Friday, May 5, 2017

ጥቂት ስለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ አርበኛ ሃና – ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን


የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን ደስታ እያጣጣምኩ እያለ ድንገት በትዝታ አምስት ወራት ወደ ሁዋላ ሄድኩኝ- -ከኤርትራ በረሃ:: ይህቺን ኢትዮጵያን ከህወሀት እስር ቤት ነጻ ለማውጣት ብረት ያነሳችውን እህታችንን ላስተዋውቃችሁ::
አርበኛ ሀና ትባላለች:: የ23 ዓመት ወጣት ናት:: የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ ወታደር ስትሆን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሳትፋለች:: በኤርትራ በረሃ ስማቸው ከጀግንነት ጋር ከሚነሳላቸው አርበኞች መሃል ሀና ግንባር ቀደም ናት:: ስሟ በአርበኞች መንደር ገኖ ይነሳል::
………አንድ ጊዜ ላይ እንዲህ ሆነ::
ሀና የምትገኝበት ወታደራዊ ክፍል ግዳጅ ይሰጠዋል:: እስከ 30 የሚጠጋ አርበኛ የሚገኝበት ይህ ቡድን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት በአንድ የህወሀት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሞ የመመለስ ግዳጅ ተሰጥቶት ይሰማራል:: ሀና መትረየሷን ታጥቃለች:: ጠዋት ከመነሻቸው ወደ ኢላማ ቦታው ገሰገሱ:: እንደታቀደው ድንገተኛ ጥቃቱ ተሰንዝሮ የታሰበውን ጉዳት አድርሰው ወደ ካምፓቸው ሊመለሱ እያለ ድንገት በህወሀት ሰራዊት ይከበባሉ:: ምን ይደረግ? ብዙ ቁጥር ያለውንና እስከአፍንጫው የታጠቀውን የህወሀት ሰራዊት መክቶ ወደ ካምፕ መመለስ ከባድ ሆነ:: የዚህን ጊዜ ነበር አንድ ጀግና ታሪክ የሰራችው:: ….ሀና::
መትረየሷን መተረች:: ገዢ መሬት ያዘች:: ቦታዋን አስተካከለች:: ….እሷ መስዋዕት ሆና የትግል ጓዶቿን ልታስመልጥ ወሰነች:: ምሽት እየመጣ ነው:: ጓዶቿ ተስናበቷት:: ዳግም በህይወት እንደማያገኟት ታወቃቸው:: …እሷ መትረየሷን ወደ ህወሀት ሰራዊት ለቀቀችው:: ለጓዶቿ ሽፋን በሚሰጥ ስልት አስካካችው:: …ፍልሚያው በአንዲት ሀና እና በህወሀት ሰራዊት መሃል ሆነ:: የሀና መትረየስ ያስካካል:: ጓዶች በዚያ ሽፋን ወደ ጦር ካምፓቸው እየተመለሱ ነው:: የሀና የመትረየስ ድምጽ እየራቃቸው ነው:: እነሱ ይተርፉ ዘንድ አንድ አርበኛ መስዋዕት መሆን ግድ አለ:: በተሰጣቸው ግዳጅ ውጤታማነት እየተደሰቱ የሃናን መስዋዕትነት እያወደሱ ከካምፓቸው ምሽት ላይ ደረሱ:: በአርበኞች መንደር ህይወት እንዲህ ናት:: ታጋይ ይሰዋል:: ትግል ይቀጥላል::
…እኩለ ሌሊት ከመድረሱ በፊት ነው:: ጭው ካለው የኤርትራ በረሃ አንድ ሰው ወደ አርበኞቹ መንደር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅጣጫ ይገሰግሳል:: በርቀት የተመለከቱት የሌሊት የካምፕ ተረኛ ዋርዲያዎች(ጠባቂዎች) መሳሪያቸውን አስተካክለው ጣት ከቃታ አገናኝተው ወደ ካምፑ እየገሰገሰ ያለውን ሰው ይጠብቃሉ:: ውድቅት ሌሊት ስለነበር ማንነት መለየት አልተቻለም:: የሚገሰግሰው ሰው እየቀረበ ሲመጣ ዋርዲያዎቹም ኢላማቸውን አስተካክለው እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጁ:: ….ሰውዬው ቀረበ:: ሴት ናት::ሃና:: ዋርዲያዎቹ አላመኑም:: የዕለቱን የይለፍ ቃል ጠየቋት:: መለሰችላቸው:: ደክሟታል:: ተአምር የሚያሰኘው ከዚይ የህወሀት ሰራዊት ከበባ ማምለጧ አይደለም:: ሁለት የጦር መሳሪያዎችንም ማርካ ተሸክማለች:: ከሷ መትረየስ ጋር ሶስት:: ዋርዲያዎቹ በሚያዩት ነገር ተደንቀዋል:: በአርበኞች መንደር ስለ ሃና እርም ወጥቷል:: ጉድ ተባለ::
….ሃናን በአካል ሳገኛት በጣም ቁጥብ ነበረች:: ብዙ አትናገርም:: ታሪኳን እንድታጫውተኝ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም:: ሲበዛ ዝምተኛ ናት:: ጀግና አይናገርም::
…ሃና ከሰሞኑ ውጊያዎች በአንዱ እንደተሰለፈች እገምታለሁ:: ልብን በኩራት በሚያሞቀው ጀግንነቷ ሁሌም አስታውሳታለሁ:: የጣይቱ ልጅ!!!!!

የነፃነት ሃይሎች ድንገተኛ ጥቃቶች እየሰነዘሩ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ ነው ተባለ


የነፃነት ሃይሎችን ወታደራዊ ና የተጠና ስልታዊ የደፈጣ ጥቃት መቆጣጠር ያቃተው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዘረኛ ቡድን በድንበር አካባቢ የነፃነት ሃይሎችን የደፈጣ ጥቃት ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ወደ ድንበር አካባቢ ተጨማሪ ጦር ያስጠጋ ሲሆን ለሱዳን ተቆርሶ በተሰጠው የኢትዩጲያ መሬት ላይ ከሱዳን ወታደሮች ጋር በመሆን የጥምር ጦር እየመሰረተ ባለበት በዚህ ወቅት በሰሜን ጎንደር፣ በጎጃም ጃዊ ፣ በቤንሻንጉል አካባቢወች የነፃነት ሃይሎች ድንገተኛ ጥቃቶች እየሰነዘሩ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱበት ይገኛል።
በቤንሻንጉል ሸርቆሌ የወርቅ ማውጫ ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት ጦር ሃይል ውስጥ በቅርብ ርቀት በጫካ ውስጥ በቅኝት ላይ ከነበሩት 8 ወታደሮች ላይ ባነጣጠረው የቀስት ጥቃት 5ቱ በእባብ መርዝ በተቀጠቀጠ ቀስት ተወግተው ወዲያውኑ ለሞት ተዳርገዋል።
ቀሪወቹ 3ቱ ወታደሮችም ውስጥ በአንዱ በጀርባው በያዘው ኮሮጆ ተሰንቅሮበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ያመለጠ ሲሆን በአንደኛው በእግሩ ላይ ተወግቶ ደቂቃወችን የቆየ ወታደር እራሱን ለመከላከል በተኮሰው ጥይት አንድ ቀስተኛ ያቆሰለ ሲሆን መሳሪያም እንደተማረኩ ታውቋል።
ይህ ቀስት ሲቀጠቀጥ በከፍተኛ መርዛማ እባቦች መርዝ እንደመሰራቱ የተወሰነ አካሉን ከበሳው ወዲያውኑ መርዞ የመግደል ሃይል እንዳለው ታውቋል።
ከዚህ ጥቃት በኃላ ዙሪያ አካባቢወች እየተፈተሹ ሲሆን ምንም ነገር ሊያገኙ አለመቻላቸው የአገዛዙን ወታደራዊ አዛዦች አስደንግጧል።
ከሰሞኑ በተለያዩ አካባቢወች በደረሰ የቀስት ጥቃት የአገዛዙ ሹመምንት ፣ሚኒሻወች ቤት ለቤት የቀስት ብርበራ እያደረጉ ይገኛል።
በገበያ ቀኖች በከተሞች መውጫ መግቢያ አካባቢ ከፍተኛ ፍተሻ እያደረጉ እንደሚገኝ ተረጋግጧል።