ፈቃድ የሱዳንን ካርታ አዘጋጅቶ ለእንግሊዝ መንግሥት ያቀረበ ሲሆን የእንግሊዝ ነገሥታቶች በካርታው ዙሪያ ከኢትዮጵያው ንጉሥ አጤ ምንሊክ ጋር ሳይስማሙ በመቅረታቸው የእንግሊዝ ፍላጎት ሳይሳካ ቀረ ሆኖም ጊዜ እና ዘመን ሲጠብቁ የኖሩት የሱዳን መሪዎች ፀሎታቸው ሰምሮ ኮትኩተው ያሳደጉት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ የቆመ ሕወሐት የተባለ መንግስት አገኙ ጫካ እያሉ እኔ የትግራይ ገዢ እንጂ የተቀረው የኢትዮጵያ መሬትን ጉዳይ እንደፈለጋችሁ በሚሉ ምክንያቶች ስምምነቶች ላይ የተፈራረሙ በመሆኑ ሕወሐት ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ ይህ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ቀን ሲጠብቁ ኖረው ዛሬ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ደርሰዋል።
ለሱዳን የሚሰጠው መሬት ከጎንደር ተነስቶ ኦሮሚያን ቆርሶ የጋምቤላ ምድር ድረስ የሚደርስ ሲሆን ርዝመቱ እስከ1600 ኪሎ ሜትር ይደርሳል ይህም ማለት ምን አልባት ከአዲስ አበባ ዳሕላክ ወደብ የሚደርስ መሬትን ያህል እኩሌታ ማለት ነው
ይህ የሚሰጠው መሬት ወደኢትዮጵያ ድንበር ከ47 እስከ 50 ኪሎ ሜትር የሚገባ መሆኑም ታውቋል ሌላው አስደንጋጩ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩት አጤ ቴዎድሮስ የተማሩበት ማህበረ ሥላሴ የተሠኘው ገዳምም በድንበር ማካለሉ ስምምነት ምክንያት የሱዳን አካል የሚሆን ሲሆን አፄ ዮሐንስ ከሱዳን ማህዲስቶች ጋር ጦርነት ላይ በነበሩበት ወቅት የተሰዉበት ሞፈር ውሃ የተሰኘው ታሪካዊ ቦታም አብሮ ለሱዳን የሚሰጥ ይሆናል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሚያ እና የጋምቤላ ተወላጅ የሆኑ በድንበሩ ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸውን እንዲለውጡ ወይም አካባቢውን ለቀው ሊሰደዱ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው።
ከዚህ ቀደም እንዳልኩት የሕወሐት መሪዎች ትልቁ ችግራቸው ለሱዳን ተላልፎ የሚሰጠው መሬት የአማራና የኦሮሞ እንጂ የኛ አይደለም የሚል የዘረኝነት ልክፍት ውስጥ መግባታቸው ነው።
የህወሐት መሪዎች ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት ጉዳይ የተፈራረሙት እኛ ሳንሆን የቀድሞ የኢትዮጵያ ገዢዎች ናቸው ይሉናል ማስረጃ ግን አያቀርቡም ማስረጃ አቅርቡልንና እንመናቹህ
ወዳጆቼ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ በኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ከሕወሐት መሪዎች ውጭ ድንበሩን ለሱዳን ለመስጠት የተስማማ የኢትዮጵያ ገዢ የለም ሌላው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የምሆንላቹህ ዝም ብለን ከተቀመጥን በቅርቡ መሬት ለሱዳን ይሰጣል ያኔ ማፈር የሚኖርበት ሕወሐት ሣይሆን እኛ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን ነን።

Saturday, November 28, 2015

ወያኔ ሰራሽ የርስበርስ ግጭት ድግሶችን እናምክን!

የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያ የተዋቀረችው በህዝብ ታሪካዊ አብሮነትና ተዛምዶ ላይ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰብ ልዩነቶችን በማጥበቅና ልዩነትንም የርስበርስ ጥርጣሬና ግጭት ምንጭ እንዲሆን በማለም ነው። ልዩነት የግጭትና የጠብ ምንጭ እንዲሆን ተደርጎ ነው የተዋቀረውና ብፖለቲካ ደረጃ የተገፋው። አንዱ ብሔረሰብ ሌላው ብሔረሰብ ክልል ውስጥ ሲሆን ባዕድነት እንዲሰማውና እንዲሰጋ አንዱ አንዱን በጥርጣሬ እንዲመለከተው ተደርጎ ነው ሀያ አራት አመት ሙሉ የተገፋውና እየተገፋ ያለው።
ይህም ሆኖ በዘመነ ወያኔ በየቦታው የተከሰቱ የብሔር ሌብሔርሰብ ግጭቶች በሙሉ የተቀሰቀሱት በራሱ በመንግስት ባለስልጣኖች እንጂ መቼም ህዝብ ለሕዝብ ሆኖ አያውቅም። በተለያዩ የደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች አማሮችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ለማባረር የተወሰዱት ርምጃዎች ራሳቸው ሰለባዎቹ እንደሚናገሩት ለስቃይ የዳረጋቸው ነዋሪው ሕዝብ ሳይሆን ባለስልጣናቱ መሆናቸውን በግልጽ ሲናገሩ ሰምተናል።
በቤኒሻጉልና ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሰሞኑን ይፋ መሆኑ የተነገረው በአስቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተቀብረው የተገኙ አማሮች አስከሬን መገኘቱ ታውቋል። ይህም ወያኔ ባስለጠናቸውና ባዘዛቸው ካድሬዎችና ባለስልጣኖች የተከወነ እንጂ በሕዝብ ተነሳሽነት የተፈጸመ አለመሆኑ የታወቀ ነው። ቀደም ሲል በመንግስት ደረጃ የተቀነባበረ አማሮችን የማፈናቀል ዘመቻ ተከታይ ስራ መሆኑን ለማወቅ ብዙ አዳጋች አይደለም። በወገኖቻችን ላይ በሚዘገንን መንገድ የተፈጸመው ግፍ ዘልቆ ይሰማናል:: ሊሰማንም የገባል። ቁጭታችንና ሀዘናችን ግን ወያኔ ወደሚፈልገው የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ምክንያት እንዳይሆን ከፍተኛ ትዕግስትና ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
ሰሞኑን በታሪክ ሊዘገብ ከሚችል ልዩነት ውጭ ባኗኗር በባህልና ቋንቋ የማይለያዩትን የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች ቅማንትና አማራ በሚል ለማጋጨት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ሰይጣናዊ አካሔድ በወያኔ የፖለቲካ ተንኮል እየተመራ እንዳለ የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች አሉ። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉም ካላንዳች መድሎና ልዩነት ሀገሪቱ ላይ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ሁሉም በየበኩላቸው የሚያደርጉትን ጥረትና ትግል እንደግፋለን። በህዝባችን መካከል ያሉት ግንኙነቶች ሊሆን የሚችለው እንዱ አንዱን የማገዝ እንጂ ርስበርስ የመጋጨትም ሆነ የመናቆር አይደለም።
ኢትዮጵያውያን ብሄርና ዘር ሳንለይ ይህንን የወያኔ ተንኮል ችግሩ ወደባሰ ደረጃ ሳይሄድ መቋቋምና ማክሸፍ ይጠበቅብናል። ይህ ታሪክነታችንና ታላቅ ሕዝብነታችንን የማይመጥን አሳፋሪ የወያኔ ፖለቲካ እንደሀገር እንዳያጠፋን ሁላችንም በንቃትና በቁርጠኝነት መቋቋም ይኖርብናል።
አርበኞች ግንቦት ፯ ልዩነት ጌጥ እንጂ የጠብና የግጭት ምክንያት የማይሆንባት ሀገር ፥ የየብሔረሰቡ መብት ሁሉ የይስሙላ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠባት ሀገር ፥ ከነልዩነታችን በጋራ ራዕይ የምንተሳሰርባትና የምንገነባት ሀገር እንድትኖረን የሚያደርገውን ትግል ይቀጥላል። የቻልክ በአካል ተቀላቀለን። ያልቻልክ በያለህበት የወያኔ ዘራፊዎች ያሰቡትን የተንኮል ጉንጉን በመበጣጠስ ተሳተፍ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

በአዲስ አበባ ስራቸውን ለመልቀቅ ማመልከቻ ያስገቡ ፖሊሶች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።


የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ስራቸውን ለመልቀቅ ማመልከቻ ያስገቡ ፖሊሶች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።7 አመት ያላገለገሉ ፖሊሶች ያገለገሉበት ዘመን ታስቦ ገንዘብ ከፍለው የሚሰናበቱ ሲሆን፣ ይህንን ክፈተት በመጠቀም ብዙዎች ስራውን እየለቀቁ ሄደዋል። ከፖሊስ የሰው ሃይል ክፍል የደረሰን አስተማማኝ መረጃ እንደሚያሳያው መልቀቂያ አስገብተው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ፖሊሶች 1 ሺ ይደርሳሉ። ብዙዎች ለመልቀቃቸው የሚሰጡት ምክንያት ከስራ ጫና፣ ከአስተዳደር፣ ዘረኝነትና ከደሞዝ ጋር የተያያዘ ነው። ለቃቂ ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ሊቀላቀሉ ይችላሉ የሚል ስጋት የገባው መንግስት ሰሞኑን ለአመታት ላገለገሉ ፖሊሶች የአግልግሎት ሰርተፊኬት በመስጠት ፍልሰቱን ለማስቆም እየተሯሯጠ ነው። ሰሞኑን በተሰጠው የአግልገሎት የምስክር ወረቀት አንዳንድ ፖሊሶች ከ1 እስከ አራት ወራት ያሉ ደሞዛቸውን በስጦታ መልክ ተቀብለዋል። ይሁን እንጅ ሽልማቱ የመልቀቂያ ጥያቄ የሚያቀርቡ ፖሊሶችን ቁጥር ሊቀንሰው አልቻለም። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ፖሊስ ፣እሱ በሚሰራበት ወረዳ በርካታ ፖሊሶች በመልቀቃቸው የስራ ጫና መፈጠሩንና በአለቆች ላይ ግምገማ መጀመሩን ተናግሯል። አማራጭ ቢያገኝ ስራው ላይ የሚቆይ ሰው አይገኝም ሲልም በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ገልጿል።

Wednesday, November 25, 2015

የባለ 11% እድገታችንና ብቃት የለሽ አስተዳደር ያስከተለው ረሃብ

ሀገራችን ላለፉት ሃያ አራትት አመታት ስለልማቷ፣ ስለእድገቷ ብዙ ተብሏል፥ እየተባለም ይገኛል። ሆኖም ግን አደገች፣ በለጸገች እየተባለ ይነገረን እንጂ ሕዝቧ/ዜጎቿ ከጊዜ ወደ ጊዜ ኑሯችን እያሽቆለቆለ፣ ፍትህ እየተዛባ፥ መብት እየተረገጠ አስከፊ ችግር ውስጥ ተዘፍቀን እንገኛለን። የሀገራችን እድገት ምስክሮች እኛውና የኛው ኑሮ መሆኑ ቀርቶ ሌሎች አውሮፓውያኖችና ለጋሽ መንግስታት ‘ለመንግስታችን’ እየመሠከሩለት፣ ወያኔም ምሥክርነታቸውን እንዳረጋገጡለት ለኛ መልሶ በቴሌቪዥንና በሬድዮ ቀንና ማታ ያደነቁረናል።
ሃገራችን ችግር ላይ ነች ብለን ስንል የታየንንና የተረዳነውን ገሃድ አውጥቶ መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ ለህዝብና ለሃገር በማሰብ እንጂ እንደወያኔ በአግድም ወይንም የተገላቢጦሽ አተረጓጎም በሃገርና በህዝብ ላይ ችግር መፍጠር ወይንም ህዝብን ለአመጽና ለብጥብጥ ማነሳሳት ወይንም መጋበዝ ማለት አይደለም።
መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠው ስብስብ የተሞላው በራስ ወዳዶች፣ ብልጣ ብልጦች፣ አስመሳዮችና የህዝብ ችግርና ሰቆቃ በማይሰማቸው ግለሰቦች ነው። ይህንን የሃገራችንን ችግር ከነችግር ፈጣሪዎቹ ልቅምቅም አድርጎ ማስወገድ የማናችንም ሃገር ወዳድ ዜጋ ሃላፊነትና ግዴታ ነው።
በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የኋሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ወያኔ ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ አስተሳሰብና የሃይል አምባገነናዊ አገዛዝ ተሸብቦ ያላስነባው ህዝብ፤ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፤ ያላፈረሰው አንድነት፤ ያላዋረደው የህዝብ ስብዕና፤ ያልገባበት የእምነት ተቋም፤ ያልበተነው የሞያ ማህበራት፤ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም::
ባለፉት አመታት በወያኔ አገዛዝ በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገውን ትግል ለማኮላሸት እርስ በርሱ የሚቃረኑ ህጎችና መመርያዎችን አርቅቆ እያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ አንገላቷል፤ ገድሏል፤ ለማምለጥ የታደሉትንም ከአገር በግፍ እንዲሰደዱ አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት በሃገራችን በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ለሚገኘው ረሃብና ድርቅ ዋና መንስዔዎች የተፈጥሮ አየር መዛባት ብቻ ሳይሆን በዋናነት የመልካም አስተዳደር እጦት ነው፡፡ የችግሩ መንስዔ አንኳር ችግር በየደረጃው የሚገኘው የመንግስት አካላት ሃገርንና ህዝብን በሰለጠነ መንገድ ለማስተዳደር ብቃት የለሽነት እና ብልሹ አስተዳደር እንጂ ባለስልጣናቱ እንደሚደሰኩሩት አካባቢያዊ ነገሮች አይደሉም፡፡
በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እስከዛሬ እየተከሰተ ያለው ረሃብ ከተፈጥሯዊነቱ ይልቅ ሰው ሰራሽነቱ ነው የሚያመዝነው፡፡ ይህም ማለት ለረሃቡ መንስዔ ሙስና፣ ብልሹ አስተዳደር፣ የሙያ እና የአስተዳደር ብቃት የለሽነት እና በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ችግር ለማስወገድ የሚያስችል የፖለቲካ ፈቃደኝነት እና ፍላጎት የሌለው አምባገነን እና ጨካኝ ዘረኛ መንግስት በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጦ የመገኘቱ ሁኔታ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን እርካብ ላይ ተንጠልጥለው የሚገኙት ቡድኖች ትክክለኛ ለሆነ ዕቅድ እና ለህዝቦች ደህንነት ጠቀሜታ ያላቸውን ፖሊሲዎች ለመንደፍ የማይችሉ፣ ህዝብን በዘርና በቋንቋ በማበጣበጥ እድሜያቸውን ለማራዘም የሚፈልጉ ጠባቦች፣ ሀሳበ ግትር እና ለተሻለ ለውጥ በምንም ዓይነት መልኩ ዝግጁ ያልሆኑ የጫካ ወሮበላ የአስተሳሰብ አድማስን የተላበሱ ፍጡሮች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ሃገራችን ሀሳብን በነፃነት ያለፍርሀት መግለፅ የማይቻልባት፤ የዜጎች የኑሮ ደረጃ ከዕለት ዕለት እየተባባስ የሚሄድባት፤ ዘመናዊ የመረጃ መገናኛዎች ሆን ተብለው የታገዱባት፤ የህዝቦቿን ጥንታዊና ብርቅዬ የሆነውን መከባበርና አንድነት በዘር ጥላቻና በሀይማኖት ለመከፋፈል አገዛዙ የሚጥርበት፤ ዜጎች አለአግባብ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት፤ ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰደዱባት፤ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያልተካሄድባት፤ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉባት፤ ለሕግ ተገዢ ያልሆነ መንግሥት ያለባት፤ ዜጎች የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር በነፃነት ሠርተው መኖር የማይችሉባት፤ ነፃ ሚዲያ የሌለባት፤ ዜጎች ለሀብት ንብረታቸው ዋስትና የማያገኙባት፤ ህዝባዊ መንግሥት የሚናፍቅ ህዝብ ያለባት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት የገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ መጠቀሚያ የሆኑባት፤ ቤቶች በቁመታቸው ማደጋቸው እንደዕድገት የሚቆጠርባት ሀገር ሆናለች። ስለሆነም ኢትዮጵያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማድረግ ለነፃነት፣ ለፍትህ እና ለእኩልነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ስለዚህ ኢትዮጵያውያን የአንድነት ሃይሎች በመተባበር፣ በመጣመርና በመዋሃድ ሃይልን፣ እውቀትን፣ ህብረትን እንዲሁም ገንዘብን በማቀናጀት የወያኔን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብር ለአንዴና ለመጨረሻ አሸቀንጥሮ ወርውሮ ሃገርንና ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርዓቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬንና ህዝቤን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የበኩሌን ሃሳብ ለማቅረብ እወዳለሁ::

Monday, November 23, 2015

በጎጃም ሸበል በረንታ ወረዳ ባመጹ አርሶ አደሮችና በመንግስት ሃይሎች መሃል ዛሬ ጠንከር ያለ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ።


በጎጃም ሸበል በረንታ ወረዳ ባመጹ አርሶ አደሮችና በመንግስት ሃይሎች መሃል ዛሬ ጠንከር ያለ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። ከወራት በፊት መሳሪያቸውን ይዘው ወደ ጫካ የሸፈቱትን አርሶ አደሮች ለማጥቃት ሲንቀሳቀስ የነበረው የመንግስት ሃይል ዛሬ በአንሻቢና ቀበሌ አድፍጦ በመጠበቅ በአርሶ አደሮቹ ላይ ተኩስ በመክፈቱ ግጭቱ ሊቀሰቀስ መቻሉ ታውቋል። በእስከአሁን የሸበል በረንታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ አባትይሁን አስረስ መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ሁለት ፖሊሶችም ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል። ከአርሶ አደሮቹ አስናቀ የምወደውና ለጊዜው ስማቸው ያልተገለጹ አርሶ አደር በግጭቱ መገደላቸው ተገልጿል።ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተኩስ ልውውጡ ቀጥሏል። በተመሳሳይ በጎንደር ጭልጋ ሳምንታት ያስቆጠረው አለመረጋጋት በአርሶ አደሮች አመጽ ተባብሷል። የመንግስት ሃይሎች ከሸፈቱ አደሮች ጋር በጭልጋ ግጭት ውስጥ መሆናቸው ታውቋል። በአከባቢው ትምህር ቤቶች እንደዘጉም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ሁኔታውን በመከታተል ተጨማሪ መረጃዎችን እናቀርባለን።

ህወሓት ክብሩ አሰፋን ረሸነው!


ክብሩ አሰፋ ተወልዶ ያደገው በጎንደር-ታች አርማችሆ ማሰሮ ደንብ ነው፡፡ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ዕድሜ ላይ የሚገኘው ክብሩ አሰፋ የጀግኖቹ አርበኞች አታለል አሰፋና ክፈተው አሰፋ ታናሽ ወንድም ነው፡፡
ጀግናው አርበኛ አታለል አሰፋ በ1994 ዓ.ም ወደ በረሃ ወጥቶ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተቀላቀለ ሲሆን በወልቃይትና በአርማጭሆ ለባንዳው የህወሓት ሰራዊት የእግር እሳት በመሆን መውጫና መግቢያ ነስቶታል፡፡
አርበኛ አታለል አሰፋ ከልቡ አርበኛ ነበር፤ አርበኛ አታለል አሰፋ እጅግ ጀግና ተዋጊ ነበር፤ አርበኛ አታለል አሰፋ ብልህ የጦር መሪና ጀግና አዋጊ ነበር፡፡
አርበኛ አታለል አሰፋ በደሙ ከፃፋቸው አስደማሚ የአርበኝነት ታሪኮቹ፣ አስደናቂ ጀግንነቱና አንፀባራቂ ጀብዱው መካከል 150 አርበኞችን እየመራ ተከዜን ተሻግሮ ሚያዚያ 16 1998 ዓ.ም አርማጭሆ ጎደቤ ላይ ሰፍሮ ይገኝ በነበረው የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ጠንካራ ምት በማሳረፍ የጦር ሰፈሩን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ በርካታ ቁጥር ያለው ወታደርና ዲሽቃ መማረኩ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡
ጀግናው አርበኛ አታለል አሰፋ ለአራት ተከታታይ ቀናት የህወሓትን ሰራዊት አያራወጠ በእሳት አለንጋ በመግረፍ ሲፋለም ቆይቶ ሚያዚያ 20 1998 ዓ.ም ስናር ላይ በጀግንነት ወድቆ ውድና ክቡር ህይወቱን ለአገሩ ኢትዮጵያና ከጎኑ ተሰልፈው ይዋጉ ለነበሩት ለሚመራቸው 150 ጓዶቹ ሲል ከፈለ፡፡ ስሙ ከአርማጭሆ እስከ ወልቃይት ገኖ ተሰማ፤ ጀግንነቱ በስናርና ቋራ በረሃዎች አስተጋባ፤ የአርበኝነት ድምፁ በኤርትራ ምድረ በዳዎች ሁሉ ከፍ ብሎ አስገመገመ፡፡
አርበኛ ታጋይ ክፈተው አሰፋ፤ እሱም ጀግና ብቻ እንዲፈጥር ከታደለው አርበኛ አታለል አሰፋ ከወጣበት ማህፀን የበቀለ ነው፡፡ አርበኛ ታጋይ ክፈተው አሰፋ የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከተመሰረተ ከአንድ ወር በኋላ በ1993 ዓ.ም በረሃ ወርዶ የአርበኝነቱን ጎራ ተቀላቀለ፡፡ አርበኛ ታጋይ ክፈተው አሰፋ 1995 ዓ.ም……. ዘመን መሪቅ ላይ ከባንዳው ህወሓት ሰራዊት ጋር በጀግንነት ሲፋለም እጁ ላይ በጥይት ተመትቷል፡፡ በተጨማሪም 1996 ዓ.ም አቡጢር ላይ አርበኝነትን ሲያፋፍም በድጋሜ እግሩ ላይ ተመትቶ ቆሰለ፡፡ ከዚያም በሱዳን ምድር ተጠልሎ ቁስሉን በመታከም ላይ እያለ የሱዳን ደህንነቶችና የፀጥታ ኃይሎች ለህወሓት አሳልፈው ሰጡት፡፡
አርበኛ ታጋይ ክፈተው አሰፋ ሰቆቃ እየተፈፀመበት በህወሓት ወህኒ ውስጥ ሲማቅቅ ለሦስት ዓመታት ከቆየ በኋላ በ2000 ዓ.ም ተመልሶ የአርበኝነት ትግሉን ተቀላቀለ፡፡ አርበኛ ታጋይ ክፈተው አሰፋ በእስር ባሳለፋቸው ሦስት ዓመታት ውስጥም የፖለቲካ እስረኞችን በህቡ በማደራጀት የጎንደሩን ግዙፍ ባህታ ወህኒ ቤት የመስበር ሙከራ አድርጓል፡፡ አርበኛ ታጋይ ክፈተው አሰፋ ዛሬም በአርበኝነት ሜዳ ላይ ይገኛል፡፡
ክብሩ አሰፋ የእነዚህ ጀግኖች አርበኞች ታናሽ ወንድም በመሆኑ የህወሓት የበቀል በትር ገላው ላይ አረፈ፡፡ ክብሩ አሰፋ ወንድሞቹ ባካሄዱትና እያካሄዱት በሚገኙት አርበኝነት ምክንያት በበቀል ስሜት ብቻ በተነሳሳው ህወሓት በ2002 ዓ.ም በደህንነት ታፍኖ ወደ ወህኒ ተወረወረ፡፡ ሰቅጣጭ የምርመራ ድርጊትም ተፈፀመበት፡፡ ቀጥሎም የፈጠራ ክስ ተመስርቶበት የይስሙላሁ የህወሓት ፍርድ ቤት የ18 ዓመት አስር በየነበት፡፡ በመጨረሻም ክብሩ አሰፋ 6 የመከራ ዓመታትን በአሰቃቂ እስር ካሳለፈበት ወህኒ በነሀሴ ወር 2007 ዓ.ም ድንገት ተሰወረ፡፡ ወላጆቹ “ልጃችን ክብሩ የት ደረሰ?” በማለት የጎንደሩን ባህታ ወህኒ ቤት ቢጠይቁ “ሸዋ ሮቢት ሂዱና ፈልጉት” የሚል ምላሽ ተሰጣቸው፡፡ ጀግኖች አርበኞች አታለል አሰፋንና ክፈተው አሰፋን ከአብራካቸው ከፍለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት መሰዋእት ያቀረቡት የክብሩ አሰፋ ወላጆች ለሦስት ወራት ከአገር አገር እየተንከራተቱ የህወሓትን እስር ቤቶች አዳረሱ፡፡ ነገር ግን ልጃቸውን ክብሩን ፈፅሞ ሊያገኙት አልቻሉም፡፡
ክብሩ አሰፋ በነሀሴ ወር 2007 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ በህወሓት ደህንነቶች ከታሰረበት አዳራሽ እንደተወሰደ አብረውት የነበሩት ታሳሪዎች መስክረዋል፡፡ ህወሓት ከደርግ የከፋ ረሻኝና በቀለኛ ሆኗል፡፡
ጀግናው አርበኛ አታለል አሰፋ ለኢትዮጵያ ነፃነት ስናር ላይ በጀግንነት ወደቀ፡፡ አርበኛ ታጋይ ክፈተው አሰፋ እሱም እንደ ወንድሙ ለአገሩ ነፃነት ህይወቱን ሊከፍል ጦር ሜዳ ውስጥ ይገኛል፡፡ ክብሩ አሰፋን ህወሓት የበቀል ጥሙን ለማርካት ሲል ብቻ በግፍ ረሸነው፡፡ እናት ያለሀኪም እርዳታ ብቻዋን አምጣ ወልዳ ፍዳዋን ከፍላ ያሳደገቻቸውን ሦስት ወንድልጆቿን በባንዳው ህወሓት አጣች፡፡
Ethio Hagere's photo.
Ethio Hagere's photo.Ethio Hagere's photo.

Friday, November 20, 2015

ከለጋሾች የተሰጠው አልሚ ምግብ በአግባቡ እየተከፋፈለ እንዳልሆነ በዛሬው ዕለት ከቦታው የደረሰን መረጃ አጋልጧል፡፡


ከለጋሾች የተቸረው የህፃናት አልሚ ምግብ ከቦታው መድረሱን ያረጋገጡት የሰባት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጎስቋላ ገበሬ እናቶች ልጆቻቸውን አንዱን በጀርባቸው አዝለው ሌላኛውን በደረታቸው ታቅፈው በዛሬው ዕለት ከየቀዬዎቻቸው ወደ ገደብዬ ከተማ ሲጎርፉ የዋሉ ሲሆን በጣት ከሚቆጠሩት እጅግ በጣም ጥቂት እድለኞች በስተቀር ሁሉም ለማለት በሚቻል ሁኔታ አልሚ ምግቡ ሳይሰጣቸው ከረሃብና ከችጋራቸው በላይ መንገድ ብቻ ተመትተው ተመልሰዋል፡፡
አልሚ ምግቡን እንዲያከፋፍሉ የተመደቡት የህወሓት-ብአዴን ካድሬዎች በዓይኖቻቸው ብቻ በመመልከት “ህፃናቱ ስላልተራቡ አልሚ ምግቡ በፍፁም አያስፈልጋቸውም” እያሉ ወላጆችን በቁጣ ጭምር በመገሰፅ ባዶ እጃቸውን እንደመለሷቸው ታውቋል፡፡ ነገር ግን አልሚ ምግቡን ለመቀበል በመጡ እናቶች ጀርባ ላይ ተጨባብጠው ይታዩ የነበሩት ህፃናት በሙሉ በረሃብ ጠውልገው አካላቸው የከሳና ዓይኖቻቸው የጎደጎዱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከባለፀጋዎች በምፅዋት የሚገኙትን አልሚ ምግቦች በተለይም ደግሞ “ፕላምፕኔት” ሸጦ ገንዘቡን ለግል ጥቅም ማዋል በወረዳው የህወሓት-ኢህአዴግ ካድሬዎች ዘንድ የተለመደ እጅግ በጣም አሳፋሪ ተግባር እንደሆነ እና አሁንም ተከማችቶ የሚገኘው አልሚ ምግብ ለተራቡ ህፃናት የተነፈገበት ዋና ምክንያት ሸጦ የግል ኪስን ከማድለብ በማለም እንደማይዘል ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የህወሓት-ብአዴን ካድሬዎች ለተለያዩ የፖለቲካ ተልዕኮዎች ወደ ገጠር ሲላኩ ለድሆች በምፅዋት የተገኘውን “ፕላምፕኔት” ስንቅ ቋጥረው አዘውትረው ሲመገቡት መመልከታቸውን በድርቁ የተጎዱ ገበሬዎች መስክረዋል፡፡
በወገራና በዳባት ወረዳዎች 9 ቀበሌዎች ለከፋ ድርቅና ረሃብ መጋለጣቸውን በቅርቡ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
Shagiz Shagi's photo.Shagiz Shagi's photo.

Swedish journalists recount their horrific experience in Ethiopia 1

Thursday, November 19, 2015

እነ የሺዋስ አሰፋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መልዕክት አስተላለፉ


‹‹ርሃቡን ለዓለም ለማሳወቅ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራት አለበት››
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለህዝብ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ መልዕክቱን ያስተላለፉት በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙት የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ ሲሆኑ በተለይ ርሃቡ ለዓለም ማህበረሰብ እንዲታወቅ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበረሰቦች፣ ሚዲያውና ሌሎችም የቻሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አደራ ብለዋል፡፡
በተለይ ከመንግስት ርሃቡን የመደበቅ ባህሪ አንፃር በሌሎች ኢትዮጵያውያን በኩል ርሃቡን ለዓለም ለማሳወቅ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ ‹‹በርሃቡ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት መጥፋት አልነበረበትም›› ያሉት የፖለቲካ አመራሮቹ መንግስት ተራበ በተባለው ህዝብ ቁጥር ጨዋታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ለተራቡት መድረስ እንደነበረበትም ገልፀዋል፡፡ መንግስት የተራቡትን ቁጥርና መረጃ ስለሚደብቅም ኢትዮጵያውያን ርሃቡን ለዓለም በማሳወቅ እርዳታ እንዲገኝ ከማድረግ ባሻገር እርዳታ በማሰባሰብ ሊያግዟቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ከርሃቡ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ መልስ አለማግኘቱን፣ ህገ ወጥ የእስረኛ አያያዝ፣ የፍርድ ቤቶች ገለልተኛ አለመሆንና በአጠቃላይ የፍርድ መጓደልን በስፋት ያነሱት ሲሆን እነዚህ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው በጠነከረ መልኩ ወደ አደባባይ መውጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ችግሮችና ጭቆና ቢኖርም አጀንዳ ሆኖ መታገያ እየሆነ አይደለም ሲሉ ትዝብታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎችም መንገዶች አጀንዳዎቹ ለህዝብ መድረስ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡

ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ እና መሳይ ደጉሰው ጥፋተኛ ተባሉ


አይ ኤስ በኢትዮጵውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ድርጊት ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ እና መሳይ ደጉሰው ዛሬ ህዳር 8/2008 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመናገሻ ምድብ ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
ችሎቱ በቢሮ ከመታየቱም ባሻገር ችሎት አስከባሪው ‹‹መግባት አይቻልም፡፡ ተከልክሏል፡፡ የከለከልኩት ግን እኔ አይደለሁም፡፡›› በማለቱ ማንም እንዳይገባ ተከልክሎ በዝግ ታይቷል፡፡ ፖሊስ ተከሳሾቹ ላይ የቪዲዮ ማስረጃ አለኝ በማለቱ ተከሳሾቹም ‹‹የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም በመከላከያ ማስረጃነት ስለሚያገለግለን ይቅረብልን›› ባሉት መሰረት ቪዲዮውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለወራት ሲቀጠርባቸው ቆይቷል፡፡
ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት ተከሳሾች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ተከሳሾቹ ከታሰሩ ከ6 ወር በላይ የሆናቸው ሲሆን በፍርድ ሂደቱ ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ እነ ማቲያስን ጥፋተኛ ያለው ፍርድ ቤቱ ለህዳር 22/2008 ዓ.ም ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
Netsanet Beqalu Mannet's photo.

ወያኔ ዛፍ እና አፋሮች:.ወያኔ ዛፍ


አፋሮች ይህን ዛፍ የሚያውቁት ወያኔ አካባቢውን ከተቆጣጠረ በኋላ ነው። ዛሬ ይህ ዛፍ ሌሎች ሃገር በቀል ዛፎችን እየገፋ የአፋር ክልልን ማጥለቅለቁ እና ለቁጥጥርም አዳጋች መሆኑ ይነገራል። አፋሮች ዛፉን ‘ወያኔ ዛፍ’ ይሉታል።ይህዛፉ አፋር ክልልን ተሻግሮ ሌሎችንም እንዲህ እያዳረሰ ወይም እንዲዳረስ እየተደረገ ነው። ወያኔ ዛፍ ግንዱ ሳይቀር ትልልቅ እሾህ ያለበት ዛፍ ሲሆን ቅጠሉን ግመልም ሆነ ሌሎች እንስሳት አይበሉትም። ይህን ዛፍ የአካባቢው ሰዎች ለከሰል ስራ አገልግሎት ቢያውሉትም ከሰሉ ግን እስከዚህም እንደሆን ሰምቻለሁ።
እውነቱን ለመናገር ወያኔ ዛፍ ያምራል። ይህም ሆኖ ዛፉ በስሙ እንዲሆን ያልፈለገው ወያኔ ግን የግብርና ባለሙያዎቹን እያሰማራ የዛፉ ስም ‘ደርጊ ሃራ’ ነው ማስባል ከጀምረ ቆይቷል። አፋሮች እና ዛፉ በሚበዛበት አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦች ግን ይህን ዛፍ እና ወያኔን የምናውቀው በተመሳሳይ ወቅት ስለሆነ የደርግ ሳይሆን “የወያኔ ዛፍ ነው!” ማለቱን እንደቀጠሉ ነው። የሚገርመው ማህበረሰቡን አስተምረው ስሙን እንዲያስቀይሩ ደሞዝ ከሚከፈላቸው አንዱ የግብርና ባለሙያ እራሱ በማህበረሰቡ ተቀይሮ ‘ይህ የወያኔ ዛፍ ይባላል።’ ብሎ ለብዙ ጊዜ በስም የማውቀውን ዛፍ ትናንት በአካል አስተዋውቆኛል። ለማታውቁት ደግሞ እኔም የወያኔን ዛፍ ይሄው አስተዋወቅኋችሁ።

የወልቃይት ህዝብ የወያኔ ስርሃትን ለመታግል በአንድነት መነሳቱ ታወቀ


የወልቃይት ህዝብ ህወሓት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍና በደል ያደረሰበት በመሆኑ መቸም የማይፈታ ቂም አለው፡፡ ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ደግሞ ሳይፈልግ ከጎንደር እንዲገነጠል ተደርጎ ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለሉ ሲያነሳው የቆየው ያልተመለሰ ጥያቄ አለው፡፡
ህወሓት የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የጀመረውን የነፃነት ትግል እንቅስቃሴ ጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ለመደፍጠጥ ወደ አካባቢው ያለማቋረጥ ሰራዊት እያዘመተ አሰቃቂ የህዝብ ጭፍጨፋ በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡
ሆኖም ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ በጥይት በመግደል ዝም ማሰኘት ሳይችል ቀርቶ ዛሬ የበለጠ ተደራጅቶበት ጠብመንጃውን ወልውሎ በአንድነት ተነስቷል፡፡ ወደ በረሃ እየወረደ አርቨኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን አርበኝነት የሚቀላቀለውም ከዕለት ዕለት ቁጥሩ በእጅጉ አይሏል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ የወልቃይት ሰው ማር ዘነብ ልዩ ቦታው ቴፍ ላይ በመሰባሰብ ስለነፃነቱ መክሯል፤ የትግል መሪዎቹንም መርጧል፡፡ በጉባኤው ላይ የአርማጭሆ ህዝብም ተገኝቶ በጋራ ጠላታቸው ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያሳርፉ ቃል ተገባብተዋል፡፡

( በእውቀቱ ሥዩም ) ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ቦታ የምታገኘው መንግስትን ብቻ ነው


እንግሊዝ ሀገር በሄድኩ ጊዜ የዛሬ ስንት እና ስንት መቶ አመት አካባቢ ሼክስፒር በጠጣበት ቡና ቤት ጠጥቼ ሼክስፒር በሸናበት ታዛ ስር ሸንቼ ወደ ሀገሬ የመመለስ ዕድል ገጥሞኛል።
.
ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ያለ ዕድል ማግኘት አይታሰብም። ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ቦታ የምታገኘው መንግስትን ብቻ ነው።
.
ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ከሳምንት በፊት ጤና ጣቢያ የነበረው ከሳምንት በኋላ ፖሊስ ጣቢያ ሆኖ ታገኘዋለህ እናም በሽተኛ ለመጠየቅ ያመጣኸውን ፍራፍሬ እስረኛ ጠይቀህበት ትመለሳለህ።
በዚህ አይነት:-
ከሳምንት በፊት ሙዚየም ከሳምንት በኋላ ጅምናዚየም።
.
ከሳምንት በፊት ላይብረሪ ከሳምንት በኋላ እኔ ነኝ ያለ ግሮሰሪ።
.
የሰውም ለውጥ ፍጥነት እንዲሁ ነው:-
ከወር በፊት ተላላኪ ከወር በኋላ አስመጭና ላኪ።
.
ከአመት በፊት የከባድ መኪና አሽከርካሪ ከአመት በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ።
ከአመት በፊት አድማ በታኝ ከአመት በኋላ የኳስ ተንታኝ ሆኖ ታገኘዋለህ።
.
በነገራችን ላይ የኳስ ነገር ሲባል አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ከሶስት ወራት በፊት መሰለኝ በአትሌቶችና በባለስልጣናት መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም የኳስ ግጥሚያ ተደርጎ ነበር። እና ኮመንታተሩ አትሌቶች ኳስ ሲይዙ
‘ኦ ••••• ቀነኒሳ ኳስ በእጁ ነክቷል አደገኛ ስህተት ‘ እያለ ትችት ሲያዘንብባቸው ይቆይና ባለስልጣኖች ኳስ ሲይዙ ይቅለሰለሳል።
.
.
‘አሁን ጀነራል ኳስ ይዘዋል ‘ ። ጀነራል አታለው አለፋ ለማለት ፈለገና አታለው የሚለው ቃል ክብር የሚነካ ስለመሰለው ጀነራል መስዋዕትነት ከፍለው አለፉ …..

በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ አምስት ቀበሌዎች በድርቅ መጠቃታቸው ታወቀ፡፡



በከፍተኛ ድርቅ ተመትተው ነዋሪዎቻቸው ክፉኛ ለጠኔ ተጋልጠው የሚልሱት የሚቀምሱት በማጣታቸው ከሞት አፋፍ ላይ ሆነው የሚገኙባቸው አምስቱ ቀበሌዎች ጨጨሆ፣ ፈንጠርያ፣ ቀንጠብጣ፣ አይጠላ እና እንድ ሌላ ለጊዜው ስሙን ያላወቅነው ቀበሌ ናቸው፡፡
በሰሜን ጎንደር የወገራ ወረዳዎቹን ሶሚያ፣ ጓሪ፣ ግጭሆ እና ቧግሽ የተባሉትን አራት ቀበሌዎች ጨምሮ እስካሁን ዘጠኝ ቀበሌዎች ክፉኛ በድርቅ ተመትተው ከ50ሺህ እስከ 60 ሺህ ህዝብ ተርቦ የስደትና ዕልቂት ደመና እያንዣበበበት ይገኛል፡፡
አገዛዙ ለፖለቲካ ወሬ ፍጆታው ለስሙ እንዲ አደረግሁ ለማለት ብቻ 10ሺህ ኩንታል በቆሎ ችፋንዝ ላይ ያራገፈ ሲሆን ከ9-10 ቤተሰብ ለሆነ ከ10-15 ኪሎ ግራም በቆሎ ብቻ እየታደለ ይገኛል፡፡ ይህም ለአንድ ቀን ምሳ እንኳን የሚበቃ እንዳልሆነ የረሃቡ ሰለባዎች ብሶታቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
እንዲሁም ለእርዳታ ችፋንዝ ላይ የተራገፈው በቆሎ በአንድ መጋዘን ውስጥ አንድ ላይ መከማቸት ሲገባው በየግለሰቦች መኖሪያ ቤት በመከፋፈል ተከማችቶ ለወዛደርና ለቤት ኪራይ በሚል ሰበብ እየተቀነሰ በሰፊው እየባከነ ይገኛል፡፡
ለእርዳታ በልመና የተሰበሰበን ገንዘብ ለጦርነት ማዋል፣ የካናዳ ስንዴ መሸጥ፣ የእርዳታ እህል በሚከፋፈልበት ጊዜ የከረጢቱን ዋጋ በማስከፈል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መሰብሰብ እና ከውጭ የመጣን እርዳታ ስርዓቱን የሚደግፉትን ብቻ እየለዩ መለገስ በህወሓት ቤት የተለመደ እና ካድሬዎቹ በህዝብ ዕልቂት ላይ ክፉ ቀን ጠብቀው የሚቆምሩት የህይወት ቁማር ነው፡፡

Wednesday, November 18, 2015

ተወዳጁ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በዛሬው እለት በአራዳ ጊዮርጊስ ፍ/ቤት ቀረበ

የቀይሽብር ወንጀለኛ በሆነው እርገጤ መድበው የተከሰሰው ጋዜጠኛ ገነነ ለክስ ያበቃው «ኢህአፓና ስፖርት» በሚለው መፅሐፉ ሲሆን የክስ መቃወሚያ አቅርቦዋል። እርገጤ መልስ እንዲያቀርብ ለህዳር 27 ፍ/ቤቱ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል። እርገጤ መድበው በደርግ ዘመን የከፍተኛ አንድ ሊቀመንበር የነበረና በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን የገደለና ያሰቃየ አረመኔ ወንጀለኛ መሆኑ ይታወቃል። ገነነ መኩሪያ የኢትዮጵያን ስፓርትና ታሪክ ከመሰረቱ ጠንቅቆ የሚያውቅና አገሪቱ ያልተጠቀመችበት (በተለይ ፌዴሬሽኑ) ትልቅ ባለራዕይ ነው። (ግልባጭ ዲሲ ለሚገኙ ራዲዮ ጣቢያዎችና ለኢህአፓ ድምፅ ፍኖተ ራዲዮ)
( በፎቶው በግራ በኩል በፍርግርግ ውስጥ ገነነ መኩሪያ፣ እንዲሁም ወንጀለኛው እርገጤ በፍ/ቤት ቅጥር ግቢ ይታያል)
አርአያ ተስፋማሪያም's photo.

Tuesday, November 17, 2015

በድርቅ ለተጎዱ አከባቢዎች መንግስት ኬክ እያከፋፈለ መሆኑን አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።


የወያኔ ስርሃት በረሀብ የተጎዱ ወገኖቻችንን እንደመርዳት የደረሰበትን እፍረት በማደባበስ ላይ ነው እያተኮረ ያለው
የቡርትካን ልጅ በረሀብ መሞት የዘገበው የBBC ዘገባ EBC ላይ ማስተባበያ እንድትሰጥ ተደርጎ ወያኔ በህዝቡ ስቃይ ላይ ቁማር ይጯወታል
እስኪ ከወያኔ ክህደቶችና የአለማቀፍ እውነታን በጥቂቱ እንመልከት
“በቆቦ አከባቢ በቀን ሁለት ህጻናት በረሃብ ይሞታሉ”
UN
“በረሃብ ሰዎች እየሞቱብን ነው”
የቆቦ ነዋሪ
“በድርቁ የሞተ አንድም ሰው የለም። የጥገኛ ፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸው ወሬ ነው” ህወሀት
.
” በድርቁ ሳቢያ በ6 አከባቢዎች ከ50ሺህ በላይ ሰው ተሰዷል” UN
” ከቀዬው የተሰደደ አንድም ሰው የለም። የሀገራችን ልማት ያበሳጫቸው የኒዮ ሊበራል አቀንቃኞች ወሬ ነው” ህወሀት
.
” በኢትዮጵያ ያለው የእንቁላል ምርት ከህዝቡ ቁጥር ጋር ሲሰላ አንድ ኢትዮጵያዊ በአመት በአማካይ የሚመገበው እንቁላል ብዛት አንድ ነው።” የመንግስት የራሱ ጥናት
” ድርቅ በተከሰተባቸው ቦታዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ካሎሪ መጠን ያለው ምግብ እየመገብን ነው።” አቶ ጌታቸው ረዳ
.
በሚቀጥሉት ቀናት የህወሀት ሚዲያዎች ያስተላልፋሉ ተብሎ ከሚጠበቁ ዜናዎች መሃል
1. UN የኒዮ ሊበራል አቀንቃኝ በመሆን የኢትዮጵያን ገጽታ እያበላሸ መሆኑን በመቃወም የባስኬቶ ወረዳ ነዋሪዎች ሰልፍ አደረጉ።
2. በድርቅ ለተጎዱ አከባቢዎች መንግስት ኬክ እያከፋፈለ መሆኑን አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ። እንደተረጂዎቹ ፍላጎት ተቆራጭ: ሚሊፎኒ: ብላክ ፎረስት: በተርፍላይና ሌሎች የኬክ ዓይነቶች መሰራጨታቸውን ጌቾ ገልጿል።

Sunday, November 15, 2015

ጋዜጠኞችና የረድኤት ድርጅቶች ረሃቡ ወደተከሰተበት ቦታ እንዳይሄዱ ተከለከለ መንግስት ረሃቡን ለመደበቅ ከፍተኛ መመሪያ አስተላለፈ


ሕወሓት የሚመራው የኢትዮጵያ ገዢ በኢትዮጵያ የተከሰተውን እና 15 ሚሊዮን ሕዝብን ለረሃብ ያጋለጠውን አደጋ ለመሸፋፈን ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋዳ ሥራዎችን ከመስራት በተጨማሪ መረጃዎች እንዳይወጡ እስከማፈን ደረጃ መድረሱን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል::

የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት; የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስተርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በአንድ ላይ ተቀናጅተው እየሰሩት የሚገኘው የመረጃዎችን የማፈን ሥራ ታች ድረስ ወርዶ እስከ ፓርቲ አባላትና “ደጋፊ” የተባሉ ሰዎች ጭምር እንዲሰራበት እየተደረገ ነው:: “ረሃቡን አስታከው ለውጭ መንግስታት ሊያሳጡን የሚሞክሩትን መታገል አለብን” በሚል እነዚህ ሶስት መስሪያ ቤቶች ባወጡት መመሪያ መሠረት የውጭ ጋዜጠኞችም ሆነ የረድኤት ድርጅቶች ረሃቡ ወዳለበት ቦታ ሄደው ፎቶ እንዳያነሱ; ቭዲዮ እንዳይቀርጹ; ማንኛውንም ቃለምልልስ እንዳያደረጉ ተከልክሏል:: በተለይ ቢቢሲ በቅርቡ በኢትዮጵያ በአንድ ትንሽ ክልል ስፍራ ብቻ በቀን 2 ህፃናት በረሃቡ እየሞቱ እንደሆነ መዘገቡን ተከትሎ አለም አቀፍ ሚዲያዎች እና የአፍቃሬ ሕወሓት መንግስት ደጋፊ የሆኑ ሃገራት ሳይቀር ከዚህ ቀደም “ልማታዊ መንግስት” እያሉ ሲያሞካሹ የነበረውን አፋቸውን በመጠራረግ ረሃቡን እና መንግስት የሚከተለውን ፖሊሲ እንደገና እየመረመሩ እንደሚገኙ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ይናገራሉ::
እንደ ምንጮች ዘገባ በቅርቡ በቢቢሲ የቀረበችውን እናት የአማራ ክልል ጋዜጠኞች አስገድደው ቃለምልልስ ያደረጓት ሲሆን በቅርቡም በመንግስት ሚዲያዎች ላይ “አልራበኝም” ዓይነት ንግግር በማስደረግ የቢቢሲን ዘገባ ለማስተባበል ሥራ እየተሰራ ይገኛል::
ከሥስቱ መስሪያ ቤቶች በተላለፈው መመሪያ መሠረት የመንግስት ሃላፊዎች ከላይ እስከታች በየሶሻል ሚዲያው በመውጣት ችግሩን መንግስት ተቆጣጥሮታል እያሉ መጻፍ እና መናገር አለባቸው:: “ተቃዋሚዎች የመንግስታችንን መልካም ገጽታ ለማጠልሸት ሆን ብለው የሚያደርጉት ሤራ ነው” እያሉም በውጭ ያሉ ኤምባሲዎችና ተላላኪዎች እንዲያነገሩ ትዕዛዝ ከመተላለፉም በላይ መንግስትን ይደግፋሉ ለተባሉ የውጭ ጋዜጠኞች ወደ ሃገር ቤት እንዲገቡና መልካሙን ነገር ብቻ እንዲዘግቡ ኢምባሲዎች መሥራት እንዳለባቸውም የወጣው መመሪያ ሲያመለክት ስለመንግስት መጥፎ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ የተባሉ ጋዜጠኞች ግን ረሃቡ ወዳለበት ቦታ እንዳይሄዱ/ ምስል መቅረጽና ቃለምልልስ ማድረግ እንዳይችሉ የኮምዩኒኬሽን መስሪያ ቤት ፈቃድ እንዳይሰጥ ት ዕዛዝ ወርዷል::
በስልጣን ላይ ያለው መንግስት 15 ሚሊዮን ሕዝብ በመራቡ የተነሳ በወዳጅ ሃገሮቹ ሳይቀር በመጥፎ አይን እየታየመምጣቱ በስርዓቱ ውስጥ “ገጽታችን ተበላሸ” በሚል ራሱን የቻለ ሽብር ፈጥሯል::

Thursday, November 12, 2015

የህዝብ መሆናችን የሚረጋገጥበት ሰዓት አሁን ነው /ቴዲ አፍሮ/

የድርቁ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቶኛል!
አንድ በጣም ሚገርመኝ ነገር አለ ፣ እኛ አርቲስቶች ትንሽ እውቅና ስናገኝ መንግስትን መተቸት ይቀነናል ። መንግስትን መተቸት ካለብን መተቸቱ ትክክል ቢሆንም ፣ መንግስትን መተቸት ብቻ ለኢ/ያ ህዝብ ጉርሻ ዳቦ የሚሆነው አይመስለኝም። ሁሌ ከመንግስት ጋር አተካራ ከመግጠም ይልቅ መጀመርያ የራሳችን ድራሻ ተወጥተን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን አንድ ነገር እንስራ !
በእውነቱ በየሚድያው ህዝቤ ወገኔ እያልን ስንነግድለት የነበረው ህዝባችን ነው ረሀብ እያንካካው ያለው።
የህዝብ መሆናችን የሚረጋገጥበት ሰዓት አሁን ነው! አዎ አሁን በክፉው ቀን ህዝባችን ባጣበት እጁን ባጠረበት ያውም ብዙ የለመደ!!
እንደ ከዚህ ቀደሙ በአውሮፓም በአሜሪካም ያሉትን የጥበብ ሰዎች እንዳይቀድሙን ፣ የአለም መሳቅያ እንዳንሆን ሰጋሁኝ !
“እኛ ነን አለም” ይህ መፈክር ብዙዎቻችን የምናውቀው ይመስለኛል። ሀገራችን በ1977 በድርቅ ስትጎዳ የሀገራችንን ህዝብ ለመታደግ የአለም አርቲስቶች በታዋቂው እንግሊዛዊው ዘፋኝ ቦብ ጊልዶፍ አስተባባሪነት የተዘጋጀ የኮንሰርት ስያሜ ነው።
በዚህ ዘመን ያንን አይነት ድምበር ዘለል ድጋፍ የምንጠብቅበት አይደለም እንደውም ያልተከፍፈለ እዳ ያለብን ሆኖ ይሰማኛል።
በተከሰተው የድርቅ አደጋ የተጎዳ ወገናችን መርዳቱ የመግስት ሰራ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮያዊ ትብብርና ድጋፍ ይጠይቃል። የማይቻል የለም ራሳቸን በራሳቸን ከተባበርን ህዝባችን ከረሀቡ ልንታደገው እንችላለን !
ስለሆነም እኛ አርቲስቶች የተለያዩ ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት የበኩላችን አስተዋፆ እንድናደርግ ጥሬዬን አቀርባሎህ።
ቸሩ እግዚአብሔር አምላክ ቅድስቲትዋ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምዋን ጠብቆ ለዘላለም ያኑርልን።
ፍቅር ያሸንፋል

Wednesday, November 11, 2015

የበጎች መንጋ ግዙፉ የመጓጓዣ አውሮፕላንን በድንገት እንዲያርፍ አሰገደዱት


ንብረትነቱ የሲንጋፖር አየር መንገድ የሆነ አንድ የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን በውስጡ ጭኖ የነበረውን በረካታ በጎች ይዞ በረራውን አቁርጦ ለሰአታኣት እንዲያርፍ ተገዷል። አቪዮሽን ሀራልድ የተሰኘው ድህረ ገጽ እንደዘገበው ከሆነ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ስደሰት (2186) በጎችን ጭኖ መነሻውን ከ ሲዲኔ( አውስትራሊያ )አደርጎ ወደ ኳላላምፑር (ማሊዢያ) ይበር የ ነበረው የማጓጓዣ አውሮፕላን በበረራ ላይ እንዳለ ከጭስ አነፈናፊው (ስሞክ ዲክተክቶር ) መሳሪያ ላይ ያለተለመደ የጭስ ምልክት የታያል ።ፓይለቶቹም አውሮፕላኑን ወዲያውኑ በድንገተኛ እንዲያርፍ አድርገው መንሰኤው ሲጣራ በውስጡ ምንም አይነት እወነተኛ የእሳት ዘር (ጭስ) አለተገኝም። ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ ምስጋና የገባውና በሁዋላ ሰለ ጭሱ መንሰኤ ሲጣራ እንዚያ ለመታረድ ይሁን ለመራባት ወደ ሲንጋፖር ሲጓጓዙ የነበርቱት በጎች “ከረጅም ጉዞ ሳቢያ ፣ ሲያመነዥጉት ከነበረው ግሳት ፣ ከተጸዳዱት (በጠጣቸው) አና በመጸዳጃቸው ካሰወገዱት ከተቃጠለው አየር (ፈስ) የወጣ ጋዝ ለካ ወደ ጭስ መመረመሪያዋ ማሽን ዘልቆ የእሳት አደጋ መመረመሪያውን አስጨንቆ እና አሰጠንቅቆ አውሮፕላኑም በአደጋ ጊዜ እንዲያርፍ ተገዷል “ ሲሉ የአየርመንገዱ ባለሰልጣናት ግምታቸወን የሰነዘሩ ሲሆን በተለይ ደግሞ የእንሰሳ ባለሙያዎች በጎች ሲደክማቸው የተቃጠለ አየር(ጋዝ) በብዛት ያሰወጣሉ ብለዋል። አሮፕላኑም ከሁለት ሰእት ተኩል የድንገተኛ ማረፍ በሁዋላ መንገዱን በማቅናት ከመዳረሻው(ኳላላምፑር) በሰላም ደርሷል ተብሏል። ከዚህ ቀደም ሌላ የሲንጋፖር አየርመንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ባለፈው ነሃሴ ወር ወስጥ ከግሪሳ ወፎች ጋር ተጋጭቶ በድንገት ለማረፍ ተገዷል። መቸም ጥንቃቄ ማድረግ ባይከፋም በሰንካላ ምክንያት አውሮፕላኖች እንዲያርፉ ሲገደዱ ማየት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ሲሆን በተለይ ከሽብር ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች በምርመራ ሰም ይያዛሉ አሊያም ከመንገዳቸው ይደናቀፋሉ። ይሁን እና ሰሞኑን ግዙፉ አወሮፕላንን በማሰደንገጥ በደንገት እንዲያርፍ ያደረጉት የበጎቹ እጣፈንታ (በቀጥታ ወደቄራ ሰለመላካቸው ወይም ወደማጎሪያ ቤታቸው ሰለመላካቸው ) ለጊዜው አልታወቀም።
Tamiru Geda's photo.

አስከፊው የኢትዮጵያ ድርቅ ከድጡ ወደማጡ!!


Monday, November 9, 2015

ሰበር ዜና ! በሶማለያ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ የማነ ገ/ማርያም ቢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጥቃት ተሰነዘረባቸዉ፤

በሶማለያ በሚገኘዉ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ዉስጥ ከፍተኛ መከፋፈል እየተፈጠረ ይገኛል፤ የመቶ አለቃ ሰጠሕኝ የተባለ ወታደር በተለያየ ወቅት በሚያነሳዉ የመብት ጥያቄ ምክንያት በተደጋጋሚ ለእስር እና ለወታደራዊ ቅጣት ሰለባ እንደነበር መረጃችን ሲያመላክት ባለፈዉ ሳምንት ከአሚሶም ዉጭ በተሰማራዉ የ44/ ክ/ጦር ላይ የደረሰዉ ከፍተኛ ጥቃት ያበሳጨዉ ይህዉ ወታደር ኮ/ል የማነ ገ/ማርያም ላይ ኤፍ 1 ተፈነጣጣሪ ቦንብ ወርዉሮ አደጋ ማድረሱን ከስፍራዉ የደረሰን ማስረጃ ያመለክታል፤
የመቶ አለቃ ሳሙኤል አደጋዉን እንዳደረሰ መሰወሩ ሲረጋገጥ ኮ/ል የማነ በውቅቱ ለጥቂት ቢተርፉም የተወረወረዉ ቦንብ በሰዉና በንብረት ላይ አደጋ አድርሷል፤
በተያያዘ ዜና በርማጭሆ የተነሳዉ ጦርነትተባብሶ ቀጥሏል በአካባቢዉ የምኖሩ አርሶ አደሮች እና የወያኔ ሚሊሻ ያነሱት ይህዉ ጦርነት ወደ ሌሎች ስፍራዎች እየተስፋፋ በመሆኑ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ወደ ስፍራዉ እንዲቀሳቀስ መመሪያ ቢወጣም ከኣርማጭሆ ወረዳ ለወረዳ እየተስፋፋ የሚገኘዉን እንቢተኝነት የወያኔ መንግስት የመቆጣጠር ሁኔት ጥያቄ ዉስጥ ገብቷል፤
ድል ለኢዮጵያ ህዝብ !!
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.
Gudish Weyane's photo.

Saturday, November 7, 2015

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቁስለኛ ወታደሮች ዳሽ-6 በተባለ አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር ከሶማሊያ አየተጫኑ ድሬ ደዋ ላይ በመራገፍ ላይ ናቸው፡፡


Patriotic Ginbot 7's photo.Patriotic Ginbot 7's photo.
Patriotic Ginbot 7's photo.Patriotic Ginbot 7's photo.
 
ራሱን በመንግስትነት ስም የሚጠራው የማፍያው ቡድን ህወሓት የምዕራባዊያንን ቁሳዊና ፖለቲካዊ ድጋፍ በማግኘት ስልጣኑን ለማደላደል ሲል ብቻ ከ10 ዓመታት በፊት ማለትም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ የሆኑ ዕልፍ አዕላፍ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያለማቋረጥ ወደ ሶማሊያ በረሃማ ምድር እያስገባ እጅግ በጣም አሰቃቂ ለሆነ እልቂት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡
የህወሓት አመራሮች የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረትን ከሁለት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በመደምሰስ አፈራርሰውት ለቀው እንደሚወጡ ለህዝቡ ገልፀው ወደ ምድራዊ ሲኦል ወደሆነችው ሶማሊያ ጦር ጭነው ያስገቡ ሲሆን ነገር ግን አልሸባብ የተባለ ሌላ ፅንፈኛ ቡድን ፈጥረው ምስኪን ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን ከማይወጡበት የጦርነት አዙሪት ውስጥ ከተዋቸው ለድፍን 10 ዓመታት ሰቅጣጭ የሞት ገፈትን ሲግቷቸው ቆይተዋል፡፡ ቀጠናውንም የባሰ አለመረጋጋት እንዲሰፍንበት አድርገውታል፡፡
በዶላር ፍቅር ዓይኑ የታወረው የህወሓት አገዛዝ ከ10 ዓመታት በፊት ጦሩን ወደ ሶማሊያ ሲያስገባ እሱ እንደሚነግረን መጀመሪያ ላይ ጦርነት የገጠመው ከእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት ከሶማሊያ ጎሳዎች መካከል በጠንካራነቱና በታላቅነቱ ከሚታወቀው የሃውዬ ጎሳ ጋር ነበር፡፡ በመሆኑም በገብረ ዲላ እና በሌሎች ህወሓታዊ ድኩማን የጦር አዛዦች የሚመሩት 43ኛ እና 44ኛ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፤ መሪዎቹ ጭነዋቸው የሄዱትን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮች ለሶማሊያ በረሃ ገብረው አምስትና ስድስት ወታደሮችን ብቻ አስከትለው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ ሞቃዲሹ ውስጥ አንድ የሃውዬ ጎሳ አባል በአንድ ህንፃ ውስጥ መትረየስ ጠምዶ ቢያንስ አንድ ሻምበል ጦር ብቻውን ጨርሷል፡፡ የድሃ ልጆች ለኢትዮጵያ ምንም አይነት ጠቀሜታ በሌለው ጦርነት በክንቱ ደማቸው ፈሶ ረግፈው ያለቀባሪ ቀርተዋል፡፡ አሁንም በዘግናኝ ሁኔታ መገደላቸው ቀጥሏል፡፡ ሬሳቸውም እንዳያርፍ ተፈርዶበት በየጎዳናው በገመድ ታስሮ ሲጎተት ታይቷል፡፡
ምንም እንኳን አሮጌዎቹ የአየር ኃይል አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች የወታደር ሬሳና ቁስለኛ ወደ ድሬ ደዋ ያለማቋረጥ ማመላለስ የጀመሩት ካለፈው 2007 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም አሁን አሁን ደግሞ የባሰውኑ ስራ በዝቶባቸዋል፡፡ ዳሽ-6 አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር በቁስለኛ ወታደሮች ጥቅጥቅ ብለው ተሞልተው ከወደ ሶማሊያ እየመጡ ድሬ ደዋ ላይ በማራገፍ ላይ ናቸው፡፡
ከሶማሊያ በአውሮፕላንና በሄሊኮፕተር ተጭነው ድሬ ደዋ ላይ የተራገፉት ቁስለኛ የሰራዊቱ አባላት ወደ ሐረር ወታደራዊ ሆስፒታል እየተወሰዱ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም የሐረሩ የመከላከያ ሆስፒታል ከአቅሙ በላይ በቆስለኞች መሞላቱን የሆስፒታሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
ሆኖም ለቁስለኞች የሚደረገው ህክምና እና እንክብካቤ በራሱ ከአድሏዊነት የፀዳ እንዳልሆነ ተጎጅዎች ቅሬታቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ የህወሓት ታጋዮች የነበሩ የሰራዊቱ አባላት ሆዳቸውን በቆረጣቸው ቁጥር ደቡብ አፍሪካና ሳዑዲ አረቢያ ድረስ እየሄዱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየታከሙ ተገደው የሶማሊያው ጦርነት ውስጥ ተማግደው ስጋቸው በእሳት ተጠብሶ የተመለሱት ወታደሮች ግን ጦር ኃይሎች ሆስፒታልን እንኳን በዓይኖቻቸው የማየት እድላቸው የጠበበ እንደሆነ እና አካላቸውን ላጡትም ምንም አይነት የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንደማይደረግላቸው ብሶታቸውን ዘርዝረዋል፡፡
በተጨማሪም ሶማሊያ ውስጥ የሚገኙ የአየር ኃይል አባላት በአውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች ብልሽትና እንዲሁም የመለዋወጫ እጥረት ምክንያት ስራ ፈትተው ለረጂም ጊዜ በመቀመጣቸው በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ያዘለ ጥያቄ በአንድነት አንስተዋል፡፡ የአየር ኃይሉ ምክትል አዛዥ ጀነራል ማዕሾ ሐጎስ ወደ ቦታው አምርቶ ጥያቄ ያነሱ አባላትን የማረጋጋት ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ለተነሳው ጥያቄ ተገቢ መፍትሄ ባለመሰጠቱ አሁንም ቅሬታው ባለበት ቀጠለ እንጂ ሊቀረፍ አልቻለም፡፡
የእነዚህን ሶማሊያ ዘማቾች የአየር ኃይል አባላት ሚስቶች የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ የሆነው ኮሎኔል አበበ ተካ በየተራ እያማገጠ እንደሚገኝም ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡
በአጠቃላይ ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር ላይ በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊትና በአልሸባብ ተዋጊዎች መካከል ከባድ ጦርነት እንደተካሄደ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን ሞተዋል



በደቡብ አፍሪቃ ደርበን ከተማ ዘነፎብያ (Xenophobia) ወይም በመጤ ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ ምክንያት ስድስት ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት የዐይን ምስክሮች ይገልጻሉ።
ቀደም ሲል በዜናችን ላይ እንደተገለጸው፣ በደቡብ አፍሪቃዋ ደርበን፣ ዘነፎብያ (Xenophobia) በተሰኘ በመጤ ባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ፣ ስድስት ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።
ዜናውን እዚያው ከደርባን ለአሜሪካ ድምፅ ያደረሱን የዐይን ምስክሮች እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያውያኑ ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያና ድብደባ ሳያንስ፣ ቤንዚን ሰውነታቸው ላይ አርከፍክፎ እስከ ማቃጠል ተደሯል።
አዲሱ አበበ ሁለት ደርባን ኗሪ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሮ ተለከታዩን አእርቧል። የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

Thursday, November 5, 2015

ወያኔ በአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን እና በገጣሚ በእዉቀቱ ስዩም ላይ ክስ ለመመስረት ሽር ጉድ እያሉ ይገኛል


ወንጀለኛዉ! ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት የሚመራዉ መንግስት ስራ አስፈጻሚዎች! ብሔራዊ መረጃ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ አምስት የተዉጣጡ አባላት በአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን እና በገጣሚ በእዉቀቱ ስዩም ላይ ክስ ለመመስረት ሽር ጉድ እያሉ ይገኛል ከብሐራዊ መረጃ ቁጥር 207 ክፍል በወጣ ትእዛዝ መሰረት!! ሕዝብን በመቀስቀስ መንግስት ላይ እንዲነሳሳ ከማድረግ ባሻገር ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ከሚሰሩ አባላቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር መንግስት ላይ እያሴሩ ነዉ በሚል መንገድ የወንጀለኝነት የክስ መዝገብ እየተሰራ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመላክቷል።
በተያያዘ ዜና በመምህር ግርማ ላይ የተመሰረተዉን የክስ ወንጀል ለማጠናከር ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር የሚሰራዉ የመረጃ ቡድን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ሲኖዶስ መምህሩ ላይ የተከፈተዉን ወንጀል ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ ድጋፍ ሰጪ ደብዳቤ እንዲሰጡ የተጠየቀ ሲሆን ፖሊስ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ የመምህር ግርማ ወንድሙን መኖሪያ ቤት ፈትሾ የሞባይል ሲም ካርድ አገኘዉ! በሚል ተልካሻ ፍሬ ከርስኪ ተጨማሪ ክስ ሊመሰርት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.Gudish Weyane's photo.

መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ


‹‹የመጣነው የሚላስ የሚቀመስ ስለሌለ ነው፡፡ ከብቶቻችን አልቀዋል፡፡ አዝመራ የሚባል የለም፡፡ ሰው በርሃብ እያለቀ ነው፡፡››››
• በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው
• ‹‹ሰው በርሃብ እያለቀ ነው››
• ‹‹የሚላስ የሚቀመስ የለም፡፡ ቤተሰባችን ፈርሷል››
• ‹‹እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አንመጣም ነበር፡፡››
መንግስት በርሃብ ለተጎዱት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ቀያቸውን ለቀው አዲስ አበባ የገቡት የርሃቡ ሰለባዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች በርሃብ የተጠቁ ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወሎ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች አልፈው ወደ ጎጃም፣ ጎንደርን እንዲሁም አዲስ አበባ እየተሰደዱ ሲሆን አዲስ አበባ በርካታ ተጎጅዎች ህፃናትን አዝለው እየለመኑ ይገኛሉ፡፡
የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ካነጋገራቸው መካከል ሁሉም መንግስት ለርሃቡ ተጎጅዎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውና ጎረቤቶቻቸውም እንደነሱ ቀያቸውን ጥለው ወደ መተማ፣ ሁመራ፣ ባህርዳር፣ ደሴ፣ እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ መሰደዳቸውን በሀዘን ገልፀዋል፡፡
ወሎ ውስጥ ጮሬ ሶዶማ ከተባለ ቦታ ተነስታ እንደመጣች፣ አዲስ አበባ ከገባች ሶስት ሳምንት እንደሆናት የገለፀችውና ሁለት ህፃናትን ይዛ ስትለምን ያገኘናት፤ በግምት በ30ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ የምትገኝ እናት ‹‹የመጣነው የሚላስ የሚቀመስ ስለሌለ ነው፡፡ ከብቶቻችን አልቀዋል፡፡ አዝመራ የሚባል የለም፡፡ ሰው በርሃብ እያለቀ ነው፡፡ እኛ ሴቶቹ ወደ ከተማው ስንመጣ ወንዶቹ ደግሞ ወደ ሁመራና መተማ ሄደዋል፡፡ እኛም ከዚህ የመጣነው ጉልበት ስላለን ነው፡፡
አብዛኛዎቹ ደካሞች በዛው አካባቢ ቀርተዋል፡፡›› ስትል በሀዘን ገልፃልናለች፡፡ መንግስት እርዳታ አይሰጥም ወይ ብለን ላነሳንላት ጥያቄም ‹‹ምንም እርዳታ አልተሰጠንም፡፡ እርዳታ ቢሰጥ ኖሮ ቤታችን ጥለን አንመጣም ነበር፡፡ ባያበቅልም መሬት አለን፡፡ የከተማው ሰው ይሻላል ብለን ነው ወደዚህ የመጣነው›› ስትል ስለ ርሃቡ አስከፊነትና መንግስትም እርዳታ እየተሰጠ እንዳልሆነ ገልፃልናለች፡፡
ባለቤቷ ወደ መታማ ሲሄድ እሷም ቤቷን ጥላ ወደማታውቀው አዲስ አበባ እየጠየቀች እንደመጣች የገለፀችልን ወጣት በበኩሏ ‹‹ቤቴ ተፈትቷል፡፡ ባለፈው አመት ከብቶችም እህልም ነበረን፡፡ ዘንድሮ ግን ምንም ነገር የለም፡፡ ጊዜው ከፍቷል፡፡ ባሌ ወደ መተማ ሄዷል፡፡ እኔም ልጄን አዝዬ እስከ ደሴ በእግሬ መጣሁ፡፡ ከዛ በኋላ እየለምንኩ ከዚህ ደርሻለሁ፡፡ ማንም እርዳታ አልሰጠንም፡፡›› ስትል ስለሁኔታው ገለፃልናለች፡፡
ከመርሳ ወረዳ እንደመጡ የገለፁልንና ከልጃቸው ልጅ ጋር እየለመኑ ያገኘናቸው የ65 አመት አዛውንት በበኩላቸው ‹‹ዝናቡ ሲቀር ከብቶቻችንም ሞቱ፡፡ አዝመራ የሚባልም ነገር የለም፡፡ ከመርሳ ደሴ እየለመንኩ መጣሁ፡፡ ደሴም እንደኛ ብዙ ሰው አለ፡፡ አገኝ ብሎ በየከተማው ተሰራጭቷል፡፡ ወደዚህ ይሻላል ብዬ በለመንኳት ተሳፍሬ መጣሁ፡፡ ርሃቡ ሲብስብን ወደማናውቀው አገር መጣን፡፡›› ሲሉ የርሃቡን አስከፉነት ገልፀውልናል፡፡
‹‹እርዱኝ!›› እያሉ እየለመኑ ያገኘናቸው ከኬሚሴ አካባቢ እንደመጡና ከ8 ቀን በፊት አዲስ አበባ እንደደረሱ የገለፁልን ሌላኛዋ እናትም ቤታቸውን ጥለው እንደመጡና፣ ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ወደ የት እንደሄዱ እንኳን እንደማያውቁ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ መንግስት እርዳታ እየሰጠሁ ነው እንደሚል ስንገልፅላቸው ‹‹ለእኔ አልደረሰኝም፡፡ እርዳታ ተሰጠኝ ያለም አልሰማሁም፡፡ እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አልመጣም ነበር፡፡ አሁን ነው ከከተማው ሰው ትንሽ ትንሽ እያገኘን ያለነው፡፡ በየ ከተማው ስንደርስ ሰው አይነፍገንም›› ሲሉ ከህዝብ እንጅ ከመንግስት እርዳታ እንዳላገኙ ገልፀዋል፡፡
ካሳንቺስ አካባቢ ልጅ አዝለው ታክሲ ተሳፋሪዎችን ምንም አይነት ቃል ሳያሰሙ ልጃቸውን በመዘርጋት ብቻ እንዲረዷቸው እየጠየቁ ያገኘናቸው እናትም የራሳቸውንና የታዘለውን ልጅ ነፍስ ለማዳን ቀያቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
የርሃቡ ተጎጅዎች አዲስ አበባ ውስጥም ነፍሳቸውን ለማቆየት በጠራራ ፀሀይ ሲለምኑ እንደሚውሉና ምቹ ያልሆነ ቦታ አንድ ላይ የሚያድሩ በመሆኑ ልጆቻቸው ለበሽታ እየተጋለጡ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ተማሪ የነበሩና በርሃቡ ምክንያት ለማቋረጥ የተገደዱት ልጆቻቸው ከእነሱ ጋር ወይንም ወደ ሌላ አካባቢ ነፍሳቸውን ለመዳን መሰደዳቸውን፣ በያለፉበት ከተማም በርካታ ስደተኛ እንዳለም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡- ነገረ ኢትዮጵያ
Netsanet Yibeltal's photo.
Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.

Wednesday, November 4, 2015

ጭልጋ እየታመሰች ነው


ያልታደለው የጭልጋ ነዋሪ በወያኔና በኩሊዎች እየታመሰ ይገኛል፡፡ ከጥቅምት 20 ቀን በፊት የወያኔ ኩሊዎች ሌሊቱን ጀምሮ በአማራና በቅማንት መካከል ያለውን ሰላም ለማኮላሸት ‹‹ማተብ የሌለው ሀይማኖት መጣብህ፤ ሀይማኖት የሚያስቀይርህ መጣ፤ ልኩን አሳየው፤….ወዘተ. ›› የሚሉ የጠብ አጫሪ መልእክቶች ያሉበት ወረቀት ሌሊት፣ ሌሊት እየተበተነ ያድራል፡፡ ይህንንም በመቃወም የጭልጋ ወረዳ የኹሉም ት/ ቤቶች ተማሪዎች ተቃውሞ በመውጣት ሲገልጹ መሳሪያ ያነገቡ ወሮበሎች በመደብደብ፤ በማንገላታት፤ በማሰር፤…ልዩ ልዩ ግፎችን እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ እስር ቤቶች ጠበው በየግለሰብ ቤት ተከራይተው እያሰቃዩአቸው ይገኛሉ፡፡
በርካታ ሰዎች በስጋት ይገኛሉ፤ በርሃ ገብተው የተሸሸጉም ብዙ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል በዳባት ወረዳ 12 ቀበሌዎች ‹ግብር አንከፍልም›› በማለታቸው ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ሲኖሩ 2 ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል፡፡
አወን ወያኔ ከሃዲ በርካታ አወናባጅና እርስ በርስ የሚያባሉ ሰዎችን ለእንደዚህ ‹አላማ› ቀጥሮ እያሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ወያኔ ቀጥሮ ከሚያሰራቸው ሰዎች ውስጥ adam getaneh በሚል የፌስ ቡክ አካውንት የሚጠቀም ሙሉአዳም ጌታነህ የሚባል ሰው በላ አካይስት ገንዘብ ተመድቦለት ጎንደርና ጎጃምን፤ ወሎና ጎንደርን፣ አማራንና ኦሮሞን፤ክርስቲያንና እስላሙን፤….ወዘተ. ለማጣላት በተለያዩ ቦታወች እየተዘዋወረ ተልእኮ ተሰጥቶት ወረቀት የሚበትን፣ ወሬ የሚነዛ፣ ከፍተኛ ቅስቀሳ የሚያደርግ የሰይጣን ውላጅ ነው፡፡ምስሉ ይኸው
ጎበዝ ከምንም በላይ አንድነታችንን አጠናክረን ወያኔንና ጀሌዎችን መፋለም ግድ ነው፡፡ በምንም መልኩ ‹የከፋፍለህ ግዛውን› ዓላማ ማስፈጸም ድርብ ክህደት ነው፡፡ለዚህ በምንም በር መክፈት የለብንም! ቆርጠን በኅብረት ክንድ ወያኔንና ጄሌዎች ላይ እንረባረብ!!!
ርትእ- ንጽሮት
አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

አወዛጋቢው ሮበርት ሙጋቤ ኬንያውያንን “ስርቆት በደማችሁ ነው ያለው!” በማለት ወረፏቸው!



ባለፈው እሁድ አንድ ቤተክርስትያን ውስጥ ለተገኘው ህዝብ ባደረጉት ንግግር ሙጋቤ ኬንያውያን ላይ ከፍተኛ ውርጅብኝ አውርደዋል.
“እነዚህ የምስራቅ አፍሪካ ሰዎች በህዝባቸው ላይ የሚያደርጉት ዘረፋ እጅግ ያስደነግጣል. እንድያውም አንዳንዴ ስርቆት በደማቸው ውስጥ ያለ ይመስለኛል. ኬንያውያን ወደ ተለያዩ ኮሌጆች ይሄዳሉ, ምርጥ የተባለ ትምህርት ይማራሉ, በስተመጨረሻም ምርጥ ሌቦች ሆነው ይመረቃሉ.” በማለት የራሳቸውን ህዝብ ከዚህ አይነት ተግባር ተጠበቁ በማለት ማስተማርያ አድረገዋቸዋል. “ሀገሩን የሚያፈቅር ዜጋ ፈጽሞ ከሀገሩ አይሰርቅም!” በማለት መክረዋል.
ይህንንም ተከትሎ በቁጣ የተሞሉ ኬንያውያን በትዊተር ገጾቻቸው ላይ ለሙጋቤ ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው.
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ከኬንያ ሌላ ጉድ ተሰምቷል. አንድ የኬንያ የሚኒስቴር መስርያ ቤት በአመቱ ከገዛቸው የንብረት ዝርዝሮች ውስጥ ኮንደምን ማስገባቱ እጅግ አስገራሚ ሆኖ እየተዘገበ ነው. ይሄው መስርያ ቤት ምንም እንኳ ለምን አገልግሎት እንደሸመተው ይፋ ባይደረግም አንድ ፓኬት ኮንዶም በ 450 የሀገሪቱ ገንዘብ መግዛቱን በበጀት ዝርዝር ውስጥ ማስገባቱ ተነግሯል.
ይህም ብቻ ሳይሆን ለመቶ የኮምፕዩተር ኪቦርዶች 4 ሚሊየን, ለ 20 ፍሬ እስክሪፕቶዎች 174,000 እና መሰል የተጋነኑ የክፍያ ዝርዝሮቹ ይፋ ሆነዋል.
ድሮ ድሮ አፍሪካ የኋላ ቀርነቷ ምክንያት መሀይምነት ወይም ጦርነት ነው ይባል ነበር. አሁን ግን ስልጣን በጨበጡ በሀገሯ ልጆች እየተበዘበዘች ሀብቷ በሙሉ እየተሟጠጠ በጥቂት ቤተሰቦች እና የአንድ ወገን ሰዎች እጅ ስር በመውደቁ ምክንያት ነው. አፍሪካ ዛሬም የእርዳታና የብድር እጆቿን ከመዘርጋት አልተቆጠበችም.ይሁን እንጂ በዚህ መልክ የምታገኛቸውን ገንዘብ በሙሉ ትዘረፋለች.
የሆነ ሆኖ ዛሬ ኬንያ እንዲህ በሙስና ይሄ ሁሉ ውርጅብኝ የሚደርስባት ከሌሎች የምስራቅም ሆነ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለየ መልኩ የሚፈጸም ሌብነት ስላለባት አይደለም. ልዩነቱ ኬንያ አይንና ጆሮ የሆኑ, ቀንና ማታ ተግተው መረጃ ለህዝብ የሚያቀብሉ ለቁጥር የሚታክቱ የመገናኛ ብዙሀን ስላሏት ነው.
በኬንያ በየቀኑ የሚታተሙት ጋዜጦች, ሳምንታዊ መጽሄቶች, የቴሌቪዥንና የሬድዮ ጣብያዎች ከምንም ነገር ቅድምያ የሚሰጡት ወሬ ቢኖር ሙስና ነው. በኬንያ ስለ ሙስና ሳይዘገብ ጸሀይ ወጥታ አትጠልቅም.የሚገርመው ነገር ደግሞ አንዳንድ ጊዜ አስር ብር ስለተቀበለ አንድ ተራ ባለስልጣንና የፍርድ ቤት ሂደቱ ሁሉ ሳይቀር ይዘገባል. ይህ ነው ኬንያን ፊት ለፊት ያደረጋት. እንጂማ ሌብነቱ በብዙ መልኩ በየሀገሩ የምናየው ነው.
የሚዲያን ባህሪ ቀድመው የተረዱና ራሳቸውን በስልጣን ከልለው የህዝብ ደም የሚመጠምጡ በርካታ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ፎቅን የሚያህል የሀገር ንብረት ሲሰርቁ እንኳ አይነቃባቸውም. ምክንያቱም አስቀድመው የመገናኛ ብዙሀኑን አፍ ዘግተዋልና. “ሞኝ ዝም ቢል ጠቢብ መሰለ” ይላል መጽሀፉ. እነዚህም ስለሰሩት ሀጢያት የሚናገር ቢጠፋ ጻድቃንና ጨዋ ሆነው ታዩ.

ወያኔ እስካለ የመልካም አስተዳደር ችግር በኢትዮጵያ ይቀረፋል የሚል እምነት የለኝም

ምክንያቱም ድርጅቱ፡-– መሰረቱ በውሸት፣ በሌብነት እና አጠቃላይ በሙስና የተዘፈቀ ስለሆነ
-በዘረኝነት ላይ የተንጠለጠለ እከክልኝ ልከክልህ አካሄድ የህልውናው መሰረት ስለሆአባላቱም ሆኑ አመራሩ በትምህርትም ሆነ 
-በእውቀት ብቃታቸው እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ ሰዎች የተመሰረተ እና የሚመራ በመሆኑ
-አባላቱም ሆኑ አመራሩ ከህግ የበላይነት ይልቅ ለዕለት ጉርስ እና ርካሽ ስልጣን ሲባል እያንዳንዳቸው ከህግ ይለቅ የበላይ አካላቸውን ፍላጎት ለማሟላት እና ለማስደሰት የሚሰሩ በመሆኑ
-በተለይ በየ እርከኑ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ከእውቀት እና ጥሩ ስነምግባር የፀዱ በመሆናቸው
-አባላቱን የሚያደራጀውና የሚመለምለው የፖለቲካ ፕሮገራሙንም ሆነ ፖሊሲውን አስተዋውቆና ተቀባይነት አግኝቶ ሳይሆን ከሆድ ባልዘለለ ርካሽ ጥቅማጥቅም መደለያ አሊያም የጉልበት ማስፈራሪያ በመሆኑ
-ከህወሓት ጥቂት የአመራሩ አስኳሎች በስተቀር አመራሩም ሆኑ አባላቱ የሚያምኑበትን እና ህግን የተከተለ አሰራር ለመከተል የራስ መተማመን የሌላቸው በመሆኑ
-ምንም እንኳ ብሔር/ጎሳ ላይ የተንጠለጠለ የስልጣን መሸሸጊያ ከማድረግ በስተቀር ለየትኛውም ጎሳም ሆነ ብሔር አሊያም አጠቃላይ ህዝብ ጠቅምና መብት ዋጋ የማይሰጥ በመሆኑ
-ስለሚከተለው ርዕዮተ ዓለም የጠራ እና ትክክለኛ ምንነት፣ ግብና ዓላማ መደናገር ውስጥ ያለ በመሆኑ
-በሀገሪቱ ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ተቋም፣ ደህንነት፣ ሲቪክ ተቋማትና ነፃ ፕሬስ ስለሌለ
-የሀገርን እና ህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝባዊ አመኔታ እና ውክልና ኖሮት የተመረጠ ስላልሆነ ከሰሞኑን የነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተራ ፐሮፖጋንዳ በዘለለ በኢትዮጵያ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር ይቀረፋል ማለት ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ነው ሚሆነው፡፡ ስለዚህ በሀገሪቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሊቀረፍ የሚችለው ራሱ ኢህአዴግ ስልጣን ሲለቅ አሊያም ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ ላይ መቅረፍ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው


ከደቡብ ጎንደር : ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም : ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪወቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ ( የትግራይ ተወላጆች ) ግፍ እየተሰራባቸው ነው :: 
ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ::
ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን እሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት ( የወሎ እና የጎጃም በሚል ) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲአወችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል ::
በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም ሲሆን በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬወችን ኩላሊት ነው ::
እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤለ በህገወጥ መልኩ የሚጉዓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪት እና አጎራባች አካባቢወች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ እሺ ዶላር በማስከፈል ይለቁአቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላልታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ ::
ለወገኖቻችን እንድረስላቸው !!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ
ሰሜን ጎንደር

Tuesday, November 3, 2015

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው


ከደቡብ ጎንደር : ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም : ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪወቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ ( የትግራይ ተወላጆች ) ግፍ እየተሰራባቸው ነው :: 
ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ::
ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን እሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት ( የወሎ እና የጎጃም በሚል ) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲአወችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል ::
በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም ሲሆን በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬወችን ኩላሊት ነው ::
እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤለ በህገወጥ መልኩ የሚጉዓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪት እና አጎራባች አካባቢወች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ እሺ ዶላር በማስከፈል ይለቁአቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላልታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ ::
ለወገኖቻችን እንድረስላቸው !!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ
ሰሜን ጎንደር