Friday, June 10, 2016

ሰበር መረጃ.. በሶማሌያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደኍላ እንዲያፈገፍጉ ትእዛዝ ተላለፈላቸው!!


በተለይ በአሚሶም ዉስጥ ሀልጋን እየተባለ በሚጠራዉ ስፍራ የኢትዮጵያ ወታደሮች የሚቆጣጠሩት ምድብ በአል ሸባብ አጥፍቶ ጠፊ ሐይሎች መመታቱን ለመበቀል የተንቀሳቀሰ የሻለቃ ምሪት ሐይል ክፉኛ መጠቃቱን ተከትሎ ከኮረኔል የማነ በተላለፈ መመሪያ መሰረት የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኍላ አፈግፈገዋል።
ድንገተኛዉን አደጋ ተንተርሶ በቦምብና በጥይት ጥቃት የፈጸመዉ አልሸባብ በሶማሌያ ሰራዊት እንዲሁም በአሚሶም ( በአፍሪካ ህብረቱ ) ጥምር ላይ ከፍተኛ አደጋ ማድረሱን ከለፈፈ ወዲህ ትንቅንቅ የገጠመዉ የኢትዮጵያ ወታደር በሶማሌያ ሴቶች ሳይቀር ከፍተኛ ጥቃት የደረሰበት ሲሆን..
በሶማሌያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ወታደር በየቀኑ እየረገፍፈ ከመሆኑ ባሻገር በዚህ ድንገተኛ ጥቃት ብቻ ከ74 በላይ ሲቆስሉ 40 በላይ መሞታቸዉንና ተከታትሎ ለማጥቃት በተደረገ ግብ ግብ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ የኢትዮጵያ ልጆች ተሰዉተዋል ቆስለዋል አሁንም እየተሰዉ እየቆሰሉ ይገኛሉ።
በዚህ ዉጊያ ላይ የሶማሌያ ሴቶች አል ሸባብን በመደገፍ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
Gudish Weyane's photo.

No comments:

Post a Comment