Saturday, July 16, 2016

አንጻራዊ መረጋጋት አግኝታ በነበረው ጎንደር እንደገና ተቃዉሞ አገረሸ


አጋዚዎች ህዝቡን ለመጨፍቸፍ እየተዘጋጁ ነው –
የጎንደር ሕዝብ ኮሎኔል ደመቀን አትወስዱም ብሎ እየዛተ ነው –
በክልሉ የጸጥታ ሃይሎችና በሕዝቡ (በነ ኮሎኔል ደመቀ) መካከል ድርድር ተደረጎ ነበር። በድርድሩ ህወሃቶች የታፈኑ የወልቃይት ሌሎች የኮሚቴ አባላትን እንዲፈቱና ኮሎኔል ደመቀም በክልሉ የፖሊስ መመሪያ እንዲቆዩ ነበር። በዚህም መክንያት ላለፉት ሁለት ቀናት በጎንደር አንጻራዊ መረጋጋት ተከስቶ ነበር።
ሆኖም ጸረ-ሰላም እና ጸረ-መረጋጋት ስለሆነ፣ የክልሉ የጸጥታይ ሃይል ነገሮችን በሰላም ተቆጣጥሮ ባለበት ሁኔታ ፣ ከትግራይ በአይሮፕላን ወደ ባህር ዳር በርካታ አጋዚዎች በማስገባት፣ ከዚያም በሌሊት ወደ ጎንደር በመግባት የሕዝቡን ጥያቄ በኃይልና በጭካኔ ለመጨፍለቅ እየተዘጋጁ ነው።
በትላንታንው እለት ሰላማዊ የሆኑትና እና ነገሮች ወደ አላስፈላጊ ደረጃ እንዳይደርስ ፍላጎት የነበራቸው ኮሎኔል ደመቀ፣ ለድርድር ሲሉ ራሳቸው በፍቃዳቸው ለክልሉ ሃላፊዎች ቢሰጡም፣ ወያኔዎች ግን በአማራዉ ክልል አይቆይም ይዘን መሄድ አለብን የሚል ግትር አቋም በመያዛቸው ፣ ድርድር ፈርሷል። ይሄንን በተመለከተ ለሕዝብ በጽሁፍ የገለጹት ኮሎኔል ደመቀ” ድርድሩ ፈርሷል፤ ኑ ና ከተከበብኩበት ነጻ አውጡኝ!” የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል። ኮሎኔል ደመቀ ባስተላለፉት ጽሁፍ ጽሁፍ ለጎንደር፣ ለትክልድንጋይ፣ ለአርማጭሆ፣ ለቋራ፣ለሶሮቃና ለበርካታ ወረዳ ነዋሪዎች ነው ጥሪ ያቀረቡት።
የሕወሃቱ ጌታቸው ረዳ ና የወያኔ ሜዲያ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን እንደ ሽፍቶችና የሻ’እቢያ ተላላኪዎች አደረጎ በማቅርብ፣ በጎንደር ሙሉ ለሙሉ መረጋጋት እንዳለ፣ ወንጀሎችም እንደታያዙ በመግልጽ የዉሸት ዘገባዎች ለሕዝብ ቢያስተላለፉ፣ በዛሬ እለት ግን እንደገና ህዝባዊ ተቃዉሞ ተቀስቅሷል። ተኩሶችም እየተሰሙ ነው። አጋዚዎች በጎንደሬው ላይ፣ በቂም በቀልና በጣላቻ፣ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸምም የቆረጡ ይመስላል።
ከዚህ በታች የምታዩት ዛረ በጎንደር ከተማ የተነሳ ሲሆን ደብዳቤው ደግሞ ኮሎኔል ደምቀ የጻፉት ደብዳቤ ነው።

No comments:

Post a Comment