Sunday, August 28, 2016

ሕዝባዊ እንቅስቃሴው በህወሓት የንግድ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ የኢኮኖሚ ጦርነት ሊጀምር ነው

በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር እና ጎጃም በደቡብ ኢትዮጵያ ከኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን አመጽ ጋር በተያያዘ በስልጣን ላይ ያለው የህወሓት የፖለቲካ መናጋት እንደደረሰበት የሚወስዳቸው ግብታዊ ርምጃዎች ያመላክታሉ።
ምንም እንኳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአማራም በኦሮሚያም የኢትዮጵያ ክፍሎች ቢገደሉም ሕዝባዊ ተቃውሞው በተቃራኒ ጉልበቱን እያደሰ ስርዓቱን ግራ አጋብቶታል።
የህወሓትን ኢኮኖሚ አቋም ለማዳከም በሚመስል ሁኔታ በጎጃም ባህር ዳር ከስርዓቱ ጋር ንክኪ ያላቸውን የንግድ ተቋማት ዝርዝር የያዘ እና የኢኮኖሚ እቀባ የሚጠይቅ ጽሁፍ ተበትኗል። በጎንደር እና ሌሎች የጎጃም አካባቢዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድም ታውቋል። የኦሮሚኛ ተናጋሪ የፖለቲካ መሪዎች ተመሳሳይ የኢኮኖሚ ጦርነት በህወሓት ተቋማት ላይ ለማድረግ እቅድ ነድፈው ወደ ስራ ለመግባት እንደተዘጋጁም ተሰምቷል።
ከህወሓት ጋር የፖለቲካ እና ጎሳን መሰረት ያደረገ ግንኙነት ያላቸው ወገኖች ያላአግባብ በመበልጸግ ሃገሪቷን ዘርፈዋል የሚል ተደጋጋሚ ክስ ከኢትዮጵያውያን ይሰነዘራል። ከጥቂት አመታት በፊት ኤፈርትን ጨምሮ ህወሓት እንደፓርቲ የሚያንቀሳቅሳቸው የንግድ ተቋማት ብቻ ከአምስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚገመቱ ባለስልጣናቱን በመጥቀስ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከዚህ በፊት የህወሓት ቁልፍ ሰው ናቸው ከሚባሉት ከስብሃት ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ስብሃት ህወሓት ግዙፍ ሃብት እንዳካበት ሳይደብቁ ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና ትላንት ቅሊንጦ እየተባለ ከሚጠራው እስር ቤት በቀለ ገርባን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞች ባለፉት ጥቂት ወራት ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ሶስት ቀን የሃዘን ቀን እንዲታወጅ እና ኢትዮጵያውያን ጽጉራቸውን በመላጨት የተገደሉትን ንጹሃን ኢትዮጵያውያን እንዲያስቡ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን በመቀበል ጽጉራቸውን በመላጨት እና የኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውን የተቃውሞ ምልክት የሆነውን የተሳሰረ እጂ በፎቶግራፍ በማሳየት ለጥሪው ምላሽ ሰጥተዋል።

Saturday, August 27, 2016

ወያኔ ከ 9 አመት እስከ 15 አመት እድሜ ያላቸውን ህፃናትን በስለላ ሬድዬ አጠቃቀም እና ጠመንጃ አተኮኮስ አሰልጥኖ አስመረቀ


ወያኔ ከ 9 አመት እስከ 15 አመት እድሜ ያላቸውን ህፃናትን በስለላ ሬድዬ አጠቃቀም እና ጠመንጃ አተኮኮስ አሰልጥኖ አስመረቀ በስልጠናው የልጆቹ አዕምሮ ሊቀበለው በሚከብድ ሁኔታ የትግራይ ልጆች ላይ ደርሶል ያሉትን ቪድዬ እንዲያዩ ተደርጎል ፤ በእለቱ ወላጆች መገኘት ብቻ ሳይሆን ሂዱና የትግራይን ህዝብ ከኦሮሞ ዱላ ከአማራ ዱላ እና ግድያ አድኑ ሲሉም ተደምጠዋል እነዚህ በህፃን ገላቸው በማባበል እንዲሰልሉ ነገር እንዲያቀባብሉ በስውር የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እንዲተገብሩ በበቂ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ለታጋይነታቸው ብዙ ብር ቃል የተገባ መሆኑም ታውቆል መልእክቱን ያደረሰን ሰው ሲቀጥል በስጦታው የማለሉት ወላጆቻችን ጭምር ናቸው ብሎል እርሱ ፈቃደኛ ቢሆንም ታናሹ ግን በዚህ አላማ መሳተፉን እንዳልደገፈ ተናግሮል የአንዶ እናት ተብዬ “ጭንቅላቱን በጥይት ቤቱን በቦንብ አጋዩት ” ሲሉ መርቀዎቸዋል ይህ ሁሉን ልጆቹን በወኔ እንዲሞሉ እንዳደረጋቸው ይህ ህፃን ተናግረዎል። የቀደሙ ታጋይ አባቶቻቸው በእነሱ እድሜ ጭምር ትግል እንጀመሩም በ ታየው ፊልም ታይቶል ሙሉውን ህጋዊ የፌስብክ ነው በሚሉት ምስሉን አሰራጭተዋል።
በ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ- Democratic Ethiopia በተባለው ፌስ ብክ መልቀቃቸው አነጋጋሪ ሆኖል ።
ከፎቶዎ ይመልከቱ።(Gebrye Yegayntu)
 

ሰበር ዜና በገዢው ሥርዓት ህወሓት-ኢህአዴግ የተገደሉ ንፁሐን ዜጎችን ለማሰብ ብሔራዊ የኀዘን ጥሪ ያቀረቡት በቂሊንጦ የሚገኙ በዞን 1 ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ጨለማ ቤት መወርወራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ገለጹ::


ጥሪውን በዋናነት ያቀረቡት በዞን 4 የሚገኙት 9 የፖለቲካ እስረኞች(በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ አበበ ኡርጌሳ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ) ቅጣት ቤት ይገኛሉ::
እስረኞቹ ፀጉራቸውን መላጨታቸው የታወቀ ሲሆን በቅርቡ የእስረኞች ልብስ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ቱታ እንዲለብሱ ግዴታ በመጣሉ ጥቁር ልብስ መልበስ እንዳልቻሉ ኢሳት ለመርዳት ችሏል:: ሆኖም በዞን 1 ያሉት እስረኞች ጥቁር ለብሰው በመታየታቸው ጨለማ ክፍል እንዲገቡ ተደርጓል::
የእስረኞቹን ጥሪ በመስማት በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችና በመንግሥት ተገፍተው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ጥቁሩ ለብሰው ፀጉራቸውን ተላጭተው በግፍ የተገደሉ ወገኖቻቸውን አስበዋል::
በተያያዘ የእስርቤት ዜና የ እስርቤት የሌሊት ጠባቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው መሰወራቸው እየተነገረ ነው። ሁኔታው በመንግሥት ላይ ድንጋጤ ፈጥሮ በእስር ቤቱ ዙሪያ ግርግር እንደነበር ተገልጿል::ኢሳት ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረገ ይገኛል::በዚህ ዓመት ብቻ በጠባቂዎች ተመሳሳይ እርምጃ ሲወሰድ ለ3ኛ ጌዜ ነው::

Wednesday, August 24, 2016

ሰበር ዜና!! ወያኔ ሰራዊቱን መምራት ተስኖታል!!


12346463_548965748583774_8352368329141136208_nከሰሞኑ በተደጋጋሚ እየተደረገ የሚገኘዉን ጦርነት በሐላፊነት የወሰደ አካል የለም! ትግራይ እና የጎንደር ጠረፎችን እየተሻገርና እየተመላለሰ የሚያጠቃ ብርቱ ሐይል ተከስቷል! በጎንደር ሶሮቃ፡ ሳንጃ፡ አሸሬ፡ ዳንሻ እንዲሁም መተማ በሱዳን በኩል አል ቃዳሪፍ ድንገተኛ ትቃቶች ተፈራርቀዋል! የወያኔ ሰራዊት እጅ እየሰጠና እየተማረከ ነዉ! በትግራይ በሂምሮ ፣ ከሻምቡካ እስከ ባድሜ እንዲሁም በቡርኩታ በተጨማሪ ከአዲ ቀይህ እስከ አዲ ግራት እንዲሁም ከአዲ ቋላህ በኩል ወያኔ እየተጠቃ ይገኛል።
ምንጮች እንደጠቀሱት የወያኔ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ በማፈግፈጋቸዉ አጥቂዉ ሐይል የወሰን መስመሮችን በብዛት ተቆናጠሯል በተለይም ጥቃቶቹ የሚሰነዘሩባቸዉ ስፍራዎች ለአየር ዉጊያ የማይመቹ በመሆናቸዉና ያልተጠበቁና ከቁጥጥር ዉጭ እየሆኑ ይገኛሉ! በጎንደር በኩል ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ የመቆጣጠሪያ ቀጠናዎች በአጥቂዉ ሐይል ሲደመሰሱ ብዛት ያላቸዉ ቀላልና ከባድ መሳሪያውችም ተማርከዋል።
ከምንጮቻችን መካከል አንዱ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ትግሬ ያልሆኑ አዋጊዎች በዝዉዉር ሰብበ እየተነሱ በምትካቸዉ ትግሬዎቹ እየተቀየሩ ሲሆን በትግሬ አዋጊዎች ብቃት ማነስና ከሰራዊቱ ጋር ያለመግባባት ምክንያት ጦሩን ማቀናጀት አልተቻለም። በተጨማሪ እራሱ ሰራዊቱ በአንድ ዘር የመመራቱ ጉዳይ የማይዋጥለት ደረጃ ላይ እየደረሰ በምምጣቱ በቡድን በቡድን ተሰባጥሮ በመከፋፈል ለመታዘዝም አስቸጋሪ ሆኗል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

25 አመታት በአማራው ህዝብ ላይ ከተፈጸመው ዝግናኝ ግድያ፥ ጀርባ እጁ ያለበት አቶ ንጉሱ ጥላሁን *የክልሉ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ*

ላለፉት 25 አመታት በአማራው ህዝብ ላይ ከተፈጸመው ዝግናኝ ግድያ፥እስራት፥ስደት እና ወከባ ዋናዎች የህወአት ሰዎች ቢገኙም በተላላኪዎች እና በጉዳይ አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ግን በክልሉ ያሉ በብአዴን ስም የተሰገሰጉ የጥፋት ሀይሎች ናቸው።
ሰሞኑን በአማራ ክልል የሚካሄደውን ህዝባዊ ትግል ጥላሸት በመቀባት ሰላማዊ ሰልፉ ህጋዊ አደለም ከማለት ጀምሮ በዜጎች ላይ የሚወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ ሳያወግዝ አለቆቹ ጽፈው የሰጡትን እንደበቀቀን የሚያስተጋባው የክልሉ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በ14/08/2016 የተገደለውን ወጣት አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ለቀረበለት ጥያቄ ሰዎች የፈለጉትን መልበስ እንደሌለባቸው እና የተገደለው ወጣትም በአመጽ እና በቅስቀሳ ተግባር ስለተሰማራ ነው እንጂ ነጭ ስለለበሰ አደለም ሲል ግድያው ተገቢ መሆኑን አረጋግጧል።ወደ ፊትም እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቋል።
ታዲያ እንዲህ አይነቱ ሰው ማን ነው?የኋላ ታሪኩስ ምን ይመስላል?እንዴት ወደዚህ ስልጣን መጣ ብሎ መጠየቅ ስለ ግለሰቡ የተሟላ መረጃ እንዲኖረን ፥መወሰድ ያለበት ቀጣይ ተግባርም ለመወሰን ስለሚረዳ እነሆ ተከታታሉኝ።
ንጉሱ ጥላሁን በ1998 አ.ም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ በፔዳጎጅካል ሳይንስ የተመረቀ ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታው የተማሪዎች መማክርት ውስጥ ይሰራ ነበር።በዚህም ወቅት ከግቢው የተማሪዎች የምግብ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመመሳጠር ጥራቱ ያልጠበቀ ምግብ እንዲቀርብ፥ነጭ ጤፍ መቅርረብ ሲገባው ቀይ ጤፍ እና በቆሎ የተቀላቀለ፥ትክልት መቅረብ ሲገባው አተር ከክ ፥ወዘተ እያደረገ በተማሪው በጀት የግል ኪሱን ሲሞላ የነበረ ሰው ነው።የ97 ምርጫ ብጥብጥ ተከትሎ በዮኒቨርሲቲው ውስትጥ የነበሩ ተማሪዎችን እየጠቆመ ያሳስር የነበረ ሰላይ ነበር።
ንጉሱ ትምህርቱን ሲይጠናቅቅ ገና በይፋ የምስክር ወረቀት ዲፕሎማው በሬጅስትራር ተሰርቶ ብይፋ ለሁሉም ከመታደሉ በፊት በነበረው የባንዳነት ተግባሩ ዲፕሎማው ተሰርቶ ተሰጦት በዳሸን ቢራ ፋብሪካ ያለ ምንም ውድድር የተቀጠረ ሰው ነው።ከዚያም በቀጥታ ለአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊነት ተመደበ።
ለዚህ ሁሉ ተግባር ከንጉሱ ጀርባ ማን አለ?ንጉሱን ማን ወደ ዳሸን ቢራ አስገባው?
ቁልፍ ካድሬዎች ተመርጠው በሚቀመጡበት የኮሙኒኬሽን ቦታ ማን ንጉሱን አስቀመጠው ብለን ስንጠይቅ መልሱ ህወአት ሁኖ እናገኘዋለን።እንግዲህ ይህ ሰው ነው የአማራውን ትግል በሌሎች ብሂሮች ላይ ያነጻጸረ እያለ የህወአትን አጀንዳ በህዝባችን ላይ የሚያስፈጽመው።
ወገኔ ትግል ሩቅ አያስሄድም።ከጎናችን ብዙ ጠላቶች አሉ ትልልቁን ዛፍ መቁረጥ ከመጀመራችን በፊት ቅርንጫፉን መመልመል ተገቢ ነው።
ንጉሱ ጥላሁን የአማራው ጠላት
 Aseged Tamene photo

Wednesday, August 17, 2016

በምስራቅ ሸዋ ዞን ዝዋይ ከተማ ሆራ ፈጀሶ የተባለ ወጣት አንድ የአጋዚ ወታደር ገድሎ ሌላ አንድ የፌደራል ፖሊስ

በምስራቅ ሸዋ ዞን ዝዋይ ከተማ ሆራ ፈጀሶ የተባለ ወጣት አንድ የአጋዚ ወታደር ገድሎ ሌላ አንድ የፌደራል ፖሊስ ካቆሰለ በሁዋላ ተገደለ።
ሌሊት ላይ ወታደሮቹ “መሳሪያ አለህ አውጣ” ብለው የቤቱን በር በሃይል ሰብረው ሲገቡ፣ ወጣት ሆራ “እጄን ለእናንተ አልሰጥም” በማለት አንዱን ግንባሩ ላይ በሽጉጥ መትቶ ሲገድለው፣ ሌላውን ደግሞ ሆዱ አካባቢ መትቶ ጥሎታል። በዚህ የተበሳጩት ወታደሮች ወጣቱን ደጋግመው በመተኮስ ከገደሉት በሁዋላ በአስከሬኑ ላይ ደጋግመው በመተኮስ ንዴታቸውን ለመወጣት ሞክረዋል። ባለቤቱና ልጆቹም ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።
Aseged Tamene photo

Tuesday, August 16, 2016

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ ወርቅ ሳይቀርብ 21.3 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ እንዲፈጽም የተደረገበትና የአገር ሀብት ዘረፋ


በጠራራ ጸሀይ አገር ሲዘረፍ
በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በወርሀ ጥር የወያኔ ካድሬዎችና የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ተቋማት የሆኑት እነ ኤ.ቢ.ሲ.፣ ዋልታ፣ ፋና፣ ኤ.ዜ.አ. ወዘተ ትግራይ በታሪኳ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ስላሉት የወርቅ ምርት መጠን በስፋት ዘግበው ነበር። የአገዛዙ ልሳን ኢ.ቢ.ሲ. እ.አ.አ. ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም. ባቀረበው ርዕሰ አንቀጽ፤ ዋልታ እ.አ.አ. ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስደመጠም የዜና እወጃ ፤ ኤ.ዚ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስነበበን ሪፖርት ትግራይ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ [በባህላዊ መንገድ] እንዳመረተችና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳቀረበች ነግረውናል።
ይህንን «ልማታዊ ዜና» የሰሙ ብዙ ሰዎች «ትግራይ ከየት አምጥታ ነው ይህንን ያህል ወርቅ አምርታ ለብሔራዊ ባንክ የምታቀርበው?» በማለት ከቁጥሩ ጀርባ ያለውን የምጣኔ ሀብት ትርጉም ሳያጤኑ አጣጥለውት አልፈዋል። ሆኖም ግን ከቁጥሩ ጀርባ ወያኔ ትልቅ አገራዊ ዘረፋና ወንጀል ፈጽሟል። ወያኔ በቁጥሩ ቁማር ተጫውቶ የኢትዮጵያን የሁለት አመት ባጀት ያህል ብሔራዊ ሃብት በአንድ ግብይት ብቻ ወደ ትግራይ አሸሽቷል ወይንም አሻግሯል። ነገሩ እንዲህ ነው።
ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት በ42 ወር ውስጥ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት ነው። ይህ ማለት ትግራይ በአመት በአማካኝ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባ ነበር ማለት ነው። በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብቸኛው ወርቅ ገዢና አስቀማጭ ተቋም ነው። ክልሎች በየክልሉ የተመረተውን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ሲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ክልሎች ላቀረቡት የወርቅ መጠን ክፍያ ይፈጽማል። ለምሳሌ ትግራይ 597.7 ቶን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስታቀርብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለትግራይ ክልል የ597.7 ቶን ወርቅ ክፍያ በገንዘብ ይፈጽማል። ያልቀረበ ወርቅ ሪፖርት ተደርጎ ብሔራዊ ባንክ ላልቀረበ ወርቅ እንደቀረበ ተደርጎ ክፍያ ቢፈጽም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሀብት transfter ይኖራል ማለት ነው።
ወያኔ የነገረን ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ያቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ማለት 597,700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማለት ነው።ይህ ማለት ደግሞ 19,216,473 ወቄት ወርቅ ማለት ነው። ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት አመታት ውስጥ አማካኝ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 1,100 የአሜሪካን ዶላር ነበር። ይህ ማለት ትግራይ አቀረበችው የተባለው 597.7 ቶን ወርቅ ዋጋ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል ማለት ነው።
ይህ ማለት [በወያኔ ዜና መሰረት] ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ብሔራዊ ባንክ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍሏታል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ያለፈው አመት ባጀት አስር ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህ ማለት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ለተባለው 597.7 ቶን ወርቅ የተከፈላት 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ የሁለት አመት በጀት በላይ ነው ማለት ነው።
ዋናውና ቁልፉ ጥያቄ እውነት ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 597.7 ቶን ወርቅ ወይንም ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ አቅርባለች ወይ? የሚለው ነው።
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የአለም አገሮችን የወርቅና የሌሎች ማዕድናትን አመታዊ ምርት ማስረጃ የሚሰበስበውንና የሚያደራጀውን የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የአለም ማዕድናት ምርት ሰንጠረዥን ማየት በቂ ነው። ይህ የአሜሪካ ተቋም በአለም ላይ ያሉ ማዕድን አምራች አገሮችን የማእድን አመታዊ ምርት አሃዝ ሰብስቦ ደረጃ ያወጣና የአለም አገሮችን በማዕድን ምርት ያወዳድራል። በዚህ መስሪያ ቤት ማስረጃ መሰረት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በአለም ላይ በወርቅ ምርት አንደኛ ቻይና ስትሆን አመታዊ የወርቅ ምርት መጠኗ 403 ቶን ነው። ሁለተኛዋ የአለም ወርቅ አምራች አገር ደግሞ አውስትራሊያ ስትሆን አመታዊ የምርት መጠኗ ደግሞ 250 ቶን ወርቅ ነው። ሶስተኛ አሜሪካ [235 ቶን ወርቅ በአመት] ፤አራተኛ ሩስያ ፌድሬሽን [217.8 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ አምስተኛ ፔሩ [161 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ስድስተኛ ደቡብ አፍሪካ [160 ቶን ወርቅ በአመት]፤ ሰባተኛ ካናዳ [103 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ስምንተኛ ሜክሲኮ [96.7 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ዘጠነኛ ኡዝቤኪስታን [ 93 ቶን ወርቅ በአመት] እና ጋና [86.5 ቶን ወርቅ በአመት] በአለም ላይ አስሩ ከፍተኛ ወርቅ አምራች አገሮች ናቸው። የዚህ ምንጭ የሚከተለውን ትር መክፈትና መመልከት ይቻላል… http://www.indexmundi.com/minerals/…።
ወያኔ ኢትዮጵያ ትግራይ ብቻ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች ያለው እውነት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ በወርቅ ምርት በአለም ደረጃ ፔሩን ቀድማ ሩስያን ተከትላ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትሆን ነበር። ልብ በሉ ከአንድ እስከ አስር የወጡ አገሮች ሁሉ ወርቅ የሚቆፍሩት በጣም ዘመናዊ በሆነ መሰርሰሪያ ማሽን ነው። ወያኔ ግን ትግራይ በየ አመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች የሚለን በባህላዊ መንገድ አምርታ ነው።
ከፍ ብዬ በለጠፍሁት የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የወርቅ ምርት እውነተኛ ደረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አመታዊ የወርቅ አምራችነት ደረጃ 29ኛ ሲሆን አመታዊ የወርቅ ምርቷ ደግሞ 12 ቶን ብቻ ነው። ልብ በሉ ይሄ አመታዊ የኢትዮጵያ የወርቅ ምርት ዶዶላ፣ መተከል፣ ለገደንቢና ወለጋ ሜድሮክ በዘመናዊ ቴክኖሎች ታግዞ የሚያመርተውን ይጨምራል። ወያኔ ግን የትግራይን አመታዊ ምርት ብቻ 171 ቶን ነው ይለናል።
ሜድሮክ በዶዶላ፣ በመተከል፣ በለገደንቢና በወለጋ የሚያመርታቸውን ዜሮ አድርገን ኢትዮጵያ ያመረተችውን 12ቱን ቶን ወርቅ ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበ የወርቅ መጠን አድርገን ብንወስድ፤ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ እንደቀረበለት ተደርጎ ለትግራይ በጠቅላላ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ውስጥ በያመቱ ላልቀረበ 158 ቶን ወርቅ ክፍያ ፈጽሟል። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ ቀረበ ተብሎ ከፍያ ከፈጸመበት 597.7 ቶን ወርቅ ውስጥ ባንኩ የተረከበው ወርቅ 42 ቶብ ብቻ ነው። የተቀረው 555.7 ቶን ወርቅ ወርቁ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሳይቀርብ ብሄራዊ ባንክ ግን ከትግራይ ወርቅ ሳይቀርብ ክፍያ እንዲፈጽም የተደረገበትና የአገር ሀብት ዘረፋ የተካሄደበት የውሸት ቁጥር ነው።
ይህ ማለት ብሔራዊ ባንክ ለትግራይ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለትግራይ የተከፈለው የአገር ሀብት ላልቀረበ የወርቅ መጠን እንደቀረበ ተደርጎ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ወያኔ ያልቀረበ ወርቅን አስታኮ 20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገር ሀብት ወደ ትግራይ wealth transfter አድርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመት የኢትዮጵያ አመታዊ በጀትን የሚያህል የአገር ሀብት ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ እንዳቀረበች ተሳቦ እንድትወስድ ተደርጓል ማለት ነው። ይህ ማለት የሁለት አመታት የኢትዮጵያ አመታዊ ሀብት ወደ ትግራይ እንዲሄድ ሲባል ዘረፋ ተፈጽሟል ማለት ነው። ወገኖች this is a huge wealth transfter. ወያኔ ከጥር ወዲህም ማራኪ ቁጥር እያቀረበ የአገር ሀብት ወደ ተስፋዋ ምድሩ እያሸጋገረ ይገኛል። በሌላ ጊዜ ከሌሎች ቁጥሮች ጀርባ ስለሚፈጸም አገራዊ ዘረፋ የምለው ይኖረኛል።
የሚገርመው ትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች በተባለ በወሩ የቀረበው ሌላ ዜና የስርዓቱ ዜና ነው። ፋና በየካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም [እ.ኢ.አ.] ያቀረበው ዜና ርዕስ እንዲህ ይላል…«ለብሄራዊ ባንክ እየቀረበ ያለው ወርቅ በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው።» ዜናው በዚህ ብቻ አያበቃም። ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም.[እ.ኢ.አ.] በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች እንዳልተባለ «ብሄራዊ ባንክ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መልኩ ተመርቶ የሚቀርበለት ወርቅ በእጅጉ ቀንሷል። በ2005 ለባንኩ የቀረበለት 8.1 ቶን ወርቅ ነበር። በ2006 ዓ.ም ደግሞ 7.4 ቶን ሆነ፤ በ2007ም በጣም አሽቆልቁሎ 5.4 ቶንድረስ ወርዷል።» አሉን። ይህ ሁሉ የሚሆነው ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ በአመት 171 ቶን ወርቅ ቀረበ ተብሎ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደቀላል ወደ ትግራይ transfter እንዲሆን ባደረጉ በአንድ ወር ውስጥ ነው።
አይ አንቺ አገር! ማፍያዎች የውሸት ቁጥር እየቀቀሉ ሌላውን ጾም ደፍተፍና አራቁተው የድሆችን ሀብት ወደ መንደራቸው ያግዛሉ። በአንድ ማጭበርበር ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር የአገር ሀብት ወደ መንደራቸው አሸሹ! በቁጥር ሊሸውዱን ሲሞክሩ በትንተና እንዲህ ባጋለጥናቸው ጉዳይ ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር በድብቅ ባልተወለደ አንጀታቸው ከገፈፉ ሰው ሳያውቀው የዘረፉት የአገር ሀብት ቢታወቅ ለሌላው ኢትዮጵያ ምን ያህል ያተርፉለት ይሆን?
[የግርጌ ማስታወሻ፡ ከላይ ለትንተና የተጠቀምሁባቸውን ማስረጃዎች ሁሉ ከታች ካለው የአስተያየት መስጫው ሳጥን መመልከት ይቻላል!]
(Achamyeleh Tamiru)

Sunday, August 14, 2016

ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ


በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ
አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ
ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ
እንደግፋለን።
ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን
ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓
1. ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን መወገድ አለበት
2. በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበሮችና ብቃት ባላቸው ግለሰቦች የሽግግር
መንግስት መቋቋም አለበት።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚከተለውን ጥሪ እያቀረብን ፣ እኛም ከህዝባችን ጐን
ተሰልፈን ለትግሉ መሳካት የአቅማችንን እንደምናበረክት ቃል እንገባለን።
1. ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮና ፋታ ሳይሰጥ አፋኙን አገዛዝ እንዲያስወግድ፣
2. በሰላማዊ ህዝብ ውስጥ የእርስ በርስ ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲደረግ፣
3. ሰራዊቱና ሌሎች የመንግስት ታጣቂዎች በህዝባቸው ላይ እንዳይተኩሱ፣
4. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ትግሉ እንዲጠናከር፣
5. የትግራይ ህዝብ በራሱ ላይ ብዙ ግፍ የሚፈፅመውንና በስሙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን
የሚጨፈጭፈውን ህወሓት አውግዞ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን እንዲሰለፍ
በተጨማሪ ነፃነት ባላቸው አገሮች ውስጥ እየኖሩ የግፍ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም የሚሞክሩት ግለ ሰቦች፣
በተለይም የህወሓት ደጋፊዎች አደብ ካልገዙ የኢትዮጵያ ህዝብ አንደሚፋራዳቸው እንዲያውቁ፣ ማሳሰብ
እንፈልጋለን።
የስም ዝርዝር᎓
1. ህይወት ተሰማ
2. ሕሉፍ በርሀ
3. ስልጣን ኣለነ
4. በየነ ገብራይ
5. ተስፋዬ መሓሪ
6. ተስፋይ ኣፅብሃ
7. ታደሰ በርሀ
8. ነጋሲ በየነ
9. ናትናኤል ኣስመላሽ
10. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
11. ኣብራሃ በላይ
12. ኪዳነማርያም ፀጋይ
13. ካሕሳይ በርሀ
14. ዘልኣለም ንርአ
15. ደስታ ኣየነው
16. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ
በዚህ መግለጫ ይዘት ሊስማሙ ከሚችሉ ሰዎች ጋር በሙሉ ስላልተነጋገርን በዚህ የሚስማሙ
ስሞቻቸውን ወደሚከተለው ኣድራሻ ከላኩልን መግለጫውን በድጋሚ እናወጣዋለን᎓
ethiocivic@gmail.com

ተመድ ለመላክ ያሰበውን የሰብዓዊ መብት አጣሪ ቡድን መንግሥት እንደማይቀበል አስታወቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ካውንስል በኢትዮጵያ ሰሞኑን በተካሄዱት ሕዝባዊ ተቃውሞዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝን ለማጣራት የጠየቀውን ፈቃድ መንግሥት ውድቅ አደረገ፡፡
በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በርካታ አካባቢዎች በተነሱት ተቃውሞዎች የሟቾችና የተጐጂዎች ቁጥጥርን አስመልክቶ በመንግሥት እየወጣ ያለው ሪፖርት ተዓማኒነትን በመጠራጠር ነው፣ የተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል ጥያቄውን ያቀረበው፡፡
በሰብዓዊ መብት የተመድ ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ዚያድ ራድ አል ሁሴን ለተለያዩ የውጭ የሚዲያ ተቋማት እንደተናገሩት፣ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በኅዳር ወር 2008 ዓ.ም. የተደረጉትን ተቃውሞዎች አያያዝ ለማጣራት ተዓማኒነት ያለው ሙከራም ሆነ ተጠያቂነት በመንግሥት በኩል አለማየታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተቃውሞው ወቅት የተገደሉ ዜጐችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ አለመቻሉንም ገልጸዋል፡፡ በማከልም መንግሥት ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረግ ላይ ሳሉ ያሰራቸውን ዜጐች በፍጥነት መልቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያና በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱት ተቃውሞዎችን አስመልክቶ ባደረገው ማጣራት፣ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ተመጣጣኝ ኃይል መጠቀሙን በአማራ ክልል ግን ተመጣጣኝ ኃይል አለመጠቀሙንና ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ማለቱ ይታወሳል፡፡ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች ግን በኦሮሚያ ክልል ብቻ 400 ሰዎች መገደላቸውን መግለጹ ይታወሳል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከቀረበው 178 ሰዎች ሞት ሪፖርት በእጅጉ ይርቃል፡፡
የተመድ የሰብዓዊ መብት ካውንስል ቃል አቀባይ የሆኑት ራቪያን ቫ ማዳስኒ፣ ‹‹እየቀረቡ ያሉት ሪፖርቶች በእጅጉ ይለያያሉ፡፡ በተለይ በመንግሥት የቀረበው የሟቾች ቁጥር ትንሽ በመሆኑ ተመድ በራሱ ቡድን ማጣራት ይፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡
ተመድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደማይልክ የገለጹት ቃል አቀባይዋ ሆስፒታሎችን የሚጐበኙ፣ የዓይን እማኞችንና የፀጥታ ኃይሎችን የሚያነጋግር ቡድን ብቻ ለመላክ ጥያቄ ማቅረቡን ጠቁመዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ይሁን እንጂ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ‹‹ተመድ የፈለገውን አስተያየት ሊይዝ ይችላል፡፡ የዜጐችን ሰብዓዊ መብት የመጠበቅ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነት ነው፤›› ሲሉ አስተያየታቸውን ለአልጄዚራ ገልጸዋል፡፡
‹‹የተመድ አጣሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት አያስፈልገውም፡፡ ምክንያቱም ተመድ በኢትዮጵያ የተለያዩ ተቋማት አሉት፤›› ሲሉ አቶ ጌታቸው አስታውቀው፣ የፀጥታ አስከባሪዎች ያላግባብ ኃይል ተጠቅመው ከሆነም መንግሥት በራሱ እንደሚያጣራው ተናግረዋል፡፡
የተመድ የሰብዓዊ መብት አጣሪ ቡድኖችን በመከልከል በተደጋጋሚ ስሟ የሚጠራው ኤርትራ መሆኗ ይታወቃል፡፡

Sunday, August 7, 2016

የጎጃም ህዝብ ለሃይለማሪያም ምላሽ ሰጠ


ወልቃይት የሚለውን ቃል ሕወሃቶች በጭራሽ እንዲነሳ አይፈለጉም። የብአዴን አመራሮችም የወልቃይት ጥያቄ ሕወሃቶችን የሚያበሳጭ በመህኑ በይፋ አይናገሩትም። “የመልካም አስተዳደር ችግር” ብቻ ብለው ነው የሚያልፉት። ሆኖም የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ማእከል ቦታ ይዟል።
ወንጀለኛና ሽብርተኛ ብለው፣ ኮሎኔል ደመቀን ዘዉዱን ወደ መቀሌ ወይም ወደ ማእከላዊ ለመዉሰድ ሕወሃት ደፋ ቀና እያለ እንደሆነና በአዴንም ጫና በዝቶበት እያንገራገረ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሆኖም ግን የጎጃም ህዝብ በማያሻማ መልኩ የጎንደር ነዋሪዎችን ድምጽ በድጋሚ በማስተጋባት “ሁላችንም ኮሎኔል ደመቀ ነን” ብሏል።
ከጥቂት ቀናት በፊት፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የጎንደር ሕዝብ ድምጹን ቢያሰማም፣ የሕዝቡን ድምጽ በመናቅ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባል እና የአማራዉን ህዝብ እወክላለሁ ባይ፣ የፌዴሬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴሩ ካሳ ተክለብርሃኑ፣ ለሕዝብ ትልቅ ንቀት በማሳየት “የወልቃይት ጥያቄ ከተፈታ ቆይቷል። ወልቃይት የትግራይ ናት” ማለታቸው በ እጅጉ የጎጃምን ህዝብ አስቆጥቷል

“ሃይለማሪያም እና ካሳ ተከለ ብርሃን ወልቃይት የትግራይ ናት ማለታቸው በአማራው ህዝብ ላይ ጦርነት አዉጀዋል እንደማለት ነው” በማለት ነበር ተቃዉሟቸውን ያሰሙት።

የለየለት ጦርነት እና አመጽ በአማራው ክልል (በጎንደር ዞኖች)


የሚከተለው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ከስፍራው ደዉሎ ካጠናከረው ዘገባ የተወሰደ ነው። የጎንደር ህዝብ ሰላማዊነቱን ያለፈው እሁድ ሐምሌ 24 አሳይቶ ነበር። ሆኖም እነዚህ ጋኔኖች ህዝቡን ከማክበር ህዝቡ እየሰደቡ፣ በህዝቡ ላይ በሚቆጣጠሪት ሜዲያዛቻ እየሰነዘሩ፣ ንቀት ያለበት የጥጋብ ንግግር እየተናገሩ አካባቢው እንዲታመስ አይደረጉት ነው። የሙሉቀንን ዘገባ እንሆ
ጎንደር፡ የጎንደርና አካባቢው ችግር እየተወሳሰበና በቀላሉም ሊፈታ የማየችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዛሬ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. አንድ የትግራይ ተወላጅ የሆነ ወያኔ ለተጋድሎ በወጡ ዐማሮች ላይ ቦንብ በመወርወር ከሦስት በላይ ሰዎችን ገደለ፡፡ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት ይህን ነፍሰ በላ ሰው ተከላክለው ለማዳን ቢሞክሩም አልቻሉም፤ ከነቤቱ መቃጠሉን ለማወቅ ተችሏል። ይህን ተከትሎ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችን መንግሥታቸው በአየር መንገድ በኩል ሲያጓጉዝ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዛሬ ከጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ወደ መቀሌና አዲስ አበባ በርካታ የትግራይ ተወላጆች መውጣታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
አዘዞ – በአዘዞ ትናንት የተሰው ሰማእታትን ለመቅበር በሚሔዱ ሰዎች ላይ የተኩስ እሩምታ የከፈተው መከላከያ ሠራዊት ሞትን የማይፈሩት የዐማራ ወጣቶች አዘዞ የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ መቆጣጠራቸው ተሰምቷል፡፡ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ ግለሰቦች የሆኑ የንገድ ተቋማት በብዛት መውደማቸው የታወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተኩስ ልውውጥ መኖሩን ለማወቅ ችለናል፡፡
ቆላድባ፡- በደንቢያ ወረዳ የቆላ ድባ ዐማሮች ተጋድሎ ከሁሉም ያየለ እንደነበርም ሰምተናል፡፡ በሌሊት በቁጣ የወጣው የደንቢያ ዐማራ ማንም የሚያቆመው ኃይል ሳይኖር የሥርዓቱ መገልገያ የነበሩ ተቋማትንና ተሸከርካሪዎችን ዶጋ አመድ አድርጓል፡፡ እስካሁን ባለመን መረጃ መሠረት ከዐሥር ያላነሱ መኪናዎች ተቃጥለዋል፤ የብአዴን፣ የአብቁተና ሌሎችም መሥሪያ ቤቶች ወድመዋል፡፡ ከወያኔ መከላከያ ሠራዊት ጋር በበነበረ ተጋድሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዐማሮች የቆሰሉ ሲሆን የሞቱ ሰዎች መኖር አለመኖራቸው የደረሰን መረጃ የለም፡፡
አይባ- ከጭልጋ ሰራባ ካምፕ ወደ ጎንደር በመጓዝ ላይ ከነበረ የትግሬ መከላከያ ጋር በተደረገ ተጋድሎ አይባ ላይ ሁለት ያክል ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡
አርማጭሆ፡- በላይ፣ ታችና ምእራብ አርማጭሆ፣ በጠገዴና በጠረፍ አካባቢዎች ዐማሮች አካባቢያቸውን ነጻ ማውጣታቸውን የተሰማ ቢሆንም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ የሱዳን መንግሥት በምዕራብ አርማጭሆ በኩል ከዐማሮች ላይ ጦርነት መጀመሩን የተሠማ ቢሆንም እስካሁን በስልክ ችግር ማረጋገጥ አልተቻለም (ዜናውን የጠናቀረው ሰው ማረጋገጥ አልቻለም)፡፡
ጋይንት፡- የነፋስ መውጫ ከተማ ዛሬ ከዝናብ ጋር ተጋድሎዋን በጠዋት ነበር የጀመረችው፡፡ ነፋስ መውጫ ዐማሮች ትናንት የታሰሩ ዐማሮችን አስፈትተው ንብረትነቱ የወያኔ የሆነን የእንጨት ክምር አቃጥለዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ አብሮ ለተጋድሎ መሠለፉን ብንሰማም በኋላ ላይ ቁጥራቸው ያልታወቀ ለተጋድሎ የወጡ ወጣቶች መሰዋታቸው ተነግሯል፡፡ ዜናውን ያጠናቀረው ስንት ሰዎች መስዋት እንደሆኑ ሊያወቅ አልቻለም፡፡
 

Saturday, August 6, 2016

This is Ethiopia, Addiss Ababba

ESAT breaking news August 06,2016

ሰበር ዜና አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞች እየተካሄዱ ነው። የፖሊሶችን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ደርሰውናል። በጎንደር ተቃውሞው ቀጥሎአል። ተኩስ ከእያቅጣጫው ይሰማል።

Friday, August 5, 2016

ጎንደር ከተማ ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥር ውጭ ሆናለች


• የትግራይ ልዩ ኃይል አርማጭሆ ወደ አርማጭሆ ሒዶ ዐማሮችን ሊበቀል እንደሚችል ተጠቁሟል
• ሁለት የትግራይ ሠላዮች አርማጭሆ አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት ተገድለው ተገኝተዋል
ዛሬ ማለዳውን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን የፍርድ ሒደት ለመከታተል በመጡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የወያኔ ሠራዊት ተኩስ መክፈቱን ተከትሎ የዐማራ ገበሬዎች የአጸፋ መልስ ሰጥተዋል፡፡ በአጋዚ ጦር እስካሁን የሁለት ዐማሮች ሕይወት ማለፉን ለማወቅ የታቻለ ሲሆን አንድ የትግሬ መከላከያ ተገድሏል፤ በርካታ የፌደራል ፖሊሶችም ቆስለዋል፡፡ 
የትግሬው መንግሥት የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነትን ለማፈን በመፈለጉ መላውን የዐማራ ሕዝብ በቁጣ አነሳስቷል፡፡ ዛሬ ሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. መለው የጎንደር ከተማ ከወያኔ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡ ከአዘዞ እስከ ሸንበቂት ድረስ ያሉ ሁሉም የጎንደር ከተማ መንገዶች ሞት በማይፈሩ ወጣቶችና የታጠቁ ገበሬዎች ተሞልቷል፡፡ የትግሬ መከላከያ ከጭልጋና እና ከባሕር ዳር እንዳይመጣ መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋል፡፡
ከኹመራ፣ ዳንሻሻ ሶሮቃ፣ አብደራፊ፣ ሳንጃ፣ ትክል ድንጋይ፣ አሽሬ፣ ዳባትና ደባርቅ፣ ከበለሳ፣ አዲስ ዘመን፣ ጋይንት፣ ፋርጣና ፎገራ፣ ከደንቢያ፣ ከጯሒት፣ አቸፈር፣ ዳንጋላና ዱር ቤቴ፣ … በቅርብ የሚገኘው የዐማራ ታጣቂ ገበሬ ሁሉ ወደ ጎንደር በመሔድ ከወንድሞቹ ጋር እንዲዋደቅ ተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበ ነው፡፡ የትግሬ መንግሥት ይህን ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሊያቋርጥ ይችላል እየተባለ ነው፡፡
አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ በዳንሻ ከተማ ዐማሮችን ማስፈራራት የቀጠለ ሲሆን አርማጭሆ በመሔድ ዐማሮች ላይ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱ ከዳንሻ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሁለት የትግራይ ሠላዮች ጎንደር ከተማ ሰንብተው ሲመለሱ አርማጭሆ ሲደርሱ ባልታወቀ ምክንያት ተገድለው መገኘታቸው ወያኔን አናዷል፡፡

የብሔራዊ መረጃ የመጨረሻዋ እድሉን በመሞከር ላይ እንደሚገኝ የዉስጥ ምንጮች ገለጹ።


viber image    የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የብሔራዊ መረጃ የመጨረሻዋ እድሉን በመሞከር ላይ እንደሚገኝ የዉስጥ ምንጮች ገለጹ። የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን የአፈናዉ ድርጅት! የጌታቸዉ አሰፋ ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባኒያ! ብሔራዊ መረጃ! ለህዝባዊ እንቢተኝነት መፋፋም ምክንያት ይሆናሉ በሚል መላ ምት ብቻ አርበኞች ግንቦት ሰባት በስነ ምግባር ጉድለት ያሰናበታቸዉን እና ህወሃት ፖለቲካዊ ትርፍ አገኝበታለዉ ብሎ በእቅፍ አበባ የተቀበላቸዉ ግለሰቦች ላይ ቀድሞ ከነበረዉ በላይ ዉስጣዊ ክትትል ምርመራ ተጠናክሮ እንዲካሄድ ወስኖአል። በከተማ ዉስጥና ከከተማ ዉጭ የሚገኙ የመከላከያ ካምፖችን፣ የፖሊስ ጣቢያዎችን፣ የደህንነት መረቦችና መዋቅሮችን፣ የፖለቲካ አራማጅና ፕሮፓጋንዳ ይዘቶችን፣ ቀንደኛ ህወሃታዊ ተቁዋማትና የግለሰብ ድጋፍ አድራጊዎችን ባጠቃላይ የህወሃትን ህልዉና የሚፈታተኑ መረጃዎች በነዚህ ሰዎች አማካኝነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ተላልፎአ በሚል ግምት አንድ አነስተኛ አፋኝ ቡድን አቁዋቁሞአል። በመፈራረስ ላይ የሚገኘዉ የጌታቸዉ አሰፋ የግል ድርጅት ብሄራዊ መረጃ 1. ማስረሻ ቢረዳ 2.ወንዶሰን አሸኔ 3. የሽታ እና ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ላይ ከማነጣጠሩ በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት እየተፋፋመ የሚገኘዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት በዋነኛነት በመረጃ ደረጃ ይመራሉ የሚል ተጨማሪ የክስ ሰነድ እያዘጋጀ እንደሚገኝ ታዉቆአል። የጌታቸዉ አሰፋ አፋኝ ቡድን ለማሕበራዊ ድህረ ገጾች እና ለሚዲያ አዉታሮች መረጃ ይሰጣሉ የተባሉ 9 የመረጃ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፡ በጎንደር የብአዴን ከፍተኛ አመራሮችም የጥቃቱ ሰለባ እንደሚሆኑ የተናገሩት ምንጮች በተለይም ገዱ አንዳርጋቸዉ የአፈናዉ ኢላማ መሆናቸዉ ሲያረጋግጡ የመረጃዉ ጽንፍ ቡድን ገዱ ላይ ምንም አይነት ጥቃት ከማድረስ በፊት ከሐላፊነቱ የሚወርድበት የራሱ ፍቃድ እንዲመጣ ጫና እንዲደረግበት ዉሳኔ ተላልፎአል። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!