Saturday, May 2, 2015

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላትና ደጋፊ በኖርዌይ ከተሞች ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ



የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላትና ደጋፊ በኖርዌይ ከተሞች ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
may 01. 2015 በመላው አለም የተከበረውን የወዝ አደሮችን ቀን ምክንያት በማድረግ በኖርዌይ ከተሞች በተለይም በኦስሎ በበርገንና በስታቫንገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል
በዚህ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ በአሁኗ ሰዓት በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ በየመንና በሊብያ የደረሰባቸውን ግፍና ጭካኔ በማውገዝ መፈክሮች ያሰሙ ሲሆን በወያኔ መንግስት በግፍ ታስረው በየወይኒ ቤቱ የሚገኙት የሕሊና እስረኞች ይፈቱ ዘንድ ጠይቀዋል በማያያዝም የኖርዌይ መንግስት ለአንባገነኑ የወያኔ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ ያጤነው ዘንድ እንዲሁም የኖርዌይ ህብረተሰብ የሚከፍለው ታክስ ለጨኝቋ አገዛዞች እንዳይውል ይቆጣጠሩ ዘንድ በራሪ ወረቀቶችን በመስጠት አሳስበዋል።

No comments:

Post a Comment