Monday, March 27, 2017

በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በብዛት አየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጫችን ገልፆ


ጎንደር የወያኔ ስርዓትን ጭንቅ ውስጥ እንደከተተችና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሰሜን ጎንደር በጠላት እጅ መውደቋን አመራሩን ዋና የችግሩ መንስኤ አድርጎ የቆጠረ ስብስባ በጎንደር ከተማ እየተደረገ እንዳለና የህውኃት ከፍተኛ መኮንኖች ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ አስተማማኝ መረጃዎች አሰታወቁ፡፡
በስብሰባው ሳሞራ የኑስን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ መኮንንኖች የተገኙበት ነው ተብሏል፡፡ ከተማዋም ከፍተኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በብዛት አየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጫችን ገልፆልናል፡፡
**
በሚያዚያ 21-28/2009 ዓ/ም በጎንደር ከተማ የሚከበረው የከተሞች ፎረም ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን በአሉንም አናከብርም የሚል ይዘት ያለው ፁሁፍ ወረቀት እንደተበተነ የተበተነውን ወረቀት ያዪ የአየን እማኞች ገልፀውልናል።
ለመሆኑ የከተሞች ፎረምና በዐል እነ መቀሌ ያክብሩት እንጂ ለ26 አመት ሆነ ተብሎ እንዳታድግ ለተደረገችው ጎንደር ከተማ ምኗ ነው፡፡ ጎንደር ላይ ባለፉት አመታት ምንስ ሰራን ብለው ሊያስጎበኙ ይሆን ለሚመጡት እንግዶች ነው ወይስ በዐሉ ጎንደርን ላለፉት 26 አመት እንዴት እንደገደሏት በተግባር ልምድ መቅሰሚያ ከተማ መሆኗን ሊያሳዯት፡፡ የወያኔ የለበጣ ስላቅ አያልቅም መቸም!

Wednesday, March 22, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ – “ይህ የፍፃሜው ጅማሮ ነው”


አርበኞች ግንቦት 7 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ – “ይህ የፍፃሜው ጅማሮ ነው”
መጋቢት 12 ቀን 2009 ዓ. ም. (March 21, 2017)
ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሠራዊት አባላት በሰሜንና ደቡብ ጎንደር በህወሓት/ኢህአዴግ የአገዛዝ ሥርዓት ተቋማት ላይ የተቀናጀ የሽምቅ ጥቃት አድርሰዋል። በማክሰኝት፣ በደጎማ፣ በጯሂት፣ በደንቀዝን፣ በበለሳ፣ በአዲስ ወረዳ፣ በደንቢያ፣ አገዛዙ ቀይ ቀጠና ብሎ በሰየመው በመተማ መስመር በጭልጋ ወረዳ፤ በቆላድባ፣ አብራጂራ፣ በቸንከር ቀበሌ በአገዛዙ የፓሊስ ጣቢያዎችና የጦር ሠራዊት ካምፓች እንዲሁም ቀንደኛ የሥርዓቱ አገልጋዮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝሯል፤ በሕዝብ ላይ በደል ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩ የሥርዓቱ ቀንደኛ አራማጆች ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል። ስለእነዚህ እርምጃዎች በወቅቱ መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት ስለሆነ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያሻም።
ይህ የፍፃሜው ጅማሮ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ህወሓት/ኢህአዴግን በማስወገድ ሕዝብ የፓለቲካ ስልጣን ባለቤት ለማድረግ በሚደረግ ትግል ውስጥ ራሱን ለመስዋዕትነት በግንባር ቀደምትነት አሰልፏል፤ የትግሉ ባለቤት ግን ሕዝቡ ራሱ ነው።
እስካሁን በጎንደር በተደረጉ ትግሎች የታየው የሕዝብ ንቁ ተሳትፎ አበረታች ነው። የጎንደር ሕዝብ ከአብራኩ የወጡትን የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን በመረጃ፣ በስንቅና በቀጥታ በውጊያ በመሳተፍ ረድቷል። ሲራቡ እያበላ፣ ሲቆስሉ እያስታመመ፣ መንገድ እየመራ ግዳጆቻቸውን በስኬት እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል። በተለይ እሁድ መጋቢት 03 ቀን በጎንደር አጼ ፋሲለደስ ስታዲዮም የተገኘው ሕዝብ የአገዛዙን ዛቻ ሳይፈራ ለታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ የህሊና ፀሎት ማድረጉ ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኗል። ሰሞኑን እየተወሰዱ ያሉትን ዓይነት የሕዝባዊ አመጽ እርምጃዎች ከጎንደር በተጨማሪ ወደ ሌሎችም የአገሪቱ ግዛቶች እንዲስፋፋ ማድረግ ይገባል።
የአገዛዙ ሠራዊት በርካታ አባላትም ታጋዮችን እያዩ እንዳላዩ በማሳለፍ፤ ጥይት አየር ላይ በመተኮስ እና የይስሙላ አሰሳዎችን በማድረግ አባል በሆኑበት ፋሽስታዊ ሠራዊት ላይ ሕዝባዊ የሆነ አሻጥር በመፈፀም ተባብረዋል። ከፊሎች ደግሞ ከዚህም በላይ በመሄድ መረጃ በማቀበል በውስጥ አርበኝነት አገልግለዋል፤ እያገለገሉም ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ለእነዚህ የሠራዊቱ አባላት ያለውን አድናቆትና ክብር ይገልፃል። ለወደፊቱ ከዚህ በላይ የሆነ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል። ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችን ናት፤ የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ስም ይዞ ለህወሓት/ኢሕአዴግ ጥቅምና ሥልጣን መቆሙ ማብቃት አለበት። በአገዛዙ የጦር ሠራዊት ውስጥ ያለውን የሀሳብ ልዩነት አርበኞች ግንቦት 7 በቅርበት ይከታተላል። “እኛ ሠራዊቱን የተቀላቀልነው ወራሪ ጠላትን ለመከላከል እንጂ መብቶቻቸውን የጠየቁ ዜጎችን ለመፍጀት አይደለም” በማለት የሚከራከሩ የሠራዊቱ አባላት እንዳሉ ንቅናቄዓችን ያውቃል። እነዚህ የሠራዊቱ ወገኖች አብዛኛውን ሠራዊት ለማሳመን እንዲጥሩ ያ ካልሆነም ሠራዊቱን ጥለው በመውጣት ንቅናቄዓችንን እንዲቀላቀሉ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
የህወሓት ተቀጥያ እና ግንባር ቀደም አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥም የሕዝብ እሮሮና እንባ እረፍት የሚነሳቸው ወገኖች እንዳሉ ይታወቃል። እነዚህ ወገኖች የህወሓት ሎሌዎች በሆኑ የብአዴን አባላት እየተመነጠሩ ከሥልጣንና ከሥራ እንደሚባረሩ፣ እንደሚታሰሩና እንደሚሰደዱ እያየን ነው። ልቦና ያላቸው የብአዴን አባላት ከሕዝብ ጎን ለመሰለፍ ከአሁን የተመቸ ጊዜ ላያገኙ ይችላሉ፤ ስለሆነም ዛሬውኑ ጎራቸውን እንዲለዩ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደረጋል።
በህወሓት የአገዛዝ ዘመን በአማራ ሕዝብ ላይ የደረሰው በደል ዘርፈ ብዙ ነው። መሬቱ ተዘርፏል፤ ማንነቱ ተደፍሯል፤ በገዛ አገሩ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ዜጋ እንዲሆን ክብሩ ተዋርዷል። አማራን እርስ በርሱ በማጣላት እንዲዳከም ብዙ ተዶልቷል፤ እየተዶለተም ነው። በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የዚህ ሁሉ በደል ማብቂያ ቁልፍ መፍትሄ ህወሓትን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ስልጣን ማስወገድ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ በስልጣን ወንበር ላይ እስካለ ድረስ ማናቸውም ዓይነት መብቶች አይከበሩም። በህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የስብዕናና የዜግነት መብትን መጠየቅ በሽብርተኝነት የሚያስከስስ ወንጀል ነው። በህወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ሥር ሆነን መብትን ለማስከበር የምናደርገው ትግል የትም አያደርሰንም፤ ያለን መፍትሄ አገዛዙን ማስወገድ ነው። በዚህም ምክንያት መብቶቻችንን ለማስከበር ተገደን ወደ ጦርነት ገብተናል። ድል እስከምናደርግ ድረስ የሚቆም አይደለም። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ የማውጣት ኃላፊነት የወደቀው በአማራ ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊያን ሁሉ ላይ ነው። ስለሆነም አገዛዙን ለማስወገድ የሚደረገው ተጋድሎ ከአማራ ውጭ ወደሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች እንዲስፋፋ አርበኞች ግንቦት 7 ጠንክሮ ይሠራል። መላዋ ኢትዮጵያ ነፃ ካልወጣች አንድ አካባቢ ብቻ ተለይቶ ነፃ ሊወጣ አይችልም።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በታጋይ ወላጆች፣ አያቶች፣ አጎቶች፣ ባለቤቶችና ሕፃናት ልጆች ላይ ፋሺስታዊ ጥቃት ማድረስ እየበረከተ መጥቷል። የበርካታ ታጋዮች ሕፃናት ልጆች ተደብደበዋል፣ ታስረዋል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶቻቸው ተግዘዋል። በአርበኛ ታጋይ ቤተሰቦች ላይ የበቀል እርምጃ በሚወስዱ የሥርዓቱ አገልጋዮች ላይ ምህረት የለሽ አፀፋ የሚሰጥ መሆኑን በደል ፈፃሚዎች እንዲገነዘቡ አርበኞች ግንቦት 7 በጥብቅ ያሳስባል። አርበኞች ግንቦት 7 እንዲህ ዓይነት እጅግ ኃላቀር የሆነ የበቀል ሥርዓት ፈፃሚዎችን ከመቅጣት እንደማይመለስ እንዲያውቁት በአጽንዖት ያስገነዝባል።
ባለፉት ዓመታት ሞቅ ደመቅ ሲል የቆየው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በተደራጀና በተጠናከረ መንገድ እንደገና እንዲቀሰቀስ የማደራጀት፣ የማስተባበርና በግንባር ቀደም የመምራት ተግባር እንዲያከናውኑ አርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎቹን ያሳስባል። ከእንግዲህ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ተደጋግፈው እንዲሄዱ ይደረጋል።
ዛሬ እያንዳንንዱ ኢትዮጵያዊ ጎራውን እንዲለይ የሚጠየቅበት ወቅት ላይ ተደርሷል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውሳኔውን ራሱ መስጠት አለበት። ምርጫው ሁለት ነው። አንደኛው አማራጭ ከበዳዮች፣ ዘራፊዎች፣ ገዳዮች ከሆኑት ህወሓት እና እሱ የፈጠራቸው ድርጅቶች ጎን መቆም ነው። ሁለተኛው አማራጭ ሕዝብን ለስልጣን ባለቤትነት ለማብቃት መስዋትነት እየከፈሉ ካሉት አርበኞች ግንቦት 7 እና አጋሮቹ ጎን መቆም ነው። ሦስተኛ አማራጭ የለም።
በዚህም ምክንያት በግል ተነሳሽነት ጭምር የተሰባሰባችሁ ወገኖች በድርጅት በመታቀፍ ውጤት ለሚያመጣ የጋራ ትግል ኃይላችሁን አስተባብሩ። የተናጠል ትግል እምንመኘው ግብ እንደማያደርሰን ተገንዝበናል። ስለሆነም መተባበር ብቻ ሳይሆን በድርጅት ታቅፎ መታገልን ባህል እናድርገው። በጋራ ትግል አምባገነኑን የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝን አስወግደን የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት እናድርግ።
አንድነት ኃይል ነው !!!

Tuesday, March 21, 2017

ከደህንነት ሚንስትር አፈትልኮ የወጣ መረጃ


የህዝብን ትኩረት ለመሳብ ወይንም ለማስቀየር በባለሥልጣኖች ላይ ትችት ማቅረብ በተለይ በውጩ አለም ያሉትን የተቃወሚ ኋይሎችን በሚያወጧቸው መረጃዎች ላይ ጥልቅ ጥናት ተካሂዶበታል።የነአባይ ጻሃየ ካብኒና በአባይ ወልዱ የሚመራው የተለያዩ አስተያየት ሰንዝረዋል፡አባይ ጻሃየ
የህወሃት ባለሥልጣናት በተለያዩ ሚዲያዎች አስመሳይ ነገሮችን ለህዝብ ተስፋ ሰጭ መርህዎችን በመስጥት የመጣብን ጫና በንደዚህ አይነት ካልሆነ ልንቋቋመው አንችልም ፡በማለት ተናግሯል።አንዱ ወገን ያቀረበ ሲሆን በሊላኛው አባይ ወልዱ ጠቅላይ ሚንስትሩን ኋይለማሪያም ደሳልኝ ለምን ከስልጣን አናወርዳቸውም፡በምትኩ ቴዎድሮስ አድኖምን ማሰቀመጥ አለብን መለስ ዜናዊ ይሂን ቦታ መያዝ ያለበት ደኩትሩ ነው ብሎ ነበር ።በማለት ሲናገር ፡ሊሎች በፈንታቸው አንድኛ ለአለም ጤና(WHO)ቦታ ከተሰጠው ለእኛ ትልቅ ድጋፍ አለን ። ይሂማ ካደርግን በውጩ አለም የድፕሎማሲያችን መርህ ይበላሻል፡በባለፈው ከአሜሪካ በኩል የአንድ ብሔር ስብስብ ነው ተብለን ተፈርጀናል ስለዚህ ሊላ እናስቀምጥ ብንል ከሊላ ብሔር እንደ ደሣለኝ ኋይለማሪያም ታዛዥ ለሥራቱ ታማኝ አይገኝም በዛው መቀጠል አለበት ብለዋል ።ይልቁንስ ይህ ሥልጣን ከእጃችን እንዳይወጣ ማድረግ ያለብን ከፍተኛ በጅት መድበን የአርበኞች ግንቦት ሰባትን መዋቅር ለማዳከም መስራት አለብን ሊላውን እንተወው ኋይል ያለውና ተፅኖ ፈጣሪው ይህ ድርጅት ነው ትኩርውታችን ውደ ዚህ መስራት አለብን በማለት ስብስባውን ባጭሩ ቋጽተውታል።
ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ።
ሞት ለባንዳ ወያኔ
ይሂን ሚስጥር ላካፈሉና ለተባበሩኝ ውድ ታጋዮች
ለውስጥ አርበኛ ታጋዮች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ
ካርበኞች መንደር አሞራው ምንአለ ባሻ

የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትላቸው ከሃገር ኮበለሉ

የበርካታ ሚሊዮን ብር ብክነት ሪፖርት የቀረበባቸው የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከሃገር መኮብለላቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ሁለቱ ባለስልጣናት ከሃገር የኮበለሉት ስራቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ መሆኑንም መረዳት ተችሏል።
ባሳለፍነው ታህሳስ ወር የ16 ሚሊዮን 863 ሺ 33 ብር ከደምብ ውጭ ህገወጥ የመድሃኒት ግዢ ፈጽመዋል በሚል በፓርላማ ሪፖርት የቀረበባቸው ዋናው ዳይሬክተር አቶ መስቀሌ ሌራ እና ምክትላቸው ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ በቦሌ በኩል በህጋዊ መንገድ ከሃገር መውጣታቸው ታውቋል።
በአለም አቀፍ ድርጅቶችና የውጭ መንግስታት ድጋፍ የሚደረግለት የኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ከተመሰረተ እኤአ ከ2007 ጀምሮ ከፍተኛ ምዝበራ ሲካሄድበት መቆየቱም ተመልክቷል። በታህሳስ ወር 2009 ለፓርላማ በቀረበ በጠቅላይ ኦዲተር ሪፖርት በህገወጥ አሰራር ወደ 17 ሚሊዮን ብር በማውጣት የተወነጀሉት ሁለቱ የስራ ሃላፊዎች፣ ለጤና ተቋማት መሰራጨት የነበረባቸው የ569 ሚሊዮን 833ሺ 919 ብር ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎች ሳይሰራጩ በመገኘታቸውም ተጠያቂ መሆናቸውን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ከለጋሾች የተገኘ ወደ መቶ ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ብር በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማባከን ስማቸው የተነሳው የኤጀንሲው ሃላፊዎች ወዲያውኑ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁ ቢሆንም፣ ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ ሃገር ጥለው መጥፋታቸው ተመልክቷል።
ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መስቀሌ ሌራ እና ምክትላቸው ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ ከሃገር ህጋዊ በሆነ መንገድ የወጡት ተባባሪዎቻቸው በሆኑት የመንግስት ባለስልጣናት ድጋፍ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ብክነት የዳረጉት የልማት ባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ ባህረም በተመሳሳይ ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ በህጋዊ መንገድ ከሃገር መውጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
99994-430426_159963350831423_915461233_n

Friday, March 17, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ ስፍራዎች ማክሰኞ ምሽት ጥቃት ፈጸሙ


ከአይን ምስክሮችና ከንቅናቄው ምንጮች ለመረዳት እንደተቻለው በጭልጋ፣ ደንቢያና በጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በተመሳሳይ ቀንና በተቀራራቢ ሰዓት በመንግስት ሃይሎችና ተቋማት ላይ ጥቃት ተፈጽሟል።
በትግል ላይ እያሉ መስዋዕትነት በከፈሉት ሻለቃ መሳፍን ጥጋቡ ወይንም ገብርዬ እንዲሁም በታጋይ ጎቤ መልኬ እና በአበራ ጎባው ስም የተሰየሙት ወታደራዊ ዘመቻዎች፣ ማክሰኞ መጋቢት 5 ፥ 2009 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን መግደልና መቁሰል ጭምር ማስከተላቸውንም ለመረዳት ተችሏል።
ዘመቻ “ዋዋ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚሁ ጥቃት ከጎንደር 80 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ በሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በተሰነዘረ ድንገተኛ ጥቃት 3 ወታደሮች ሲገደሉ፣ 15 መቁሰላቸው ተመልክቷል። በአምስቱ ላይ የደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ጎንደር ሬፈራል ሆስፒታል ሲወስዱ፣ ቀላል ጉዳት የደርሰባቸው 7 ወታደሮች በመተማ ገንዳ ውሃ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን የተገኘው ዜና ያስረዳል።
በቅርቡ በትግል ሜዳ ላይ እያሉ የተሰውትን ጎቤ መልኬን ለማስታወስም በስማቸው መጠሪያ “ዋዋ” የተሰየመው ዘመቻ ተሳታፊ የሆኑት የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊዎች ጥቃቱን ፈጽመው ወደ ነበሩበት መመለሳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በመከላከያ ሰራዊት በኩል በቡድን መሳሪያ የተደገፈ የአጻፋ ምላሽ መሰጠቱም ተመልክቷል። በመትረየና ላውንቸር የተደገፈውን የአጸፋ ምላሽ ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱንና የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡም ተመልክቷል።
በዚሁ በጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ በተመሳሳይ ቀን ዘመቻ ገብርዬ በሚል በተሰየመው ወታደራዊ ዘመቻ በቆላ ድባ ከተማ በሚገኝ የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በተከፈተ ዘመቻ የአስተዳደር ጽ/ቤቱ በከፊል ሲወድም፣ የአስተዳዳሪው መኪና መቃጠሉንም የመጣው ዜና ያስረዳል። በተመሳሳይ ጯሂት ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በካምፕነት በሚጠቀሙበት ቁጥር 2 በተባለው ጽ/ቤት ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በወታደሮቹ ላይ የቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአብራጅራ ከተማ አብራጅ ጽ/ቤት በሰፈሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ እንዲሁም በቸንከር ቀበሌ የከተማዋ ኮማንድ ፖስት ማዘዣ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። በጥቃቱ የቸንከር ቀበሌ ኮማንድ ፖስት ማዘዣ ጣቢያ ሲወድም፣ አንድ የኮማንድ ፖስቱ አባል መጎዳቱንና አንድ መጋዘን መቃጠሉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች መሳሪያ አንስተው በትግል ላይ ከነበሩት አንዱ በነበረውና መስዋዕትነት በከፈለው በአበራ ጎባው ስም በተመሳሳይ ቀን በጎንደር ዙሪያ የአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎች ጥቃት መፈጸማቸውም ተመልክቷል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊዎች ማክሰኞ መጋቢት 5 ፥ 2009 እኩለ ሌሊት አካባቢ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በደጋማ ከተማ በወህኒ ቤት እንዲሁም ኮማንድ ፖስቱ በሚጠቀምባቸው ቢሮዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል። እንዲሁም የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል በሆኑት በአቶ ደሴ ዘገየ መኖሪያ ቤት ላይም ተመሳሳይ ጥቃት መከተሉንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከኢሕአዴግ ጋር በጋራ ለመደራደር ያደረጉት የመጀመሪያ ጥረት አልተሳካም


ሃያ አንድ አገር አቀፍ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከኢሕአዴግ ጋር በተናጠል ወይም በጋራ ለመደራደር ለመወሰን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ያደረጉት ስብሰባ ባለመሳካቱ፣ በተናጠል ውይይት የሚያደርጉት ዕድል እየሰፋ መምጣቱ ተጠቆመ፡፡
ዋናው ድርድር ከመጀመሩ በፊት ድርድሩ የሚመራባቸው ዝርዝር የሥነ ሥርዓት ደንብ ላይ ውይይት እያካሄዱ ያሉት 21 አገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ በዚሁ ጉዳይ ላይ አምስት ዙር ውይይት አድርገዋል፡፡ በመጪው መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚካሄደው ስድስተኛ ዙር ውይይት በደንቡ ላይ የሚደረገው ውይይት እንዲጠናቀቅ ባለፈው ሳምንት መስማማታቸው ይታወሳል፡፡
ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮችን ለመቋጨት ኢሕአዴግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተናጠል አልያም በቡድን ወይም በተወካይ አማካይነት መደራደር እንደሚፈልጉ ራሳቸው እንዲወስኑ ባቀረበው ሐሳብ መሠረት፣ 21 ፓርቲዎች መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ተገናኝተው ለመወሰን ተቀጣጥረው ነበር፡፡ ነገር ግን በዕለቱ የ12 ፓርቲዎች ተወካዮች ብቻ ናቸው የተገኙት፡፡
ኢሕአዴግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይ በተናጠል ወይም በቡድን ወይም በተወካዮች ለመደራደር እንዲወስኑ ሐሳብ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ በቡድን ሲደራደሩ የሚቀር የተለየ አጀንዳ ካለው አካል ጋር የተናጠል ድርድር ለማድረግም ፈቃደኝነቱን አሳይቷል፡፡ በዕለቱ የተገኙት ፓርቲዎች በአንድ ተወካይ ለመቅረብ ያላቸው ሐሳብ በዚሁ ስምምነት የተነሳ እንደተደናቀፈ ተገልጿል፡፡ ከተገኙት ፓርቲዎች መካከል ኢዴፓ፣ ሰማያዊና ኢራፓ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዕለቱ ካልተገኙ ፓርቲዎች መካከል መድረክ፣ መኢአድና ወለኔ ተካተዋል፡፡ ወለኔ የማንነት ጥያቄ የማያራምድ በመሆኑ በተወካይ ለመደራደር እንደማይችል መግለጹ ታውቋል፡፡
የኢዴፓ የጥናትና ምርምር ክፍል ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ፣ በመርህ ደረጃ ጠበብ ብሎ በተወካይ አማካይነት መደራደርን ኢዴፓ እንደሚደግፍ ገልጸዋል፡፡ 22 ፓርቲዎች ባደረጉት ስምምነት መሠረት በዕለቱ የተገኙት ፓርቲዎች በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ የሐሳብ ልውውጥ ቢያደርጉም፣ በአንድ ተወካይ ቡድን መደራደርን ተግባራዊ እንዳላደረጉም አክለዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ፓርቲዎቹ በተናጠል ከኢሕአዴግ ጋር የመደራደር ዕድላቸው እየሰፋ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን አሁንም ጠበብ ብለን በተወካዮች አማካይነት ለመደራደር ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥላለን፤›› ብለዋል፡፡
መድረክ በአምስኛው ዙር ውይይት ከኢሕአዴግ ጋር ለብቻው ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህ የተነሳ በሰኞው ስብሰባ አለመገኘቱ ብዙም የሚገርም አልሆነም ተብሏል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተናጠል ከሚደራደሩ ይልቅ በጋራ ቢደራደሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ያሳስባሉ፡፡ ስለጉዳዩ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ‹‹ኢሕአዴጎች በባህሪያቸው ትምክህተኞች ናቸው፡፡ ሁሉም ነገር የሚቻለው ሲፈቅዱና ፍላጎት ሲኖራቸው ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በቡድን ወይም በተወካይ መቅረብም ሆነ በተናጠል መደራደር ብዙ ልዩነት ያለው አይመስለኝም፤›› ብለዋል፡፡
ይሁንና መድረክ በተናጠል የመደራደር ሐሳብ ለማቅረብ የተገደደው በጋራ ለመሥራት የመረጣቸው የሰማያዊና የመኢአድ ፓርቲዎች የፀና አቋም ስለሌላቸው  እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
‹‹መድረክ በአቋሙና የፖለቲካ ምኅዳሩ እየፈጠረ ካለው ችግር አኳያ ለሰማያዊና ለመኢአድ ይቀርባል፡፡ ሌሎች ፓርቲዎች እንዲህ ዓይነት ጫና ደረሰብን ሲሉ አላይም፡፡ ስለዚህ ከሁለቱ ፓርቲዎች ጋር ሰፊ ጊዜ ወስደን ተነጋግረን ነበር፡፡ በኋላ ሐሳባቸውን ቀይረው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመሆን መረጡ፤›› ብለዋል፡፡
ከየካቲት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ የሰማያዊ ፓርቲ ሕጋዊ ፕሬዚዳንት መሆናቸው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፀደቀላቸው አቶ የሺዋስ አሰፋ ግን፣ የጋራ አጀንዳ እስካለ ድረስ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ቢሆን አብሮ ለመሥራት ሰማያዊ ዝግጁ እንደሆነ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹የጋራ አጀንዳዎቻችን አንድ እያደረጉን ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ፤›› ብለዋል፡፡
በሰኞው ስብሰባ ስምምነት ላይ ሳይደረስ መቅረቱ መነገሩ ትክክል እንዳልሆነም አመልክተዋል፡፡ ‹‹ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት አምስት ዙር ውይይቶች በተቃራኒ የሰኞው ስብሰባ የተቀናጀና ኃላፊነት ወስዶ የሚያስተባብር አካል ያልነበረው ነው፡፡ የተሻለ ቅንጅትና የማስተባበር ሥራ ቢሠራ የተለየ ለውጥ ሊኖር ይችላል፤›› ሲሉም አቶ የሺዋስ አክለዋል፡፡
ኢሕአዴግን በመወከል በፓርቲዎች ድርድር እየተሳተፉ የሚገኙትና የውይይቱ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በቡድን በቡድን ከኢሕአዴግ ጋር እንደራደር የሚል ጥያቄ ለገዢው ፓርቲ እንዳልቀረበ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ድርድሩ በጋራ ይሁን በተናጠል የሚወሰነው በሚቀርበው አጀንዳ እንደሆነ ነው የማምነው፡፡ ኢሕአዴግ ለተመሳሳይ አጀንዳ የተለያየ ድርድር አያደርግም፡፡ የተለየ አጀንዳ አለኝ ከሚል ማንኛውም ፓርቲ ጋር ለመደራደር ግን ዝግጁ ነን፡፡ ምርጫው ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተተወ ነው፤›› ብለዋል፡፡

Monday, March 13, 2017

የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ጋምቤላ በመግባት በትናንናው እለት 14 የአኙዋክ ወገኖቻችንን ገድለው እና 22 ወገኖችን ደግሞ ጠልፈው መውሰዳቸው ተነገረ



በአ.አ በተለምዶ ቆሸ ተብሎ የሚጠራው የቆሻሻ ተራራ ተደርምሶ እስከ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ድረስ ድብቅ የህዋህት ሴራ መሆኑን እያወቀ ግን ርካሽ በወገን ላይ የእልቂት ዘመቻ ያወጀው የከተማ አስተዳደሩ አፉን ሞልቶ 34 ሴት እና 12 ወንድ በድምሩ 46 እስካሁን ሒወታቸው አልፏል አለ፡፡ የሞት መጠኑም በጣም እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል በማለት ከ100 በላይ የሟች ቁጥር እንደሚሆን እያወቀ ድሪባ ኩማ የሀዘን አዋጅ እንደታወጀ እንኳ ሳይናገር ቀረ።
በመቀጠል ትላንት ምሽት ከደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በተነሱ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች 11 ኢትዮጵያን ተገድለው 21 ህፃናትንታፍነው ተወሰዱ
17264928_10208637586998168_2504252691641835292_n

Thursday, March 2, 2017

በቤንሽልንጉል ጉሙዝ ገሰንገሳ ተብሎ ከሚጠራው ሰማይ ጠቀስ ተራራ ላይ ለግዳጂ የተላኩ የህወሓት ወታደሮች ካደሩበት ስፍራ ተገለው ተገኙ።


ከቀናት በፊት በወንበራ ወረዳ ቦጎንዲ ተብሎ ከሚጠራው ከፍተኛ ስፍራ የተተከለው የመረጃ መሰብሰቢያ ቋት (ራዳር) በወያኔ አገዛዝ የተማረረ ወታደር ጉዳት ካደረሰበትና አንድ ፖሊስ ከገደለ ወዲህ ራዳሩን ሲጠብቁ በነበሩት የህዳሴ ዲቪዥን የፈጥኖ ደራሽ የፌድራል አባላት እርስ በርስ አለመተማመን የነበረ ሲሆን ከበላይ አዛዦች በተላለፈ መመሪያ መሰረት ገዳዩ ፖሊስ በከፍተኛ ስቃይ ሲመረመር ቆይቶ የተረሸነ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 11 የፌድራል አባላት እንዲታሰሩ ና ራዳሩን የሚጠብቀው ሃይል በአስቸኳይ እንዲቀየር ተደርጓል።በዚህ ወቅት ከፖዊ በግልገል በለስ አድርጎ ድባጢ ወረዳ አቋርጦ በቡለን ወረዳ ወደ ወንበራ ያቀነው የወታደር ሃይል ገሰንገሳ ከሚባለው ሰማይ ጠቀስ ተራራ ላይ በተከፈተበት ጥቃት 4 ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል። በዚህ እጂግ ከፍተኛ ቅዝቃዜ በሚስተናገድበት ስፍራ የተሰገሰጉ የነፃነት ሃይሎች አሉ በሚል ከሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አዲስ ተዋጊ ሃይል የተላከ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት 14 የቡድኑ አባላት ባደሩበት ተገለው ተገኝተዋል። የተገደሉት የህወሓት ወታደሮች በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ ቅዝቃዜ መቋቋም ካለመቻላቸው በላይ የአካባቢው መልከዓምድር እጂግ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ሪፖርት ሲያደርጉ መቆየታቸው ታውቋል። 5ቱ ወታደሮች በሳንጃ ተወግተው የተገደሉ ሲሆን 9ኙ ግን የተመታ አካል እንደሌላቸው ተረጋግጧል። ከአሳሽ ቡድኑ ውስጥ 2 ወታደሮች ያሉበት አለመታወቁም የሁኔታው አደገኝነት በግልፅ እንደሚያሳይ ለመረጃው ቅርብ የሆኑ ሰወች ይናገራሉ።16427630_1823259841262824_7449098933742497578_n