Tuesday, May 5, 2015

የአውሮፕላን ማቆሚያ እጦት በላስ ቬጋስ የተገኙ ቱጃሮችን ምቾት መንሳቱ ረተነገረ


የትናንት ለሊቱ የፍሎይድ ሜይዌዘርና የማኑ ፓኪያ የመካከለኛ ሚዛን የላስቬጋስ የቡጢ ፍልሚያ አለም እንዴት ሲያብድለት እንደከረመ መታዘባችን አልቀረም ይህ የቡጢ ፍልሚያ በታሪክ እጅግ ውድ የመግቢያ ትኬት የተሸጠበት, ውድ ክፍያ ተፋላሚዎቹ ያገኙበት, እጅግ የገነነ የሚዬ ሽፋን ያገኘ … ወዘተ ምናምን ብቻም አይደለም
ይልቁንም ከውድድሩ ጋር ተያይዞ እጅግ የበረከቱ አስደናቂና አስገራሚ ነገሮች በሪንግ ላይ ለተኩል ሰአት እንኳን ካልቆየው ፍልሚያ ጋር ተያይዞ እስከአሁንም በመውጣት ላይ ነው የሚገኙት
ለዚህ ውድድር እድምተኝነት ሲሉ ከተለያዩ የአለም ማእዘናት ሀብታሞችና ቱጃሮች ከየአለም ማእዘናቱ ወደላስቬጋስ ፈሰዋል እነዚህ ቀበጥ ቱጃሮች ታዲያ ከትኬት ግፊያው, ከሆቴል ወረፋው ወይም ከሌላ ሌላው ጣጣ ሁሉ ለግል ጀቶቻቸው ማቆሚያ ማግኘትም አንድ ራስ ምታት ሆኖባቸው ነበር ይላል ስፖርቲንግ ኒውስ በፎቶ አስደግፎ ባወጣው አጭሩ ዘገባው
ለእንደኛ አይነቱ ወሬውን በሩቅ ለሚሰማ የታዳጊው አለም ህዝብ “ከኖሩ አይቀርስ እንዲህ ነው አቦ የግል ጀት ማቆሚያ እያጡ” ብሎ የቱጃሮቹን ህይወት ሊጎመዥ ይችል ይሆናል ላስ ቬጋስ ቦቅሱን ለመታደም የተገኙት ቱጃሮች ግን በዚህ የፓርኪንግ ችግር እንደተማረሩና ምቾት እንደነሳቸው ነው የተነገረው

No comments:

Post a Comment