Friday, May 29, 2015

ፍ/ቤቱ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የቀረቡ የሲ.ዲ መረጃዎችን ውድቅ አደረገ


በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ዛሬ ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ የተቀጠረው አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ባለመፍቀድ ከዚህ በኋላ ምስክሮቹን እንደማይሰማ አመልክቷል፡፡
አቃቤ ህግ በኤግዚቢትነት ይዟቸው የቆያቸውን የ12ቱን ሲ.ዲዎች ጉዳይ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ሲ.ዲዎቹ በማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ ፕሪንት ተደርገው የተያያዙ ሰነዶችን እንደያዙ ስለተገለጸ ሲ.ዲዎቹ ከማስረጃነትም ሆነ ከኤግዚቢትነት ውድቅ መደረጋቸውን ገልጹዋል፡፡
አቃቤ ህግ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የሲ.ዲ ዶክሜንተሪ ማስረጃ ማቅረቡን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትለት የጠየቀ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አቃቤ ህግ ሲ.ዲውን በጽ/ቤት በኩል እንዲያስገባ በማዘዝ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን ዶክሜንተሪ በቢሮ ዳኞቹና ጠበቆቹ እንዲመለከቱት ከተደረገ በኋላ ሲ.ዲው ሌሎችን ተከሳሾች ይመለከታል ወይስ አይመለከትም የሚለውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 8/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ተከሳሾች ጥያቄያቸውን ለፍርድ ቤቱ ለማስረዳት በሞከሩበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ የመናገር እድል ሲነፈጉ የተስተዋለ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቅድላቸው ሲጠይቁ ‹‹ስነ-ስርዓት አድርጉ!›› ባለ ጊዜ ጦማሪ አቤል ዋበላ ‹‹እናንተ ራሳችሁ ስነ-ስርዓት አድርጉ….እንናገርበት! ይህ የመብት ጉዳይ ነው…በግልጽ ችሎት ላይ ህገ መንግስታዊ መብታችንን አክብሩ እንጂ…ጥያቄ አለን ተቀበሉን›› ሲል በመናገሩ ችሎት ደፍረሃል ተብሏል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ በአቤል ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና የፋይናንስ ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ አዲሱ ካሳሁን ከ ሀገር ተሰደዱ.

አንድነት ፓርቲ በህዝብ ዘንድ እያገኘ በመጣው ከፍተኛ የህዝብ ተቃባይነት ስርአቱ ለስልጣኑ አንደ ሚያሰጋው በመገንዘብ ፓርቲውን ማፍረሱ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው::
ፓርቲውን አፍርሶ ጠንካራ የሚባሉ ለፓርቲው ብዙ ያገለገሉ ሰዎችን እያሳደደ በማሰር በመደብደብ ላይ ይገኛል ……
አቶ አዲሱ ካሳሁን ለረዥም ግዜ በፓለቲከው ላይ የራሱን እስተወፆ ሲያበረክት በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የፓለቲካ ስራ ሲሰራ ቆይቶል በዚህም ምክነያት በስረአቱ ጥርስ ውስጥ ሊገባ ችሎል….
ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ስረአቱ በተለያዩ ግዜያቶች ስራውን በአግባቡ እንዳይሰራ እና ኑሮውን እንዳይመራ ሲያደርገው ቆይቶል …..
አተቶ አዲሱ ካሳሁን ከቅርብ ግዜያቶች ወዲህ በእሱ እና በቤተሰቡ ላይ መንግስ ከፍተኛ ወከባ እን እንግልት እየደረሰበት በመሆኑ ከዚህ ብሆላ አገር ውስጥ ቢቆይ ለሂወቱ አደጋ መሆኑን በመገንዘብ አገር ጥሎ ሊሰደድ ችሎል::


Matewos Arbu's photo.

Tuesday, May 26, 2015

ትንሻ የዴሞክራሲ መስፈርት ያላማላ ምርጫ 2007


ታዛቢዎችና ተቃዋሚ ፓርቲ ኣባሎች በማዋከብ ተጀምሮ ያለ ተቀዋሚ ፓርት ታዛቢ ቆጠራ የተጠናቀቀው ምርጫ 2007 ኣምባገነኑ የሕወሓት ስርዓት ያለ ህፍረት ኣይኑን በጨው ኣጥቦ ኣሸነፍኩኝ ለማለት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦር የወያኔ ኣጋር ፓርቲ እስኪመስል ድርስ ሙሉ ድጋፉን ለወያኔ የሰጠው ቦርድ ስለ ምርጫው ዴሞክራሲነት ለማዉራት ሞራሉ እንካ ባይኖሮው ነገር ግን ወያኔ ከዓለም መንግስታት ለየት የሚያደርገው የክህደትና የማጭበርበር ስልቱ ይህንን የሞተ ቦርድም መግለጫዎች ሲያጎርፍ ተመልክተናል፡፡
ወያኔ እንደ ሰለማዊ ትግልን የሚፈራው ነገር እንደሌለ ምርጫ በመጣ ቁጥር የሚያስገለብጠው ኮሮጆ እና የሚያዋክባቸው ተቆዋሚ ፓርቲዎችን በማየት የሚገለፅ ሲሆን ኣሁንም ግን ወያኔ ሃገሪትዋ በማጭበርበር ዳግም ለመግዛት ኣቅዶዋል፡፡
በሰለማዊና ነፃ ምርጫ ተወዳድሮ ኣሸንፎ የማያዉቀው ኮሮጆ ገልባጩ ወያኔ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ወደ ጦርነት ለማስገባት እየጣረ ይገኛል፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን ኣንድነታችን በማጠናከር ወያኔን ለመገልበጥ መዘጋጀት ኣለብን፡፡
ሁሌም ቢሆን ወያኔ ኮሮጆ በማስገልበጥና እና ወላጆቻችን እዚች ንብ ላይ ምልክት ኣድርጉ እየተባለ እየተዋከበ ብግድ ምልክት ቢያደርግም እኛ ተቀዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና መድርክ በቅርቡ ዉህደት ፈጥራችሁ ህዝባችሁን እንድታስደስቱትና በምርጫ 2012 ዓ/ም ለመወዳደር እንድትዘጋጁ እያልኩኝ በወያኔ ድራማዊ የምርጫ ሂደት ፍፁም ፀረ ዴሞክራሲ በሆነ ምርጫ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባችሁ ኣሳስባለሁኝ፡፡
በእርግጥ የወያኔ መንግስት የተንኮልና የማጭበርበር እንጂ በህዝብ ተቀባይነት የሌለው በምርጫ ሁሌም እየተሸነፈ በጠመንጃ እና በምርጫ ቦርድ ትብብር ስልጣኑን የሚደላድል ወያኔ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያወግዘው ይገባል፡፡
ወያኔ የበረሓ ባሕሪዉን ያልለቀቀው ገና 25 ዓመት ኣዲስ ኣበባን ከትሞ የዘመናዊነት ኣስተሳሰብ ያልተላበስ ሁሌመ በጫካ ሕግጋትን እቺ ሃገር ለማተራመስ እንዳቀደ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ዘላለሙ እንደዋሸ ለሞኖር የሚያደርገው ጉዞ የሚያከትምበት ዘመን ሩቅ እንደማይሆን መገመቱ ኣያስቸግርም ኣሉ የተባሉት ተቀዋሚፓርቲዎች ልዩነታቸው ኣጥብበው ፀረ-ወያኔ ከተሰለፉ ፡፡
ኑና ሁላችንም ፀረ-ወያኔ እንሰለፍ፡፡

« በጉልበት ወደ ዘመናዊነት » የጀርመን ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ ስለ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ሲዘግብ

እሁድ በመላው ኢትዮጵያ የተካሄደውን 5ኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ባይሄዱም ፤ የዶይቸ ቬለን ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን ጨምሮ የጀርመን ጋዜጦች ስለምርጫው ዘግበዋል። የጥቂቱን የጀርመን ጋዜጦች ዘገባ እንደሚከተለው ነበር።
የጀርመን ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ « ዙድ ዶይቸ ሳይቱንግ» ስለ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ሲዘግብ ርዕሱን« በጉልበት ወደ ዘመናዊነት » ነው ያለው። የጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ፓርቲ ኢሀዲግ እንደሚያሸንፍ ጥርጥር የለውም ሲል የዘገበው ይህ ጋዜጣ ፤ «ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርግጥ ጥሩ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበች ሀገር ብትሆንም አሁንም ድረስ እንደ « ልማታዊ አምባገነን» ነው የምትታየው፣ መንግሥት የኤኮኖሚውን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡንም ይቆጣጠራል ሲልም አትቷል ።ጋዜጣው የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶችን ዋቢ በማድረግ፤ ሂስ ሰንዛሪ ጋዜጠኞች በሀገሪቱ ቦታ እንደሌላቸው ወህኒ ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችን እና የኢንተርኔት ዘጋቢዎችን በምሳሌነት ጠቅሶ ያብራራል። ጋዜጣው ስለ ሃገሪቱ ልማትም ፅፏል። ምንም እንኳን ልማቱ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማህበረሰበብ ጋር ባይደርስም፤ በአዲስ አበባ ትላልቅ ፎቆች እየተሰሩ ስለመሆኑና በቅርቡ የቀላል ባቡር አገልግሎት ስራውን እንደሚጀምር ይጠቁማል።

« ዙድ ዶይቸሳይቱንግ»የኢትዮጵያ ምርጫ ሀተታውን ከማጠናቀቁ በፊትም፤ የተቃዋሚዎች እጣ ፋንታ ከባለፈው ምርጫ ጋር ሲነፃፀር አለመሻሻሉንም አንስቷል። እንደ ጋዜጣው ቀውስ ውስጥ ከሚገኙት ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን ጋር ስትነፃፀር ምዕራባውያን ኢትዮጵያን የተረጋጋች ደሴት አድርገው ስለሚመለከቷት የዲሞክራሲ ርዕስ ሲነሳ ፤ ጆሮ ደባ ልበስ ብለው ያልፉታል።
ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ የዘገበው «ታገስሻው» የተባለው የጀርመን የዜና ማሰራጫ ነው። «ተቃዋሚ ድምፅ የለውም» በሚለው ርዕሱ፤ የምርጫው አሸናፊ ፓርቲ ኢሀአዲግ እንደሚሆን እንደማያጠራጥር ያትታል። ታገስሻው ከዚህም በተጨማሪ ፤ በቴሌቪዥን ሥርጭቱ እና በድረ ገጹ ከሀገር ሸሽቶ ናይሮቢ ውስጥ ጥገኝነት ስለጠየቀው ጋዜጠኛ የትነበርክ እና ደረሰብኝ ስለሚለው በደል ዘግቧል።

«ፍራንክፈርተር አልገማይነር » የተባለው የጀርመን ጋዜጣም ቢሆን እንደሌሎቹ ጋዜጦች ፤ማን ምርጫውን እንደሚያሸንፍ ግልፅ ነው ይላል፤
 « እንደ ብረት የጠጠረ አገዛዝ ባላት ሀገር» በሚለው ርዕሱ ከ457 የምክር ቤት መቀመጫ 456ቱን ኢሀአዲግ ይዞ የመራው ሀገር እንደሆነ በመግለፅ፣ ጋዜጣው ፤ የተቃዋሚዎችን ነፃ አለመሆን እና ብሶት ያትታል። ከዚህም በተጨማሪ ጋዜጣው ፤ ምናልባትም ነፃ ምርጫ ታይቶበታል ያለውን የ97ቱን ምርጫ እና ከዛም በኋላ ስለተነሳው አመፅ እና በወቅቱም ከ200 በላይ ሰዎች ስለመሞታቸው አውስቷል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ አሸባሪ ቡድናትን በመዋጋት የዩናይትድ ስቴትስ ስልታዊ አጋር መሆኑን ጋዜጣው ጠቅሷል ።

©ዶይቸ ቬለ

Monday, May 25, 2015

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ


ወኪላችን እንደዘገበው በሰቆጣ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።
ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው።
ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
መንግስት በአካባቢው ስለተከሰተው ድርቅ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም።
ESAT's photo.
ESAT's photo.ESAT's photo.

ፓስተር ዳዊት ሞላልኝ የተባለ ግለሰብ ህጋዊ የትዳር አጋሬን ባለቤቴን በቁሜ ነጠቀኝ:: አቶ ግርማ ዱሜሶ

Petros Ashenafi Kebede's photo.
Petros Ashenafi Kebede's photo.Petros Ashenafi Kebede's photo.
ይህንን ጽሁፍ እራሳቸው አዘጋጅተው ከእነ ፎቶግራፋቸው የላኩት ግለሰብ ነዋሪነታቸው በሰሜን አሜርካ በአትላንታ ጆርጂያ ግዛት የሚኖሩት አቶ ግርማ ዱሜሶ የተባሉ ግለሰብ ህጋዊ ባለቤቴን ወ/ሮ ትግስት አበበ ደምሴን ፓስተር ዳዊት ሞላልኝ የተባለ ግለሰብ አስነውሮብኝ ትዳሬን አፍርሶታል:: እኔም እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ባደረሱብኝ ከባድ የህይወት ወንጀል በተደጋጋሚ ሁለቱም ግለሰቦች በቤተክርስትያን በኩል እንዲጠየቁልኝ እና ክርስቲያናዊ ይቅር እንድንባባል በተደጋጋሚ አሜርካ ውስጥ ለሚገኙ የኢትዮጵያናውያን ቤተክርስትያኖችን ጠይቄ ከቤተክርስትያኖቹ ምላሽ አጥቼያለሁ ስለሆነም ውድ የእግዚያብሔር ቤተሰቦች የሆናችሁ እውነተኛ ክርስቲያኖች ይህንን እውነተኛ ታሪኬን አንብባችሁ ፍርዳችሁን እንድትሰጡኝ በጌታ ኢየሱስ ስም እማጸናችኋለሁ
ቀን 03/16/2015
ለቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና
አትላንታ ጆርጂያ (USA )
ጉዳዩ ፡ በኔና በትዳሬ ላይ የደረሰውን በደል ፤ ነውርና ጥቃት ይመለከታል!
በእግዚአብሔር የተወደድክና በጣም የማከብርህ መንፈሳዊ አባቴ ( ፓስተሬ ) ነህና “አንተ “ ብልህ እንደ ድፍረት እንደማትቆጥርብኝ ተስፋ አደርጋለሁ ። ተወልጄ ባደኩበት ማህበረሰብና እንዲሁም በእግዚአብሄር ቃል ውስጥም ቢሆን ሰው ፈጣሪን የሚያህል አምላኩና የሥጋ ወላጅ አባቱን “አንተ “ እንጂ “እርስዎ አምላኬ ሆይ “ ብሎ ስጣራ አልሰማሁም ።
በመሆኑም በሚገባኝ መንገድ ከልቤ በሆነ አክብሮት የጌታ ሰላም ፤ ምህረት ፤ጥበቃና ቸርነት እየተመኘሁልህ ፤ እንዲሁም ረጂም ዕድሜና በረከት ይብዛልህ ለማለት እወዳለሁ።
ፓ/ር ፡
ምንም እንኳን አንተን ማድከምና ማሰልቸት ቢሆንም ከዚህ ቀደም በአካልና በሰልክ ደጋግሜ ያጫወትኩህን (በሰፊው የተነጋገርንብትን ) እና አሁንም ድረስ የተቸገርኩበትን ብርቱ ጉዳዬን ከዚህ እንደምከተለው እንደገና ልገልጽልህ ወደድኩ ። ያም ጉዳይ ቀደም ሲል አንተም የሚታውቀውና በቅርቡም በቢሮህ ተገኝቼ በዝርዝር ገልጬልህ በተነጋገርነው መሰረት ሚስቴ የነበረችው ወ/ሮ ትግስት አበበ ደምሴና ፓ/ር ዳዊት ሞላልኝ አበጋዝ የሚባሉ ግለሰቦች ያደረሱብኝን በደልና ጥቃት የሚመለከት ነው ፡፤
እነዚህ ግለሰቦች እንደ ሌሎቹ ቅዱሳን አማኞች መልካምና ጥሩ ስነ-ምግባር ያላቸው እውነተኛ አገልጋዮች መስለውኝ አመንኳቸውና በቅንነትና በየዋህነት በልበ-ንጽህና ቀረብኳቸው እንጂ ከኋላዬ ዞረው ፈጣሪን በመዳፈር ለብቻቸው የተደበቀ እና ስውር የሆነ የግል ሚስጢርና ግንኙነት ኖሮአቸው ነውርን በትዳሬ ላይ ሊሰሩ ይችላሉ ብዬ ለማሰብ አንዳች ስጋትና ግምት አልነበረኝም ፤ ትዳሬን አፍርሰው ህይዎቴን አደጋ ላይ ይጥሉኛል ፤ ለከፋ ብስጭትና ኪሳራ ይዳርጉኛል ፤ ያዋርዱኛል ብዬ ጨርሶ አላሰብኩም ነበር ።
ይሁን እንጂ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በመሆናቸው እምነት ጥዬባቸው ሳለ በገርነቴና በቀናነቴ በነዚህ በእግዚአብሔር አገልጋይ ተብዬዎች በደል ደረሰብኝ ፤ ተጎዳሁ ፤ ተጠቃሁ ።በዚህ በተፈጸመብኝ በደል የተነሳ እጅግ በጣም አዝኛለሁ ። በዋናነት የበደለኝም ብልጣ-ብልጡ አፈ-ጮሌ ፤ አስመሳይ መንፈሳዊ ሰው መሳይ ዳዊት ሞላልኝ የተባለ የ “FBI “ ቤተክርስቲያን ፓ/ርና መሪ ግለሰብ ነው ።
ይህ ያለንበት ዘመን በተለያየ ስፍራ በሃይማኖታዊና በመንፈሳዊነት ስም የምመላለሱ መንፈሰዊ ዱሪዬዎች እጅግ የበዙበት ወቅት በመሆኑ በእግዚአብሄርና በአገልግሎት ስም እያመኻኙ ባለቤቱ የከደነውን አለፈቃድ የሚከፍቱ ፤ ያስቀመጠውን አንስተው የሚወስዱ ፤ የሰውን ኑሮ የሚያናጉ ንጹሕ ፍቅር ባላቸው ጥንዶች መካከል እየገቡ በሰላምና ደስታ ፋንታ ጭቅጭቅንና ሃዘንን የሚያደርሱ የፍቅርና የቅድስና ጠላት የሆኑ ጉዶች የፈሉበት ጊዜ ነው ቢባል ያጋነንኩ አይመስለኝም ።
ፓ/ር ዳዊት ከዚህ ቀደም ማንንም ገጥሞት በማያውቅ ሁኔታ በሃይማኖት ተጀቡኖ ፤ በአገልጋይነት ሰበብ ተሸፍኖ፤ በእግዚአብሄር ስም እየነገደ ፤ በንቀት ድፍረት ተሞልቶ የሥጋ ፊላጎቱን ማርኪያና መደሰቻ ሲል ትዳሬን አፈራርሶታል ።ይህንንም ያደረጉት በተጋባን ዕለት ካረፍንበት ሆቴል ሙሽሪት( ወ/ሮ ትግስት) ቬሎ ልብሷን ቀይራ እኔን በሆቴል ውስጥ ጎልታኝ ሁለቱ ግን የግል ሥጋዊ ፊላጎታቸውን ለመፈጸም አንዴ ብቻ ሳይሆን ሁለቴ የድፍረት ሙከራ ፈጽመውብኝ አክሽፈዋለሁ ፤በመቀጠልም በቤተዘመድ በታላቅ እህቴ ቤት በተዘጋጀልን የመልስና ቅልቅል ጥሪ ላይም በዕለቱ የተጠሩት የሥጋ ዘመዶቼ እንኳ ሳይታደሙ በሚያስደነግጥ ሁኔታ እኔን (ሙሽራውንም) ሆነ ዘመዶቼን በንቀት ተመልክተውን ከምንም ሳይቆጥሩን አሳዝነውን እና አሳፍረው ግብዣውን አቋርጠው ተያይዘው መሄዳቸው ፤ በሌላ ቀን ደግሞ ወደ አረፍንበት ሆቴል ድረስ በራሱ መኪና ልወስዳት ሲመጣ ፈቃደኛ አለመሆኔን ለመግለጽ ቢሞክርም ጉልቤው ዳዊትና ሚስቴ ራሷ “ አንተን ያወቅንህ ገና ቅርብ ጊዜ ነው ፤ እኛ ግን የቆዬ ጓደኝነትና የጋራ አገልግሎት አለን ፤ ስለዚህ ከተስማማህ እረፍና ቁጭ በል ካልተመቸህ የራስህ ጉዳይ “ ብለው ዓይኔ እያየ ያለፈቃዴ ሚስቴን ነጥቆኝ ሄዷል ።
እንዲሁም ሌላ ጊዜ ደግም አብረን በአውሮፕላን እየተጓዝን ሳለን እኔን ባሏን “ አንተ መጽሐፍ አንብብ ፤ ዳዊት ብቻውን ነውና እሱ ወደ ተቀመጠበት ወንበር ሄጄ ላጫውተው “ በማለት በአውሮፕላን ውስጥም እንኳ ለብቸኝነት ዳርጋኛለች ። በአንድ ወቅት ደግሞ አንድ
ከተማ ውስጥ አብሬን በተመሳሳይ ሆቴል ውስጥ ባደርንበት ጊዜ (ዕለት) “ከዳዊት ጋር የአገልግሎት ጉዳይ የሆነ የሚናወራው ነገር አለን “ በማለት lab top computer ይዛ ያረፍኩበትን ሆቴል መኝታ ክፍል በር ዘግታብኝ ከሄደች በኋላ የት እንዳደረች ሳላውቅ በ2ኛው ቀን ምግብ መመገቢያው ውስጥ ከግለሰቡ (ዳዊት ) ጋር ቁርስ ስበሉ ለዚያውም ከሩቅ እስካ አየኋቸው ሰዓት ድረስ የትና ምን ሲሰሩ እንዳደሩ እግዚአብሔርና እነሱ ብቻ ናቸው የሚያውቁት ።
በሌላውም የምሳና የእራት ፤ እንዲሁም የቁርስና ቡና ሰዓታት እሷ ሁሌ ከሰውዬው (ዳዊት ) ጋር በመሆን ለብቻቸው ተጣብቀው ስላሉ (ስለምቀመጡ ) ከሙሽራዋ ሚስቴ ጋር ማዕድ ለመቆረስ እንኳ አልታደልኩም ነበር ።የስልክ አጠቃቀሟም ቢሆን ባለሁለት ቀፎ ስለሆነ ከዳዊት ጋር በስልክ ስታወራ ከኔ ርቃ ወይም መኝታ ቤት ገብታ ዘግታ በመቆለፍ ስለሆነ አብሬያት በቆየሁባቸው ጥቂት ወራት የብቸኝነትን ህይዎት ነበር የተጋፈጥኩት ።
አትላንታ ከተማ ተመልሰን በገዛ ቤታችን በእንግድነት ሰውዬውን ( ዳዊትን ) ባስጠጋነው ወቅትም ቢሆን እኔን ሳሎን ( ምግብ ቤት ውስጥ) ትተውኝ “ ስለ አገልግሎት የምንመካከረው ጉዳይ አለን” ወዘተ .. በማለት በራሴ መኝታ ቤት ወይም እንዲተኛበት በሰጠነው መኝታ ክፍል ውስጥ ቢያንስ ለ2 እና ከዚያ በላይ ሰዓታት ያህል በር በመቆለፍ ያደረጉትን አገልግሎት ፈጣሪ ብቻ ይመልከተው ከማለት ሌላ ለማውራት የማይቻለኝ የሚቀፍና ህሊናን የሚያደማ ነገር ነው ።
ይህ ብቻም ሳይሆን ባጋጣሚ እኔ አስቀድሜ ወደ መኝታ ቤቴ ውስጥ ከገባሁ ደግሞ ሌላ ሰበብ ይፈጥሩና “ ከዳዊት ጋር የሚንሰራው አጣዳፊ ጉዳይ አለኝ “ በማለት ኮምፒዩተሯን ይዛ እስከ እኩለ-ሌልት አንዳንዴም እስኪነጋ በሌላው ክፍል ወይም በሳሎናችን ውስጥ አብረው ያድሩ እንደነበር እነሱ ራሳቸው (ዳዊትና ትግስት ) ባሉበት ያንተ ረዳት ፓስተሮችም በተገኙበት ቢሮህ ውስጥ ለበርካታ ሳዓታት ( 7 ሰዓት ) ሙሉ በግልጽ ስንነጋገር አለመካዳቸው የሚታወስ ነው ።
ይህ ድንበርና ገደብ የለሽ መንፈሳዊ ሽፋንና ሃይማኖታዊ ሰበብ ከባል ስልጣንና ፈቃድ ውጪ የተሰወረ ሚስጢራዊ አገልግሎት ሊደረግ ሲታሰብ ምን ሊሆን እንደሚችል ፍርዱን ለፈጣሪና አመዛዛኝ ህሊና ላለው ሰው ሁሉ ትቻለሁ ።
ሌላው ደግሞ በአጋጣሚ እንኳ እግሯን አንድ ነገር ስያደናቅፋት ፤ ዕቃ ስወድቅባት እና ድንገት የሆነ ድንጋጤ ስሠማት በቁልምጫ “ዴቭ ድረስልኝ “ ስትል መስማት፤ እንዲሁም ከወላጆቿ ፤ከሥጋ ዘመዶቿና አብሮ አደግ ጓደኞቿ እንዲሁም ከኔና እሷ ፎቶግራፎች ይልቅ የዳዊትን ፎቶዎዎች በመኝታዬ ራስጌና ግርጌ ፤በሳሎን ቤትና የማድ ቤት ( ኩሽና ) ማቀዝቀዣ ላይ ዘወትር ማየት አዕምሮን የሚያደማና ህሊናን የሚያቆሽሽ ትዕይንት ነበር ። እስቲ አትታዝቡኝና በሷ ልብና አምሮ ውስጥ ይህ ዳዊት ምኗ ይሆን ? እኔስ ምኗ ነበርኩ ?
በአጋጣሚ ይህንን ደስ የማይል ታሪክና ዜና ለሚሰሙትም ሆነ እሮሮዬን ለሚያነቡት ሁሉ ለማለት የሚፈልገው ነገር ቢኖር 1ኛ እንዲህ ያለው እልህን ጭሮ ለከፋ ወንጀል የሚገፋፋው አደናጋሪና አጠያያቂ ክፉ ፈተና በገዛ ቤቴ ስለገጠመኝ እንኳን መሸከምና መታገስ ቀርቶ ለመስማትም ሆነ ለማውራት የማይቻለው የስቃይ ጦርነት እየተፈራረቀብኝ በእግዚአብሔር ጸጋ እስካሁን ድረስ በህይዎት መኖሬ እኔን እራሴ ስገርመኝና ስደንቀኝ የሚኖር የጌታ ጥበቃና ውለታ ነው ። እግዚአብሔር አምላክ የማይቻለውን አስችሎ ከክፉ ሁሉ ጠብቆ ነፍሴን ስላኖራት ክብር ምስጋና ይህንለት እላለሁ ፤ 2ኛ የተወደደች ፤ እግዚአብሔርን የሚታውቅ ፤ የምትፈራ ፤ በቃሉም የምትመራ ፤ ለፈጣሪ ፤ ለባሏ ፤ለህሊናዋ ፤ለኑሮዋ ታማኝ የሆነች መልካም ሴት ( ሚስት ) አግኝቶ አዕምሮው ካልተቃወሰ ( የጤና ችግር ከላጋጠመው ) በቀር ማን በዋዛ ሚስቱን ይጥላል ? ( ይተዋል ) ? ያልታደልኩትን እኔን ካልሆነ በቀር እንዲህ ዓይነቱ ውንብድና ፤ ሃፍረት የሌለው ጥቃት በማን ላይስ ደርሶ ያውቃል ?
ይህ ከመሆኑ በፊት ምንም እንኳን በውቅቱ የገባሁበት አጣብቂኝ ለማውራትም እንኳ የሚቀፍ ፤ ውስብስብ ፤ የከረፋ ቆሻሻና ጸያፍ ከመሆኑ የተነሳ ልታገሱት የማይቻል ቢህንም ፤ ለብዙ ዘመን ተጠምቼ ፤ ተመኝቼና በትዕግስት ጠብቄ ያገኘሁት ፤ ብዙ ዋጋ የከፈልኩበት ትዳሬ ስለሆነ ሙሉ ለሙሉ ከመበላሸቱ በፊት እስቲ ይሁን ብዬ ፤ ይቅር ለእግዚአብሔር በማለት ሁሉን ረስቼ ፤የማይቻለውን ችዬ ፤የማይረሳውን ረስቼ ፤ ነገን ብቻ ተስፋ በማድረግ እንደገና ጠጋግኜ ለማዳን የሞከርኩት ትዳሬ አፈር ድሜ በልቷል ።
እንዲህም እንኳን ሆኖ ወዲያውኑም ውዬ ሳላድር ባንድም ሆነ በሌላ ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኔ ሰበብ የእግዚአብሔር ቤት መጠቋቋሚያና መሳለቂያ ከሚሆን ፤ሌሎች ቅዱሳንና እውነተኛ ታማኝ የሆኑ አገልጋዮችና መሪዎች ስም በመጥፎ ምሳሌ አብሮ ከሚነሳ ( ከሚጠፋ) ፤አገልግሎታቸው ከሚተች ፤ራዕያቸው ፤ ዓላማቸውና ትጋታቸው ዋጋ እንዳያጣ ፤ሳይጣን ከሚደሰት ፤ ሁላችንም የዓለም አጀንዳ ከሚንሆን፤ እግዚአብሔርንና መንፈሱን ከማሳዘን ፤ በተለይም በእምነታቸው ያልበረቱ አዳዲስ አማኞች ግራ እንዳይጋቡ እኔው ደግሜ ደጋግሜ ልጎዳና የሚቻል ከሆነ እስቲ እንደገና ትዳሩን ወደ ነበረበት ልመልሰው በማለት ያሰብኩት ቀናነት ዋጋና ትኩረት ተነፈገው።
ይህ ሁሉ ሆኖ ሰውየው ( ፓ/ር ዳዊት ) ይህንን ለፈጸመበት ጥፋትና አስነዋሪ ተግባር እስካሁን አልተገሰጸም ፤ አልተወቀሰም ፤ አልተከሰሰም ይቅርታም አልጠየቀም ። ነገር ግን የከበረውን ትዳሬን አፍርሶ እሱ ግን ዛሬም እያሾፈ በሰላም ይኖራል ፤ እንዳውም ይባስ ብሎ ቤተክርስቲያንን ይመራል ፤ የእግዚአብሄርን ቃልና ፈቃድ አስተምራለሁ ፤ የክርስቶስን ዓላማ እያራመድኩ፤ እያስፈጸምኩ ነኝ ይላል ።ግብረ አበሩ የሆነችውም ወ/ሮ ትግስት የራሷን ትዳር ንዳ ዛሬም አብረው በመሆን ሥፍራና ጊዜ እየቀያየሩ በየአብያተክርስቲያናቱ ዘንድ የተለመደውን ተራ ግርግር እየፈጠሩ መንፈሳዊ አገልጋይ ለመባል እየጣሩ ናቸው ። በኔ ላይ በለመዱት ዓይነት አኳኋን በተመሳሳይ ሁኔታ የኔ ዓይነቶቹን ሌሎች የእግዚአብሔር ህዝብ መተራመስ የለበትምና ድርጊቱ ተገላልጦ የማያዳግም ትምህርት ተሰጥቶ ህዝበ-እግዚዝብሔር ከመታለልና ተመሳሳይ ሰለባ ከመሆን መዳን አለበት ።
እነዚህ ፌዘኛ ግለሰቦች ፤ እጥቤ አሿፊ ጩሉሌዎች ሃፍረትና ይሉኝታ የሌላቸው ደንታ-ቢስ ባይሆኑ ነው እንጂ እንኳን በቤተ-እግዚአብሔር ውስጥ ካህን የሆነ ሰው ቀርቶ በዓለም ያሉቱ ካሃዲዎች ዘንድም እንኳ እንዲህ ዓይነቱን ወንጀል ስፈጽሙ ተሰምቶና ተደርጎ አይታወቅም ። እኔ ተራ እቃ ( ንብረት ) ብቻ አይደለም የጠፋብኝ ፤ ገንዘብና ጊዜ ብቻ አልነበረም የባከነብኝ ።ነገር ግን ትዳሬ እኮ ነው የፈረሰው ፤ መተኪያ የሌለውና የዚህ ምድር አስፈላጊ እና እግዚአብሔር ባርኮ ከፈቀደልን እድሎችና መብቶች አንዱ ነው ትዳር::
በሌላ አባባል ትዳር ከእግዚአብሔር ቃልና መመሪያ ውጪ ሌላ ፎርሙላ የለውም ፤ “ ሰው እናት አባቱን ይተዋል ከሚስት (ከባል ) ጋር አንድ ይሆናል፤(ይጣበቃል) “ እንደሚል አንድ ሥጋ ፤አንድ አካል ፤አንድ መንፈስ በመሆን አንድ ዓላማ ይዘው ጥንዶች በፍቅር የሚጣመሩበት ነው ። በዚህ ዓላማ የተጣመሩ ጥንዶች አንዳቸው ከሌላኛው የተለየ ፊላጎት እና የተደበቀ ልዩ ሚስጢርና ፊላጎት ሊኖራቸው አይገባም ፤
ነገር ግን ያልታደለው የኛ ትዳር ግን ገና ስፈጠር ከአጀማመሩ በጨቅላነቱ በአጭር የቀጩት ቢሆንም ትዳሬ ለኔ ህይወትና የከበረ የአምላኬ ስጦታ ነበር ። ትዳር አንዴ ብቻ ነው ፤ ማፍቀርም የምቻለው አንዲትን ሴት ፤ ለዚያውም ከተቻለ አንዴ ጊዜ ብቻ ። ዳስታም ቢሆን ሁሌ የለም፤ በየዓመቱ ሠርግ ለማድረግም የማይታሰብ ነው ። የሆነው ሆኖ ለአንዲት ደቂቃ ( ዕለትም ) እንኳ ቢሆን ያፈቀርኳትን ሴትና የከበረውን ትዳሬን በቀላሉ በፓ/ር ዳዊት ሞላልኝ ምክንያት አጥቻለሁ ።
ስለዚህ የከበረና የናፈቅኩት ፤ የተመኘሁት ጅምር ደስታዬ በእንጭጩ ከመቅጽበት በመቀጨቱ ወደ ሃዘንና ውርደት ተቀይሮ አንገት አስደፍቶኛል ፤እልሀኛ ፤ ቂመኛና በምሬት የተሞላሁ ተናዳጅ አድርጎኝ ሄዷል ።ነገ ደግሞ ምን እንደሚሆንና ምን እንደሚገጥመኝ እርግጠኛ አይደለሁም ።
ይህ ግለሰብ (ዳዊት) ግን ኑሮዬን አፍርሶ ፤ ህይዎቴን አበላሽቶ እንዲህ እንደ ቀልድ እያሾፈ ሊኖር ነው ? ካደረሰብኝ ብርቱ ፈተና የተነሳ በህይወት ለመኖር የማያስችል ፤ ለወንጀል የሚገፋፋ ፤ ለከፋ በሽታና ጥልቅ ሃዘን የምዳርግ ነው የገጠመኝ ። አረ ለመሆኑ በትዳርና በርስት ቀልድ አለ ? በዓይንና በሚስትስ መጫወት ይፈቀዳል ? እንኳን ግፍና በደል በግልጽ በቤቴ ተፈጽሞብኝ ቀርቶ ድርጊቱ ደግሞ ከጥርጣሬ ያለፈ የአደባባይ ጥቃት መሆኑ ይቅርና እንዲሁ በጥርጣሬም እንኳን ቢሆን በሚስቴ የልቅነት ድርጊት የተነሳ የመቅናትም ሆኔ የተጣመመውን የማቅናት መብቱ ለኔ የሚገባኝ ህጋዊ ባል (አባወራ ) አይደለሁምን ?
እስቲ ፍረዱኝ አንድ መንፈሳዊ አገልጋይ በአገልግሎት አሳቦ የራሱን ሚስት እቤቱ አስቀምጦ “ዘመዴ( ካዝኔ) ናት “ እያለ አንዲትን ሌላ ሴት እንደ ኮሮጆ ሸክፏት ፤ እንደ ሻንጣ እየጎተተ ከሀገር ሀገር ፤ ከከተማ ወደ ከተማ በየሆቴሉ ሁሉ አስከትሎ ስጓዝ ትንሽ እንኳን ይሉኝታ አይዘውም ? ያቺስ ሴት ብትሆን የ”ሶሎ ዘማሪ ፤ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ፤ ወይም በመድረክ ላይ የቋንቋ አስተርጓሚ (ሰባኪ ) ሳትሆን የራሷን መደበኛ ኑሮ ትታ እንደ ጭን ገረድ በየሀገሩና መንደሩ የማንንም ወጠምሻ ጎሮምሳ ተከትላው እየዞረች አብራው በየሆቴሉ አብራው ስታድር ሁለቱም ህሊና የላቸውም ዎይ ?
ሁለቱም በገዛ ህሊናቸው ባይኮረኮሩ ፤በመንፈስ ቅዱስ ለምን አልተወቀሱም ? አዕምሮ ቢደነዝዝ ፤ ህሊናቸው የማይወቅሳቸው ፤ የአውዋቂን ምክርና ተግሳጽ የማይሰሙ ፤የህዝብን ትዝብትና ግልምጫን ከምንም የማይቆጥሩ ቢሆኑም ከነአካቴው ሁሉም ይቅርብኝ እንጂ እኔ ግን ትዳሬን በማንም ማስነካት ፤ ሚስቴንም ከማንም ጋር መጋራት ስላልፈለኩ ሳልወድ በግድ ከመካከላቸው ወጣሁ ።በዚህም በዘመኔ ሁሉ የማልረሳ የህይዎት ጠባሳ እና ስብራት ትቶልኛል ፤ አንዳንዴ ቁጭ ብዬ እያሰላሰልኩ ሳስብ ባልጠፋ ሰው ከነዚህ ቅንነት ከጎደላቸው ሰዎች ጋር እኔ ስገጣጠም እግዚአብሔር ለምን ዝም አለኝ ? ይህ ሁሉ ጉዳት ፤ መቁሰል ፤ መድማት ፤ መፈራገጥ ፤መላላጥ ብሎም ለብርቱ ሃዘን መጋለጥ ለማን ይጠቅም ይሆን ? ማንስ ይከብርበት ይሆን ? ማን ከስሮ ቀርቶ ማንስ ያተርፍ ይሆን ? እንዳው ባጭሩ ይህ ዳዊት የሚባል ሰውዬ እንዲህ አቃጥሎኝ አዋርዶኝ እስከመጨረሻው የሚሳካለት መስሎት ይሆን ? ደስታዬን እንዲህ በአጭር
አጨልሞ እሱ ግን እንደ ፈነጨ ሊኖር ? ለማንኛውም የመጨረሻውን ውጤትና ድምዳሜ በያንዳንዷ ሰኮንድና ደቂቃ ከአምላኬ በትዕግስት እጠብቃለሁ ።
ዶ/ር ፡
ፓ/ር ዳዊት የበደለኝ በብዙ አቅጣጫ ነው ፤ለምሳሌ አስቀድመን በጋራ በተስማማነው መግባባት መሰረት በራሱ ቤተክርስቲያን (FBI ) ባለሙያዎች ተቀርጸው የተሰሩትን የሠርጌን ቪዲዮና ከ5000 በላይ የሆኑ ፎቶግራፎችን ኮፒም ሆነ ኦሪጂናል ቅጂዎችን እስከ ዛሬ ድረስ እንዳለገኝ ከልክሎ በማስቀረቱ እንኳን ለዘመድ አዝማድ ፤ ጎደኞቼና ጎረቤቶቼ ፤ የስራ ባልደረቦቼ ፤ ለአብሮ አደጎቼ ይቅርና እኔ ራሴ የጉዳዩ ባለቤት የሆንኩት የሠርጌን ማስታወሻ የማየትና በታሪክነቱ ለማስቀመጥ ዳዊት ከልክሎኛል ። የጋብቻ ወረቀቴንም (Marriage Certificate ) እስካሁን ድረስ በጉልበቱ አስቀርቶታል ።
እኔ ብቻ ሳልሆን መልካም ትዳር እንዲገጥመኝ ተመኝተውልኝ ለጋብቻችን መሳካት የጸለዩ ፤ የለፉ ወገኖች ፤ የረዱን እና በብዙ የደከሙልን ፤ እሩቅና የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲንደርስ ከልባቸው ያማጡ ጓደኞችና የስጋ ዘመዶቼ ሁሉ ጭምር በደረሰብኝ ሁኔታ አፍረዋል ፤ አዝነዋል ፤ተበሳጭተዋልም ።
በቆየው የሀገራችን አባባል “ከምርት እንክርዳድ አይጠፋም” እንዲሉ ጥቂት ግለሰቦች (የነዳዊት ግብረአበሮች ) ካላቸው ተመሳሳይ ሥነምግባር እና ባህሪ፤ የግል ጓደኝነት ፤ ውለታና ቀረቤታ የተነሳ ግድፈትና ነውራቸውን ሊያስተባብሉ ፤ እርኩሰትንና ቅጥፈትን አድበስብሰው ነጻ ናቸው ለማለት ደፋ ቀና ሲሉ ፤ የጥፋተኛውን ወንጀል ሸፋፍነው ነውረኛውን በጉያቸው ወሽቀው በመደበቅ ፤ሃቅን በሃሰት በመጨፍለቅ ፤ እኔን በማግለል ለነገራችን ቅርበት የሌላቸውን ንጹሃንን በማታለል ፤ እውነትን በማፈን ፍትህን ለማዛባት ትርምስ ፈጥረው ቅዱሳንን ግራ ለማጋባት ሞክረው ነበር ።
ነገር ግን እኔን የገረመኝና ያናደደኝ “ በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት “ ዓይነት አባባል ካልሆነ በቀር የገጠመኝ መከራና ፈተና ከመርግ ይልቅ እጅግ የሚከብደው ውርደትና ሃዘን ፤ ጥቃት ሁሉ እነሱን ገጥሞ ቢሆን ኖሮ ( ራሳቸው በኔ ቦታ ቢሆኑ ኖሮ ) ያለማጋነን ነፍሳቸውን በዛፍ ላይ የሚያንጠለጥሉ ፤ ምናልባትም አዕምሮያቸውን ስተው ፤ ጨርቃቸውን ጥለው የሚያብዱ ወይም ደግሞ በንብረትና በሰው ህይዎት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ አልጠራጠርም ። ፓ/ር ዳዊት ራሱ እኔን የገጠመኝ ዕጣ-ፋንታ ገጥሞት ቢሆን ኖሮ ምን ይውጠው ነበር ? ሁሉም ቢጤዎቹ ካንድ ጉድጓድ የተቀዱ ፤ አንድን ጽዋ በጋራ የጨለጡ አሳፋሪዎች እና selfish ስለሆኑ ታዘብኳቸው ።
መቼም ቢሆን እንደ ሰው ያልሆነ እግዚአብሔር ጻዲቅና መልካም አምላክ ነውና ምህረት ፤ ቸርነት ፤ ጥበቃው ፤ ፍቅሩ ፤ ርህራሄው ያማያልቅበት ፤ ወረት የሌለው በመሆኑ ራራልኝና አጽናንቶ የማይቻለውን እንዲችል ረዳኝና ከክፉው ሁሉ ጠብቆ እስካሁን በህይዎት አኖረኝ እንጂ የተጋራጠብኝ ፈተና ማንም ብርቱ ነኝ ባይ ልታገሰውና ልቋቋመው የማይቻል ከባድ አደጋ ነበር ። የራራልኝ እግዚአብሄር ይመስገን ፤ ነገንም በርሱ ፈቃድ እኖራለሁ ፤ አሜን ።
ለመሆኑ በማንአለብኝነት ይህንን ሁሉ ጥቃት የሚፈጽም ይህ ጉልቤ ጀብደኛ (ዳዊት ) ማን ነው ? “ከወፈሩ አይፈሩ” ነው ነገሩ ? ወይስ ምንን ተማምኖ ? ይህንን ሁሉ በደልና ግፍ ሰው አይቶ ባይፈርድልኝ እግዚአብሔርስ ይወደዋል ዎይ ? ይህ ግድየለሽ ሰላሜን አደፍርሶ ፤እና ህይዎቴን አበላሽቶ ፤ ኑሮዬን አናግቶ እሱ ግን ልፈነጭ ? አይደረግማ !!
የፈጸመውን ድርጊት ተናግሮ ፤ ጥፋቱ ተዘርዝሮ ስህተቱ ተብራርቶ ነውርና ድፍረቱ ተገልጦ ለአደባባይ መቅረብ አለበት ። ምናልባት በመንፈሳዊ አገልግሎት ሽፋንና ሰበብ ያካባተው ሃብት ፤ ያተረፈው ዝናና ክብር አለኝ ብሎ ስለምያስወራ ፤ እንዲሁም የጥፋቱ ተባባሪ ቢጤዎች ፤ ጓደኛና ምኑንም በውል ያልተረዱ ቅንና የዋሆች ያለእውቀት ደጋፊዎች ልኖሩ ስለምችሉ ከሰው ዘንድ እውነተኛ ፍርድ ላላገኝ እችላለሁ ፤ ቢሆንም ከቲፎዞ (ደጋፊ) ብዛት የተነሳ የፍትህ ዳኛና ሃቀኛ ምስክር ስለማይገኝ ፤ ትዳሬ ፈርሶ ፤ህይዎቴ ተበላሽቶ ፤ ራዕዬ ተጨናግፎ ፤ ተስፋዬ ጨልሞ ከአቅሜ በላይ የሆነ አበሳና ውርደት ተሸክሜ ለመኖር ለኔ እጅግ ከባድ ነው ።
ፓ/ር፡
ከዚህ ቀደም ውድ ጊዜህን ሰውተህ ከረዳቶችህ ጋር በመካከላችን ተገኝተህ ለበርካታ ሰዓታት እኛን ( ዳዊት ፤ ትግስትንና እኔን ) ስታወያየን አንተ ራስህ ሰምተህ ፤ አይተህ ፤ግንዛቤ እንዳገኘሀው (እንዳረጋገጥከው ) ፓ/ር ዳዊት እኔና ሚስቴን ባጋባበት ዕለት ወዲያውኑ ከመቅጽበት ከሚስቴ ጋር እንዲንለያይ ዋና ምክንያት ሆኗል፤ ለዚያውም አንዴ ብቻ ሳይሆን ሁለቴ ሦስቴም እንጂ ።
ይህ ድርጊት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአበሻ ታሪክ በኔ ብቻ ካልሆነ በቀር የት ሀገር ? መቼ ? በነማን ላይ ደርሶ ያውቃል ? እነዴትስ በጫጉላ ሽርሽር ወቅት ( honey moon time ) ሙሽሪት ሙሽራውን ትታ ፓስተሯን ለመዝናናት በሚል ሰበብና ድፍረት የቃል ኪዳን ሙሽራ ባሏን በሆቴል ውስጥ እንዲሁም በሌላ ጊዜ ደግም በባዶ መኖሪያ ቤት ውስጥ ጥላ ፤ጨርቋን ጥላ እና አዕምሮዋን ስታ ለ7 ቀንና ሌሊት ያህል የምትጠፋው ? በገዛ ቤታችን ውስጥስ ቢሆን ባልን ሳሎን ውስጥ ትቶ ከፓ/ር ጋር መኝታ ቤት ገብቶ በር በመቆለፍ ለሰዓታት ያህል አገልግሎት ላይ ነን ማለትና…ወዘተ ጸያፍና ድፍረት የተሞላባቸው አሳፋሪ ድርጊቶችን መፈጸም የጤና ነው ? ወይስ የእብደት ?
እንዲህ ዓይነቱ ነውርና ልቅ የሆነው ጥፋት ከልክ ያለፈ ፤ መረን የለቀቀ ፤ሚዛኑን የሳተ ፤ ከድንበርም የዘለለ ስለሆነ ልሸከመው የማልችለው በቤቴ ፤ በትዳሬ እየተፈጸመ ነውና የከፋ ነገር ከመምጣቱ በፊት ይታሰብበት በማለት በግልጽ ውይይትና ምክክር አድርገን እናስወግድ ፤ መፍትሄ በመፈለግ እርማት እንውሰድበት የሚል ገንቢ እና ቀና ሃሳብ እንደ አገልጋይ ክርስቲያንና አማኝ በአክብሮት ያቀረብኩላቸው አቤቱታ ና ጥያቄ “ ጌታ ይገስጽህ ! ይህ ሰው (ፓ/ር ዳዊት ) በእግዚአብሔር የተቀባ ፤ የተለቀለቀ መንፈሳዊ ሰው ነው ፤ ስለዚህ ጌታ በቀባው ላይ እጅህን አታንሳ ፤ “ ተብዬ ተኮነንኩ ። ራሱ ዳዊትም ቢሆን “ ያቀረብከው ጥያቄ ለኔ የሚመጥን አይደለም “ በማለት ናቀኝ እንጂ ጆሮውን እንኳ ለጥቂት ለደቂቃ ያህል ልሰጠኝ አልፈለገም ፡፡ በዚህም ተግባሩ የኔን መብት ለራሱ አደረገ ፤ እኔን ግን ለውርደት ለጭንቀት ፤ ለሃዘንና ለኪሳራ ዳረገ። አሁን በዚህች ደቂቃና ሰከንድ ይህንን ደብዳቤ በማዘጋጅበት ሳምንት (ቀናት ) በሀገር ቤት ኢትዪኦጵያ ውስጥ ከዚህቺው ሴት ጋር አብረው ናቸው ። ጨርሰው ልላቀቁ ስላልቻሉ በረቀቀ ሚስጢር ያለሀፍረት አሁንም አብረው እንደተጣበቁ ናቸው ።
ፓ/ር ፡
ምናልባት “ድፍረት ፤ ንቀት ፤ ትዕቢት ወዘተ…የተባሉትን ዓረፍተነገሮች (ቃላት) ለምን ተጠቀምክ ? ለምንስ ደጋገምክ ? ትለኝ ይሆን ?በጣም የሚያናድደው ፤የሚያስገርመውና አሳፋሪው ነገር ይህ ግለሰብ ራሱን ነቢይ እያስባለ መገለጥ ቢጤ እያቀነባበረ የእግዚአብሔርን ቃል እየጠቃቀሰ “ የዓዞ እንቧ “ እንደተባለው የሀገራችን አባባል “ኢየሱስ ያድናል “ ወዘተ….በሚል ቋንቋ የዋሁን ህዝበ-እግዚአብሔር ፊት በእግዚአብሔር ፑልፒት ላይ እየተንጎራደደ መፈክር እያሰማ የትዳርን ክቡርነት ፤ የባልና ሚስትን ህጋዊ ግንኙነት (አብሮነት) ከፈጣሪ የሆነና የተቀደሰ ቃል ኪዳን መሆኑ እንደት ተሰወረበት ? የራሱን ሚስት እቤቱ አስቀምጦ በአፍላ ፍቅራችንና ጅምር ትዳራችን ወስጥ እንደ እርጎ ዝንብ ጥልቅ ብሎ ለምን ገባብን ?
ለነገሩማ ቀድሞውንም ቢሆን ሴራቸው ስላልገባኝ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው በሚል አምኜ ቀረብኳቸው እንጂ እነሱ ግን ያኔም ቢሆን ማስመሰል በተሞላበት የህሰት ትንቢት አደንቁረውኝ ፤በመገለጥ አዋክበውና አጣድፈውኝ ለስውር ዓላማቸውና የግል ጥቅማቸው ማሟያ አቅደው ለይስሙላ ከአጠገባቸው ሊያስቀምጡኝ ፈለጉ እንጂ ያኔ ያላወቅኩት ቆይቼም ቢሆን በኋላ እንዳረጋገጥኩት ለ5 ዓመታት ያህል ዘልቆ የቆየ ግነኝነትና አሳፋሪ ቃል-ኪዳን ነበራቸው ።
በሀገራችን አባባል “ የአይጥ ምስክር ዲንቢጥ ናት “ እንደተባለው ካልሆነ በቀር እነዚያ ቢጤዎቹስ ቢህኑ “ እሱ ዳዊት የፈጸመብህ ድርጊት አግባብ ባይሆንም ጸጥ ፤ ለጥ ብለህ ተቀበልና ዝም በል ። አለበለዚያ ትቀሰፋለህ ፤ ወደ ሲኦል ትገባለህ፤ ለሳይጣን አሳልፎ ይሰጥሃል ፤ ትረገማለህ “ ወዘተ.. እያሉ አስፈራርተው ሲያሸማቅቁ ፤ በሌላ በኩል ደግሞ “ የሚናከብረውና በጌታ የተቀባ ፤የተለቀለቀ ፤በመገለጥና ጥበብ ብሎም የፈውስ ጸጋ ስጦታ አገልግሎቱ እጅግ የጠለቀ ፤ የመጠቀ ነውና የተደረገብህን ድርጊት ሁሉ አሜን ብለህ አርፈህ ኑር” በሚል ማባበል እኔን አታሎ ለማዘናጋት ለሃጥያት ሲተባበሩ ፤በሃሰት ሲመሰክሩ ፤ አንዳች ፈጣሪን ባይፈሩ ፤ለማንም ባይራሩ ፤ ለሃቅ ባይቆረቆሩ ፤ በእግዚአብሔርም ሳይጠሩ ለክብራቸው ፤ ለዝናቸው ፤ ለጥቅማቸውና ለእንጀራቸው ያንን ያህል በድርቅና ከተከራከሩ ትዳሬ ደግሞ ለኔ ከእንጀራና ሆድ የሚበልጥ ፤ ከዝና ፤ ከክብርና ጊዜያዊ ጥቅም ያለፈ ህይዎትና ኑሮዬ መሆኑን ለማወቅ እንዴት ተቸገሩ ?
ስለዚ ይህ መቼም “ በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት “ እንዲሉ ንቀት ፤ ትዕቢት፤ ድፍረትና “ ነጌ በኔ” አለማለት ካልሆነ በቀር ሌላ አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም እንዳውም በኔ ቦታ ሆኖ ካዩት ከድፍረት ያለፈ ጭካኔ ነው እላለሁ ። እኔ ደግሞ ተበድዬ ፤ ተጎድቼ ፤ ተጠቅቼ ፤ ተደፍሬና ተንቄ ሽንፈትን አሜን ብዬ በውርደትና በሃዘን የተሞላ ህይዎት ለመኖር ስለማልፈልግ አንድ ስፍራ ላይ ባንድ ወቅት
ባንዴ መቋጨትና መቆረጥ አለበት ። ያንን ለማምጣት ደግሞ እስከ ህይዎቴ ፍጻሜ ድረስ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ፤ የእውነት አምላክ ፤የቅኖች ወዳጅ ፤ የምስኪኖች አለኝታ የሆነው ፈጣሪዬ ደግሞ ለአረመኔዎችና ለነውረኞች አሳልፎ ስለማይሰጠኝ ፤ ጥቃቴንም ስለማይወድ በሱ እየታመንኩ ላደርገው የወሰንኩትን በአርሱ ታምኜ እፈጽማለሁ ።
አዎን ከዚህ በላይ ያልኩት ሁሉ በኔ ላይ የተፈጸመ እውነት የሆነ ዓይን ያወጣ ጥርሱን ያገጠጠ ብልግናና በቃላት የማይገለጽ ከባድ በደልና ግፍ ነበር ። ዛሬ ዛሬ በየቦታው አፈ-ጮማ አተራማሽ መተተኛና ፈጣጣ ጋጠ-ወጥ ጮሌ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት እያጥለቀለቀ የስንቱ ምስኪኖች ትዳር ደቀቀ ? አረ የፍትህ ያለህ ! የጽድቅ ያለህ ! የቅድስና ያለህ ! አለቅን ፤ ደቀቅን !! እባካችሁ ድረሱልን !!!
ለመሆኑ ትዳርን ማፍረስ ቤተክርስቲያንን ማፍረስ አይደለምን ? ለዚያውም የቤተእምነት መሪና አገልጋይ ሆኖ የንጹሃንን ትዳር እያረከሱ ፤ ቤተሰብን እያፈረሱ ቤተክርስቲያንን እያስወቀሱ “የተቀባ ፤የበቃ “ ወዘተ … አገልጋይ መሆን ይቻላል ? ትንቢት እየተናገሩ መገለጥ እየቀበጣጠሩ የትዳርን ክቡርነት እንዴት ዘነጉ ? ሚስት ለባል ፤ ባልም ለሚስት ብቻ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለነሱ ብቻ ሲባል ሌላ ነቢይ መቅጠር ( ልዩ መላዕክት ከሰማይ ማስመጣት ) አለብን ዎይ ? “እግዚአብሔር እንዲህና እንድያ ብሎሃል” እያለ ሌት ተቀን እየሰበከ እራሱ ግን ለምን አልኖረበትም ? ራሱ ልፈጽመው ያልቻለውን በጉልበት ልያሽክመን ለምን ይጥራል ?
ደግሞስ የኔ አንዲቷ ነጠላ ህይዎት (ነፍስ) ቤተክርስቲያን አይደለችምን ? የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያ ፤ የክብሩም መገለጫ ቤተክርስቲያን አይደለሁም ዎይ ? ይህ ዓይኑን በጨው የታጠበ ደፋር ግለሰብ ህይዎቴንና ዕድሌን አበላሽቶ ደስታዬን ወደ ሃዘን ለውጦ ቤተክርስቲያንን ሊመራ ?ህዝብን ሊያገለግል ? “ It is not fair “ (ፍትሃዊና አግባብ አይደለም ) ፤ እሷስ ወ/ሮ ትግስት ብትሆን ልማደኛ ባትሆን ኖሮ ከበፊተኛው ስህተቷ ለምን አልታረመችም ? ከኔ በፊት ጀምሮ ነጋ ጠባ የትዳር ቀበኛና ጸር “Allergy “ (የፓስተሮች ቀማሽ ) ይመስል በበፊቱ ነውርና ስህተቷ ትምህርትም ሆነ ምክር ችግርና ግሳጼው ሁሉ መታረም ስገባት እንዴት እንደገና ለአግልግሎት በቃች ? ከኔ በፊት የነበራትን ትዳሯንም እንዲሁ በተመሳሳይ ተግባር ከሌላኛው ፓስተሯ ጋር በዝሙት ተጠርጥራ ትዳሯ እንደፈረሰ ከኔ በቀር ሁሉም የአከባቢያችን መንፈሳዊ መሪዎች የሚታውቁት የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው ። የራሷን ጽንስ (የኑሮ ጅምር ) አጨናግፋ (አኮላሽታ ) ፤ በተለያየ ጊዜና ወቅት ካገባቻቻው ባሎቿ መካከል አንዱንም እንኳ በአግባቡ ይዛ የራሷ ለማድረግ አቅቷት ሁሉንም በየተራ በየቦታው በአደባባይ እያፈረጠች ፤ እንደገና አዘናግታ ከሌሎች ተረኞች ጋር የምትከንፍ ያልሰከነች ሴት አሁን ከሰሞኑ ደግሞ ስፍራና ቤተክርስቲያን ቀይራና ለዋውጣ አዳዲሶቹን መሪዎች ጥብቅ ብላ የቤተእምነቱን ቁልፍ እንዴት ተረከበቻቸው ?
ለማስመሰልና ለጉራ፤ ብሎም ለዝና ብሎም ለድብቅ ዓላማ ካልሆነ በስተቀር የራሱን ቤት ያቃተው ሰው የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠበቅና ለማገልገል እንዴት ተገባው ? ለማጭበርበር ካልሆነ በቀር የራሱን ጽንስና ራዕይ ገሎ የሰው ቤት ሄዶ የሌላውን ልጅ ተንከባክቦ ለማስተማር ቀርቶ ጉንጭ እንኳን ለመሳም ሃላፊነት የሚጣልበት ስበእና አለው ለማለት አያስችልም ።እንዲህ ዓይነቱ ሰው ካለ ራዕይ ለመጠበቅ ከቶ አይቻለውም ፤ ምክንያቱም እውነተኛ አገልግሎትና ታማኝነት ከራስ ቤትና ትዳር መጀመር ስለምገባው ። እውነተኛዋ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ካለች እንዲህ ዓይነቱን ዓይን ያዋጣ ድፍረትና ተራ ቁማር መዋጋት ተጋቢ ይመስለኛል ።
ምክንያቱም በኔ በኩል የችግሩ ሰለባ ከመሆኔም በላይ እንደ ባለ አዕምሮ ሳሰላስል እነዚህ እና ቢጤዎቻቸው ባለቤቱ የከደነውን ያለፈቃድ የሚከፍቱ ፤ አንዱ የገነባውን የሚንዱ ፤በፈጣሪ ስም ፤ በሃይማኖት ሰበብ ተገቢ ያልሆነን ተግባርን የሚሰሩ ፤ለማንም የማይራሩ ከስህተታቸው የማይማሩ ፤ የራሳቸውን ትተው የሰውን ሚስት ( ባል ) ለመቅመስ ሌት ተቀን የሚዞሩ ፤ ለከበረው ትዳርና ጤነኛ ፍቅር እንቅፋት ብቻ ሳይሆኑ ለሰሩት ጥፋትና ስህተት በንቀት ጆሮ ዳባ ብለው (ችላ ባይ ከመሆናቸው የተነሳ )ጉዳቴ ዕለት በዕለት ይበልጥ እየተሰማኝ ስለሆነ የሚወስነው ውሳኔ እየክፋ እንደመጣ ተገንዝቤያለሁ ።
በመሆኑም ስማቸው ከዚህ በላይ በተደጋጋሚ የጠቀስኳችው ግለሰቦች (ፓ/ር ዳዊትና ግብረ አበሩ ወ/ሮ ትግስት ) እንዲሁም ቢጤዎቻቸው በሰው ላይ በደልና ነውር እያደረሱ ፤የንጹሃንን ትዳር እያፈረሱ በእግዚአብሔር ቤትና በቅዱሳን መካከል መሽገው ፤ሃጥያታቸውን ሸሽገው ሚስኪኖችን አንገት እያስደፉ ፤ የሰላማዊ ኑሮን ጣዕምና ትርጉም እያጠፉ መላውን ቅድዱሳን በሃሜትና በአሉባልታ እያተራመሱ ቤተ-እምነቶችን መነጋገሪያ ፤ መሳለቂያ እያደረጉ መቀጠል ተገቢ አይደለምና ጉዳዩን ለህዝብ ሚዲያ እና ለመላው አብያተ-ክርስቲያናት ለማቅረብ ወደድኩ ።
አዎን ፤ በቃ ፤ የእግዚአብሔር ቤት ይህንን ከመሳሰለ የነውር ተግባር ከነዚህ ዓይነቶቹ አስመሳይ ነውረኞች ልጠራ ይገባል ፤እኔም ከእንግዲህ ጥፋተኛው ቅጣቱን እስኪቀበል ፤ ነውረኛው በነውሩ እስኪጸጸት ፤ እግዚአብሔርን ፤ ህዝቡንና ተበዳዩን ይቅርታ እስኪጠይቅ ፤ ቁስሌ እስኪጠገን ፤ህመሜ እስኪፈወስ ፤ ምናልባት ተመሳስለው እና ተደብቀው በየቦታው የተሸሸጉ ነውረኞች ካሉ ያጨለሙት
ተስፋዬ እስኪታደስ ፤ ሃላፊነት የጎደላቸው መንፈሳዊ ጀብደኞች ያኮላሹት ራዕዬ እስኪመለስ ፤ የጌታ ፈቃዱ ሆኖ በህይዎት እስካለሁ ይህንን ስድ አልለቀውም ።
ሌላው ቢቀር እንኳ የዚህን ጨዋ መሳዪ ተግባር ሰው ሁሉ ይስማውና ባላጌዎች ይፈሩበት ፤ ጥፋተኞች ይታረሙበት ፤ ትውልድ ይማርበት ፤ያፈለገው ንሰሃ ይግባበት ፤ዱሪዬዎች አደብ ይግዙበት ፤ ዝንጉዎች ይጠንቀቁበት ፤የተጎዳው አእምሮና መንፈሴ ይታደስበት ፤ እግዚአብሔር ይክበርበት ።
እንዲሁም ተመሳሳይ በደልና ግፍ በሰውር በቅዱሳን የግል ኑሮና ቤተሰብ ህይዎት ላይ እየተፈራረቀባቸው በአጓጉል ኋላ ቀርና በሃይማኖት ስም ማስፈራሪያነት ከደረሰባቸው በደልና ጥቃት ጋር ተሸማቀው “ታሪኬ ከበደለኝ ሰው ጋር አብሮ ከሚጋለጥ ጥቃቱን ተሸክሜ ፤የጎዱኝን ነውረኞች አበሳ ደብቄ ልኑር “ የሚሉት ሳይቀሩ ሌባውን ሌባ ፤ነውረኛውን ነውረኛ ፤ዋሾ አስመሳዩን ቀጣፊ ፤ወዘተ…እያሉ በድፍረት ተናግረው ለማጋለጥ ጉልበት ያግኙበት።
በሌላ በኩል ሰውዬው ( ፓ/ር ዳዊት ) ብልጣ-ብልጥ ፤ አስመሳይ ጮሌ ፤ ምላሱ ቅቤ ፤ልቡ ጩቤ ስለሆነ ፤የገነነ ዝና ፤ እውቅና ፤ ገንዘብና ብዙ ቢጤዎች ስላሉት ብቻ እኔው ተጠቅቼ ፤ፍትህ አጥቼ ፤ በቀሪ ዘመኔ ሁሉ ተቀጥቼ አልኖርምና ሃቀኛ ዳኛ ፤አመዛዛኝ ህሊና ፤ ከአድልዎ የጸዱ ፍትህን የሚያስከብሩ ፤ ለእግዚብሔርና ቤቱ የሚቆረቆሩ ፤ ህዝበ-እግዛብሔርን የሚያፈቅሩ፤ በጽድቅ የሚኖሩ ፤ለሚስኪኖች የሚከራከሩ ፤ነውረኛ ጥፋት ፈጻሚዎችን በድፍረት በመገሰጽ የሚመክሩ የሚያስተምሩ በፍቅር የሚገሩ ፤ ነውርንና እርኩሰትን የሚጸየፉ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ዳኞች አሁንም በአምላኬ ቤት ልኖሩ እንደሚችሉ እርግጠኛ በመሆን ይህንን ጉዳቴን ፤ አበሳዬንና ገበናዬን ዘርዝሬ አቅርቤያለሁ ።
ፓ/ር፡
ይህንንም ሳደርግ አንተ ብቻ ሳትሆን ሌሎች የእግዚአብሔር ሰዎች ፤ የጌታ አገልጋዮች ፤መንፈሳዊ መሪዎችና መላው ቅድሳን ሁሉ “ እኛ በቦታው አልነበርንም ፤ አልሰማንም ፤ አላየንምና አንዳች ነገር ከቶ አያገባንም” ወዘተ… እንዳይሉ ይህንን ደብዳቤና የከዚህ ቀደሞቹን ዝርዝር ጉዳዮች የያዙ ኮፒዎችን ሁሉም በያሉበት አድራሻ በተከታታይ የሚልክላቸው (የማሰራጭ ) መህኑን አልሸሽግም ።
ለዚህም ዋና ምክንያቴ ኪሳራዬ ባይካስም ፤ጉዳቴ ስብራቴ ባይጠገንም ፤ ቁጭት እልሄ በርዶ ቁስሌ ባይፈወስም ትዳሬን እንደሆነ እስከመጨረሻው ያጣሁ፤ የፈራረሰ እና ያከተመለት ፤ የሞተ ነገር ቢሆንም እኔ ተጎድቼ ፤ተዋርጄ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሌላው ትውልድ ዘላቂ መፍትሄና ያማያዳግም ትምህርት ያገኝበታል ብዬ በመገመት ነው ፤ አዎን ከተቻለ የኔ ትዳር ተኮላሽቶ ታሪኬም ተበላሽቶ ከእንግዲህ ግን የምስኪን ወገኖቼን ትዳርና ኑሮ ከሚያኮላሹና ከሚያበላሹ አገልጋይ ተብዬ መንፈሳዊ ዱሪየዎች ለመታደግ ነው።
ፓ/ር ፡ እጅግ በጣም የማከብርህ ትልቅ የእግዚአብሔር አገልጋይና መሪ ነህ ። ፓስተሬ እንደ መሆንህ መጠን በአከባቢዬ አንድ የእግዚአብሔር ሰው የሚለው እና የጉዳዬን ዝርዝር ታሪክ በቅርበት የሚያውቅ ካንተ የበለጠ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ ማንም የለም ።
ከመነሻው እስከሁን ያለውን ታሪኬን ከሞላ-ጎደል ታውቀዋለህ ፤ በተለይም ጉዳቴን ፤ ስብራቴን ፤ሃዜኔና እንባዬን ፤ እንዲሁም ጥልቅ ቁጭቴን መገመት ከቶ አያቅትህም ብዬ አስባለሁ ። ስለሆነም ከዚህ ቀደም ከአንዴም ሁለቴ በኛ ጉዳይ እንባህን ስታፈስ ደጋግሜ አይቸሃለሁ ።በሌሎች ቅዱሳን ዘንድም ቢሆን የነዚህ ነውረኞች ነውርና ቀልድ ከማንም የተሰወረ አይደለም ፤ ያለንበት ወቅት ከምንጊዜውም በለይ በእርኩሰትና በክፋት የተሞላ ሆኗል ፤ ክህደት በመብዛቱ ቅጥፈት ነግሶ ዘመኑ እጅግ ከባድ ሆኖብናል ።
ስለዚህ እውነት ታፍኖ ሃቅ በመታነቁ ምክንያት ፍትህን አስከብሮ ለጽድቅ የሚፈርድ ዳኛ ይቅርና የቅርብ የሆነ ታማኝ ጓደኛ የታጣበት አስደንጋጭ ወቅት ላይ ደርሰናል። እኔ ያለእግዚአብሔር በቀር ሃብት ፤ ዘመድ፤ ወገንና ደጋፊ የለኝም ።
በዚህ ቁርጥና ፈታኝ ወሳኝ ወቅት አንተ ግን እንደ አባት ፤ የእምነት ሰው ፤ የቤተከርስቲያን መሪና የህዝብ አገልጋይ የመፍትሄ ምክርህ ፤ እገዛህ ፤ አስተያየትና ውሳኔህ ምንድን ነው ?
በተጨማሪም የተፈጸመብኝ በደል ፤ ግፍና ጥቃት ዘርዝሬ ከላይ በጠቀስኩት መሰረት ለሚዲያዎችም ጭምር ለማሰራጨት የወሰንኩ መሆኔን በክብሮት እየገለጽኩ ከፈጣሪዬና ካአንዲት ነፍሴ በቀር አንዳች ለሌለኝ ለኔ ለብቸኛውና ምስኪኑ ሰው አሁንም እንዲትጸልይልኝ ጭምር በጌታ አደራ እላለሁ ።
በጌታ እወደሃለህ
እጅግም አከብርሃለሁ
እግዚአብሔርና ቃሉ ብቻ እውነትና ትክክል ናቸው !
ከእንግዲህ በዘመኔ ሁሉ ማንንም አላምንም !!
እውነት ብትቀጥን እንጂ ጨርሳ ተበጥሳ አታውቅም !!!
ግርማ ዱሜሶ
Email; gelgela09@yahoo.com
ግልባጭ ፡
ለኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉየእግዚአብሔር ቅዱሳን ሁሉ በያሉበትአበሻ ነክ ለሆኑ የኢትዮጵያዊያን ሚዲያዎችና ድህረ-ገጾች በሙሉ ።

ኢዴፓ የእሁዱን ምርጫ ውጤት ለመቀበል እንደሚቸገር ገለጸ


የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዘዳንት ዶክተር ጫኔ ከበደ በትናንትናው ምርጫ ፓርቲያቸው ከሞላ ጎደል በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ባሉ አባላቱና ታዛቢዎቹ ላይ ጫና ሲደረግባቸው እንደነበር ገለጹ፡፡
አጠቃላይ የምርጫው ሂደት አሳፋሪ ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ በርካታ ምርጫ ታዛቢዎቻችን የታዛቢነት ካርዳቸው ተነጥቆ ከምርጫ ጣቢያዎች ተባረዋል ሲሉ ከሰዋል፡፡ “በዚህ ሁኔታ የሚካሄድ የድምጽ ቆጠራ በትክክል ይካሄዳል ብለን አናምንም፡፡ የዚህን ምርጫ ውጤት ለመቀበልም አስቸጋሪ ሆኖ ነው ያገኘነው” ሲሉ ነው ዶክተር ጫኔ ለድሬ ቲዩብ አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡
ከዚሁ የፖለቲካ ዜና ሳንወጣ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፓርቲያቸው ለወደፊቱ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጥምረት ለመስራት አልያም በርካታ ፓርቲዎችን ባስጠለለው መድረክ ስር ራሱን ለማዋቀር እያጤነበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አቶ ዮናታን ፓርቲው ስለዚህ ሁኔታ ለመነጋገር ራሱን ዝግጁ እንዳደረገ የገለጹ ሲሆን በዚህ በኩል ራሱን ማጠናከር እንደሚፈልግም ጠቁመዋል፡፡                                                                                                                                                        ሳምሶን አበራ

Sunday, May 24, 2015

ኢህአዴግ በተደራጀ መልኩ በክልሎች መራጮችን በማስገደድ ንብን እያሶመረጠ ይገኛል



ሰማያዊ ፓርቲ የመደባቸው 4 የምርጫ ታዛቢዎች በገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች መደብደባቸው ተዘገበ::
ምስራቅ ስቴ የተበደቡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች
1. ታደለ ግዛው (ዳጉት ቀበሌ)
2. እሱ ያውቃል በላይ (ለዋዬ ቀበሌ)
3. ገብሬ ተፈራ (ደንጎልት ቀበሌ)
4. መልካሙ ነጋ (አበርጉት ቀበሌ)
በተጨማሪም ይስማው ወንድሙ የተባለ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ በጥይት መሳቱን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
*****
‹‹ጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ ከተማ ብርብር ምርጫ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎችን አዋክበው እንዳይታዘቡ አድርገዋል፡፡ ካቢኔ ኮሮጆው ክፍል ድረስ ገብተው ኢህአዴግ ላይ ምልክት እንዲያደርግ ጫና አድርገዋል፡፡ በተለይ ሴቶችንና ሽማግሌዎችን በግዳጅ ነው ያስመረጧቸው፡፡ በአጠቃላይ በጋሞጎፋ የህዝብ ታዛቢዎች የተመረጡት በኢህአዴግ ነው፡፡ ይህን ቀድመንም ተናግረናል፡፡›› አቶ ወንድሙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ
*****
‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ
*****
‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመራሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ/ከደጀን
*****
ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ አንድ እና ምርጫ ጣቢያ ዘጠኝ ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ምክንያት ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡
****
‹‹የኢህአዴግ አባላት ናቸው የምርጫ ወረቀቱን እየተቀበሉ ምልክት የሚያደርጉት፡፡ ታዛቢ የሚባሉት ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው፡፡›› ከዱር ቤቴ
*****
‹‹ባለስልጣናት ምርጫ ጣቢያው በር ላይ ቁጭ ብለው እጅ ይዘው እያስፈረሙ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ውጭ እንመርጣለን ያሉ ወጣቶች ከአካበቢው ተባረዋል፡፡ ችግሩን ለሌሎች ይገልጻል የተባሉ ወጣቶች ስልካቸውን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ከአካባቢው ርቀናል፡፡›› ስልጤ ዞን ላንፎሮ ወረዳ አርጢማ ቡላ ቀበሌ
(ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው)

በጉደር አምቦ ጸጥታው ደፍርሷል::ምርጫው ቆሟል::



በአቦ በባድዮ ጉደር አምቦ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ከቁጥጥር ውጪ ያደረጉ ችግሮች የተፈጠሩ ሲሆን በየምርጫ ጣቢያዎቹ የኢሓዴቅ የቅስቀሳ ፖስተሮች ተለጥፈዋል::ይህን ተከትሎ በጉደር ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ተፈጥሯል::በታዛቢዎች እና በምርጫ ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ አለመግባባቶች ተፈጥረው እስከ ድብድብ ተደርስል::‹‹ከንብ ውጭ ምልክት የለም፡፡ ከዛም ካርድ ይቀዳሉ፡፡ ሶስት ቀበሌዎች ተዘዋውሬ አይቻለሁ፡፡ መምህራን ስለሚጠይቁ ችግር እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህ ምርጫ ይበላል?›› ኦሮሚያ ክልል አደሬ ጮሌ ቀበሌ
‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ
ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 1 እና ምርጫ ጣቢያ 9 ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡ ከደጀን ‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ

ሰበር ዜና የተሰረቀውን ምርጫ በማውገዝ በኦሮሚያ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ መጀመራቸው ተሰማ።

Saturday, May 23, 2015

ከእንግዲህ ቀልድ የሆኑ ምርጫዎችን አብረን ማፅደቅ የለብንም ብለን ስለወሰንን ነዉ። Ana Gomes ( አና ጎሜስ ) European Parliament


የእሁዱ ምርጫና ታዛቢዎች

ኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2007ዓ,ም አምስተኛዉን ብሔራዊ ምርጫ ታካሂዳለች። ከአፍሪቃ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ደረጃ ላይ በምትገኘዉ ሀገር በዘንድሮዉ ምርጫ ከ50 በላይ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ።
በምርጫዉ ድምፁን ለመስጠትም ከ36,8 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ መመዝገቡን የሀገሪቱን የምርጫ አስፈፃሚ አካል የጠቀሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ምርጫዉን ለመታዘብ ከሀገር ዉስጥ ምርጫ ቦርድ ከሚያሰማራቸዉ ሌላ ከዉጭ የአፍሪቃ ኅብረት ታዛቢዎች ብቻ እንደሚገኙ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የተካሄዱ ምርጫዎችን የታዘቡ የአዉሮጳ ኅብረትም ሆነ የአሜሪካዉ ካርተር ማዕከል ታዛቢዎች አይገኙም። የ1997ቱን ምርጫ የታዘቡት የአዉሮጳ ኅብረት ልዑካን መሪ ታዛቢ መላክ አስፈላጊ አይደለም ይላሉ። 
የዘንድሮዉ ምርጫ ከ1983 እስከ 2004,ም ድረስ በመንግሥት ስልጣን ላይ ከነበሩት ከቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ሕይወት በኋላ የሚካሄድ የመጀመሪያዉ ምርጫ ነዉ። ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ድምፁን ለመስጠት የተመዘገበዉ ሕዝብ ብዛት በሀገሪቱ የተሻለ ዴሞክራሲ ሰፍኖ እንደሁ የሚፈትንበት አጋጣሚ እንደሆነ መጠቆሙን የዜና ዘገባዎች ያመለክታሉ
የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ገዢዉ ፓርቲ የተቃዋሚዎችን ደጋፊዎች እና ጋዜጠኞችን ይጫናል፤ እንዲሁም ፀረ ሽብር ሕጉን በመጠቀም የዜጎችን ድምፅ ያፍናል ተቺዎቹንም ያስራል ሲሉ ይከሳሉ። ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ስልጣን ጨብጦ የሚገኘዉ ገዢዉ ፓርቲ በበኩሉ በምርጫዉ ስኬት ለማግኘት ያከናወናቸዉ የልማት ተግባራት በቂ እንደሆኑ እንደሚገልፅ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል። 
የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር በጎርጎሪዮሳዊዉ 2012,ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸዉ በመንበራቸዉ የተተኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሀገሪቱን የፖለቲካ ስርዓት ለቀቅ በማድረግ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሻለ ስፍራ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸዉን መግለፃቸዉም እንዲሁ ተሰምቷል። ባለፈዉ ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያ በሰጡት መግለጫ «ትክክለኛ የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በዚህች ሀገር ካልኖረ ሀገሪቱ እንደሶማሊያ ልትሆን ትችላለች» ማለታቸዉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ጠቅሷል። ተቃዋሚዎች ግን መንግሥት በምርጫዉ ድሉን ለማረጋገጥ የፈላጭ ቆራጭነት ስልት ይጠቀማል ሲሉ ይከሳሉ። ፓርቲና መንግሥት አለመለየታቸዉ፤ መገናኛ ብዙሃን፤ የፀጥታ ኃይሎችና ገንዘብ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆናቸዉንም እንደዋና ችግር ይጠቅሳሉ። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ እጩዎቻቸዉም መጠነሰፊ ወከባ እየደረሰባቸዉ ነዉ ሲሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች አቤቱታቸዉን ያሰማሉ። 

 
የምርጫዉ አስፈፃሚ አካል ግን እነዚህን አቤቱታዎች ሁሉ መሠረተ ቢስ ሲል ያጣጥላል። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና የዘንድሮዉ ካለፉት ዓመታት እጅግ የተሻለ ነዉ፤ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተመቻቸዉ ምህዳርም ልዩ ነዉ ማለታቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። 
ለእሁዱ ምርጫ የምርጫ ኮሚሽኑ 40 ሺህ የሚሆኑ የሀገር ዉስጥ ታዛቢዎችን በ45 ሺህ 795 የምርጫ ጣቢያዎች ያሰማራል። ዘንድሮ ብቸኛዉ የዉጭ የምርጫ ታዛቢ አካል የአፍሪቃ ኅብረት ነዉ። ኅብረቱ 59 ታዛቢዎችን ያሰማራል። የ1997ቱንና የ2002ቱን ምርጫ የታዘቡት የአዉሮጳ ኅብረትና የአሜሪካዉ የካርተር ማዕከል ግን ዘንድሮ አይገኙም። የዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ክፍል ኃላፊ ሉድገር ሻዶምስኪ ያነጋገራቸዉ በ1997,ም የአዉሮጳ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑካን መሪ የነበሩት አና ጎሜዥ ምርጫዉን ለመታዘብ መሄድ እንደማያስፈልግ መወሰኑን ይናገራሉ።
«ላለመሄድ በትክክል የወሰንነዉ የሀሰት ምርጫ እንደሚካድ እያወቅን ያንን ለማረጋገጥ ታዛቢ መላክ እንደሌለብን ስላመንን ነዉ። ቀልድ ነዉ የሚሆነዉ፤ ምክንያቱም ፍፃሜዉ ልክ በ2002 እና በ1997 እንደነበረዉ ነዉ የሚሆነዉ። ሕዝቡ በብዛት ድምፁን ሊሰጥ ወጣ በቆጠራዉ ላይ አጭበረበሩ።» ፓርቱጋላዊቱ የአዉሮጳ ኅብረት አባል አና ጎሜዥ አያይዘዉም ኅብረቱ የምርጫ ታዛቢ ወደኢትዮጵያ ያልላከበትን ምክንያት እንዲህ ያስረዳሉ። 
«በዚህ የተነሳ ምክር ቤቱ ለሚስ ሙጌሪኒ ኢትዮጵያ ዉስጥ ምርጫ የሚታዘብ ተልዕኮ ሊኖር እንደማይገባ በማስታወቅ ደብዳቤ ጽፏል። የቲየስ በርመን እና የእኔ የ1997 የምርጫ ትዝብት ዘገባዎች በመንግሥት ተቀባይነት አላገኙም። ተግባራዊ ማድረግ ይቅርና እዚያዉ ተመልሰን እንኳን ዘገባችንን እንድናቀርብም አልፈቀደም። ምክንያቱን የሰሉ አስተያየቶችን በመያዛቸዉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ የአዉሮጳ ኅብረት ለምርጫ መታዘብ ያልመጣዉ በገንዘብ እጥረት ነዉ ማለቱን አዉቃለሁ። ሆኖም ይህ ፍፁም እዉነት አይደለም። እኔ ራሴ ከአዉሮጳ ኅብረት የናይጀሪያን ምርጫ ለመታዘብ ሄጄ ገና መመለሴ ነዉ፤ በተለያዩ የአፍሪቃ ሆነ ከአፍሪቃ ዉጭ ሃገራትም የምርጫ ታዛቢ ልዑካን አሉን። ወደኢትዮጵያ የማንሄደዉ በበጀት ጉዳይ ሳይሆን በፖለቲካዊ ምክንያት ነዉ። ይህም ማለት ከእንግዲህ ቀልድ የሆኑ ምርጫዎችን አብረን ማፅደቅ የለብንም ብለን ስለወሰንን ነዉ።» 


በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ስርጭት
- ኤርትራ በረሃ የሚገኙትን ታጣቂ ሃይሎች የሚቀላቀሉ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ሰራዊትአባላት ቁጥር እየጨመረ ነው። በዛሬው ዕለት አንድ የአጋዚ ክፍለ ጦር አባል ከነሙሉ ትጥቁ አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅሏል። በሌላ በኩል በቡናና በቁም ከብት ንግድ የተሰማሩ አንድ የጎንደር ባለሃብት ኤርትራ በረሃ ወርደዋል።
_የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ጽ/ቤት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ሊመረምረው ነው። ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ እንደዘገበው ጽ/ቤቱ ጥያቄውን ለህወሀት መንግስትና ለእንግሊዝ አቅርቧል።
_ምርጫው አንድ ቀን ብቻ ቀረው። የህወሀት መንግስት የተቃዋሚዎችን ታዛቢዎች እያደነ ነው። ብዙዎች ታስረዋል። ከህግ ውጭ በመጨረሻው ሰዓት ለካድሬዎቹ የታዛቢነት ደብዳቤ ዛሬ መበተን ጀምሯል። ተቃዋሚዎች የህዝቡ ልብ ሸፍቷል እያሉ ናቸው። ስርዓቱን ለማስወገድ ዝግጁ የሆነን ህዝብ እንድናገኘው ምርጫው አጋጣሚ ፈጥሮልናል ይላሉ።
_በኦሞ ወንዝ ዙሪያ ያለውን የጎሳ ግጭት እንዲሁም የመሬት ቅርምት፡ በጋምቤላና በኦሮሚያ ክልሎች በተመሳሳይ ያለውን የመሬት ቅርምት ላይ በማተኮር ጥናት የሚያደርጉና ጉዳዩን ለዓለም ያሳወቁ 7 ኢትዮጵያውያን ሽብርተኛ ተብለው ማዕከላዊ የሰቆቃ ማጎሪያ እስር ቤት መታሰራቸው ተገለጸ።
_በየመን በተፈጸመ የአውሮፕላን ጥቃት 5 ኢትዮጵያውያን ተገደሉ።
http://ethsat.com/esat-radio-fri-may-22-2015/

!! ወያኔ በጦር እንጂ በምርጫ የሚያምን አለመሆኑ በብዙ ተሞክሮ ተረጋግጧል ስለዚህ ምርጫው ኃይል ብቻ ነው።

Friday, May 22, 2015

Ginbot7 Popular Force Song Ethiopia

Ginbot7 Popular Force

በጎንደር፤ በደብረብርሃን፤ በደሴ የወያኔ የምረጡኝ ፖስተሮች እየተቀደዱ ሲሆን ጎንደር ከዚሁ ጋር ተያይዞ ዜጎች እየታሰሩ ነው


የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ሚያዚያ 1/2007 ዓ.ም በብአዴን ኢህአዴግ ስርዓት የተለጠፈውን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም እያሉ እየቀደዱት መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፣
በጎንደር ከተማ ቀበሌ 04 በኢህአዴግ የተለጠፈውን የምርጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት እየቀደዱት መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ በህብረተሰቡ ተግባር የተናደዱት የስርዓቱ ካድሬዎች ምንም አይነት ወንጀል ላልፈፀመ ዜጋ አንተነህ የለጠፍነውን ፖስተር የቀደድከው እያሉ በማሰር ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ታውቋል፣
የደረሰን መረጃ ጨምሮ- የኢህአዴግን ፖስተር ቀድዳችኋል ተብለው በስርዓቱ ታጣቂዎች ከታሰሩት ውስጥም። ታደሰ ታፈሰ፤ አቶ ጫቅሌና ሌሎችም በርካታ ዜጎቻችን የሚገኙባቸው በእስር ቤት እየተሰቃዩ እንደሚገኙና ህብረተሰቡ ደግሞ በላዩ ላይ እያወረደ ያለውን ግፍ ለማስቆም ለሚመለከታቸው አካላት እያደረገ ያለው አቤቱታ ምንም አይነት ውጤት እንዳላመጣለት ከምንጮቻችን ያገኘውነው መረጃ አመለከተ፣
በተመሳሳይ በደብረብርሃንና ደሴ ከተሞች በየቀበሌው የተለጠፈ የብአዴን/ኢህአዴግን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር ቀለም በመቀባትና በማበላሸት ልማት ይሁን እድገት ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት ተቃውሞአቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው አክለው አስታውቀዋል፣                                                                ሳምሶን አበራ

መንግስት በምርጫ ዋዜማ የሀይማኖት ጣልቃ ገብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል * ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ከአዲሱ መጅሊስ ጋር በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ አህባሽን ከምርጫ በሁላ የማስቀጠያ መንገዶቹን ተነጋገሩ -

yisema
Muslim
ሰበር ዜና ቢቢኤን
ቢቢኤን፡- ግንቦት 13/2007
መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ሃይማኖት ጣልቃ በመግባት የአህባሽ አስተምህሮን በፌድራል ጉዳዪች አስተባባሪነት፤በመጀሊስ ሽፋንነት የህገ-መንግስቱን አንቀጾች በመጣስ የሚፈጽመውን አስነዋሪ ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ
ከግንቦት7 እስከ 8 የፌድራል ጉዳዪች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ከአዲሱ በርሳቸው ትእዛዝ ከተመሰረተው አዲሱ የአህባሽ መጅሊስ ፕሬዝዳንትና ሌሎችም በተገኙበት ከዚህ ቀደምም የአህባሽ ጠመቃ በተካሄደበት የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሰጥቷቸዋል፡፡
”የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አደጋ እና የመታገያ ስልቶች ” በሚል ርእስ በተሰጠው ስልጠና ላይ ዶክተር ሽፈራው ያስቆመጧቸውን የመንግስት መጅሊሶች ኢህአዴግ እንዲመረጥ የሚችሉትን እንዲያደርጉና ከዚያ በሁላ የአህባሽ አስተምህሮትን በሰፊው ለማዳረስ ያላቸውን እቅድ ተነጋግረዋል፡፡
ምርጫ ሊደረግ ጥቂት ቀናት በቀረቡት ዶክተር ሽፈራው የተለመደ ጣልቃ ገብነታቸወን መቀጠላቸው ኢህአዴግን ምረጡ አህባሽን በግዳጅ እንድጠመቁ የሚል መልክት እያስተላለፉ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተችተዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ኢህአዴግ ዛሬም ከሙስሊሙ እምነት ላይ እጁን እንዳላወረደ አመላካች ነው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ከነዶክተር ሽፈራው ጋር የህዝብን ጥያቄ ይዘው ሂደው ሲወያዩ የነበሩት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በአሁኑ ጊዜ በማረሚያ ቤቱ በኩል በህወሃት ደህንነቶች ትእዛዝ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡
ድምጸችን ይሰማ በበኩሉ ትላንት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ በፊትም ሆነ በሁላ ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥለበት መግለጹ ይታወቃል፡፡

የወያኔን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ


berhanu-nega-election1
የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!! አገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::
ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ። ሀይማኖታችን ተዋረደ፤ ባህላችን ረከሰ፤ ታሪካችን ተናቀ። በልማት ስም ወልደን ከከበድንበት ተፈናቀልን፤ አገራችን አደገች እያለ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ተሰቃየ። በልቶ ማደር ብርቅ ነው። እንደሙጫ የሚያጣብቀንን ማህበረሰባዊ ትስስር በስልጣን ለመቆየትና ህብረተሰቡን ለመዝረፍ ሲል ሆን ብሎ እያፈራረሰው ነው:: ይኽ ሁሉ አይበቃንምን? ይኸ ሁሉ አይመረንምን?
ወላጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ!ውርደት ይብቃን። የተረገጥንና የተገደልን አንሶን ፍጹም ማንንም ሊያሞኝ በማይችል የለበጣ ምርጫ ወደን የተረገጥን፤ ፈልገን የተገዛን ለማስመሰል ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እናክሽፈው:: ከፊታችን ያለውን ምርጫ ባለመሳተፍ ምሬታችንን እንግለጽ።
ዛሬ በግሌ እና በአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። በዚህ ምርጫ አትሳተፉ። የምርጫ ካርዳችሁን ቀዳችሁ ጣሉት። እናምርር። ካላመረርን ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ይልቅስ ለማይቀረው የመጨረሻው ትግል ራሳችንን እናዘጋጅ::
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር ትብብር በመፍጠር የአገር አድን ኃይል በመገንባት ላይ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት አንከፋፈልም። ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ያካተተ ስብስብ ፈጥረን በኅብረት አገዛዙን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ትግል ነው። የትግሉም ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው። ክርስቲያን ሙስሊም፤ ወንድ ሴት፤ ወጣት አረጋዊ ሳንል፤ በብሔርም ሆና በቋንቋ ሳንከፋፈል ሁላችንም ይህን አስከፊ ሥርዓት በቃህ እንበለው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህንን የውሸት ምርጫ ባለመሳተፍ ለለውጥ ያለህን ዝግጁነት አሳይ! ደግሜ እለዋለሁ – የምርጫ ካርድህን ቅደድ!!!
የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!
እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። በወገኖቻችሁ ላይ አትተኩሱ። ይልቁንስ አፈሙዛችሁን አገራችንን ለውርደት በዳረገውና በሙስና በተጨማለቀው ዘራፊው የህወሓት አገዛዝ ላይ አዙሩት። ታሪካችሁን ከምታበላሹ፤ ታሪክ ሥሩ። ለራሳችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለልጆቻችሁ እና ለሕዝብ የሚጠቅም አገርና መንግሥት እንዲኖረን የእናንተ የግልም ሆነ የጋራ ተነሳሽነት ወሳኝ ነው። ወያኔ ህዝቡን የሚዘርፈው በእናንተ ትከሻ ላይ ቆሞ እንደሆነ ላንዳፍታም አትርሱት:: እንደመላው ህብረተሰብ እናንተም በነጻነትና በኩራት የምትኖሩበት ሀገር እንደምትሹ አልጠራጠርም:: ስለዚህም ይህን የህወሓት የውሸት ምርጫ ተቃወሙ። ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ትግላችን እስከ ነፃነት ድረስ ይቀጥላል። ነፃነታችንን በእርግጠኝነት በትግላችን እንቀዳጃለን። የምትወዷት፣ የምትኮሩባት አገር – ኢትዮጵያ – ትኖረናለች። ለዚህ ግን ዛሬ ተደራጅተን፣ ፀንተን መታገል የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ዛሬ ሁላችንም በፍላጎትና በመንፈስ የተገናኘን ነንና ሁሉም በያለበት ትግሉን ያጧጡፍ። ውጤቱ ቀድሞ በታወቀው በዚህ ምርጫ አለመሳተፍ ለትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ነውና ለውሸት ምርጫ ያለን የመረረ ተቃውሞ በምርጫው ባለመሳተፍ እናሳይ።
ነፃ እንወጣለን!
የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል!ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!                                                                                           ሳምሶን አበራ

Thursday, May 21, 2015

የወያኔ መንግስት በመላው አዲስ አበባ በታንክ የተደገፉ ታጣቂዎችን ማሰማራቱ ተነገረ *በለምለም ከበደ*




ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ በባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ  በማስፈራራት ጀምሮአል። በምርጫ ቅስቀሳ የፈራው የወያኔ መንግስት ፓርቲዎችን በክርክሩ መርታት ሲሳነው በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ አይተናል በክርክሩ የህዝብ አመኔታን ያጣው ገዢው ወያኔ የሚጨብጠው ቢያጣ ንቢቱን ተመስሎ በተሰራ ባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ ላይ ይደነፋ ጀምሮአል ድሮም ኮሮጆ በመስረቅ  ነው 25 ዓመት በሃይል የገዛው ።
ገዥው የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አምስተኛው የኢትዬጲያ ብሄራዊ ምርጫ ግይካሄዳል ፡፡ ሶስተኛውና ተስፋ የፈነጠቀው አገራዊ ምርጫ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ የፓለቲካ ምህዳር መዘጋት ከተጠናቀቀ በኋላ የተካሄደውን አራተኛው ምርጫ ኢህአዴግ 99.6  በመቶ የፓርላማ መቀመጫ “በማሸነፍ” ተቆጣጥሮታል፡፡  ከቀናት በኋላ የሚካሄደው አምስተኛ አገራዊ ምርጫ የፓለቲካ ምህዳሩን ለማሻሻል የሚረዳና መጠነኛ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ቢጠበቅም በተቃራኒው ገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እያዳከመ ተቺዎችን እና ሌሎች ነጻ ድምጾችን ለእስር ዳርጎ በከፍተኛ ጫና ታጅቦ ይካሄዳል፡።
የወያኔ መንግስት ህዝብን ማስተዳደር የማይችል አሸባሪና ዘረኛ ፓርቲ ነው። የኢትዮዽያ ህዝብም አንቅሮ ከተፋው ቆይቷል ወያኔም የተረዳው መሆኑን በሰሞነኛ ድርጊቱ እየታየ ነው። አንዳንድ የአፍሪካ አንባገነን መንግስታት ሽንፈታቸውን በሃይል ለምቀበል የሚደረገው ሙከራ ወያኔ ከምርጫው ቀድሞ ወታደሩን እና ታንኩን በአደባባይ ኮልኩሎ ህዝብን ማሸበር የተሸናፊነት ምልክት መሆኑን አውቀናል።
ወያኔ ተንቦጫብጯል ወያኔ ፈርቷል እንደለመደው የህዝብን ድምጽ ሊሰርቅ አሰፍስፋል ለተከታይ ፭ አመት የህዝብን በዘረኛ እና በግፍ አገዛዝ ሊገዛ አሰፍስፎ በማስፈራራት ታንክ ጭምር ከተማ ላይ በማሰማራት የህዝብን ድምጽ ለመገደብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለዚ የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃ በቃ በቃ በቃ በማለት ይህን የዘረኛ መንግስት በአንድነት ልናስወግድ ይገባል።
ሞት ለወያኔ
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር

አረና ቅስቀሣውን አቋረጠ፤ በአባሎቹ ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ ….VOA


ተቃዋሚው አረና ትግራይ “በአባሎቼ ላይ ተፈፅሟል” ባለው ድብደባና ለምርጫ ቅስቀሣ ሥራ በተከራያት መለስተኛ አውቶቡስ ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት በመላው የትግራይ ክልል የጀመረውን የምረጡኝ ቅስቀሣ ዛሬ ማቋረጡን ይፋ አድርጓል።
ዘጋቢያችን ግርማይ ገብሩ የተሽከርካሪዋ የኋላ መስትዋትና መብራት መሰባበሩን በሥፍራው በአካል ተገኝቶ ተመልክቷል።
ድብደባ ተፈፀመብን ከሚሉ ሰዎች መካከል ደግሞ ከአፅቢ ከተማ የመጡት አቶ ሄድሮም ኃይለሥላሴ እራሣቸው ላይ በመፈንከታቸው መቀሌ ውስጥ ሕክምና ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡
አረና “የህወሓት ካድሬዎች ያደራጇቸው ወጣቶች አድርሰውታል” ያለውን ጥቃት አስመልክቶ የክልሉ የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሓዱሽ ዘነበ ተጠይቀው “ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት ለማጣራት መርማሪዎቻችንን ወደ አካባቢው ልከናል፤” ብለዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ http://amharic.voanews.com/…/arena-suspends-ca…/2780525.html

እነሀብታሙ፣ የሺዋስ፣ ዳንኤል፣ አብርሃ …ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ 19ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ፣ እና በእነዘላላም ወርቅአፈራሁ የክስ መዝገብ ተከስሰው የሚገኙት እነሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ባህሩ ታዬ …የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 1፣ 2 እና 3 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ዛሬ በችሎት ጸሀፊ በኩል እንደተሰጣቸው ጠበቃቸው አቶ ተማም አባቡልጉ ገልጸዋል፡፡
ተከሳሾቹ ወደፍርድ ቤት ቢመጡም የችሎት ጸሐፊው ‹‹ተጠርጣሪዎቹ በታሰሩበት ቦታ ከ20 ቀናት በፊት ቀኑ መቀየሩ ተናግሯቸው ነበር፡፡ እርሶንም ማግኘት ስላልቻልን ነው ቀኑን ያልነገርኖት›› እንዳሏቸው የጠቆሙት ጠበቃ ተማም በዛሬው ዕለት ችሎት ስላልተሰየመ ደንበኞቻቸው ተመልሰው ወደቂሊንጦ እንደሚያመሩ ተናግረዋል፡፡
ተከሳሾቹ፣ ከዚህ ቀደም በነበራቸው የፍርድ ቤት ውሎ ለዛሬ ተቀጥረው የነበሩት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን በተከታታይ ቀናት ለመስማት መሆኑ ይታወሳል፡፡
Elias Gebru Godana's photo.

EthioSwedish Taskforce Against Woyane Killing

GINBOT 7 POPULAR FORCE IN SWEDEN meeting with Andargachew Tsege

Wednesday, May 20, 2015


ሰማያዊ ፓርቲ ከምርጫ እንደወጣ ተደርጎ እየተቀሰቀሰ እንደሆን ታወቀ
• ‹‹ሰማያዊ በሚያደርገው ቅስቀሳ ስለተደናገጡ ያደረጉት ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ
ሰማያዊ ፓርቲ ከ2007 ዓ.ም ምርጫ ራሱን አግልሏል በሚል አዲስ አበባ ውስጥ የተሳሳተ ቅስቀሳ እየተደረገበት እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ማንነታቸውን ያልታወቁ አካላት ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በገዥው ፓርቲ በሚደርስበት ጫና ምክንያት ራሱን ከምርጫ ለማግለል ተገዷል›› የሚል መልዕክት እያስተላለፉ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው በዚህ በተሳሳተ ቅስቀሳ ምክንያት ከትናንት ጀምሮ ‹‹ከምርጫው ወጥታችኋል ወይ?›› በሚል ከዜጎች ጥያቄ እንደቀረበላቸው ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ከምርጫው እንዳልወጡና አሁንም ቅስቀሳውን አጠናክረው እንደቀጠሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በትናትናው ዕለት ለኢህአዴግ ባስደነገጠ መልኩ በ8 መኪና ስንቀሰቅስ ውለናል፡፡ ዛሬና ነገም በተመሳሳይ መንገድ እንቀሰቅሳለን፡፡ በትናንትናው ዕለት ደማቅ ቅስቀሳ በማድረጋችን ኢህአዴግ ተደናግጧል፡፡ ሰማያዊ በሚያደርገው ቅስቀሳ ስለተደናገጡ ያደረጉት ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

አቤል ኤፍሬም በደረሠበት ድብደባ ኩላሊቱ ተጎድቶ ምንሊክ ሆስፒታል ገብቷል፡፡


በትላንትናው እለት በገዢው ፓርቲ የደህንነት ሀይሎች ተይዞ ወደማዕከላዊ ተወስዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲው አቤል ኤፍሬም ማዕከላዊ በሚገኙ የገዢው ፓርቲ ደህንነቶች ከትላንት ከቀኑ 5 ሠዓት ጀምሮ እስከ እኩለሌሊት በተፈፀመበት ከፍተኛ ድብደባ ኩላሊቱ በመጎዳቱ ዛሬ ጠዋት 11 ሠዓት ላይ ወደምንሊክ ሆስፒታል እንደተወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቤል ከመያዙ ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ላይ የሚገኙ 13 መምህራን በፖሊስ ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን አቤል ማዕከላዊ በገባበት ቀንምበአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ መምህራንን በህቡዕ እንደምታደራጅ ደርሰንበታል የተባለ ሲሆን አቤል ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለፀ ሲሆን ብሔሩን ሲጠየቅ ብሔሬ ኢትዮጵያዊ ነው ማለቱ ያናደዳቸው የደህንነት ሀይሎች መታወቂያውን በመቀበል ብሔሩን ለማጣራት ሲሞክሩ ብሔር የሚለው ስፍራ ላይ ምንም ብሄር አለመጠቀሱን ተመልክተው ተያዥ በሚለው ስፍራ ላይ ግን ታማኝ በየነ የሚል ፅሁፍ በማግኘታቸው ለድብደባ እንደተዳረገ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሌሊቱን በሙሉ ያለምግብ እና ውሃ ሲደበድቡት ያደሩት የደህንነት ሀይሎች የአቤልን መድከም ሲረዱ ምንሊክ ሆስፒታል የወሰዱት ሲሆን በስፍራው የነበሩ ሠዎች እንደገለፁልኝ ከሆነ Abel Ephrem ሆስፒታል ሲደርስ በድብደባ ብዛት ኩላሊቲ እንዳበጠ እና የለበሰው ልብስ ከጥቅም ውጪ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Tuesday, May 19, 2015

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢህአዴግ ላይ ያሰሙት ተቃውሞ ክፍል 2 ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም

ኢትዮጵያና አሜሪካ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ግንቦት 200


ዱሮ ዱሮ ምዕራባውያን የሶቭየት ኅብረትን ኮሚዩኒዝም መስፋፋት ለመቋቋም ከእሥራኤል ሌላ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ አገሮችን ሲያስሱ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱርክና ፋርስ እየታጩ ነበር፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተወዳጀበትና በአስመራ ቃኘው ጣቢያን የተከለበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፤ የፋርስ ጉዳይ ከንጉሠ ነገሥቱ መፈንቅለ መንግሥትና ሞት ጋር አበቃ፤ ቱርክ እያንገራገረም ቢሆን የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ማኅበር ውስጥ አለበት፤ እሥራኤል በአረቦች አካል ላይ እሾህ እንደሆነች ጥጋበኛ የአሜሪካ ቅምጥል ሆናለች፡፡
የፋርሱ ጉዳይ ከፋርሱ ንጉሠ ነገሥት ጋር እንደተያያዘው ሁሉ የኢትዮጵያም ጉዳይ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ጋር የተያያዘ ነበር፤ የእውቀት ጥበብ (ቴክኖሎጂ) እያደገ ሲሄድ የቃኘው ጣቢያ ለአሜሪካ አማራጭ የሌለው መሆኑ ቀረ፤ አሜሪካ ኮተቱን ይዞ ወደህንድ ውቅያኖስ ሲሄድ ኢትዮጵያን ችላ ማለት ተጀመረ፤ መቃቃሩ እየበረታ ሲሄድ የአሜሪካ እብሪትና የኢትዮጵያ ኩራት ተጋጩ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ የአሜሪካኑን አምባሳደር አስከማስወጣት ደረሱ፤ ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ያኔ ተጀመረ፤ የፋርሱ ንጉሠ ነገሥት ሲገለበጥ ቀጣዩ አገዛዝ ከአሜሪካ ጋር ጠላት እንደሆነው የአጼ ኃይለ ሥላሴም አገዛዝ ሲገለበጥ ቀጣዩ አገዛዝ ከአሜሪካ ጋር ጠላት ሆነ፡፡
አሜሪካ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ጣልቃ እየገባ የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ግፍ የጀመረው ከዚያ ወዲህ ነው፤ የደርግ አገዛዝ ኮሚዩኒስት መሆኑን አወጀ፤ የደርግ አገዛዝ ከሶቭየት ኅብረት ጋር ማኅበርተኛ መሆኑን አወጀ፤ የደርግ አገዛዝ የአሜሪካ መንግሥት ዓለም-አቀፍ ቄሣራዊነትን የሚያራምድ መሆኑን እየደሰኮረ የአሜሪካ ባላጋራ መሆኑን አስታወቀ፤ ይህ ሁሉ እውነት ነው፤ ነገር ግን አንዱም የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈቃድ ያዘለ አይደለም፤ አንዱም ኢትዮጵያን እንደአገር የሚያስጠይቅ አይደለም፡፡
ከላይ ለተጠቀሱት የደርግ ‹አዋጆች› የአሜሪካ መንግሥት መልስ የሰጠው ለደርግ መንግሥት ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ነበር፤ መልሱ ይህ ነበር፤ አንደኛ ኢትዮጵያን የወረረችውን ሶማልያን ረዳ፤ ሁለተኛ ሻቢያንና ወያኔን የሚረዳውን የኑሜሪን ሱዳንን ረዳ፤ ሦስተኛ ሻቢያንና ወያኔን ረዳ፤ አራተኛ የኤርትራን መገንጠል ደገፈ፤ አምስተኛ የወያነን አምባ-ገነን አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ተክሎ አቅፎታል፤ እነዚህ የአሜሪካ መልሶች ደርግ ወንበሩን አስረክቦ ቃሊቲ ከገባ በኋለም መቀጠላቸው የአሜሪካ ጠብ ከደርግ ጋር ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያም ጋር የሆነ ያስመስላል፡፡
በኢትዮጵያውያን ድካምና በአሜሪካ ጫና ኢትዮጵያ ዛሬ ሁለት ሆናለች፤ በአንዱ ክፍያ ላይ አሜሪካ እግሩን ዘርግቶ አድራጊ ፈጣሪ ቢሆንም በሌላው ክፍያ ላይ እግሩን ማስገቢያ አላገኘም፤ ብዙ ሰው ያልተረዳውና የሚያስደንቀው የአሜሪካ ዶላርና የአሜሪካ ጫና ኤርትራን ማንበርከክ አለመቻሉን ነው፤ ሎሌ ሆኖ ጌታ ከመምሰል ደሀ ሆኖ መከበር ይሻላል፤ ይህ የቀድሞው የኢትዮጵያዊነት አልበገርም-ባይነት፣ የክብርና የኩራት ምልክት ነው፤ አልጠፋም!
በአለፉት ዓመታት ውስጥ አሜሪካ በኢራቅ ምን አደረገ? ማንን ጠቀመ? ማንን ጎዳ? በአፍጋኒስታንስ? በፓኪስታንስ? በሶርያና በየመን የሚካሄደውስ ብጥብጥ የት ድረስ ይሄዳል? የትስ ይቆማል? ቀደም ሲል በኮሪያ (ኢትዮጵያን አስከትሎ) ምን ፋይዳ ሠራ? ሁለት ኮሪያዎችን ፈጠረ፤ በቭየትናም ሕዝብ ጀግንነት ቭየትናም አንድነቱን ይዞ በድል ወጣ፤ መከፈል ለሱዳንም ደረሰው፤ መከፋፈል ሲጀምርም የማይቆም መሆኑን በሱዳን እያየን ነው፡፡
ነገ በኬንያ ምን ይሆናል? ዛሬ ኬንያውያን ሳይገባቸው አገራቸው ውስጥ እሳት እየተቀጣጠለ ነው፤ እሳቱ ወዴት እንደሚዘምትና ማንን እንደሚያጠፋ ወደፊት እናያለን፤ በየመን በኩል የሚቀጣጠለው እሳትም በጂቡቲና በሶማልያ በኩል ባሕር የሚገባ አይመስለኝም፡፡
ኢትዮጵያን የማላነሣው ረስቼ አይደለም፤ አንዴት ብዬ! አንዱ የወያኔ ጮሌ ‹ምሁር› በፌስቡክ ላይ መቀሌ አይባልም፤ መቐሌ ተብሎ መጻፍ አለበት ብሎ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር ነበር፤ እንደሚመስለኝ አሸነፈ መሰለኝ! አዋቂነት መሆኑ ነው! ነገ ደግሞ አንዱ ተነሥቶ ባቄላ አይደለም፤ ባኤላ ነው፤ ቢል ማን እንደሚያሸንፍ አላውቅም፤ እንደፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴ (ነፍሱን ይማረውና)፣ እንደፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽና እንደፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ያሉ የታሪክ አዋቂዎች ስድስት ሺህ ዓመታት ሲቆጥሩ ገና ፊደል የቆጠሩት የዘመኑ ደርሶ አዋቂዎች ደግሞ ዳዴ ሊያስኬዱን ይፈልጋሉ፤ ስለዚህም ገና የእውቀትን መስፈሪያና የታሪክን ማበጠሪያ አላረጋገጥንም፤ ከግራም ሆነ ከቀኝ ለሚመጣብን አደጋ በአሜሪካ ላይ የምንተማማን ከመሰለን የደቡብ አሜሪካን፣ የምሥራቅ እስያንና የመሀከለኛው ምሥራቅ አገሮች ከአሜሪካ ጋር የነበራቸውን ታሪክ እናጥና፡፡
አሁን ደግሞ የጦርነት ዓይነት በጣም እየተለወጠ ነው፤ በሰልፍ የጦር ሜዳውን የሚሞለው ወታደር የለም፤ የመሣሪያው ዓይነትና ብዛት እምብዛም ዋጋ የለውም፤ ጥቂት ሰዎች በጥቂት ፈንጂዎች ከባድ ጥፋትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ አሸባሪ ቡድኖቹ ለሰው ሕይወት ዋጋ የላቸውም፤ ለሀብትም ሆነ ለባህላዊ ቅርስ ግድ የላቸውም፤ የራሳቸውን ሕይወት ወደመሣሪያነት ለውጠውታል፤ አንድ ቦታ አይቆዩም፤ ይዘዋወራሉ፤ ጥላቻ እንጂ ፍቅር አያውቁም፤ ሞት እንጂ ሕይወት አያውቁም፤ ጥፋት እንጂ ልማት ዓላማቸው አይደለም፤ አቃጥሎ መቃጠልን እንደመጨረሻ ዓላማ የሚከተሉ ናቸው፤ የሚያከብሩት ሕግ፣ የሚፈሩት ኃይል የለም፤ ከነዚህ ጋር ጦርነት መግጠም የማይበርድ እሳት ውስጥ መግባት ነው፤ ታላቁ አሜሪካ ከማያልቀው ሀብቱና ወደር ከሌለው የጦር ኃይሉ ጋር ለለፉት ስድሳ ዓመታት ከደቡብ አሜሪካ ጀምሮ እስከእስያ፣ ከብይሩት እስከቭየትናም ጥረቱ ሁሉ ከሽፏል፤ ውድና ክቡር የአሜሪካ ሕይወት በአረመኔዎች እንዳይቀጠፍ ከደሀ አገሮች የእሳት እራት የሚሆኑ ወታደሮችን ይከራያል፡፡

የህወሓት አየር ኃይል ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ፡፡


በበረራ፣ ጥገና፣ ድጋፍ ሰጪ፣ ዘመቻና አስተዳደር ከ200 በላይ አባላቱን በከፍተኛ ወጪ ለ6 ወራት ሲያሰለጥን የባጀው አየር ኃይል የሰላም ማስከበሩ ተልዕኮ ወደሚከናወንበት ደቡብ ሱዳን ሊጓዙ የተመረጡት መንገደኞች ከየአየር ምድቦቻቸው ተነስተው ደብረ ዘይት ከከተቱ በኋላ ጉዞው ድንገት ተዘርዟል፡፡
ጉዞው የተሰረዘባቸው ምክንያቶች በአባላትና አባላት፣ በአባላትና አመራሮች እንዲሁመም በአመራሮችና አመራሮች መካከል አለመተማመን በመስፈኑ፤ ያለመጠን ስር ሰዶ የተንሰራፋው ጎሰኝነት ተባብሶ በትግርኛ ተናጋሪ የህወሓት ሰዎች መካከልም ውቅሮና አዲግራት ወደሚሉ የመንደር ቡድንተኝነት ቁልቁለቶች በመውረዱ፤ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አሁንም አብራሪዎች ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን ይዘው ሊኮበልሉ ይችላሉ ከሚል ስጋት በመነጨ፣ ከፍተኛ በሆነ የአቅም ማነስ ችግር፤ ከምርጫው ጋር በተያያዘና ብረት ያነሱ የነፃነት ኃይሎች ጦርነት ይከፍታሉ ተብሎ በመሰጋቱ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው አየር ኃይል ከዚህ በፊት በ2005 ዓ.ም በብቃት ማነስ ምክንያት ከዳርፉር ተባሮ የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን ሳያሳካ ጓዙን ጠቅልሎ ውርደት በመከናነብ መመለሱ አይዘነጋም፡፡

“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)

የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ! እነሆ መልዕክቱን ያንብቡ፤ ሼር በማድረግም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይደርስ ዘንድ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ተጠይቃችኋል!
“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)
ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳሸዋ ተበትናችሁ የምትገኙ ወገኖቼ እኔ የተጎዳሁትን ያህል እናንተም የተጎዳችሁ መሆናችሁን በተለያዩ ሀገሮች በተደረጉ ሰልፎች ፤ የዉይይት መድረኮች ላይ በንዴት፤ በቁጭት እና በእልኸኝነት በእንባ ስትራጩ በመሃላችሁ ተገኝቼ ያየኻችሁ ሲሆን ይህም በጣም በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል። አንዳርጋቸውም በወያኔ የጨለማ እስር ቤት እየከፈለ ያለውን መከራና መስዋትነት የትም እንዳልወደቀና እንዳልቀረ በማሰብ እጽናናለው።
ዛሬ አንዳርጋቸው ፅጌ በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ “የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ“፤ “የኢትዮጵያ ልዩ አፈር“፤ “የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ” ወዘተ…. የሚሉ መገለጫዎችን እና መጠሪያዎችን የተጎናፅፈው ታናሽ ወንድሜ አንዳርጋቸው ፅጌ በእኔ እይታ ደግሞ የቤተሰባችን ልዩ ልጅ ነው።
አንዳርጋቸው የቤተሰባችን የመጀመረያ ወንድ ልጅ ስለነበረ ብርቅዬ መሆን የጀመረው የካቲት 1 ቀን 1947 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ሆስፒታል ከእናታችን ከወ/ሮ አልታዬ ተሰማ ሮቢ እና ከአባታችን ከአቶ ፅጌ ሀብተማርያም ጨሜሳ ከተወለደ ቀን ጀምሮ ነው።
አንዳርጋቸው ለወላጅ አባታችን እና እናታችን፤ ለአያቶቻችን እና ለቅድመ አያቶቶቻችን ፤ ለእህቶቻን እና ለወንድሞቻችን ፤ ለዘመድ አዝማድ፤ ለአብሮ አደግ ጓደኞቹ በአጠቃላይ በአካባቢው ለነበሩት ዘመድ እና ወዳጅ ሁሉ ትልቅ እና ትንሽ ፤ ሐብታም እና ደሃ ፤ ወንድ እና ሴት ሳይል እንዲሁም በትምህርት ቤት አክብሮት እና ትህትና ሲያሳይ የኖረ ነው። የአንዳርጋቸው ሌላው ትልቁ እና አስገራሚው ስጦታዉ ወደር የማይገኝለት ትግስቱ ነው።
በቅርበት ከነበርው አካባቢው ሰፋ ባለው ክልል ወስጥም ቢሆን አንዳርጋቸው ስለ ሀገሩ እና ስለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር እና ደህንነት የነበርው የተቆርቋሪነት ስሜት ገና የአንደኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ከነበረበት ዘመን የጀመረ ነበር። ለዚህም ነው ዛሬ “ለአንቺነው ነው ሀገሬ ” የሚል ግጥም ለገጠመላት የልጅነት ፍቅረኛው “ኢትዮጵያ” ሲል ልጆቹን ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ጥሎ የሀገርን ጥቅም እየነገደ የቡድን ምቾትን እና ሀብትን በማካበት ላይ የሚገኘውን የዘረኛ ባንዳ ወያኔ መንግስት በቁርጠኝነት ለመታገል የተነሳው።
አንዳርጋቸው አገሩን በበጎውም በክፉም ዘመን የሚያውቃት የ1960ቹ ትውልድ አካል በመሆኑ ነው፡ በዚህም በዚያም የተነሳ ይችን አገር ለማዳን የመጨርሻው ትውልድ እንደመሆኑ ይህንን አደራ ለመሸከም ታረክ የጣለበትን ሀላፌነት ከዚህ የመነጨ ነው ብዬ አስባለው ስለሆነም አንዳርጋቸው ቁጭ ብሎ ከመፅፅት በላይ እራሱን ለዚች አገር የመስዋት ጠቦት አድርጎ ማቅረቡና ታፍኖ ያለው ነጻነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንን ተረድቶ በልቡ መሀደር ላይ በክብር የጻፈው በመሆኑ ማንም ምድራዊ ሀይል ምንም አይነት ጥላሸት በመቀባት ሊቀይርው እንደማይችል ባለፉት 10 ወራት የታየው አብሮነት ትልቅ ምስክር ነው።
እነሆ! ይህ ጉዞው ዛሬ በወረበላው የየመን መንግስት ሹማምንት ተባባሪነት በጠላቶቹ እጅ እንዲወድቅ አድርጎታል። አንዳርጋቸው በጠላቶቹ እጅ ከወደቀ አስርኛ ወራቶች በላይ ቢቆጠሩም እስከ ዛሬ ድርስ ከአረመኔዉ ወያኔ አፋኞች ውጭ እና ከፈጣረው በስተቀር የት ስፍራ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ የሚያውቅ ሰው የለም።
አንዳርጋቸው በዚህ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ መዉደቁ ልቤ ውስጥ የተቀመጠ የእሳት ረመጥ ሆኖ በየቀኑ እያቃጠለኝ ቢገኝም በሀገሬ ኢትዮጵያ ፤ ከአሜረካ እስከ ካንዳ ፤ከጃፓን እስክ ደቡብ ኮረያ፤ ከአዎሮፓ እስከ ደቡብ አፍረካ፤ ከአውስትራሊያ እሰከ እስራኤል እንዲሁም በተለያዩ የአርብ አገራት ባለው የአለማችን ስፋት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን ወገኖቼ ” እኔም አንዳርጋቸው ፅጌ ነኝ !” ፡ “ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን” ብለው በመነሳት የወያኔን እና የተባባሪዎቹን እብሪት፤ትዕቢት እና ህገወጥነትን ለማጋለጥ እያደረጉ ያለው ትግል ታላቅ መፅናናትን ይሰጠኛል።
አንዳርጋቸው የትናንሽ ልጆች አባት ከመሆኑ በላይ በተጨማሪ የ 85 ዓመት እድሜ ባለፅጋ የሆኑ አባታችን እዚያው ታፍኖ በተቀመጠበት ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራል። ከዚህ በተረፈ በጣም ከሚወዱት እና ከሚያፈቅሩት ከቅርብ ቤተሰቦቹ አልፎ አሁን ግን በአንዳርጋቸው የሀገር ፍቅር ፤ ለነጻነት ፤ ለፍትህ ፤ ለእኩልነት እና ለዴሞክራሲ የሚታገሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባት እና እናቶች ፤ ወድም እና እህቶች ፤ ልጆች አፍርቶ ይገኛል።
ይችን አጭር ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት ለዚህ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ቤተሰቤ ልባዊ ምስጋናዬን በአንዳርጋቸው ስም ለማቅረብ ነው። በዚህ ክፉ ጊዜ የታየው ቆራጥነት በወያኔ ታፍኖ የተወሰደው ወንድማችንን ሙሉ ነጻነቱን እንዲሁም በወያኔ እስር ቤት እየማቀቁ ላሉት የነጻነት ታጋዮች እንዲሁም መብትና ነጻነቱን ተገፎ በሰፊዉ እስርቤት እየማቀቀ ላለው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን እንደሚቀጥል እና ከግቡ እንደሚያደርስ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ።
በመጨርሻም ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ አንዳርጋቸው እና እሱን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮች እና የፖለቲካ መሬዎች ካለፍርድ በየስር ቤቱ በግፍ ታጉረው ላሉ ሁሉ እና ለቤተሰቦቻቸው ጭምር ፍጣሪ አምላካችን ብርታቱን ይስጥልኝ። የመጨርሻውም ፍርድ የሚመጣው ከሱ ከእግዛብሄር ስለሆነ ይችን የምንወዳትን የጋራ ሀገራችንን ለመታደግ በጋራ የጀመርነውን በጋራ እንውጣው ስል በወያኔ ጭለማ እስር ቤት ውስጥ በሚሰቃዩት ወገኖች ስም እማፅናለው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ

Monday, May 18, 2015

በእስር ቤት በድብደባ ብዛት ሆነ ተብሎ ስለተገደለው ወጣት ቤተሰቦቹ የሚሉትን ስሙ

ኢ/ር ይልቃል የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በደል ከደረሰባቸው ከቤሻንጉል የአማራ ገበሬዎች ጋር ሲወያዩ የሚያሳይ ቢዲዮ

አቶ አሊ ሱሌማን በቪርጂኒያ የገጠመው ከባድ ተቃውሞ ቪዲዎውን እነሆ

Migrant crisis Hundreds more people flock to Italy የጣሊያን የባህር ሃይል ከ 400 የሚበልጡ ስደተኖችን አዳነ ቪዲዮውን ይመልከቱ Video: 400+ Migrants Rescued off Libya

ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች የ አይ ኤስ ታጣቂዎችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው


ቢቢሲ ባወጣው መረጃ መሰረት አንድ የሊቢያ ባለስልጣን ለቢቢሲ እንደገለፁት በሜዲትራኒያን ባህር በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ አውሮፓ አዘዋዋሪዎች ከስደተኞች ጋር ታጣቂዎቹን በመቀላቀል ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው
ታጣቂ ቡድኑ በሰሜን አፍሪካ ጀልባ ባለቤቶች ስራውን እንዲሰሩ በመፍቀድ ከገቢያቸው ደግሞ 50 በመቶ ያህሉን ይቀበላሉ እንደ ቢቢሲ ዘገባ
የአይ ኤስ ታጣቂዎች በባህር በሚደረገው ጉዞ ከሌሎቹ ስደተኞች በምን ይለያሉ? ከዘገባው ያገኙታል .
Islamic State (IS) fighters are being smuggled into Europe by gangs in the Mediterranean, a Libyan official has told the BBC.
Government adviser Abdul Basit Haroun said smugglers were hiding IS militants on boats filled with migrants.
He based his claim on conversations with boat owners in parts of North Africa controlled by the militants.
He alleged that IS was allowing them to continue their operations in exchange for 50% of their income.
The UN estimates that 60,000 people have already tried to cross the Mediterranean this year.
More than 1,800 people are feared to have died making the journey in often overcrowded and unseaworthy boats in 2015 – a 20-fold increase on the same period in 2014.
Read More at BBC
 

Sunday, May 17, 2015

ዓረና መድረክ በመቐለ ማዘጋጃ ቤት ኣዳራሽ የተጠራ የህዝብ ስብሰባ የተሳካና ሁሌ በዓረና-መድረክ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍ ኣንጀታቸው እርር የሚሉ ህወሓቶችም ድንጋጤኣቸው ለከት ኣጥተውለት ያሳበዳቸው መድረክ ሁኖ ኣልፏል

ቅዳሜ 08 / 09 / 2007 ዓ/ም በዓረና መድረክ በመቐለ ማዘጋጃ ቤት ኣዳራሽ የተጠራ የህዝብ ስብሰባ የተሳካና ሁሌ በዓረና-መድረክ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍ ኣንጀታቸው እርር የሚሉ ህወሓቶችም ድንጋጤኣቸው ለከት ኣጥተውለት ያሳበዳቸው መድረክ ሁኖ ኣልፏል።
ስብሰባው የተከፈተው በትጥቅ ትግሉ የተሰዉ ሰማእታትና በሊብያ በኣያኤስ ኣያኤስ የታረዱ ወገኖቻችን የኣንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር።
በስብሰባው የዓረና-መድረክ ኣማራጭ ሃሳቦች፣ የገዢው ፓርቲ ድክመቶች፣ ዓረና-መድረክ ያሉት ምርጥምርጥ የመፍተሄ ሃሳቦች ቀርበዋል። ህወሓትም ካድሬዎችዋን ልካ ከፍተኛ ተሳትፎ ኣድርጋለች።
ከህዝብ ከቀረቡ ሃሳቦች ህወሓት የምትባል የድሮ ድርጅት ኣሁን እንደሞተች፣ እንደጠፋች፣ ኣሁን ያለችው ህወሓት ከድሮዋ ህወሓት በፍፁም የማይገናኙና የኣሁንዋ በድሮዋ ህወሓት ስም ለመነገድ እየሞከረች ያለችው ፎርጅድ (ቓንጫ መርዓት፣ ኣሻንጉሊት) እንደሆነች ታላላቅና ወጣት ተሳታፊዎች ድምዳሜ የደረሱበት ሁኔታ በግልፅ ቋንቋ ገልፀዋል።
ህወሓት ስብሰባው እንዳይ ሳካ መጀመርያ ከሰዓት ሰልፍ እንደሚያደርጉ በመኪና የቀሰቀሱ ቢሆኑም ህዝቡ ለዓረና-መድረክ ቅስቀሳ ያሳየው ታላቅ ድጋፍ በመደንገጣቸው ከምሽቱ 2 ስዓት ጀምረው ቤት ለቤት እየዞሩ ሰለማዊ ሰልፉና ስብሰባው ለጥዋት እንደተቀየረና ማንኛውም ኑዋሪ የግድ መገኝት እንዳለበት ኣዘው ነበር።
ይህ ሁሉ ኣድርገው ህዝቡ ወደ ስብሰባው መጣና ኣንጀታቸው ቅጥል፣ እርር ፣ ድብን ኣሉ።
የህወሓት የቀበሌ ካድሬዎችም በኣዳራሹ መግብያ በር ኣጠገብ ሁነው የገባው እየመዘገቡ፣ ፎቶ ግራፍ እያነሱ ዋሉ።
ስብሰበው የዓረና-መድረክ ኣማራጭ ፖሊሲዎች በመገባ ወደ ተሳታፊው እንዲደርሱ ተደርገዋል።
ህወሓቶች ምክሬን ተቀበሉ።።። ህዝቡ በጣም ጠልቷቹሃል። ስለዚህ የህዝብ ድምፅ ለመቀበል ተዘጋጁ፣ መድረክም ለሰራቹት ጥፋት ሁሉ ይቅር ሊላቹና በሚመሰርተው ሃገራዊ እርቅ የሚመሰረት መንግስት ኣካል ያደርጋቹሃል። ይህ ሲባል ከሁሉም ሰለማዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ከትጥቅ ትግል የመረጡ ወገኖች፣ በውስጥና በውጭ ኣገር ከሚኖሩ ኢትዮዽያውያን ምሁራት የተውጣጣና የሽግግር መንግስት ኣካል ት ሆናላቹ።
ኣለበለዝያ እንደለመድነው ኮሮጆ ዘርፈን በስልጣን እንቆያለን የሚል ቅዠት ካላቹ ግን ለናንተም ጥሩ ኣይደለም፣ ለሃገሪቷም ኣይጠቅምም።
የትግራይ ህዝብ ግን ምርጫው በግልፅ ቋንቋ ዓረና-መድረክ እንደሆነ እየተናገረ ነው።
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!
IT IS SO...!