Saturday, May 14, 2016

በዲላ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መንገድ ዘግተው ፈተሻ ሲያደርጉ ዋሉ


ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት፣ የመከላከያ ስራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገዶችን ዘግተው ፍተሻ ሲያደርጉ እንዲሁም በመኪና ላይ ሆነው ቅኝት በማድረግና የሚጠርጥሩዋቸውን ወጣቶችም ይዘው ሲጠይቁ መዋላቸውን ተናግረዋል። ወታደራዊ ፍተሻውና ቅኝቱ፣ በመንግስት ታጣቂዎችና በአርበኞች ግንቦት 7 መካከል በአርባምንጭ አካባቢ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ የተካሄድ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ፍተሻውን እና ጥበቃውን በተመለከተ በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
Haregeweyn Abeje Iwnetu's photo.

No comments:

Post a Comment