Tuesday, July 26, 2016

ፍ/ቤቱ ያለ ይግባኝ የራሱን ትእዛዝ ራሱ ሻረ፤


ፍ/ቤቱ ለቃል ክርክር የተባለውን በመሻር የጽሁፍ ይሁንልኝ አለ፡፡ black & white በ15/11/2008 በዋለው ችሎት የተሰጠው ትዕዛዝ፣ ዐ/ህግ <ለቃል ክርክር ተዘጋጅቶ ይቅረብ> የሚል ነበር፡፡ ይህንን ትዕዛዝ እኔ ራሴ በዓይኔ በብረቱ አንብብያለሁ፡፡
በሀብታሙ አያለው ጉዳይ ፍ/ቤቱ ሌላ ትእዛዝ መሰጠቱ ምንም አልገረመኝም፡፡ ኢ-ፍትሀዊነቱ ትላንትም የነበረ፣ ነገም የሚኖር፣ ዛሬም የምናየውም ነውና …ይህ ሥርዓቱ እስካለ ድረስ የሚቀጥል ነውና፡፡
በሀብታሙ ጤና ሰነድ ላይ የዐ/ህግ ክርክር ያስፈልጋል/አያስፈልግም የምለውን ለጊዜው እንተውውና በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ዐ/ህግም የደረሰኝ ትእዛዝ ለቃል ክርክር ነው በማለት ገልፆ ነበር፡፡ ጠበቃ አመሃ መኮንንም ይህንን ነበር በአጽንኦት የተናገረው፡፡ ፍ/ቤቱ ግን መስሚያ አልነበረውም፡፡ ዐ/ህግ ለቃል ክርክር ተዘጋጅችያለሁ እያለ ሌላ ቀጠሮ መሰጠቱን ያልተቀበለው የህግ ምሁሩ አቶ አመሃ በበኩላቸው እሺ! ይህ ህመምተኛ በሞትና በሕይወት መካከል ያለ ስለሆነ ለአዳሪ ይሁን ብሎ ተማጸናቸው፡፡ ነገር ግ በቅርቡ ከቀኝ ወደ መሀል (ሰብሳቢ) ዳኝነት የመጡ ዳኛ ከድር አልይ ጆሮ ዳባ አሉን፡፡ በቃ ጨረሰን! አሉን፡፡ እኛም እልሃቸውን እናስጨርሳቸዋለን ብለን ወሰነን፡፡
ቀጣዩ ለሐምሌ 22, 2008 ዓም ተቀጠረ፡፡
(ዳንኤል ሽበሽ)

No comments:

Post a Comment