Wednesday, September 21, 2016

የ 24 ተኛ ክ/ጦር እና የ25 ተኛ ክ/ጦር አባላት በእጅጉ መመናመናቸዉ ወያኔን አሳስቦታል



በጎንደርና በአካባቢዉ ጠረፎችና ከተማ በግዳጅ ላይ የተሰማራዉ የ 24 ተኛ ክ/ጦር እና የ25 ተኛ ክ/ጦር አባላት በእጅጉ በመመናመናቸዉ ምክንያት የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች የመጠቅለል ስራ እንዲያከናዉኑ ወታደራዊ ደህንነቱ መጠየቁን ታማኝ መረጃዎች ጠቆሙ፤
ለቃኘዉ ለዋርድያ እንዲሁም ለግዳጅ የሚላኩ የክ/ጦሩ አባላቶች ከጕድ መሪ አንስቶ እስከ ከፍተኛ አመራሮች ስርአቱን በመክዳት እየተሰወሩ በመሆኑና አብዛኞቹ አፈሙዛቸዉን አዙረዉ የትግራዩን ነጻ አዉጭ ሰራዊት እየቀጡት መሆኑን ወታደራዊ ክንፉ በግልጽ አስቀምጦአ።
ወታደራዊ ደህንነቱ ከእንግዲህ ወዲህ አዲስ ሰራዊት ስለመገንባት ሳይሆን ያለንን ሐይል በመጠቅለል ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረግ ይጠበቅብናል ይህ መንገድ ብቻ የተወሰነ እራስን የማዳን ግዜ ይሰጠናል ሲል የህወሃትን የቀብር ስነ ስርአት አፈጻጸም በግልጽ አንጸባርቆአል።
በተያያዘ መረጃ በነፍሰ በላዎቹ የህወሃት ጄኔራሎች በሳሞራ የኑስና በሲራጅ ፈርጌሳ የሚመራዉ የመልሶ ማጥቃትና መከላከል እንዲሁም የህዝባዊ እንቢተኝነት ቅልበሳ ቡድን ያሳለፍነዉ ሰኞ በጎንደር በከፍተኛ ሚስጥር ለዉሳኔ ስብሰባ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን አንድ የአማራ ክልል መኮንን የዝሆኑ ሁለት የፊት እግሮች ተቆርጠዋል ኦህዴድና ብአዴን ከእንግዲህ በህዝቡ ትግል ተቀብረዋል ዝሆኑ በሁለት የሁዋላ እግሮች በአጋዚና በዚህ መከላከያ መቆም አይችልም በማለት በድፍረት የተናገሩ ሲሆን ሌላኛዉ ከፍተኛ መኮንን ተቀብለዉ የአርበኞች ግንቦት 7 ይገባበታል ተብሎ የሚታመንባቸዉ ስፍራዎች ላይ የተሰማራዉ የሐገሪቱ አጠቃላይ የአቅም መጠን ነዉ!!!!! ነገር ግን አርበኞች ግንቦት ሰባት አሸንፎናል እነርሱ አንዳችም ጥይት መተኮስም ሆነ የሰዉ ህይወት ማጥፋት አይፈልጉም ከመሐል ጨርሶ አፍርሰዉናል!! የምንዋጋዉ ከምሁራን ጋር በመሆኑ ሽንፈታችን አልታየንም አሁን ያለን አማራጭ ስልጣን ማስጠበቅ ሳይሆን ህዝቡን መጠበቅ መሆን አለበት በማለት ያስጠነቀቁ ሲሆን ስብሰባዉ እንደተገባደደ ሁለቱ መኮንኖች በሳሞራ የኑስ ጠባቂዎች ተወስደዋል፥፤
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
( ጉድሽ ወያኔ )

Monday, September 19, 2016

ወጣቷ የነጻነት ታጋይ ንግሥት ይርጋ በወያኔ መታፈኗ ተሰማ፥


ወጣቷ የነጻነት ታጋይ ንግሥት ይርጋ በወያኔ መታፈኗ ተሰማ፥
ወጣት ንግስት ይርጋ፥ አርብ መስከረም 6 ቀን 2009 ዓ.ም ከጎንደር ከተማ ተነስታ፥ በታች አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ ወደ ሚገኘው ቤቷ ስታመራ መንገድ ላይ ታፍና ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ የማሰቃያ ቤት መወሰዷ ታውቋል።
ወጣት ንግስት ይርጋ ተፈራ፥ ሰሞኑን ጎንደር በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ ላይ ባደረገችው የማስተባበር ተሳትፎ በከተማው ታዋቂነትን ያተረፈች፥ ገና በሃያዎይቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የምትገኝ፥ ምንም ወንጀል የሌለባት ወጣትና ፍትህ ፈላጊ ታዳጊ ዜጋ መሆኗ ነግሯል።
ወጣት ንግስት ወደ ትግሉ የገባችውና በሕዝብ ዓይን ጎልታ መታየት የጀመረችው፥ የወልቃይት ማንነት ኮሚቴዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ዓፍነው ለመውሰድ በመጡ የወያኔ ታጣቂዎችና በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የመከላከል እርምጃ ምክንያት ጎንደር ላይ በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ፥ ሰልፍ በመምራትና በማስተባበር ባደረገችው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነበር።
ይህች ወጣት ንግስት የአማራ ተጋድሎ በመባል የሚታወቀውን ሕዝባዊ ንቅናቄ የተቀላቀለችው ቂሊንጦና ቃሊቲ እስር ቤት ጓደኛ ለመጠየቅ ሂዳ ባየችው የወጣት ኢትዮጵያውያን እስረኞች ብዛትና የአማራ እስረኞች ስቃይ፥ በተለይም ከገጠሪቱ ጎንደር ባልሰሩት ወንጄል ታፍነው ተወስደው መዳረሻቸው ሳይታወቅ ለእረጅም ጊዜ ያለጠያቂ ሲሰቃዩ ላየቻቸው ወገኖቿ ጩኸትና የመከራ ድምጾች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ያጫወተቻቸው የትግል አጋሮቿ ይናገራሉ።
ትግሉ ይቀጥላል፥ ሕዝብ ያሸንፋል፥
Image may contain: 1 person

በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የኮር አመራሮች ስብሰባ ካሳ ተ\ብርሀን በብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እንደታገደ ታወቀ


በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የኮር አመራሮች ስብሰባ ካሳ ተ\ብርሀን በብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እንደታገደ ታውቇል።
ስብሰባው በነ በረከት ስምኦን፣በነ ተፈራ ዋልዋ፣በነ ህላዌ፣በነ ገዱ፣በነ ደመቀና ሌሎችም የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ሲሆን ተሰብሳቢዎች ከስልክ ጀምሮ ምንም አይነት የቴክኖሎጅ ውጤቶችን መጠቀም እንደማይቻሉ እና ሦስት ጊዜ ተፈትሸው እንደሚገቡ ተናግረዋል።ስብሰባው በወልቃይት ጉዳይና በህዝቡ እምቢተኝነት ዙሪያ ከሚነገረው መልስ ጋር ተያይዞ ከኮር አመራሮች ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ ከ3_7\1\09 ሊጠናቀቅ የነበረው ስብሰባ ተራዝሞ ዛሬም በመካሄድ ላይ ይገኛል።የክልሉ ስቢል ሰርቢስ ም\ሀላፊ የሆኑት አቶ ሻምበል በመረጃና ማስረጃ የህዝቡን ጥያቴ በማቅረብ ግንቦት ሰባት ነህ እስከመባል ደርሰዋል።”ህዝቡ ተጨቁኖ ቆይቷል።አሁን ግን በየቦታው ተነስቶብናል።ሊበላን ነው ምን ምላሽ እንስጥ?” ብለው ለጠየቁት ጥያቄ አቶ በረከት አርፈህ ተቀመጥ”አንተን የሚመለከትህ የሲቪል ሰርቢስ ሪፖርት ነው “በማለት መመለሱን ተከትሎ “የተሰበሰብነው በወልቃይት ጉዳይ መሰለኝ።እንጂማ አንተ የምትመራውን ኢፈርት ብናነሳ ኑሮ ከነ ድርጅትህ መግማትህን እንሰማ ነበር “በማለት ለሰጡት አፀፋ ከተሰብሳቢው የድጋፍ ጭብጨባ ተደርጎላቸዋል።
አቶ ገዱ ከአመራሮች ሁሉ” ወልቃይት የትግራይ ነው “ብለው በድፍረት ያልተናገሩ ሲሆን “እርስ በርስ መተላለቃችን አይቀርም” በማለት አሳስበዋል።”ስብሰባው ከህወሀት ተልኮ የፀዳ አይደለም።በረከት ህወሀት ነህ “የሚል አስተያየት እንደሚበዛ ተሰብሳቢዎች ተናግረዋል።
Image result for በረከት ስምኦን

Friday, September 16, 2016

ወያኔ መንግስት በኮንሶ በሚኖሩ አማራ ህዝብ ላይ ጥቃት እየፈፀመ ነው


*ከ60 ዓመታት በላይ በኮንሶ የኖሩ፣ ቋንቋቸው ኮንሶ የሆኑ ከ200 በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች ማሳቸው በእሳት ነዶ፣ ቤታቸው ተቃጥሎ ተፈናቅለዋል። በ4 አይሱዙ ጭነት መኪና ሼሌ ላይ የተበተኑት አማሮችን ኮንሶዎች ምግብ እና መጠለያ እየሰጡ ረድተዋቸዋል።
የኮንሶን የአስተዳደር ጥያቄን ወደ ብሔር ግጭት ለመውሰድ በገዢው ስርዓት ህወሓት_ደኢህዴን የተፈጸመ ሴራ እንደሆነ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የአማራ ብሔር ተወላጆች ዛሬ አርባምንጭ እንደገቡ ታውቋል። ከሰሞኑ ከ50 በላይ ሰዎች በኮንሶ መገደላቸው ይታወቃል።
በሱማሌና በጋንቤላ ክልልም እንዲሁ አማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመደረግ ላይ ነው ማምሻውን ደሞ በአርባ ምንጭ ከተማ የአፄ ቴውድሮስን ፎቶ የለጠፉ የባጃጅ ሹፌሮች በመደብደብ ላይ ናቸው ወያነ ሆን ብሎ የአማራውን መደራጀትና ትግል ለማዳከም ሲል ከተለያዩ ክልል ተወላጆች ጋር አማራውን የሚያነካክስ ተግባር በመፈፀምና በማስፈፀም ላይ ነው። የአማራ ህዝብ ሆይ ባለህበት ተደራጅ ተራዳዳ አለዛ የወያነ ትግሬ አንተን ከማጥፋት ወደኋላ አይልም።

በህዝብ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ አልሰጥም ያለ መኮንን ከህወሃት ደህንነቶች ጋር ተዋግቶ ህይወቱ አለፈ


ኢሳት ዜና :- መቶ አለቃ ደጀን ሞቅያለው በሰላም አስከባሪነት ከተሰማራበት ሶማሊያ ወደ ወልቃይት ጠገዴ አካባቢ እንዲዛወር ከተደረገ በሁዋላ፣ በህዝብ ላይ እሱ የሚመራቸው ወታደሮች ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወስዱ ማዘዙን ተከትሎ፣ የህወሃት ደህንነቶች ሊይዙት ሲሞክሩ ተታኩሶ ህይወቱ አልፏል።
“ወታደር ድንበር ሊያሰጥብቅ እንጅ ህዝብ ሊገድል ተልእኮ አልተሰጠውም” የሚል ጠንካራ አቋም የነበረው የስማዳ ተወላጁ መቶ አለቃ ደጀን፣ በአካባቢው ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ በስሩ ያሉ ወታደሮች እርምጃ እንዲወስዱ ትእዛዝ እንዲሰጥ ቢጠየቅም፣ አላደርገውም በማለቱ በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ህይወቱ ሲያልፍ፣በህወሃት ደህንነቶች በኩልም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ደህንነቶች ተገድለዋል።
የመቶ አለቃ ደጀን ጓደኞች ወደ ቤተሰቡ በመሄድ ትናንት መርዶ መናገራቸውንም ምንጮች ገልጸዋል።
መቶ አለቃ ደጀን አገር አረጋጉ ተብሎ ሲገባ ያጋጠመው ሰላማዊ የሆነ ህዝብ መሆኑንና በዚህ ህዝብ ላይ እንዴት ልተኩስ እችላለሁ በማለት ለሚቀርባቸው ሰዎች በመደወል ጭንቀቱን ሲያጋራቸው መቆየቱን ከጓደኞቹ መካከል አንደኛው ለኢሳት ገልጿል። “ እኔ ከሞትኩ በሁዋላ ይገድላሉ እንጅ እኔ በህይወት እያለሁ አባሎቼን ህዝብ ግደሉ ብዬ አላዝዝም፣ ምታ ብለው የሚያስገድዱኝ ከሆነ ከእነሱ ጋር ገጥሜ እሞታለሁ” በማለት ለሚቀርባቸው ሰዎች ሲናገር እንደነበር እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል።
የመቶ አለቃ ደጀንን መገደል ተከትሎ በህወሃት ደጋፊ ወታደሮች እና በህዝብ ላይ አንተኩስም በሚሉት መካከል መከፋፈል መፈጠሩንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

Saturday, September 10, 2016

በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሰላማዊ ምላሽ ካላገኘ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ተባለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለአፍሪካ ህብረትና ለተለያዩ አለም አቀፍ አካላት ልዩ ትኩረት እየሆነ መምጣቱንና ተቃውሞ ሰላማዊ ምላሽ ካላገኘ በመላው ሃገሪቱ ተቃውሞ ሊቀሰቅስ እንደሚችል የቱርክ የዜና አገልግሎት አርብ ዘገበ።
መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባልተለመደ መልኩ በሃገሪቱ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ ስጋቱን እየገለጸ እንደሆነ ያወሳው አናዱሉ የዜና አውታር፣ ተቃውሞው አሁንም ድረስ እልባት አለማግኘቱን የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ አቅርቧል።
በሃገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከወራት በፊት የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ተክትሎ ኢትዮጵያን በመስቀለኛ መንገድ ውስጥ እንድትገባ ማድረጉን ለቱርኩ የዜና ወኪል በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል።
ከ500 የሚበልጡ ሰላማዊ ሰዎች በዚሁ ተቃውሞ መሞታቸውን የዘገበው የዜና አውታሩ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ውጥረቱ አሁንም ድረስ ዕልባት ሳያገኝ መቀጠሉን አመልክቷል።
የመንግስት ባለስልጣናት ህዝባዊ ተቃውሞው እልባት እንዳገኘ በተደጋጋሚ ቢገልጹም በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ጸረ-መንግስት የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መቀጠሉ ታውቋል።
በሃገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ካለው እርምጃ እንዲቆጠብ ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የቱርኩ የዜና አናዱላ በዘገባው አመልክቷል።
የአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ነው ያሉትን የሃይል እርምጃ በአስቸኳይ በማቆም ለህዝባዊ ጥያቄው ሰላማዊ ምላሽ እንዲሰጥ ማሳሰባቸው ይታወሳል።
14 አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በበኩላቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጋር ጥያቄን በማቅረብ በመንግስት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ሃሙስ ይፋዊ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል።
በተያዘው ሳምንት የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ይፈጸማል ያለውን ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማውገዝ ለሃገሪቱ የሚሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲቋረጥ ያደረገ ሲሆን፣ ከሳምንት በኋላ የተባበሩትን መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተወካዮች በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከር ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Monday, September 5, 2016

የትግራይ ክልል መንግስት የአማራ ህዝብ የዘር ማፅዳት ፈፅሞብኛል የሚል ይፋዊ መግለጫ አወጣ።


በአማራ ክልል የሚገኙ ሁሉም የትግራይ ተወላጆችንም የተከፈለው ሁሉ ተከፍሎ ከአማራ ክልል እንዲወጡ ለማድረግ እየተሰራው ነው እንደ መግለጫው።
በትግራይ ክልል መንግስ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚቴ በሰሞኑ በአማራ ክልል በተነሳው እና በርካታ (ከ200 በላይ ሰዎችን ህይወት ለጠፈበት) በባህር ዳርም ይሁን በጎንደርግጭት የትግራይ ተወላጆች ዘራቸው እንዲጠፋ በዘር ተለይተው ጥቃት ደርሶባቸዋል ነው ያለው በትግራይ online በተደረገው ምስልና ፅሁፍ መግለጫ።
ይሁና ሁላችንም እንደምናውቀው በጎንደርም ይሁን በባህርዳር እንዲሁም በመተማ ትግሬ በመሆናቸው ሳይሆን በስርዓቱ ተጠግተው መዥገር የሆኑ በዝባዥ የብአዴንም ይሁን የትግራይ አባላት ላይ ህዝቡ ድንገይ በመወርወር ስሜቱን ገልጿል። በርካታ ህይወትም ተቀጥፏል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የአማራ ክልል መንግስት ባለፈው እስካሁን በትግሬነት ብቻ ያነጣጠረ የዘር ማፅዳት(Ethnic cleanising) ቀርቶ ድብደባ እንኳን እንዳልተፈፀመባቸው የጎንደሩን ማስረጃ ማቅረቡ ይታወሳል።
እኔ በግሌ ይህ የትግራይ መንግስት አስፀያፊና የውንብድና መግለጫ ግን ከእንግዲህ የአማራን ህዝብም ለራሲ ህልውና እንዲቆም ማስጠንቀቂያ ደወል ይመስለኛል።
2.4 ሚሊዮን አማራ እንኳን ከምድረ ገፅ ሲጠፋ የወቀስን ህወሃትን እንጀ የትግራይን ህዝብ አልነበረም።ከእንግዲህ ግን እኛም ማምረር ሳይኖርብን አይቀርም።

Sunday, September 4, 2016

ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በክረምቱ መርሃ ግብር ተቀብሎ የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች የትምህርት ወቅት ከማለቁ አስቀድሞ በአሁኑ ወቅት በክልሉ የአለው ሁኔታ አስጊ ስለሆነ ሁሉም ወደየመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ መወሰኑ ታወቀ።


ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በክረምቱ መርሃ ግብር ተቀብሎ የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች የትምህርት ወቅት ከማለቁ አስቀድሞ በአሁኑ ወቅት በክልሉ የአለው ሁኔታ አስጊ ስለሆነ ሁሉም ወደየመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ መወሰኑ ታወቀ። ተማሪዎቹ ሊወስዱት የነበረው የሚድ ፈተና ወደ አሳይመንት መቀየሩን እና ከነገ ጀምሮ ግቢ እንደሚለቁ የጠቆሙት መረጃዎቼ ተማሪዎች ምንም አይነት ክሪላስ ሳይሰራላቸው ድንገት እንዲወጡ መደረጉ አግራሞትን ጭሯል።በተመሳሳይ ሁኔታ ጎንደር ዩኒቨርስቲም ይህን መሰል ውሳኔ ያሳልፋል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ይህን መሰል ውሳኔዎች የተሰባሰበውን የተማሪዎች ህብረት ተቃውሞ ከመፍራት እና የሰው ሀይሉን ለመበታተን የታለመ ሊሆን እንደሚችል ይጠቆማል።

ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ቀጥሏል በደሴ ከቤት ያለመውጣት አድማው ተጀምሯል።


በደሴ ከቤት ያለመውጣት አድማው ተጀምሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኮምቦልቻ የተቃውሞ ጥሪ መደረጉን ተከትሎ ሹመኞች በትናትናው ዕለት ነጋዴዎችን እና የመንግስት ሰራተኞችን ሰብስበው አስፈራርተዋል በዛሬው ዕለትም ከስዓታት በፊት በከንቲባው ጽ/ቤት ነጋዲዎች ከዞን እና ከወረዳ ባለስልጣነት ተሰብስበዋል። ከንቲባው ደነቀ ምትኩና ም/ከንቲባው አዲሱ ነጋዴዎችን በግልጽ አስፈራርተዋል። “ድርጅቶቻችሁን ብትዘጉ ንግድ ፈቃዳችሁን እንቀማለን፣ እርምጃ እንወስዳለን” በማለት ዝተዋል።ስብሰባዊ በዚሁ በሹመኞቹ ዛቻ ተጠናቋል። ትግሉ እስከ ነፃነት ጥግ ይቀጥላል!!!!

Saturday, September 3, 2016

አገር አቀፍ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች የሚኖሩን ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብ ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!>>ድምፃችን ይሰማ

‹‹ነቀፌታን የማይቀበል መንግስት ዘላቂነት የለውም!››
ሙስሊሙ 40 ዓመት የሞላውን የተቃውሞ መፈክር ዛሬም ዳግም ያነሣል!
አገር አቀፍ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች የሚኖሩን ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብ ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!
ቅዳሜ ነሐሴ 28/2008
ትግላችን ከአምስት ዓመታት በፊት ሲጀመር ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ይዞ የተነሳ ሲሆን ጥያቄዎቹን ለማስመለስም ሰላማዊ እና ህጋዊ መንገዶችን ተከትሎ ዘልቋል። ይህም ሆኖ መንግስት ለጥያቄዎቻችን መልስ ከመመለስ ይልቅ የሀይል እርምጃ መውሰድን እና በአምባገነንነቱ መቀጠልን መርጧል። ኢትዮጵያዊው ሙስሊም በሙስሊምነቱ ብቻ ከድብደባ እስከ ቶርቸር፣ ከእስርና ስደት እስከ ሞት፣ ከቁርአንና ሂጃብ መቃጠል እስከ መስጂድ መደፈር ድረስ ጥቃት አስተናግዷል። ዛሬ ላይ ትግላችን ማዕቀፉን በማስፋት በሶስት ጥያቄዎች ሳይገደብ ብሄራዊ ጭቆናን ለመታገል እና ሙሉ መብታችንን በዘላቂነት ለማስከበር በሚል ዓላማ ቀጥሏል።
ትግላችን የአምባገነኖችን ምርኩዝ ሰብሯል!
አምባገነኖች ህዝብን ረግጠው ለመግዛት የሚጠቀሙበት ዋነኛው መሳሪያ ፍርሀትን በህዝብ ውስጥ መልቀቅ ነው። ህዝብን ከብዙ አቅጣጫ ሊያስፈራሩት ይሞክራሉ፡፡ ሞትንና አካል የሚያጎድልን ከባድ ቅጣት በመቅጣት፣ ‹‹የውጭ ጠላት መጣላችሁ›› በማለትና ህዝቡን ከፋፍሎ እርስ በርስ እንዲፈራራ በማድረግ ህዝብን ፀጥ ለጥ አድርገው ይገዛሉ፡፡ የኢህአዴግም መንግስት ወደስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በአገራችን አስፍኖት የነበረው ይህንኑ ስልት ነበር።
መንግስት በሀምሌ 2003 ግልጽ ያወጣው ቀጥተኛ የሆነ የሀይማኖት ጣልቃ ገብነት ህዝበ ሙስሊሙ ቤት ለቤት አውርቶት ወይም በጋዜጣና መጽሄት አንብቦት የሚቀር ጉዳይ አልሆነም። ፍርሀትን ሰብሮ መውጣት እና መብትን መጠየቅ ግድ ሆኖበታል። በዚህም የአምባገነኑን ስርዓት ትልቅ ምርኩዝ ዳግም ላይጠገን መስበር ችሏል። የሙስሊሙን ጥያቄ ሙስሊም ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን በጥርጣሬና በፍርሀት እንዲያዩት፣ ብሎም የመንግስትን ፍትህ አልባ እርምጃ እንዲደግፉ የሞከረ እና ሌሎችም በርካታ የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን የሰራ ቢሆንም አንድ ጊዜ የተሰባበረ ፍርሀት ዳግም በህዝባችን ላይ ላይሰፍን ብን ብሎ ጠፍቷል። በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ተቀጣጥሎ የምናየው እና ኢትዮጵያዊያን በአምባገነናዊው ስርዓት የጭካኔ እርምጃ ሳይበገሩ፣ ለንብረታቸውና ለነፍሳቸው ሳይሳሱ እያደረጉ ያለው ተጋድሎ ለዚህ ከምንም በላይ ማስረጃ መሆን ይችላል።
መንግስት ከሁለት አስርት አመታት በላይ ለሆነ ጊዜ በአገራችን አስፍኖት የነበረው የፍርሀት ድባብ ተገፏል፡፡ አምባገነንነትን ያሰፈነው የፍርሀት መጋረጃ ተቀዷል። የአገሪቱ ሁለት ትላልቅ ብሄሮች (የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች) በተቃውሟቸው ሰፊ የአገሪቱን ክልል እያዳረሱ ነው። ከስህተቱ መማር የማያውቀው ስርዓት ግን አሁንም የህዝቦችን ጥያቄ ከመስማትና ከመመለስ ይልቅ በአረመኔያዊ እርምጃው ህዝባችንን በማሸማቀቅ ዳግም ፍርሀት ለማንገስ ሲማስን ይስተዋላል። የሙስሊሙን ህብረተሰብ የእምነት ተቋማት በመድፈር እና እሴቶቻችንን በማውደም በአምልኮ ቦታችን ውስጥ ሳይቀር በግፍ መግደሉን ቀጥሎበታል። ይህ ሁሉ ከንቱ ልፋት የህዝባችንን የመታገል አቋም ይበልጥ ቢያጠናክረው እንጂ ዳግም ፍርሀት በጫንቃችን ላይ ሰፍኖ ዘላቂ መብታችንን ለማስከበር ከምናደርገው ትግል እንድናፈገፍግ አያደርገንም።
የኢህአዴግ መንግስት የተነሳበትን የህዝብ ቁጣ ለመቀነስ፣ ብሎም አቅጣጫ ለማሳት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርጓል። ራሱ ያቀነባበራቸውን ‹‹የሽብር ስራዎች›› የሚተርኩ ዶኩመንታሪዎችን ሰርቶ በመገናኛ ብዙሃን ለቋል። ጥይት ከመተኮስ አልፎ ቦንብ እስከመወርወርም ደርሷል። ታህሳስ 01/2008 በአንዋር መስጊድ በተላላኪዎቹ የቦንብ ጥቃት እንዲሰነዘር አድርጓል። ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ በምዕራብ ሀረርጌ መሰላ ወረዳ መስጊድ ላይ ቦንብ በመጣልና የእምነት ተቋማችንንም በማቃጠል ከሀያ በላይ ሙስሊሞች ገድሏል። ይህ እርምጃ ባለፉት አምስት አመታት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የደረሰውን በደል ከፍ የሚያደርግ እና ሙስሊሙን እና እስልምናን በተመለከተ ስርዓቱ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ እና አቋም የሚያሳይ ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ በዛሬው እለት በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳ ቃጠሎ እና የተኩስ እሩምታ በርካታ ታሳሪዎች ስለመጎዳታቸው የተሰማ ቢሆንም መንግስት በጉዳዩ ላይ የተጣራ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ለማጣራት የሞከሩትን በማባረርም ከአንድ ሰው ውጭ ህይወቱ ያለፈ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ በትንሹ ከ22 ሰዎች በላይ ህይወታቸው እንዳለፈ የወጡ መረጃዎች መኖር እና የመንግስትም የማጣራት እገዳ ታክሎበት አንዳች ተንኮል መኖሩ የሚያጠራጥር አይመስልም፡፡ ዜጎች በሃሰት ክስ እስር ቤቶች ገብተውም ሰላም እንደማያገኙ እስከዛሬ የነበሩት በርካታ ክስተቶች ምስክር ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ክስተት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ማእበል አማካይነት ስርዓቱ የገባበትን ጭንቀት እና ከማይወጣበት አሮንቃ ውስጥ መዘፈቁን፣ መጨረሻውም ሩቅ አለመሆኑን የሚያመላክት ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብም ከአምስት አመታት በፊት የጀመረውን ህዝባዊ እምቢተኝነት አቀጣጥሎ ለመቀጠል እንደሚገደድ ግልጽ ነው፡፡
‹‹ነቀፌታን የማይቀበል መንገግስት ዘላቂነት የለውም!››
ዛሬ በአገራችን ሙስሊሙንም ጨምሮ የተነሳው ተቃውሞ በመሸንገያ ለውጦች የሚቆም አይሆንም። ለህዝቡ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ ጥያቄ በጥይትና በቦንብ ምላሽ ለመስጠት መሞከር ከንቱ ጥረት መሆኑን ስርዓቱ ሊረዳው በተገባ ነበር። ይህ አይነት እርምጃ ህዝብን ለበለጠ ቁርጠኝነት የሚያበቃ እና ከመታገል ውጭ አማራጭ እንደሌለው ግልጽ በማድረግ የሚያጠናክር እንጂ ከትግሉ እንዲያፈገፍግ አያደርገውም። ህዝባዊ ጥያቄ ተጨማሪ አፈና በማድረግ፣ ተጨማሪ የአፈና መዋቅር በመዘርጋት፣ ተጨማሪ ደም በማፍሰስ፣ ተጨማሪ የማስመሰል ለውጦች በማሳየት የሚቆም አይደለም። ጥቂት ግልገል ካድሬዎቹንና የበታች ባለስልጣናቱን ለእርድ በማቅረብ የሚገላገለውም አይሆንም። ከዚህ እውነታ በመነሳት ከዛሬ 40 አመታት በፊት ለአጼው ስርዓት መንኮታኮት በር ከፋች በነበረው እና ህዝበ ሙስሊሙ ባደረገው ትዕይንት ላይ ተሰምቶ የነበረውን መፈክር ዛሬም ላይ ለስርዓቱ እናስታውሳለን – ‹‹ነቀፌታን የማይቀበል መንግስት ዘላቂነት የለውም!››
አዎን! የህዝብን ድምፅ ማዳመጥ እና ለጥያቄው ፍትሃዊ መልስ መስጠት አንድን መንግስት ታማኝ እና ጠናካራ ያደርገዋል። በተቃራኒው የህዝብን ድምፅ አለመስማት ደካማ ያደርገዋል፡፡ የደካማ ስርዓት ማክተሚያ ደግሞ ሩቅ አይሆንም፡፡ ‹‹ብሶት የወለደው›› ኢህአዴግ ሌላ ብሶት የወለደውን ህዝባዊ ማእበል በዘላቂነት መቋቋም የሚችልበት ሁኔታ በፍጹም አይኖርም።
ህዝበ መስሊሙ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል!
የጀመርነው የዙልሂጃ ወር ትልቅ የአምልኮ ወር ነው። በዚህ ወር ለዲናቸው ሲሉ ራሳቸውን ለእሳት አሳልፈው የሰጡትን፣ ‹‹እኔ ፈጣሪ ነኝ›› ይል የነበረን አምባገናዊ ስርዓት ለብቻቸው ገጥመው የረቱትን፤ ልጃቸውን ለእርድ አቅርበው ለመሰዋት ቁርጠኛነታቸውን ያሳዩትን፣ በሰላታችን ሁልጊዜ በተሸሁድ እሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የምናስታውሳቸውን የነብዩላህ ኢብራሂምን ታሪክ እንዘክራለን። በዚህች አላፊ ዱኒያ ላይ ስንኖር ፊት ለፊታችን የሚደቀኑብንን እንቅፋቶች ለማለፍ የሚያስችልን ታሪካዊ ክስተት በማስታወስ ለየትኛውም ኢ-ፍትሃዊ ስርዓት በማንበገርበት ወኔ እና ጽናት ራሳችንን እናንጻለን። ለሙሉ መብታችን መከበር የምናደርገውን የትግል ቁርጠኝነት እናድሳለን፡፡ ብሄራዊ ጭቆናን በዘላቂነት ለማስወገድ የምናደርገውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን። ይህንንም በተመለከተ አገር አቀፍ የተቃውሞ መርሃ ግብሮች የሚኖሩን ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብ ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በቅርቡ በምዕራብ ሀረርጌ መሰላ ወረዳ በመስጂድ ሳሉ የስርዓቱ የሽብር ሰለባ ለሆኑ ሙስሊሞች አላህ ጀነተል ፊርደውስ እንዲወፍቅልን እየለመንን ለቤተሰቦቻቸውም ጽናቱን እንመኛለን። በዚህ ዓመት የሀጅ ስርዓት ላይ ለመሳተፍ ለበቁ ሙስሊሞችም አላህ ጉዟቸውን እንዲቀበላቸው እየተመኘን ‹‹ሀጁን መብሩር!›› እንላለን።
በሁሉም የአገራችን ማዕዘናት በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት እየተዋደቁ ላሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ለፍትህ መዋደቅ ልዩ ክብር መሆኑን በመግለጽ ዛሬ ላይ የሚፈሱ ደሞች እና የሚከሰከሱ አጥንቶች ለነገይቱ ፍትሃዊት ኢትዮጵያ በር ከፋች በመሆናቸው ለፍትህ የምናደርገው ትግል ላይ በአንድነት ጸንተን እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!
Bilderesultat for ድምፃችን ይሰማ

የቂልንጦ እስር ቤት ከሚታሰበው በላይ በመንደድ ላይ ይገኛል የከተማ ፖሊስ ህዝብ እንዳያልፍ መንገዱን አጥሯል


ቂሊንጦ እስር ቤት እየጋየ ነው
አካባቢው በጥይት እሩምታ እንደቀለጠ ነው
አካባቢው በጣም ያስፈራል አራት አምፑላስ ጉዳተኞችን ወደ ጡሩነሽ ዲባባ ቤጂንግ ሆስፒታል ወስደዋቸዋል።
እነ አቶ በቀለ ገርባ እና ብርሃኑ ተክለያሬድ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙት በዚህ እስርቤት ነው።

Friday, September 2, 2016

በአርብ ገበያ በመከላከያና በአርሶ አደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው።

በደቡብ ጎንደር ዞን፣ በደራ ወረዳ – በአርብ ገባያ በአርብ ገበያ በመከላከያና በአርሶ አደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው፡፡የግጭቱ ምክንያት ትላንት ምሽት ከእስቴ ወረዳ የተጫነ 90 ኩንታል ጤፍ ጭኖ የመጣ መኪና አርብ ገበያ ሲደርስ በህዝብ እንዲቆም ከተደረገ በኋላዳ መጣበት እንዲመለስ መደረጉ ነው፡፡
ህዝቡ ከእንግዲህ ወዲያ ጤፍም ሆነ ሌላ ማናቸውም እህል ከአካባቢያችን ወደ ሌላ ስፍራ አይንቀሳቀስም በሚል ተቃውመው መኪናውን ማስቆማቸውን ያይን ምስክሮች የገለጡ ሲሆን ከጥቂት ሰዓታት እገታ በኋላ ወደ መጣበት እስቴ ወረዳ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ረፋዱ ላይ በአርሶ አደረ እና መከላከያ አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ እንደሚገኝ ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአምባ ጊዮርጊስ በተደረገው ግጭት 18 የመከላከያ አባላትና በአርሶ አደሮች ደግሞ 30 ያህሉ መገደላቸውን ተከትሎ በዛሬው ለት የአጋዜ ታጣቂዎች በከተማው ወጣቶች ላይ መጠነ ሰፊና ዘግናኝ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከእርምጃው የተረፉ በርካታ የከተማው ወጣቶች ጫካ መመሸጋቸውም ታውቋል፡፡

አገሯን በመዉደዷ የልጅ እናት ታሰረች # ግርማ_ካሳ


አንዱዋለም አራጌ የሚባለውን ስም እናውቀዋለን ? ሃብታሙ አያሌው የሚባለውን ስም እናውቀዋለን ? ናትናዔል መኮንን፣ አንድዋለም አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺን ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ዘሪሁን ገሰሰ፣ አንጋው ተገኝ፣ አባይ ዘዉዱ መሳይ መትኩ፣ ምርቱ ጉታ የተባሉትን ስሞች እናውቃቸዋለን ? የአንድ ወንድ ልጅ እናት የሆነችዉን የጎንደር ጀግና ሴት አስቴር ስዩምን እናውቃታለን ?
እነዚህና ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ በመታቀፍ ለአገርና ለሕዝብ ሲሉ ዋጋ የከፈሉና እየከፈሉ ያሉ በየቦታው በየወህኒ ቤቶች ይገኛሉ። የአንድነት ፓርቲ በሕወሃት የፖለቲክ ዉሳኔ የምርጫ ቦርድ ሰርተፊኬቱን ቢነጠቅም፣ አባላቱና መዋቅሩ ግን አሁንም አለ። አንድነት ፓርቲ አሁንም አለ። አባላቱ አሁንም ባገኙት አጋጣሚዎች ሁሉ የሕዝብን ብሶት እያጋለጡ ይሄንን ጨካኝ አገዛዝ እየታገሉት ነው። እስር ፣ እንግልት እንደሚመጣም እያወቁ፣ ሳይፈሩ፣ ሳይሸማቀቁ ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት።
ላለፉት በርካታ አመታት እየታሰሩ፣ እየተገደሉ ለአገርና ለሕዝብ ለቆሞ ወገኖቼ አክብሮቴ በጣም በጣም ትልቅ ነው። እያወሩ ብቻ ሳይሆን እየሰሩ ትግል ምን ማለት እንደሆነ ያሳዩን የለዉጥ ሃይሎች ናቸው።
ዛሬ ደግሞ እህት ወይንሸትን ስለሺን( winahabeshawit) ወስደዋታል። ወይንሸት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና የሴቶች ጉዳይ ም/ሃላፊ ነበረች። ነፍሰ ጡር የነበረች ጊዜ ደህንነቶች ሆዷን በመርገጥ ባደረሱባት ድብደባ ለከፍተኛ ሕመም ተዳርጋ ለብዙ ጊዜ በሆስፒታል እንድትተኛ ተደርጓል። በሐኪሞች ከፍተኛ ጥረት እና በመድሃኔ ዓለም ቸርነት ሕይወቷ ተርፎ አንዲት ቆንጅዬ ሴት ልጅም በሰላም ተገላግላለ። የወይንሸት ባለቤት፣ የልጇ አባት ፣ እርሱም በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ትልቅ አስተውጾ ሲያደርግ የነበረ አንጋፋ ታጋይ ሲሆን፣ የእስር ማዘዣ እንደወጣበት ሲረጋገጥ ወደ ጎሮቤት አገር ለጊዜው ፈቀቅ ማለትን መርጦ በዚያ ትግሉን እየቀጠለ ነው። ሕጻን ልጅ እናቷን በእሥር፣ አባቷን በስደት አጣች ማለት ነው።
እነርሱ ማስፈራራት ልማዳቸው ነው። ግን ወይንሸትን አላወቋትም። አንድነትን ስትቀላቀል፣ ትግሉን ስትቀላቀል፣ ዋጋ እንደሚያስፈለግ ጠንቅቃ ታውቃለች። ከአላማዋም ከግቧም ወደ ኋላ ዝንፍ የማትል ጀግና እህታችን ናት።
ወያኔዎች እየጨለመባቸው ነው። ወይንሸትን ጨመሮ የታሰሩ እስረኞች በሙሉ በቅርብ ይፈታሉ።
ከዚህ በታች ካሉት ፎቶዎች መካከል ወይንሸት በሰላማዊ ሰልፍ፣ አዎን በባህር ዳር ከተማ፣ “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” የሚል መፈክር ይዛ፣ ተቃዉሞን ስታሰማና ሰልፈኛውን ስትመራ የሚያሳይ ሲሆን ሌላው ደግሞ በደህንነቶች ተደብድባ ሃኪም ተኝታ የሚያሳይ ነው፡፡
የሕወሃት ደህንነቶች እህቶች፣ እናቶች፣ ልጆች ላይ ሳይቀር እንደ አውሬ መጨቀኝ የለመደባቸው ናቸው። ብርቱክን ሚደቃሳ፣ ርዮት አለሙ፣ ማህሌት ፋንቱን፣ ኤዶም ካሳዬ …ይመስክሩ።