ይህንን የተናገሩት የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የአሁኑ እስረኛ ኢሁድ ኦልመርት ናቸው። ኢሁድ ኦልመርት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት የኢየሩሳሌም ከንቲባ በነበሩበት ወቅት በኢየሩሳሌም ሪል ስቴት በመገንባት ከሚታወቁ ባለሐብቶች ስጦታ ተሰጥቷቸዋል ተብለው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን በእለቱም እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል “አዎ በሪል ስቴቱ ምረቃ ላይ እንኳን ደስ አለህ ተብዬ ስጦታ ተሰጥቶኛል ስጦታው የአመራር ሂደቴን ባይቀይረውም መቀበሌ ስህተት ነበር በጠቅላይ ሚኒስተርነቴ ወቅት ለሀገሬ የተቻለኝን መስራቴን ህዝቡ ያውቃል በዚህ እኮራለሁ ጠቅላይ ሚኒስትሯን ፍርድ ቤት አቁማ ወንጀሉን መርምራ የምታስር ሀገር ዜጋ እና ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኔ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል ማንም ከህግ በላይ አይደለም የተፈረደብኝን ፍርድ በሙሉ እቀበላለሁ”
ኢሁድ ኦልመርት በፍርድ ቤቱ የ19 ወራት እስር ተፈርዶባቸው ከየካቲት ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን በእስር ቤት ቆይታቸውም በእስር ላይ የሚገኙ የህግ ታራሚዎችን እያስተማሩ ይገኛሉ። ሀሊም ግሊክ የተሰኙት የማረሚያ ቤት ኃላፊ ስለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የእስር ቤት አያያዝ ተጠይቀው ሲናገሩ “በጥሩ ሁኔታ ይዘነዋል ነገር ግን ከሌሎች ታራሚዎች የተለየ እንክብካቤ አይደረግለትም በእስር ቤት ሁሉም እኩል ነው” ብለዋል። የኛስ ሀገር ፍርድ ቤት የት ነው?

No comments:
Post a Comment