Tuesday, November 15, 2016
ካናዳ በኢትዮጵያ ስር ነቀል የፖለቲካ ተሃድሶ እንዲደረግ ጠየቀች
ካናዳ በኢትዮጵያ ስር ነቀል የፖለቲካ ተሃድሶ እንዲደረግ የጠየቀች ሲሆን መንግስት የሚወስደው እርምጃ እጅግ ኣስጨንቆኛል በማለት ተናግራለች። ስላማዊና ኣስቸኳይ ውይይት እንዲደረግ የጠየቀችው ካናዳ በቅርቡ በኣማራና በኦሮሚያ ክልል ቤመንግስት የተፈጸሙ ግድያዎችና ኣፈናዎች ኣሳሳቢና ሊጣሩ የሚገቡ ናቸው ስትል ኣስታውቃለች። ካናዳ ለኢትዮጵያ እርዳታ ከሚሰጡ ኣገሮች እንዲሁም በፖለቲካ የተገፉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከሚያስጠጉ ኣገሮች አንዷ ናት።

በሰሜን ጎንደር በመንግስት ወታደሮችና ራሳቸውን ባደራጁ ሃይሎች መካከል ያለው ፍጥጫ እንደቀጠለ ነው።
ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ ራሳቸውን ያደራጁ የነጻነት ሃይሎች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ለሳምንት የዘለቀው ፍጥጫ ዛሬም ቀጥሎአል። የቡድኑ አስተባባሪ ለኢሳት እንደገለጸው፣ ቀደም ብሎ ተደርጎ በነበረው የተኩስ ልውጥ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ምንም እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች አካባቢውን ከበው በመጠባበቅ ላይ ቢሆንም፣ ጫካ የገቡት ሃይሎች አሁንም በጥሩ የጥንካሬ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። አገዛዙ በሃይማኖት አባቶች በኩል እጃችንን እንድንሰጥ ጥረት ቢያደርግም፣ እኛ ግን የሚደርስብንን ስለምናውቅ እጅ ለመስጠት ፍለጎቱ የለንም ብለዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው አስተባባሪው ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል በርካታ ቁስለኛ የስርዓቱ ወታደሮች በጎንደር ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በአገዛዙ ወታደሮችና በእያካባቢው እየተደራጁ በሚታገሉ የነጻነት ሃይሎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ለውውጥ እንደሚካሄድ የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
Sunday, November 13, 2016
የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባላት ተሰብስበው በሙስና ወንጀል ታስረው የነበሩትን የፓርቲው አባላት ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል

የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባላት ተሰብስበው በሙስና ወንጀል ታስረው የነበሩትን የፓርቲው አባላት ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል
በዚህ መሰረት በሙስና ወንጀል የተፈረዱና የተጠረጠሩ እስረኞች (የህወሓት አባላት) በሙሉ ከእስር መለቀቃቸው ተረጋግጧል። ምክንያት፡ ሁሉም የህወሐት አባላት በሙስና መጨማለቃቸው በመረጋገጡና “ማን ታስሮ ማን ይቀራል?!” የሚል ውዝግብ በመነሳቱ ነው። እናም ሁሉም የህወሓት አመራር ከሚታሰር የታሰረ ሁሉ ይፈታ ተብሏል። ለህወሓት ሰዎች ሙስና ህጋዊ የሆነ ይመስላል። It is so!!
-አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ሰሜን ጎንደር እንቃሽ
ሰሜን ጎንደር እንቃሽ ላይ አምስተኛ ቀኑን በዘለቀው ጦርነት የተበሳጨው ወያኔ ያለ የሌለ ሃይሉን በመላክ ከበባ በማድረግ ላይ ስለሆነ በጀግንነት እየተዋጋ ያለው የገበሬ ጦር አፋጣኝ ትብብር ከቅርብም ከሩቅም ላለ ወገን አቅርቧል።
1) በተለይም በጃኖራ፣ በአጅሬ፣ በቆላ ወገራ ያለው ወገን በፍጥነት እንዲደርስ።
2) በኪንፋዝ በለሳ ያለው ወገን አቆራርጦ እንዲደርስ።
3) በቆላ መረባና በመሬና ያለው ወገን ደግሞ በበርሃው አቋርጦ ለከበባ እየመጣ ያለ የአጋዚ ሃይል ስላለ እዛው እንዲያስቀሩት።
4) የዳባት የገደብጌ የአምባ ጊዮርጊስ ወጣት መንገድ በመዝጋት መረጃ በመለዋወጥና ጠላትን በያለበት በመወጠር ትብብራቹህ እንዳይለየን ብለዋል።
በቄስና ሽምግልና ስም ወያኔ የሞከረውን አክሽፈው አሁንም ጠላትን እንደገጠሙ ነው። አደራ ጥሪው ለሁሉም ይድረስ። እየደወላቹህ ወገን አስተባብሩ። አደራ ይህን መልእክት በፍጥነት አሰራጩት።
ሙሉነህ ዮሃንስ
1) በተለይም በጃኖራ፣ በአጅሬ፣ በቆላ ወገራ ያለው ወገን በፍጥነት እንዲደርስ።
2) በኪንፋዝ በለሳ ያለው ወገን አቆራርጦ እንዲደርስ።
3) በቆላ መረባና በመሬና ያለው ወገን ደግሞ በበርሃው አቋርጦ ለከበባ እየመጣ ያለ የአጋዚ ሃይል ስላለ እዛው እንዲያስቀሩት።
4) የዳባት የገደብጌ የአምባ ጊዮርጊስ ወጣት መንገድ በመዝጋት መረጃ በመለዋወጥና ጠላትን በያለበት በመወጠር ትብብራቹህ እንዳይለየን ብለዋል።
በቄስና ሽምግልና ስም ወያኔ የሞከረውን አክሽፈው አሁንም ጠላትን እንደገጠሙ ነው። አደራ ጥሪው ለሁሉም ይድረስ። እየደወላቹህ ወገን አስተባብሩ። አደራ ይህን መልእክት በፍጥነት አሰራጩት።
ሙሉነህ ዮሃንስ

Sunday, November 6, 2016
“ኮማንድ ፖስቱ ገና አልተደራጀም ተብያለሁ። እስከዛሬም ማንም ያነጋገረኝ አካል የለም”
ዳግማዊ ተሰማ

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሃላፊና የምክር ቤት አባል የነበረው ዳግማዊ ተሰማን እኔ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አናንያ ሶሪ፣ ሃብታሙ ምናለና ፍቃዱ በቀለ ካዛንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጠይቀነው ነበር።

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሃላፊና የምክር ቤት አባል የነበረው ዳግማዊ ተሰማን እኔ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አናንያ ሶሪ፣ ሃብታሙ ምናለና ፍቃዱ በቀለ ካዛንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጠይቀነው ነበር።
ዳግምም “ከታሰርኩ ዛሬ ሳምንቴ ነው። እስከዛሬ ማንም ያነጋገረኝ አካል የለም። ስም፣ አድራሻዬንና የትምህርት ደረጃዬን ብቻ ነው የተጠየኩት። ኮማንድ ፖስቱ ገና አልተደራጀም ተብያለሁ። ጠፍተህ ከርመሃል…’ ከመባል ወጪ ለምን እንደታሰርኩ እንኳን በዝርዝር አላውቀውም። ከምኖርበት ኦሎምፒያ አከባቢ ግን በርከት ያሉ ልጆች ታስረዋል።” ብሎናል።
ያው የመጠየቂያው ደቂቃ በጣም ትንሽ በመሆኑ ብዙ ነገር መነጋገር ሳንችል ቀርተናል። ከፖሊስ ጣቢያው ቅጥር ግቢ ያለው የጸሐይ ሙቀት ደግሞ አይጣል ነው። ጸሐይቷ እንኳን ቀዝቀዝ ብትል ምናለበት ….
Thursday, November 3, 2016
የኢትዮ-ምህዳር ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ታስረ
የሳምንታዊው ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ፣ በጋዜጣው ላይ ግንቦት 2007 ዓ.ም ታትሞ በወጣውና በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም ላይ የገንዘብና የንብረት ሙስና መኖሩን የሚያጋልጥ ዜና መስራቱን ተከትሎ፣ የቀረበበትን ክስ ሲከታትል ቆይቶ ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 6ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኘት ውሳኔ ተሰጥቶት ታስረ።
የጋዜጠኛውና የጋዜጣው ጠበቃ አቶ በሀይሉ ተስፋሁን እንደገለጹት፤ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 613/3 መሰረት ከባድ የስም ማጥፋት በሚል ደንበኛቸው ጥፋተኛ መባሉን ተናግረዋል።
እንደጠበቃው ምላሽ ከሆነ፣ በወቅቱ ዜናውን የሰራው ሪፖርተር ከሰበካ ጉባዔው የውስጥ ምንጮች በመረጃ ተገቢውን መረጃ ከማጠናቀር ባሻገር፤ የዜና ዘገባውን ሚዛናዊ ለማድረግ ሪፖርተሩና ጋዜጠኛ ጌታቸው ጉዳዩ የሚመለከተውን ሃይማኖታዊ ተቋም ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም “ዜናውን እንዳታወጡት!” የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበር።
ክሱ ከተጀመረም በኋላ ክሱን በበቂ ሁኔታ መከላከላቸው የሚናገሩት ጠበቃ በሃይሉ፣ በዛሬው የፍርድ ቤት ወሎ የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት ከተሰማ በኋላ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 06 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
ጋዜጠኛ ጌታቸውም ዛሬ ፖሊስ ጣቢያ የታስረ ሲሆን ከነገ በኋላ ባሉ ቀናት ወደቂሊንጦ እስር ቤት ይዘዋወራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮ-ምህዳር በሀገራችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትታተም የነበረች ጋዜጣ ስትሆን በተለያዩ ጊዜያት ህትመቷ እየተቋረጠ በዋና አዘጋጁ የግል ጥረት አሁንም ደረስ ዘወትር ቅዳሜ የምትነበብ ጋዜጣ ነች። ጋዜጠኛ ጌታቸውም በተለያዩ ጊዜያት እየተከሰሰና እየታሰረ አስቸጋሪውን የኢትዮጵያ የጋዜጠኘት ሙያ በመጋፈጥ ላይ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስና የዜና ዘገባ ቀርቦበት ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ላይ ክስ አቅርቦ ነርበ። ጌታቸውም እንደዋና አዘጋጅነቱ ክስ ቀርቦበት ከባልደረቦቹ ጋር ሀዋሳ ፍርድ ቤት ሲመላለልሱ፤ እነሱ ተጭነውበት የነበረው ባጃጅ ተሽከርካሪ ሆነ ተብሎ ተገጭቶ የመገልበጥ አደጋ ገጠመው።
የጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነም በአደጋው በደረሰበት ከባድ አደጋ ከወገቡ በታች ፓራላይዝድ ሆኖ ዛሬም ድረስ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ይገኛል።
ጋዜጠኛ ኤፍሬም በሀገርና ከሀገር ወጪ የህክምና እርዳታ ቢደረግትለም ከገጠመው ችግር ሊፈወስ አልቻለም። በወቅቱም ጋዜጠኛ ጌታቸው ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶበት እንደነበረ አይዘነጋም።

ጀርመን እና የአውሮጳ ኅብረት ፣ከወያኔ መንግሥት ጋር መሥራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አንድ የጀርመን ፖለቲከኛ አስታወቁ ።
ጀርመን እና የአውሮጳ ኅብረት ፣ ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የማያደርግ ፣ ከመሬቱ የሚያፈናቅል እና በሰላማዊ ሰልፈኞችም ላይ ተኩስ ከፍቶ የሚገድል ካሉት መንግሥት ጋር መሥራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አንድ የጀርመን ፖለቲከኛ አስታወቁ ። ይህን አሰተያየት የሰጡት ኒማ ሞቫሳት በጀርመን ምክር ቤት የግራዎቹ ፓርቲ ተወካይ ፣ ጀርመን እና የአውሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ ህዝብን ተጠቃሚ የማያደርጉ አሠራሮች እንዲቀየሩ ጥረት እንዲያደርጉ በሰጡት ቃለ ምልልስ ጠይቀዋል። በርሳቸው አስተያየት ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት ወደ አውሮጳ የሚጎርፉ ስደተኞችን ማስቆም አይቻልም። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የጀርመን የህዝብ እንደራሴን ኒማ ሞሶቫትን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

Subscribe to:
Posts (Atom)