ምንም መፍትሔ የሌለው ቢሆንም የህዝቡ ብሶት ያለምንም ፍርሃት የተንፃበረቀበት እና ግልፅ አቋም የተቀመጠበት ስብሰባ ነበር፡፡ የድንበሩ ጉዳይ ያው ተከዜ መሆኑን ህዝቡ በጋለ ስሜት ነበር አስረግጦ የተናገረው፡፡ የታሰሩ እና ታፍነው የተወሰዱ ኮሚቴዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ተጠይቋል፡፡ ኢቲቪ፡ ፋና እና ጌታቸው ረዳ ግልፅ ይቅርታ እንዲጠይቁ ተጠይቀዋል። ከበረከትም ሆነ ከገዱ የተለየ ነገር አልተደመጠም፡፡ …. መቋጫ ሊያበጁ አልነበረም የመጡት፡፡ ገዱ “እናንተን ልንሰማ ነው የመጣነው” ቢልም የህዝቡ ስሜት ግን ከአቅማቸው በላይ ነበር የሆነው። በዛ መሃል ሰው ካነሳው ሀሳብ ውጭ በረከት ስለ መልካም አስተዳደር ጉድለት ዲስኩሩን ሲያሰማ በስብሰባው በተገኘው ህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ አስተናግዷል። በረከት ሰለ ወልቃይት ጉዳይ ምንም አለመናገሩ እና ነገሮችን አድበስብሶ ማለፉ በብዙዎች ላይ ቅሬታ አሳድሯል። ይህም ባብዛኛው ተሰብሳቢ ላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ እና መልሱ አፈሙዝ ብቻ እንደሆነ ግንዛቤ የተወሰደበት ነበር፡፡ የሚገርመው የህዝቡ አስተያየት በራሳቸው ሰው ሲቀረፅ እነሱ የሚመልሱት መልስ ግን እንዲቀረፅ ፈቃደኛ አልነበሩም። በተለይ በረከት፡፡ በሞባይልም መቅረፅ አይቻልም ነበር፡፡
አጠቃላይ ስለቀረቡት ጥያቄዎች ዝርዘር ይዘን እንመለሳለን፡፡
No comments:
Post a Comment