Saturday, July 30, 2016

ታላቅ እና ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ ስቶኮልም በሚገኝው የወያኔ ኤንባሲ ፊት ለፊት ተደርጎ ዋለ ።

በዚህ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የተለያዩ የሲፊክ ማህበራት እና የፓለቲካ ድርጅቶች የተገኙ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የህዝቦችን የሰብአዊ መብት ጥሰትን እና የወያኔ ሰራዊት ሰላማዊ ዜጎችን መጨፍጨፉን እንዲያቆም ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በወልቃይት ህዝቦች ላይ በሀይል የተጣለባቸው የትግሬነት ድርጊት እንዲቆም በኦሮሚያና በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ላይ የሉ የህዝብ ጥያቄዎች ባስቸኳይ እንዲመለሱ እና የህዝቦች በሰላም የመኖር ነፃነት እዲከበር በተጨማሪም በነፃነት ታጋዩ በሀብታሙ አያሌው ስቃይ እያበዙበት ያሉ ዳኞች ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እና ወጣቱም ባስቸኳይ የሀኪሞች ቦርድ የሰጠው ወደውጪ ወጥቶ የመታከም መብቱ እንዲከበር እና ከህመሙ እዲያርፍ በመጠየቅና እልህ የተቀላቀለበት ንግግሮችን በማድረግ በቀጣይ ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ተወያይቷል ተጠናቋል።






No comments:

Post a Comment