Saturday, October 22, 2016

ሰበር ዜና በሱማሌያ የሚገኘዉ የህወሃት ሰራዊት በአል ሸባብ ተመታ።


በሶማሌያ በኑር ፋህን መንደር አካባቢ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት በአልሸባብ ቀለበት ዉስጥ በመግባቱ ድንገተኛና ያልተገመተ ጥቃት ደርሶበታል በዚህ ድንገተኛ ጥቃት 11 ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ሲገደሉ 3ቱ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳታቸዉን ትናንት ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ሲያመለክት።
ይህንን የልሸባብ ጥቃቱን ተንተርሶ የሶማሌ ደህንነት ሚኒስቴር አብዱረዛቅ መሃመድ አህመድ ወደ ስፍራዉ የሶማሌ ወታደሮች እንዲንቀሳቀሱ ቀደም ብለዉ ወደ አካባቢዉ የመከላከያ አዛዦች ጥያቄ ማቅረባቸዉን ከስፍራዉ የወጣ መረጃ ጠቁሟል።
ህወሃት በኢትዮጵያ ላይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲህ ኮማንድ ፖስቱን ወይም ተወርዋሪን በማጠናከር ያጋጠመዉን የሐይል እጥረት ለማስተካከል ከሶማሌያ ወታደሮችን ወደ ሐገር ቤት ካሸጋገረ በኋላ አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የፈጸመዉ ይህ ጥቃት ነገሮችን የተወሳሰቡ አድርጓቸዋል።
በመሆኑም ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዉስጥ መረጃ የሰጠን ወንድማችን እንዳስቀመጠዉ ከአሚሶም የአፍሪካ ህብረቱ ጦር ዉስጥ በማፈንገጥ ወደ ኬንያ ሁለት የኢትዮጵያ ወታደሮች ያፈነገጡ ሲሆን በኮረኔል አይኖም መስፍን የሚመራ አሳሽ ቡድን ባዶ እጁን በመመለሱ ምክንያት በሶማሌያ የሚገኘዉ የህወሃት ወታደሮች ላይ የህብረቱ ጦር ያለዉን እምነት እያጣ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment