ከቀናት በፊት በወንበራ ወረዳ ቦጎንዲ ተብሎ ከሚጠራው ከፍተኛ ስፍራ የተተከለው የመረጃ መሰብሰቢያ ቋት (ራዳር) በወያኔ አገዛዝ የተማረረ ወታደር ጉዳት ካደረሰበትና አንድ ፖሊስ ከገደለ ወዲህ ራዳሩን ሲጠብቁ በነበሩት የህዳሴ ዲቪዥን የፈጥኖ ደራሽ የፌድራል አባላት እርስ በርስ አለመተማመን የነበረ ሲሆን ከበላይ አዛዦች በተላለፈ መመሪያ መሰረት ገዳዩ ፖሊስ በከፍተኛ ስቃይ ሲመረመር ቆይቶ የተረሸነ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 11 የፌድራል አባላት እንዲታሰሩ ና ራዳሩን የሚጠብቀው ሃይል በአስቸኳይ እንዲቀየር ተደርጓል።በዚህ ወቅት ከፖዊ በግልገል በለስ አድርጎ ድባጢ ወረዳ አቋርጦ በቡለን ወረዳ ወደ ወንበራ ያቀነው የወታደር ሃይል ገሰንገሳ ከሚባለው ሰማይ ጠቀስ ተራራ ላይ በተከፈተበት ጥቃት 4 ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል። በዚህ እጂግ ከፍተኛ ቅዝቃዜ በሚስተናገድበት ስፍራ የተሰገሰጉ የነፃነት ሃይሎች አሉ በሚል ከሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አዲስ ተዋጊ ሃይል የተላከ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት 14 የቡድኑ አባላት ባደሩበት ተገለው ተገኝተዋል። የተገደሉት የህወሓት ወታደሮች በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ ቅዝቃዜ መቋቋም ካለመቻላቸው በላይ የአካባቢው መልከዓምድር እጂግ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ሪፖርት ሲያደርጉ መቆየታቸው ታውቋል። 5ቱ ወታደሮች በሳንጃ ተወግተው የተገደሉ ሲሆን 9ኙ ግን የተመታ አካል እንደሌላቸው ተረጋግጧል። ከአሳሽ ቡድኑ ውስጥ 2 ወታደሮች ያሉበት አለመታወቁም የሁኔታው አደገኝነት በግልፅ እንደሚያሳይ ለመረጃው ቅርብ የሆኑ ሰወች ይናገራሉ።

No comments:
Post a Comment