ትንናት በምስራቅ ሀረርጌ ቆቦ ከተማ የተጀመረው ተቃውሞ ወደ መሰላ ከተማም ተዛምቷል። የኢህአዴግ ወታደሮች በሚወስዱት ጭካኔ የተሞባለት እርምጃ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። የስርዓቱ ወታደሮች የሚወስዱት ጭካኔ የተሞላበት የሃይል እርምጃ ያሳሰባቸው የክልሉ ነዋሪዎች፣ የህወሃት ንብረት በሆነው ሰላም አውቶብስ ላለመሳፈር እንቅስቃሴ ጀምረዋል:፡ የክልሉ ወኪላችን እንዳለው ዜጎች በሰላም አውቶቡስ አንሳፈርም ማለታቸው ብቻ ሳይሆን፣ አውቶቡሱ በአካባቢው እንዳይንቀሳቀስ እየወሰዱት ያሉት እርምጃ ስጋት ላይ የጣለው ፣ ገዢው ፓርቲ፣ በእያንዳንዱ የሰላም ባስ ተሽከርካሪ ላይ ጠባቂ ወታደሮችን ለመመደብ ተገዷል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአጋዚ ወታደሮች በክልሉ ህዝብ ላይ የወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መከፋፈል መፍጠሩን፣ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላት እየገለጹ ነው።
ከፍተኛ መፈራራትና ቅሬታ አለ የሚሉት ምንጮች፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች “የተወሰደው እርምጃ ተገቢ ነው” ብለው ሌላውን ሰራዊት ለማረጋጋት እየተሯሯጡ ነው። ቅሬታው የእሰፋ በመምጣቱ በመሃል አገር ውስጥ የሚገኙ ወታደሮችና አዛዥ መኮንኖች እርስ በርስ እንዲጠባበቁ እንዳደረጋቸው አክለው ገልጸዋል።
ገዢው ፓርቲ በሚወስደው እርምጃ የተጎዱ በርካታ ዜጎች ፎቶግራፎች በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን እየተሰራጩ ነው።
እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ100 በላይ ሰዎች በወታደሮች ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ታስረዋል።
No comments:
Post a Comment