Friday, February 27, 2015

የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ያስደፋ ክስተት

‹‹ያለ ኢኮኖሚ የበላይነት የፖለቲካ የበላይነት አይመጣም››
የሚለው የህውሃት ኢህአዲግ ፖለቲካ ኢኮኖሚውን ከመቆጣጠር ባለፈ ደጋፊዎቹን በኢኮኖሚ በማብቃትና በተጠቃሚነታቸውም ፖለቲካውን በመጠበቅ የበረኛነት ሚና እንዲጫወቱ በ97 ምርጫ ማግስት ከተወሰዱትርካሽ እርምጃዎች አንዱ በግምታዊ አቀማመጥ መሃከለኛ ገቢ ያላቸውን የመርካቶ ጉራጌዎች በማዳከም የህውሃትን ተጠቃሚዎች ማጠናከር ነበር::
የወቅቱ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ ኤርሚያስ ለገሰ ይህንን ይላል

በምርጫ 97 ማግስት አቶ መለስና በረከትን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ ካድሬዎች ‹‹ጉራጌ አብዮት አካሄደብን›› በማለት ይናገሩ ነበር፡፡ በኢህአዴግ ማእከል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የጉራጌ ብሄረሰብ ከትምክህት ጎራ ጋር በተቀላቀሉ ልጆቹ ምክንያት የሀይል አሰላለፍ ቀውስ ውስጥ በመግባት ከጥገኛ ኃሎች ጋር ተሰልፎ ወደ ዝቅጠት ገብቶ እንደነበር ይገልጻል፡፡ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የብሄረሰቡ ተወላጆች(በጉራጌ ዞን ያለውን መዋቅራችንን ጨምሮ) የዜጎችን በነጻነት የማሰብና የመምረጥ መብት በመጋፋት እስከ ጎጣቸው በመሄድ ‹‹ኢህአዴግን የመረጠ ውሻ ይውለድ!›› የሚሉ ቃል ኪዳኖችን እስከ ማጥለቅና መማማል ዘልቀው ነበር በማለት ይከሳቸዋል፡፡ የጉራጌ ብሄረሰብ እንደ ሌሎች የሀገራች ጭቁን ብሄረሰቦች ህገ-መንግስታዊ መብቱ በተከበረበት፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በተጎናጸፈበት ሁኔታ ወደ ትምክህት ሀይል ሽግሽግ ማድረጉ ያልተጠበቀ እንደነበር ሰነዱ አመላከተ፡፡( ቅንፍ የራሴ በምርጫ ኢህአዴግን አለመምረጥ መብት ሳይሆን ትምክህተኝነት የሚባል ሃጥያት ነበር ዛሬም ነው)
በቀረበው ዶክመንት ላይ በመመስረት በየወረዳው የተካሄዱት መድረኮች አስደንጋጮች ነበሩ፡፡ የምርጫ 97 ውጤት የኢትዮጵያ ህዝቦች የትግ ውጤት መሆኑን በመካድ ‹‹ጉራጌ መራሽ አብዮት›› የሚል ስያሜ እስከ መስጠት ተደረሰ፡፡ ጣቶች በሙ ወደ ጉራጌ ብሄረሰብ በተለይም የብሄሩ ተወላጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች ላይ ተቀሰሩ፡፡ ነጋዴው ጸረ-ኢህአዴግ እንዲሆን ከአመታት በፊት የተጠነሰሰ ሴራ እደሆነ በሰፊው ተነገረ፡፡ የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ደፉ፡፡

ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠር ኃይል በሂደት ፖለቲካ ኢኮኖሚው ላይ የበላይነት ማሳረፉ ስለማይቀር ጉራጌን ከንግዱ ዓለም ማስወጣት ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡ ሮማን (የህወሃት ባለሃብቶችን መፍጠር አላማ አስቀጣይ የሆነች) የጉራጌ ነጋዴዎችን እንዳያሰራሩ የምትቀጣበት ምክንያት ይህ ነበር፡፡
እነ ሮማ በፈጠሩት ልዩነት ጉራማሌዋ መርካቶ ይበልጥ ተዘበራረቀች፡፡ ተመሳሳይ እቃዎች በነባሮቹና አዲሶቹ ነጋዴዎች መካከል የዋጋ ልዩነት አሳየ፡፡ የግብርና የሊዝ እፎይታ ያገኙት አዲሶቹ ነጋዴዎች ዋጋቸውን አወረዱ ሸማቹሚስጥሩ ሳይገባው ቅናሽ ወዳገኘበት አዲሶቹ ነጋዴዎች ፊቱን አዞረ፡፡ ቀስ በቀስ ነጋዴው ከገበያ ወጣ፡፡
የማፊያ ባህሪ ያላቸው አዲሶቹ ነጋዴዎች ሰው ሰራሽ እጥረት በመስከሰትም ተወዳዳሪ አልነበራቸውም፡፡ በሰአታት ውስጥ አንድ ኪሎ ጨው ዋጋ ከአንድ ብር 50 ብር የተሸጠበት አጋጣሚ ልብ ይሏል፡፡
ነባሩ ነጋዴ ከገበያ መውጣቱ እልህ የተጋቡት የጉራጌ ካድሬዎቹ እነ ሺሰማ ክትትል ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ሸፍጥ የሚሰራበትን ቦታ ይደርሱበታል፡፡ ሮማንና ወዳጆቿ ፋይል የሚሰርዙና የሚደልዙት፣ ግብር የሚጨምሩትና የሚቀንሱት፣ ሱቅ የሚሰጡትና የሚቀሙት አምባሳደር ፊልም ቤት የሚገኘው ካፍቴሪያ የሕገወጥነቱ ማዕከል ነበር፡፡….
ከምርጫ 97 በኋላ የጉራጌ አብዮትን ለመቀልበስ በስብሰባ ማዕከል በተጠራ የመጀመሪያው ዙር ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ በጉባኤው የተሳተፉት ከአንድ ሺህ በላይ የጉራጌ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ነበሩ፡፡ ይህን ለአንድ ሳምንት የዘለቀ ጉባዔ የመራው ዶ/ር ካሱ ኢላላና ሚኒስትር መኩሪ ነበሩ፡፡ ነጋዴዎች በሲቃ ስለ ሮማንና ሉሌ የሚነሱት ወንጀል ጨጓራ የሚልጥ ነበር፡፡ በተለይ የክፍለ ከተማው የገቢዎች ኤጀንሲ ሙያተኛ የሆነ የጉራጌ ተወላጅ ስራየን ለመልቀቅ ብዙ ተሟግቻለሁ በማለት የገለጸው ታሪክ ዶ/ር ካሱ አንገቱን አቀርቅሮ አንዲቀር አድርጎታል፡፡ ከመቀመጫው ተነስቶ የኮንፈረንሱን ተሳታፊ አንባ እየተናነቀው ይቅርታ ጠይቋል፡፡
እንዲህ ነበር ያደረጉት፣
ሎሌና ሮማን ከቢሮአቸው ሳይወጡ ከአስር እጥፍ በላይ ግብር እንዲጥሉ ሙያተኞችን አስገደዱ፡፡ ከስረው ለመዘጋት አፋፍ ላይ ያሉ ነጋዴዎችን ከግብር ሕጉ በተቃራኒ ታክስ አስከፈሉ፡፡ በድርጊቱ የተበሳጨ አንድ ነጋዴ ራሱን በገመድ አንጠለጠለ፡፡ ተመሳሳይ ሱቅና የንግድ ዓይነት ያላቸውን ጎረቤት ነጋዴዎች አንዱን በዜሮ ፣ሌላውን በአስር ሺዎች ታክስ እንዲከፍል አድርገዋል፡፡ ይህ በዘር ላይ የተመሰረተ እርምጃ ቀድሞ በነጋዴዎች ዘንድ የነበረን በደጋገፍ እንዲቀር በማድረግ እርስ በራስ በጥላቻ እንዲተያዩ አድርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት መሳሪያ የተማዘዙ፣ በገጀራ ተፈነካክተው ወህኒ የወረዱ ነጋዴዎች ይገኙበታል፡፡
(ለግምገማ ቀርባ የነበረችው ሮማን እንዳትጠየቅ አርከበ ተከላክሎ አትርፏታል)

በዓለማችን ትልቁን የማፍያ ቡድን ያውቁታል?? (ማሙሽ ከማል)

እንግዲያውስ ስትሰሙ እንዳትደነግጡ . . . . ረጋ ብላቹ አንብቡት፡፡
Ndrangheta syndicate ይባላል፡፡ ዋና መቀመጫውን በጣልያኗ ካላበሪያ ከተማ ያደረገው ይህ ግሩፕ እንደ ኤ .አ በ1960 ዓ . ም የተመሰረተ ሲሆን ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ከኮሎምብያ እስከ አውስትራልያ የተዘረጋ ግዙፍ መረብ አለው፡፡ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በሗላ በቀጠናቸው ካላብሪስ የሚተላለፉ ስደተኞችን በማገት ስራውን ሀ ብሎ የጀመረው ቡድኑ ለተከታታይ አስር ዓመታትም እያገቱ ቤዛ ሊሆናቸው የሚችለውን በመልመልና በማሰልጠን ኮኬን የተባለውን አደገኛ ዕፅ ለማምረት መጠቀም መጀመራቸው ለቡድኑ እዚህ መድረስ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ ይነገራል፡፡
አብዛኞቹ የካላብሪያ ከተማ ነዋሪዎች ከዙህ ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል፡፡ በተለያየ አለም ላይ ያሉ የቡድኑን ካምፓኒዎችም በዚሁ ከተማ ተወላጆች ስውር ጠባቂነት የሚንቀሳቀሱ ሲሆን የቤተሰባቸው በከተማዋ መቀመጥ እንደ ተያዥ ይቆጠራል፡፡ ማንም ከቡድኑ የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሳ ተቀባይነት አኖረውም፡፡ በድብቅ ከቡድኑ የተገነጠለ እንኳን ቢኖር ተከታትለው ይገሉታል፡፡ ለምሳሌ ካርሜሎ ኖቬላ የተባለ የቡድኑ የሎምባርዴ ክንፍ ሃላፊ የተወሰኑ የቡድኑን እሴቶች ይዞ ለመገንጠል ሲሞክር በ2008 ተገሏል፡፡
ይህ ቡድን ከውንብድና ስራው ውጭ ማንኛውም ለቡድኑ አስጊ የሆነን መንግስታዊም ሆነ የሌላ ማፍያ ቡድን አባል እሳዶ በመግደል የተዋጣለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በ1992 እና በ1994 ዓ. ም ሁለት ከፍተኛ የጣልያን የፀረ-ማፍያ ቡድን ግብረሃይል ሃላፊዎችን ገለዋል፡፡ የጣልያን መንግስት መሰል የማፍያ ቡድኖችን ለማጥፋት ብዙ ግዜ የፀረ- ማፍያ ህጎችን አውጥቶ ቢንቀሳቀስም በዚህ ቡድን ላይ ግን ሊሳካለት አልቻለም፡፡
ከሲሲሊ ፤ ኮሰታስትራስ ከተባሉ መሰል የማፍያ ጉርፖች እጅግ ስውርና ከባድ የአሰራር አደረጃጀት ያለው ይህ ቡድን 80% የሚሆነውን የአውሮፓ የኮኬን ዝውውር ብቻውን እንደሚሰራ ይነገራል፡፡
ባሁን ግዜ በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ከ500 በላይ ትላልቅ ካምፓኒዎች አንዳሉት ይነገራል፡፡ ከቅርብ ግዜ የሽብርተኞች እንቅስቃሴና የአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀውስ ለቢዝነሳቸው ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረና ትርፋማነታቸውን እንዳሳደገው ይነገራል፡፡
ባሁን ሰዓትም 60 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ካፒታል እንዳለቸው ይነገራል፡፡
ይህ ማለት ከጣልያን የጂ .ዲ ፒ (GDP) መጠን ሶስት ፐርሰንቱ መሆኑ ነው፡፡
ወይም የአባይን ግድብ በጀት 11 እጥፍ ማለት ነው፡፡
በፎቶው ላይ የምትመለከቱት በቅርብ በቁጥጥር ስር የወዋለ ከቡድኑ ዋና አንቀሳቃሾች አንዱ ነው፡፡
'በዓለማችን ትልቁን የማፍያ ቡድን ያውቁታል??

(ማሙሽ ከማል)

እንግዲያውስ ስትሰሙ እንዳትደነግጡ . . . . ረጋ ብላቹ አንብቡት፡፡

Ndrangheta syndicate ይባላል፡፡ ዋና መቀመጫውን በጣልያኗ ካላበሪያ ከተማ ያደረገው ይህ ግሩፕ እንደ ኤ .አ  በ1960 ዓ . ም የተመሰረተ ሲሆን ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ከኮሎምብያ እስከ አውስትራልያ የተዘረጋ ግዙፍ መረብ አለው፡፡ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በሗላ በቀጠናቸው ካላብሪስ የሚተላለፉ ስደተኞችን በማገት ስራውን ሀ ብሎ የጀመረው ቡድኑ  ለተከታታይ አስር ዓመታትም እያገቱ ቤዛ ሊሆናቸው የሚችለውን በመልመልና በማሰልጠን  ኮኬን የተባለውን አደገኛ ዕፅ ለማምረት መጠቀም መጀመራቸው ለቡድኑ እዚህ መድረስ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ ይነገራል፡፡

አብዛኞቹ የካላብሪያ ከተማ ነዋሪዎች ከዙህ ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል፡፡ በተለያየ አለም ላይ ያሉ የቡድኑን ካምፓኒዎችም በዚሁ ከተማ ተወላጆች ስውር ጠባቂነት የሚንቀሳቀሱ ሲሆን የቤተሰባቸው በከተማዋ መቀመጥ እንደ ተያዥ ይቆጠራል፡፡ ማንም ከቡድኑ የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሳ ተቀባይነት አኖረውም፡፡ በድብቅ ከቡድኑ የተገነጠለ እንኳን ቢኖር ተከታትለው ይገሉታል፡፡ ለምሳሌ ካርሜሎ ኖቬላ የተባለ የቡድኑ የሎምባርዴ ክንፍ ሃላፊ የተወሰኑ የቡድኑን እሴቶች ይዞ ለመገንጠል ሲሞክር በ2008 ተገሏል፡፡

ይህ ቡድን ከውንብድና ስራው ውጭ ማንኛውም ለቡድኑ አስጊ የሆነን መንግስታዊም ሆነ የሌላ ማፍያ ቡድን አባል እሳዶ በመግደል የተዋጣለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በ1992 እና በ1994 ዓ. ም ሁለት ከፍተኛ የጣልያን የፀረ-ማፍያ ቡድን ግብረሃይል ሃላፊዎችን ገለዋል፡፡ የጣልያን መንግስት መሰል የማፍያ ቡድኖችን ለማጥፋት ብዙ ግዜ የፀረ- ማፍያ ህጎችን አውጥቶ ቢንቀሳቀስም በዚህ ቡድን ላይ ግን ሊሳካለት  አልቻለም፡፡

ከሲሲሊ ፤ ኮሰታስትራስ ከተባሉ መሰል የማፍያ ጉርፖች እጅግ ስውርና ከባድ የአሰራር አደረጃጀት ያለው ይህ ቡድን 80% የሚሆነውን የአውሮፓ የኮኬን ዝውውር ብቻውን እንደሚሰራ ይነገራል፡፡

ባሁን ግዜ በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ከ500 በላይ ትላልቅ ካምፓኒዎች አንዳሉት ይነገራል፡፡ ከቅርብ ግዜ የሽብርተኞች እንቅስቃሴና የአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀውስ ለቢዝነሳቸው ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረና ትርፋማነታቸውን እንዳሳደገው ይነገራል፡፡

ባሁን ሰዓትም 60 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ካፒታል እንዳለቸው ይነገራል፡፡

ይህ ማለት ከጣልያን የጂ .ዲ ፒ (GDP) መጠን ሶስት ፐርሰንቱ መሆኑ ነው፡፡

ወይም የአባይን ግድብ በጀት 11 እጥፍ ማለት ነው፡፡

በፎቶው ላይ የምትመለከቱት በቅርብ በቁጥጥር ስር የወዋለ  ከቡድኑ ዋና አንቀሳቃሾች አንዱ ነው፡፡'

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ISIS በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት የተቀመጠው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ የእስልምና እምነት ተከታዬች ፍጹም ጨዋዎች መሆናቸውን ለመመልከት ላለፉት ሶስት ዓመታት በአገሪቱ ያደረጓቸውን ሰላማዊ ተቃውሞዎች መታዘብ ይበቃል፡፡ሺህዎች በታደሙባቸው ተቃውሞዎች አማንያኑ የሚጤስ ጧፍን ሳያጠፉ ቅጥቅጥ ሸንበቆ ሳይሰብሩ ወደየቤታቸው ተመልሰዋል፡፡
እነዚሁ ሙስሊሞች ፓርቲዎች በጠሯቸው ሰላማዊ ሰልፎች (አንድነትና ሰማያዊ) በመገኘት አቡበከር እንዲፈታ የጠየቁትን ያህል እስክንድር ነጋ፣ርዕዮት ዓለሙ፣አንዷለም አራጌና ሌሎችም ነጻነታቸውን እንዲያገኙ ጠይቀዋል፡፡
ዛሬ አርብ ከጁምዓ ሰሏት በኋላ ደግሞ ይህንኑ ድምጻቸውን ያስተጋባሉ፡፡
በአንጻሩ ስርዓቱ ISISዊ ተግባሩን በወታደሮቹ በኩል በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡እነ ጋዜጠኛ የሱፍና ሰለሞን በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ የተፈጸመባቸው ማሰቃየት ፣በኮፈሌ፣ደሴ፣በአዲስ አበባና በሌሎች ስፍራዎች አይ ኤስ አይ ኤስ (ፌደራል ፖሊስ) በወሰደው ጭፍን እርምጃ ብዙዎች ደማቸው ፈሶ ይህችን ዓለም ተለይተዋል፡፡ይህ ድርጊት መንግስታዊው ISIS የፈጸመው ከማለት ውጪ ምን ሊሰኝ ይችላል ?
ሽብርተኛው ቡድን ያርዳል፣ያሰቃያል፣ሰብዓዊ ክብርን ያዋርዳል ፡፡ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ይሀንን አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ነገር ግን በመንግስታዊው ሽብርተኛ ቡድን ይታሰራሉ፣ባልዋሉበት በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመሰረት አሲረናል በሉ ተብለው እንዲፈርሙ ይደረጋሉ፣ውሃ የተሞሉ ላስቲኮች ብልታቸው ላይ ተንጠልጥሎ፣እግራቸው ተገልብጦ ይገረፋሉ፣በአፍጋኒስታን፣በኢራቅ ፣በሶማሊያ ስልጠና ወስደናል እንዲሉ ይገደዳሉ፣መንግስት የለም ወይ በማለታቸው ብቻ በአደባባይ ይረገጣሉ፣በጥይት ይመታሉ፣መንግስት በሚቆጣጠረው ሚዲያ ሹማምንት ቀርበው ‹‹ሽብርተኞች ፣ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የተላኩ የጥፋት መልእክተኞች ይባላሉ፣ጥናት አቀረብን የሚሉ የሌላ ሐይማኖት መምህራን ኢትዮጵያዊያኑ ሙስሊሞች እየደረሰባቸው የሚገኘውን የመብት ጥሰት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ‹‹አክራሪዎች ››ይሏቸዋል፡፡
እውነት ብትቀጥንም ፈጽማ የማትጠፋ መሆኗ ግን የትግል ተስፋ ነው የሚለው ማን ነበር?

Thursday, February 26, 2015

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን። በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡ ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡ የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት የካቲት 19 2007 ዓ/ም

ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ

'ሁላችንም በተባበረ ክንድ ቦይኮት እናረጋለን  !! ወያኔን እናከስረዋለን!!!!

‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› - ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ

ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!

/ (y) ////ሼር በማደረግ ያሰራጩ ///// (y)

መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን

በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ

ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ

የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ

ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም

በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው

ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡

ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን

በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም

ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡

አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡

ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው

መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን

እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ

አይደለምና!!!

አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ!

አላሁ አክበር!

Like ☑ Comment ☑ Share ☑'
‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!
መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን
በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ
የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ
ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም
በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው
ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን
በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም
ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡
አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡
ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው
መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን
እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ
አይደለምና!!!
አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!

ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፣ከኤርሚያስ ለገሰ /የመለስ ትሩፋቶች /የተሰጠ ምላሽ

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ።
1• ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት( ከኃላም ከፊትም) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው።
1•1• በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2001 አ• ም• ኢሕአዴግ ለሕዝቡ ይዞለት የመጣው እቅድ ” በአክራሪነት ” ስም ሀይማኖቶችን ማዳከም ነበር። ይህንንም ለማቀጣጠል እንዲረዳው በኢህአዴግ ቢሮ፣ በኮሙዩኒኬሽን ጵ/ ቤት፣ ፌደራል ጉዳዬች እና ፌደራል ፓሊስ መረጃ እንዲሰባሰቡ ተደረገ። የእስልምና ጉዳዬች ላይ ዝርዝር ጥናቱን እንዲሰራ የቤትስራ የተሰጠው ሽመልስ ከማል ነበር። ዛሬ አንተ ካቀረብክልን ውስጥ ግማሹ የቃላት ለውጥ እንኳን ሳይደረግለት በሽመልስ ከማል ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ነበር። በወቅቱ እጅግ ከመደንገጤ የተነሳ ሽመልስ እንዴት እንዲህ አይነት ጥናት እንደሰራ ለማወቅ ከጀርባው መጓዝ ነበረብኝ ። መጓዜ ያልጠበኩትን ውጤት አመጣ። ሽመልስ በእስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የያዘው በቤተሰቡ ውስጥ በተፈጠረው ምስቅልቅል እድገት መሆኑን ተገነዘብኩ። አባቱ በአንድ ወቅት የመስኪድ አስተዳደር ነበሩ። በኃላ የሳውዲ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ አስተዳደሩን በመነጠቃቸው ከሀይማኖቱ በተቃራኒ ተሰለፋ ። ” ከመካ መዲና ደርሶ መልስ” የሚል መጵሀፍ አሳትመው ክርስትና ተነሱ። ስማቸውም ወደ ሀይለየሱስ ተቀየረ። ባስታወቀው እርምጃ ቤታቸው ተመሰቃቀለ። ወንድማማች እና እህታማቾች የሚጠሩበት የአባት ስም እስከ መለያየት ደረሰ። ባጭሩ የሽመልስ ፀረ -እስላም የመሆን ምንጩ ይሄ ነው። በመሆኑም በሽመልስ ሲቀርቡ የነበሩ ዳታዎችና ትንታኔዎች እንደወረዱ ከአንተ ሲቀርቡ ስሰማ የመረጃ ምንጭህን ተጠራጠርኩ። በተለይ ቴኳንዶ ፣አክሱም፣ መያዶች …ወዘተ ብለህ የገለጵከው የካርቦን ግልባጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
1•2• ሌላኛው ዳታ የሰበሰበው የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር የነበረው ዶክተር ሽፈራው ከፓሊስ ጋር በመሆን ነበር። ዶክተሩ ያጠናቀረው መረጃ ተመሳሳይ ሲሆን በማጠቃለያው ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት አለ” የሚል ነበር። የአክራሪነቱ አስኳል ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቶበት ነበር። ይህ የዶክተሩ መረጃ በአንተ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ አልቀረበም ።
( ግምቴን አስቀምጬ ለማለፍ ይህን የዶክተር ሽፈራው ዳታና ትንታኔ ለሌላ የእስልምና መምህር እንዲደርሰው ይደረግና እንደአንተ እንዲያቀርብ ይደረጋል ። ርዕሱንም ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት ” ብሎ እንዲጠራው ይደረጋል ።)
2• የመረጃዎቹ ምንጭ እንደተጠበቀ ሆኖ ኩነቶቹ ሲፈጠሩ ሀገሪቷ የነበረችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ ከግምት አላስገባህም። ለምሳሌ ከምርጫ 97 በኃላ በኦሮሚያ የተከሰቱት የሐይማኖት ግጭቶች የተጠነሰሱት በአቶ መለስና ደህንነት ጵ/ ቤት ሲሆን ዋነኛ አሰፈጳሚዎቹ እነ አባዱላና የኦህዴድ ካድሬዎች ነበሩ። ” ቅንጅት የክርስቲያን ጠበቃ ነው” የሚለው መልእክት የተቀረፀው አንተ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ ” ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” የሚለው መርሆ አቀንቃኝ የሆነው አቶ በረከት ነው። በየጉራንጉሩ መልእክቱን ያሰራጩት ደግሞ ” እኔ ከሞትኩ… ” በሚለው ብሂል እነ አባዱላና ጁነዲን ናቸው። በተለይ በድሬደዋ የጠነሰሱት ሴራ ባይከሽፍ ኖሮ ዘግናኝ እልቂት ይከሰት ነበር። በመሆኑም ከምርጫ 97 በኃላ የተከሰቱት ግጭቶች ( በተለይ በኦሮሚያ) ጠንሳሾቹ አሁን እየመሩን ያሉት ፓለቲከኞች ሲሆኑ መንስኤውም ፓለቲካው የፈጠረው ነበር። አንተ ግን በየትኛው ቦታ ላይ የፓለቲከኞቹን ሚና ማንሳት አልፈለክም ። ይልቁንስ መንግስት አበረደው፣ መከላከያ አረገበው ማለትን መርጠሀል። ጥናትህን ሰፋ ብታደርገው ኢትየጵያ ውስጥ አክራሪነት በዋነኛነት እየሰፋ የሄደው በፓለቲካው መበላሸት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ትደርስበት ነበር። አሁንማ በድጋሚ ለማየት ጊዜው አልረፈደም።
3• በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች ” ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ” ማንሳት አልፈለክም ። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃወሙት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ነው።ኢህአዴግ ከሀይማኖቱ ላይ እጁን እንዲያነሳ ነው በሰላማዊ መንገድ እየጠየቁ ያሉት። አመራራችን በእኛ ይመረጡ፣ ተቋማችንን ራሳችን እናስተዳድር የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ እኔ በየትኛውም ቦታና ሰአት ምስክር መሆን እችላለሁ። ታዲያ አክራሪን፣ አክራሪ ካልሆነው ለይቶ የማስረዳት አላማ ካነገብክ ለምን ፍትሐዊ የሆነውን ይህን ጥያቄ ሳታነሳ ቀረህ? እንደ ገዥዎቻችን ” የሙስሊሙ ጥያቄ አክራሪነት የወለደው ነው” የምትለን ከሆነም ወደ መድረክ አውጣውና እንነጋገርበት ።
4• አጀንዳህ ስለ ” ሙስሊም አክራሪነት ” ሆኖ ወደ ማጠቃለያህ ላይ በውጭ ሀገር ያለውን ሲኖዶስ ወደ መዝለፍ ለምን ተሸጋገርክ። ከአንደበትህ የወጣው ቃል ” የሐሰት ሲኖዶስ ተቋቁሞ መንጋ የማይጠብቅ ጳጳሳት ይሾማል ” የሚል ነው። ይህ ንግግር በራሱ አንድነት የሚያመጣ ነው? ውጭ ያለው ሲኖዶስ የሐሰት ነው / አይደለም ከሚለው ትርክት በፊት ይህ እንዲፈጠር ያደረገው ምክንያት ምንድነው የሚለውን ብታነሳ የተሻለ መልስ ታገኝ እንደነበር እገምታለሁ። ሐገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ ማን ከጀርባ ሆኖ እንደሚያሽከረክረው ካላወክ በኢትዮጵያ ምህዳር ላይ መኖርህን እንድጠራጠር ያደርገኛል።
4• ሌላኛው ” ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር አለ?” የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጐኛል ። የሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በተጠናከረበት፣ መንግስት በጅምላ ማሰር በጀመረበት ፣ ማህበረ ቅዱሳን ላይ በተዛተበት ወቅት ለምን የሚከፋፍል አጀንዳ ይዞ ብቅ ማለት ተፈለገ? የማን አጀንዳ ነው እየተራመደ ያለው የሚለውን ማየት ተገቢ ይሆናል
Ermias Legess / የ መለስ ትሩፋቶች/

በወላይታ ዞን 30 የሰማያዊ አባላትና ደጋፊዎች ታሰሩ

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን 30 የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች መታሰራቸውን የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ አስታወቁ፡፡
ከዞኑ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ታደመ ፍቃዱ እና ፓርቲውን በመወከል ለተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት መምህር አለማየሁ አዴ እንደገለጹት በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ልዩ ስሙ ዋቺጋ አሼ በተባለ ቀበሌ 30 የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ከትናንት በስቲያ (የካቲት 17/2007 ዓ.ም) ለእስር ተዳርገዋል፡፡
አቶ ታደመ ፍቃዱ እንዳስረዱት አባላቱና ደጋፊዎቹ የታሰሩት ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን ለምን ትደግፋላችሁ፣ ለምን አባል ትሆናላችሁ…ፓርቲው እኮ ከምርጫ ታግዷል፣ ህገ-ወጥ ነው›› በሚል ሰበብ ስሙን እንኳን ‹‹ሰማያዊ ብላችሁ አትጥሩ›› ተብለው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከታሳሪዎች መካከል አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን የሚገልጹት መምህር አለማየሁ በበኩላቸው እስረኞችን እንዳነጋገሯቸው በመጥቀስ፣ ‹‹የምትመርጡት ማንን እንደሆነ እናውቃለን፣ ሌላ ፓርቲ መምረጥ የለባችሁም….ኢህአዴግን ነው መምረጥ የሚኖርባችሁ›› እያሉ እንደሚያስፈራሯቸው አስረድተዋል፡፡
መምህር አለማየሁ አዴ ‹‹አንተ ለምን ልትጠይቃቸው መጣህ›› ተብለው እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውሰው፣ እስረኞቹ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንም ገልጸዋል፡፡ አባላትና ደጋፊዎቹ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በእስር ላይ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የፊታችን አርብ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል «እስር ከትግላችን አያስቆመንም!» ድምጻችን ይሰማ!!

መንግስት ህገ መንግስታዊ መብቶቻችንን በመጣስ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ በደል ሲፈጽምብን ቆይቷል። እኛም እንደህዝብ ድምጻችንን አዋህደን እና በአንድነት ቆመን ሰላማዊ ትግል ስናካሂድ ቆይተናል። ትግላችን እስካሁን አንድም ከሰላማዊነት መርህ ዝንፍ ሳይል የቀጠለ ሲሆን መንግስት ትግሉን ለማስቆም የሚወስዳቸው ግልብ እና አገር አጥፊ እርምጃዎችም ከመርሃችን ሊያዛንፉን እንደማይችሉ በተደጋጋሚ በተግባር ለማረጋገጥ ችለናል።
ሰሞኑን መንግስት በተለመደው ግፍ መር እርምጃው በርካታ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን በማሰር ዘመቻ ላይ ተጠምዷል። አንዳችም ጥፋት ያልፈጸሙ ወጣቶችንም የ28 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ በመጠየቅ ወደማጎሪያ ካምፖቹ አስገብቷል። ይህ «ሙስሊሞችን በማሰር ከትግላቸው አስቆማለሁ!» ከሚል መናኛ ቀቢጸ ተስፋ እና ባዶ ምኞት የመነጨ ለመሆኑ እማኝ መጥራት አያሻም – ካሁን ቀደምም መንግስት ሲፈጽመው የቆየው፣ ግና ሊያሳካቸው ያልቻለው ህልሙ ነውና!
አዎን! ደጋግመን ስናሳይ እንደቆየነው ሁሉ ህዝብን ማንገላታት አንጂ ማሸነፍ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም! ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው! በአላህ ፈቃድ ያሸንፋልም! ይህን ህገወጥ እና ሊሳካ የማይችል እኩይ የመንግስት ምኞት በተለያዩ ስልቶች መታገል የነፍስ ወከፍ ሐላፊነታችን የሚሆነውም ለዚሁ እንጂ ለሌላ አይደለም። በመሆኑም ከነገ ወዲያ አርብ የካቲት 20/2007 መላው አገሪቱን ያሳተፈ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል። የተቃውሞውን መርሃ ግብር አስመልክቶ በነገው እለት የምናሳውቅ በመሆኑ እስከዚያው መረጃውን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ ተዘጋጅተን እንጠብቅ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን ገለጸ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸው በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን የትብብሩ ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ዕጩዎቻችን በዝርዝር ሊያሳውቀን አልቻለም፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ከምንም በላይ ግን በዕጩዎች ስረዛና ወከባ በርካታ ጊዜ አጥፍቶብናል፡፡›› ሲሉም ሰልፉ የተራዘመበትን ምክንያት ገልጸዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ የትብብሩን አባል ፓርቲዎች ዕጩዎች በዝርዝር ባለማሳወቁ፣ አባል ፓርቲዎቹ ለምርጫ ቦርድ ቅሬታ እያቀረቡ በመሆኑና አሁንም ድረስ ከምርጫ ቦርድ ጋር ያሉት ችግሮች ያልተፈቱ በመሆናቸው ትብብሩ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀን ወደፊት ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል፡፡

በአሰሪዎቾ የታገተችው ኢትዮጵያዊት የሰቆቃ ደምጽ !

ገነት አበበ ሞላ ትባላለች የልጅነት ግዜዎን ሩጣ ያልጠገበች በ አስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ኮረዳ ነች። ከዛሬ 3 አመት በፊት ነበር በኑሮ ውድነት የተጎሳቆሉ ቤትሰቦቾን ከደህንነት ለመታደግ በወቅቱ እስከ ገጠር በዘለቀው የአሰሪና ሰራተኛ የደላሎች ዘመቻ ከአርሲ ኮሌ ወረዳ ኩዬ ከተማ ተመልምላ የማይጨበጠውን የአረቡን ዓለም መከራ ለመጋፈጥ፡ተስፋ ሰንቃ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናቸው ። በወቅቱ በስው ልጆች ህይወት ዶላር ለማግበስበስ በየአካባቢው በተከፈቱ የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች ከእናቶቻቸው ጉያ ተነጥቀው ለአቅመ ሄዋን ያለደረሰውን እድሜዎቻቸውን ቆልለው ፓስፖርት የወሰዱ ህጻናት ሳይቀሩ በቀን ከስክ 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የኮንተራት ሰራተኞች የለህይወት ዋስትና ወደ ሳውዲ አረቢያ በጅምላ ይላኩ የነበረበት ወቅት በመሆኑ ወጣት ገነትም ሰው እንደሆነው እሆናለሁ ብላ በፌስታል የተሞሉ ልብሶቾን እንደነገሩ ይዛ ነበር የምተወዳቸውን ወላጆቾኝ በዕንባ የተሰናበተቸው ። አንድም ቀን ከቤት ወጥታ የማታውቀው ገነት አስረክበው ወደ ቀዬያቸው የተመለሱ ወላጆቾ የገነትን ድምጽ ቢናፍቁም ባህር አቋርጣ ሳውዲ ሄደች ከተባለ ወዲህ ወራት ተቆጥረው ዓመት ቢደፍንም ገነትን የበላ ጀብ አልጮህ አለ ።
ወትሮስ ለማን አቤት ሊባል ? « የገነትን ስቃይ ማን ይወቅላት » ክፉ አጋጣሚ ሆኖ በአሰሪዎቾ « ኃይል» ወደ ሚባል ገጠራማ የሳውዲ ግዛት ለስራ የተወሰደችው ገነት ወግ ባህሉ ቋንቋው ባዕድ በሆነባት ሃገር ሁሉም ነገር እንዳሰበቸው እና እንደተነገራት አልነበረም። ታዲያ ገነት ከቤትሰቦቾ ጋር ስትለያይ ሲያነቡ የነበሩት አይኗቾ እንባ እንደቋጠሩ ነበር ፍጹም ከባድ የሆነውን የአረቡን ዓለም የቤት ስራ የተጋፈጠቸው ፡፤ በማለዳው ምናምን ቢጤ ቀማምሳ ለአመታት ተጠርጎ የሚያውቀውን አቧራ የለበስና ቆሻሻ የተከመረበትን ግቢ ከአሰሪዎቾ በምለክት በተሰጣት ተዕዛዝ ስታፀዳና ከ 4 ያላነሱ መኪኖችን ስታጥብ የዋለቸው ። በዚህ መልኩ ለወራት የተዋሃዳትን የአሰሪዎን የቤት ውስጥ ስራ ጨምሮ የማይመለክታትን ከባድ ስራዎች ሁሉ ካጠናቀቀች በኃላ ለሌላ አረብ ተላልፋ እይተሰጠች የቤት ሰራተኛ ለሌላቸው የሰፈሩ አረቦች ሁሉ አገልጋይ ሆናለች ። ገነት እረፍት የላትም እንደ ዘበኛ መኪና በመጣ ቁጠር የግቢ በር ትከፍታለች የአሰሪዎቾን መኪናና ግቢ ታጥባለች ከባድና ቀላል የሆኑ እቃዎችን እስከ 3ኛ ፎቅ ተሸክማ በመውጣት ከአቅሞ በላይ የሆነና የማይመለከታትን ስራ በግዳጅ እንድትሰራ ትደረጋለች። ከቤተሰቦቾ ከተለየች ወዲህ በስልክ ወላጆቾን አጊታቸው የማታውቀው ገነት ከሥራው ክብደት ይልቅ በናፍቆት ከሰውነት ጎዳና የወጣው ስውነቷና የልጅነት ወዝዎ በቁም የተገነዘች ሬሳ አስመስሏታል ፡፡
በአስሪዎቾ ታግት በደል የሚፈጸምባት ገነት ከሚፈፀምባት ግፍ እና በደል እግር ወደ መራት በመሄድ እርሷን ከባርነት ለመታደግ የሞከርቸበትም አጋጣሚ እደነበር ይነገራል። ከዚያ ወዲህ ገነትን ለማግባባት ብዙ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው የተረዱት አሰሪዎቾ ገነት ላይ የሚያደርጉትን ክትትል በማጠናከር የስራ ግዳጆዎን ስትጨርስ ባዶ ቤት ይቆለፉባታል። የቤት ሰራተኛ እጥርት የገጠማት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በአሰሪዎቾ የታገተቸው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ገነት አበበ ለአሰሪዎቾ እያበረከተች ካለው ነጻ አገልግሎት ባሻገር በወር እስከ 3800 በሚደርስ ክፍያ ለሦስተኛ ወገን ተላልፋ በመሰጠት ጥሩ የገቢ ምንጭ እስከ መሆን መድረሷ ይነገራል። ከአንዱ የአረብ መኖሪያ ወደ ሌላው የአረብ መኖሪያ ቤት እይተቀባበሉ ያለ በቂ እረፍት የአረብ አገልጋይ ለመሆን የተገደደቸውን ኢትዮጵያዊት የኮንተራት ሰራተኛ ከማለት ይልቅ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ህጋዊ ፈቃድ አጊቶ በሚንቀሳቀስ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የተሸጥች ባሪያ ማለት ይቀላል።
አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ሚክሲኮ አደባባይ አካባቢ ሴብሪን « sebirn » እይተባለ በሚጠራ አንድ ኤጀንሲ አማካኝነት ተዋውላ ህጋዊ በሆነ መንገድ ለስራ ሳውዲ እንደገባች የሚነገርላት ገነት ዛሬም የይደርሱልኝ ይሰቅቃ ድምጾን ታሰማለች ፡፤
አሁን አሁን ለህይወቷ የምትሳሳው ገነት ይገሉኛል በሚል ስጋት በድብደባ ከተጓሳቆለው አካሏዎ ባሻገር ሌሎች ምስጢራዊ በደሎችን ለግዜው ከመግለጽ መቆጠቧን ለልጅቷ ቅረበት ያላቸው ወገኖች ይገልጻሉ። እነዚህ ወገኖች አቤቱታቸውን በጅዳ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ቢገልጹም እስክ አሁን የገነት የሰቆቃ ድምጽ ምላሽ አላገኘም፤
Ethiopian Hagere Jed Bewadi

Tuesday, February 24, 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡
ከሁሉም በላይ በየመንገዱ ጠመንጃ የያዘ ሊያስፈራራን የሚሞክር ሆድአደር እያየን፣ እንደዚሁም በየጫካው ያሉትን እያሰብን ሰላማችንን ከምናጣ አበባውን ትተን፣ ሩዙን ትተን፣ የተወደደልንን ጤፋችንን እያመረትን አዲስ ኑሮ ብንጀምር የተሻለ ነበር፡፡
ግን አንድ እንቅፋት አለብን፤ እነዚህ ከየኪዮስኩ እውቀት ገዝተን አዋቂዎች ሆነናል የሚሉት እንትኖች እንመጀመሪያ ችግሩ እንዲገባቸው፣ ሁለተኛ መፍትሔው እንዲገባቸው፣ ሦስተኛ ጉልበትና እውቀት አንድ አለመሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በጉልበት እውቀት የማይገኝ መሆኑን ማሳመን በረዶ እየወረደ የስሜን ተራራን መውጣት ነው፤ በረዶ ሳይኖር ወጥቼዋለሁ!
እነዚህን የጉልበት አዋቂዎች — ስለሽማጌሌዎችና አሮጊቶች ሳያስቡ፣ ስለመብራት ኃይል ሳያስቡ፣ ስለውሀ ሳያስቡ ሁሉም በጉልበት ፎቅ ይውጣ የሚሉ! ይባስ ብለው ለእስረኛውም ፎቅ እየሠሩለት ውጣ! ሊሉት ነው!
እነዚህ የጉልበት አዋቂዎች የአበሻ ኑሮ፣ ቡናው፣ ሙቀጫው፣ ምጣዱ፣ በርበሬው፣ ቁሌቱ፣ ቄጤማው፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ ኧረ ስንቱ! ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው! እናውቃለን ስለሚሉ እንዴትስ ይማራለ? በእውነት ለመማር ቢፈልጉስ ስንት ዓመት ሊያስፈልጋቸው ነው! እግዚአብሔር እንሱንም እኛንም በምሕረቱ ይጎብኘን! የሚያስተምር ጎረቤት አያሳጣን!

የዚህ ሁሉ እልቂት “ኩሹፍ” ሲገለጥ( አርአያ ተስፋማሪያም)

ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም፣ ባለቤታቸውና ሌሎች አንገታቸው ላይ ስላጠለቁት በተመለከተ አንድ የቀድሞ አንጋፋ የድርጅቱ ታጋይ በግል ያደረሱኝ መልእክት እንዲህ ሲል ይጀምራል « በታጋዮች ዘንድ “ኩሹፍ” ተብሎ ይጠራል። ታጋዩ ከሞተ በኋላ የሚገነዝበት ጨርቅ ነው። ድርጅቱ አላማ ያለው የመሰለው አብዛኛው ታጋይ ያን ጨርቅ አንገቱ ላይ በማጥለቅ ለመሰዋት (ለመሞት) ቁርጠኝነቱን የሚያሳይበት ነበር። 98 በመቶ የሚሆነው ተዋጊ ያልተማረ ስለነበረ የድርጅቱ አላማና አካሄድ ሊያውቅበት የሚችል አንድም መንገድ አልነበረም። በእሱ ደምና አጥንት ተረማምደው ሲያበቁ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ አስፈፀሙ። 36 ሺህ የህወሀት ታጋዮችን ገና በጠዋቱ አባረው ለአስከፊ የጐዳና ህይወት ዳረጓቸው። ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን በብሄር ፖለቲካ እርስ በርስ እንዲናቆሩ እነመለስ የጥፋት ወጥመድ ዘረጉ። “ፓርቲው ወዴት እየሄደ ነው?..ግምገማ መካሄድ አለበት፤ ሙስና ተቀጣጥሏል..” የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሱና ከጋንታ እስከ ሬጅመንት አዛዥነት (ኋላ መኮንኖች) ቦታ የነበራቸው 5 ሺህ ታጋዮች ሆለታና ታጠቅ እስር ቤቶች ታጐሩ። አቶ መለስ 36 ሺህ ታጋይ በ84 ዓ.ም ሲያባርሩ «ጓሃፍ ፅረጉለይ..» ማለትም “እነዚህን ቁሻሻ ጥራጊዎች አስወግዱልኝ” ነበር ያሉት። ትእዛዙን ደግሞ ስዬ አብርሃ ተፈፃሚ አደረጉ። ለ5 ሺህ መኮንኖች ደግሞ ያቀረቡት ሰበብ «መፈንቅለ ፓርቲ ለማድረግና እኔን ለመገልበጥ ሲያሴሩ..» የሚል የፈጠራ ክስ በመለስ ዜናዊ ቀረበባቸው። በሆለታ እስር ቤት በ1988 ዓ.ም እንዶድ የተባለ መርዝ ጨቅጭቀው የጠጡ 1 ሺህ 5 መቶ (1,500) መኮንኖች ህይወታቸው ሲያልፍ የሁሉም ሬሳ በአንድ ጉድጓድ በሌሊት እንዲከተት ተደረገ። በታጠቅ ከ1 ሺህ የሚበልጡ በተላላፊ ሳንባ እንዲያልቁ ተፈረደባቸው። የዚህ ሁሉ እልቂት ምስጢሩ ታጋዮቹ “የሃየሎም ግሩፕ” በሚል በነመለስ ስለተፈረጁ ነበር። እነሱን ከጨረሱ በኋላ እሱንም አስገደሉት። ሃቁ ይህ ሲሆን ዛሬ እነሃ/ማርያምና ሌሎቹ ባልዋሉበትና ባልነበሩበት ትግል ያን “ሽኩፍ” አጥልቀው መታየታቸው ያሳፍራል። ለነገሩ በታጋዩ መስዋእትነት የተረማመዱት የዛሬው ሚሊየነሮች አጥልቀው ታይተው የለ!! ታሪክና ጊዜ ይፈርደናል!» ይላል። …በነገራችን ላይ የሆለታና ታጠቅ እስር ቤት የጅምላ እልቂትና ስቃይ በተመለከተ በ1994 ዓ.ም ጥቅምት ወር አንስቶ የአንዳንድ ሟች ታጋዮች ፎቶ በማስደገፍ እንዲሁም በእስር ቤት የፃፏቸውን መልእክቶች በማያያዝ በኢትኦጵ ጋዜጣ በተከታታይ መረጃው ይፋ ተደርጓል።

ሽመልስ ከማል አሜሪካ ጥገኝነት ሊጠይቁ ነው ?

አርአያ ተስፋማሪያም
February 23, 2015
የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል። በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል።

ሽመልስ ከማል – አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከህትመት ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች ላይ የሞት ቅጣት እንዲበየን በመጠየቅ፣ እነእስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት እንዲፈረድባቸው በማድረግ፣ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች እስር ቤት እንዲገቡና በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ በማድረግ እንዲሁም ሙስሊሙንና ተቃዋሚዎችን በጅምላ በመስደብና በማንጓጠጥ፣ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለ2 አመት በጨለማ እስር ቤት እንድትማቅቅ በመፍረድ..ወዘተ የመብት ረገጣ ያካሄደና በበርካታ ወገኖች ህይወት ላይ የጭካኔ ፍርድ ያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።

Monday, February 23, 2015

ሰበር ዜና አዋሳ ከተማ በእሳት ጋየች በሚልየን የሚቆጠር ንብረት ወድማል

freedom4ethiopian
በሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ
በጣም በዙ ሰው ህወታቸው ሳያጡ እንዳልቀሩ የደረሰን መረጃ ጠቅሷል
ቪዲዮ ለመመልከት ሊንኩን የጫኑ

የግፍ ሰለባ! አቶ ተስፋዬ ብሩ ተፈቱ።

አቶ ተስፋዬ ብሩ (ኋላ ዶ/ር) የደረሰባቸው ግፍና ስቃይ እጅግ አሳዛኝ ነው። ጉዳዩ እንዲህ ነው፤ ተስፋዬ የቴሌ ስራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት በ1995ዓ.ም ነበር። አንድ በቴሌ የሚሰራ ኢንጂነር ወዳጄ በወቅቱ « ተስፋዬ ብሩ እውቀትና ብቃት አለው። ግን አያሰሩትም» ያለኝን በኢትኦጵ ጋዜጣ በወቅቱ አስፍሬው ነበር። እርሳቸው ከመሾማቸው በፊት ቴሌን በአዜብ መስፍን “አዝማችነት” ኢያሱ በርሄን ጨምሮ 38 ግልሰቦች ለ7 አመት በደንብ አድርገው ገሽልጠውታል። በቁጥጥር ስር ቢውሉም ወዲያው አዜብ አስፈታቻቸው። የቴሌ አመራሮችም በቦሌ ተሸኙ። ድርጅቱን የተረከቡት ተስፋዬ ብሩ በአግባቡ ማስተዳደር ቀጠሉ። በ1998 ዓ.ም “ሪፖርተር” ጋዜጣ 20ኛ አመቱን ለማክበር ሲል ቴሌን የ250ሺህ ብር ስፖንሰር እንዲሆነው ይጠይቃል። ሃላፊውም “አይሆንም” ሲሉ ይመልሳሉ። አማረ አረጋዊ በተስፋዬ ብሩ ላይ አከታትሎ ዘመቻ ይከፍታል። በዛው አመት ከስልጣን ተነስተው የጠ/ሚ/ሩ አማካሪ ተደርገው ይሾማሉ። ከዚያም ወደ ውጭ ለትምህርት ይሄዳሉ። አማረ መፃፉን አላቆመም። ተስፋዬ ክስ ሲመሰረትባቸው ውጭ አገር ነበሩ። ትምህርታቸውን በማቋረጥ « እኔ የሰራሁት ወንጀል ስለሌ እሄዳለሁ» በማለት መጡ። ከቦሌ ተይዘው እስር ቤት ተወረወሩ። የሚገርመው ረቡዕ የወጣ ሪፖርተር ጋዜጣ በፊት ገፁ የተስፋዬን ፎቶ በማስፈር ሙሉ ሽፋን ሰጥቶ «ደስታውን» ገለፀ። በክሱ ላይ «ተስፋዬ ሳንቲም ሰርቀው ወሰዱ፣ ይህን ያክል ሃብት አፈሩ» የሚል ነገር በጭራሽ አልቀረበም። እነሆ ከ7 አመት ግፍና ስቃይ በኋላ ባለፈው ሳምንት ተፈቱ። እንደተስፋዬ ሁሉ የቀድሞ የፕራይቬታይዜሽን ስራ አስኪያጅ በሻህ አዝምቴ፣ የወንጂ ስኳር ብርሃኑ ጃጆ፣ አሰፋ አብርሃ፣ ኢ/ር ግዛቸው ተ/ማርያም፣ ጉልላት ጥላሁን ያለሃጢያታቸው በግፍ የተሰቃዩ ናቸው። (ስለነዚህ እመለስበታለሁ)…የሪፖርተሩ አማረ በሙስና ዙሪያ የፃፈው « ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በሙስና ይጠየቁ» ሲል ስለ2 ቢሊዮን ያጋለጠበትና የግርማ ብሩ ይጠቀሳሉ። ከዛ ውጭ አባይ ፀሐዬ፣ ስብሃት ነጋ፣ አዜብና በረከት እንዲሁም የጄኔራሎችን ሙስና በተመለከተ አንስቶ አያውቅም።
(የግፍ ሰለባው ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ እኚህ ናቸው….) እየሩሳሌም አርአያ
'የግፍ ሰለባ!

አቶ ተስፋዬ ብሩ (ኋላ ዶ/ር) የደረሰባቸው ግፍና ስቃይ እጅግ አሳዛኝ ነው። ጉዳዩ እንዲህ ነው፤ ተስፋዬ የቴሌ ስራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት በ1995ዓ.ም ነበር። አንድ በቴሌ የሚሰራ ኢንጂነር ወዳጄ በወቅቱ « ተስፋዬ ብሩ እውቀትና ብቃት አለው። ግን አያሰሩትም» ያለኝን በኢትኦጵ ጋዜጣ በወቅቱ አስፍሬው ነበር። እርሳቸው ከመሾማቸው በፊት ቴሌን በአዜብ መስፍን “አዝማችነት” ኢያሱ በርሄን ጨምሮ 38 ግልሰቦች ለ7 አመት በደንብ አድርገው ገሽልጠውታል። በቁጥጥር ስር ቢውሉም ወዲያው አዜብ አስፈታቻቸው። የቴሌ አመራሮችም በቦሌ ተሸኙ። ድርጅቱን የተረከቡት ተስፋዬ ብሩ በአግባቡ ማስተዳደር ቀጠሉ። በ1998 ዓ.ም “ሪፖርተር” ጋዜጣ 20ኛ አመቱን ለማክበር ሲል ቴሌን የ250ሺህ ብር ስፖንሰር እንዲሆነው ይጠይቃል። ሃላፊውም “አይሆንም” ሲሉ ይመልሳሉ። አማረ አረጋዊ በተስፋዬ ብሩ ላይ አከታትሎ ዘመቻ ይከፍታል። በዛው አመት ከስልጣን ተነስተው የጠ/ሚ/ሩ አማካሪ ተደርገው ይሾማሉ። ከዚያም ወደ ውጭ ለትምህርት ይሄዳሉ። አማረ መፃፉን አላቆመም። ተስፋዬ ክስ ሲመሰረትባቸው ውጭ አገር ነበሩ። ትምህርታቸውን በማቋረጥ « እኔ የሰራሁት ወንጀል ስለሌ እሄዳለሁ» በማለት መጡ። ከቦሌ ተይዘው እስር ቤት ተወረወሩ። የሚገርመው ረቡዕ የወጣ ሪፖርተር ጋዜጣ በፊት ገፁ የተስፋዬን ፎቶ በማስፈር ሙሉ ሽፋን ሰጥቶ «ደስታውን» ገለፀ። በክሱ ላይ «ተስፋዬ ሳንቲም ሰርቀው ወሰዱ፣ ይህን ያክል ሃብት አፈሩ» የሚል ነገር በጭራሽ አልቀረበም። እነሆ ከ7 አመት ግፍና ስቃይ በኋላ ባለፈው ሳምንት ተፈቱ። እንደተስፋዬ ሁሉ የቀድሞ የፕራይቬታይዜሽን ስራ አስኪያጅ በሻህ አዝምቴ፣ የወንጂ ስኳር ብርሃኑ ጃጆ፣ አሰፋ አብርሃ፣ ኢ/ር ግዛቸው ተ/ማርያም፣ ጉልላት ጥላሁን ያለሃጢያታቸው በግፍ የተሰቃዩ ናቸው። (ስለነዚህ እመለስበታለሁ)…የሪፖርተሩ አማረ በሙስና ዙሪያ የፃፈው « ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በሙስና ይጠየቁ» ሲል ስለ2 ቢሊዮን ያጋለጠበትና የግርማ ብሩ ይጠቀሳሉ። ከዛ ውጭ አባይ ፀሐዬ፣ ስብሃት ነጋ፣ አዜብና በረከት እንዲሁም የጄኔራሎችን ሙስና በተመለከተ አንስቶ አያውቅም።

(የግፍ ሰለባው ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ እኚህ ናቸው….)'

የ.ህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ለመከላከያ ምስክርነት ተጠርተው ባለመቅረባቸው በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ተባል

እሊና ቢሶቹ የ.ህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ለመከላከያ ምስክርነት ተጠርተው ሁለት ጊዜ በኢምቢተኝነት ሲቀሩ ለሶስተኛ ጊዜ በፖሊስ ተይዘው
እንዲቀርቡ መቐለ የሚገኝ አንድ የወረዳ ፍርድቤት ዳኛ አዘዙ::
በከሳሽ  ብስራት አማረ በተከሳሽ  ኣስገደ ገ/ስላሴ የነበረ ክርክር መቋጫ ለማግኘት አቶ አስገደ ለመከላከያ ምስክርነት
የጠራቸው አንጋፋ የህውሓት መሪዎች እነ  ሱዩም መስፍን፣ ኣርከበ ዕቁባይ፣  ስብሓት ነጋ፣  ኣባይ ፀሃየ ፣  ገብሩ ኣስራት
፣  ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ለ10/06/2007 ዓ/ም በመቐለ ሰሜን ወረዳ ፍርድ ቤት የ’ይቅረብ’ መጥርያ ትእዛዝ ተሰጧቸው
ጀነራል  ፃድቃን ሲቀርቡ ሌሎች ግን በመቐለ ከተማ እያሉ ሳይቀርቡ በመቅረታቸው ለሁለተኛ ጊዜ የሰሜን ወረዳ ዳኛ በፖሊስ ተይዘው
ለ13/06/2007 ዓ/ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት እንዲቀርቡ ታዘው በድጋሚ በመቅረታቸው ዳኛው ለሦስተኛ ጊዜ  ለ24/06/2007 ዓ/ም ከጥዋቱ ሶስት ሰዓት ቀርበው የመከላከያ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ለሶስተኛ ጊዜ ለሰሜን ወረዳ ፖሊስ አዛዞች ትእዛዝ
ተሰጥተዋል።
ይቀርባሉ ኣይቀርቡም እንከታተል። የዳኛው ድፍረት ቢገርመኝም በአረመኔ የህወሀት ባለስልጣኖች ሊደርስባቸው የሚችለውን ሳስበው በዳኛው ኩራት ተሰምቶኛል ።
ለሆድ አደሮች የከፍተኛና ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ከዚህ ትምህርት ለመቅሰምና ሀገራቹን ከአረመኔ መንግስት ነፃ ለማውጣት የበኩላቹን ትግል ይጠበቅባቹሃል።

Ethiopia’s imprisoned bloggers have not been forgotten

In April 2014 BBC Trending covered the arrest of six bloggers and three journalists in Ethiopia. The bloggers are part of a group known as Zone 9, and are well known for campaigning around censorship and human rights issues in Ethiopia. Ten months on from their arrest, the hashtag #FreeZone9Bloggers continues to be used in the country as the trials continue.
That’s not typical – campaigning hashtags often tail off over time. This one is being kept alive by activists both inside and out of Ethiopia who are challenging the government’s decision. The total number of tweets is still only in the tens of thousands, but that is enough to be noticed on the global map (Twitter does not produce an official trending topics list for Ethiopia).
Why are they so focussed on social media? It certainly isn’t the best way to reach the Ethiopian people: the internet is estimated to reach just over 1% of the population there. But it does allow them to network with the global blogging fraternity and the international media. Recently a blog began in support of the nine prisoners, and to report on the hearings. A campaign video has also been released in which complaints are raised over the conditions of Kalinto prison and Kality prison, where the bloggers are being held.
These complaints include torture, unlawful interrogation tactics and poor living conditions. The Ethiopian Embassy in London told BBC Trending that allegations of torture and unlawful interrogation tactics are unfounded, and that they have taken a series of measures “in collaboration with stakeholders, including civil society, to improve the conditions of prisons”. They say the nine individuals are charged with “undermining the constitutional order, inciting violence and advocating the use of force to overthrow the legitimate government.” They are also accused of working with an organisation proscribed by the Ethiopian Parliament as a terrorist organisation. However, activists in support of the group maintain that Zone 9’s actions were constitutional.
Blog by India Rakusen

አየር መንገድ ያለማስታወቂያ ከ500 በላይ አዲስ ሠራተኞች መቅጠሩ ቅሬታ አስነሳ

ቅጥሩን የፈጸምኩት ግልጽነት በተሞላበትና በሕጋዊ መንገድ ነው›› የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዘመናት ይጠቀምበት የነበረውን የአዳዲስ ሠራተኞች ቅጥር በመተው፣ ያለምንም ማስታወቂያ ከ500 በላይ ሠራተኞችን መቅጠሩ ቅሬታ አስነሳ፡፡
አየር መንገዱ ቅጥር መፈጸሙን አረጋግጦ በሕገወጥ መንገድ ሳይሆን፣ ግልጽነት በተሞላበትና በሕጋዊ መንገድ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡
አየር መንገዱ ከወራት በፊት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያ በማውጣት በርካታ አመልካቾችን ከተቀበለ በኋላ ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከ37 በላይ አመልካቾችን መቅጠሩን ያስታወሱት የሪፖርተር ምንጮች፣ ሥራ እንዲጀምሩ መሠልጠን እንዳለባቸው ተነግሯቸው ጊዜያዊ መታወቂያ ተሰጥቷቸው እስካሁን ሳይጠሩ እንደ አዲስ ቅጥር መፈጸሙ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል፡፡
ቀድሞ ከሚሠሩበት መሥሪያ ቤት በመልቀቅ አየር መንገዱ ከዛሬ ነገ ይጠራናል ብለው በመጠባበቅ ላይ እያሉ፣ ከ500 በላይ አዲስ ሠራተኞችን ያለማስታወቂያ በመቅጠር ወደ ሥልጠና እንዲገቡ ማድረጉ አግባብ አለመሆኑን እየተናገሩ መሆኑንም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድም ሆነ ኃላፊዎቹ በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዲሰጡበት መጠየቃቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከሁሉም ያጡ ሆነው ከነገ ዛሬ ይጠሩናል በሚል ተስፋ ውስጥ ያሉትን ከ37 በላይ ቅጥር የፈጸሙ ሰዎችን በአዲሱ ቅጥር ውስጥ እንዲያካትታቸው ጠይቀዋል፡፡
ያለማስታወቂያ ከ500 በላይ አዲስ ሠራተኞችን ቅጥር ፈጽሟል የተባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በሪፖርተር ለቀረበበት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ ቅጥሩን መፈጸሙን አምኗል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የሠራተኞች ቅጥር የፈጸመው በሕገወጥ መንገድ ሳይሆን፣ በትክክለኛና በሕጋዊ መንገድ መሆኑን የአየር መንገዱ የሰው ኃይል ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አዚዛ መሐመድ በወኪላቸው በኩል ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
አዲስ ተቀጠሩ ስለተባሉት ሠራተኞች ምክትል ፕሬዚዳንቷ በወኪላቸው በኩል እንደገለጹት፣ አየር መንገዱ በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም. ለ31 ዩኒቨርሲቲዎች ደብዳቤ ጽፏል፡፡ አየር መንገዱ በደብዳቤው የገለጸው ዩኒቨርሲቲዎቹ ከሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ከ2.5 በላይ ውጤት ያላቸውን ከነአድራሻቸው እንዲልኩ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲዎቹም በተላከላቸው ደብዳቤ መሠረት ለአየር መንገዱ የላኳቸው ተማሪዎች ቁጥር 6,000 እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ አየር መንገዱ የተላኩትን ተማሪዎች በአድራሻቸው በመጥራት በሰኔ ወር 2006 ዓ.ም. ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማዕከል ፈተና መስጠቱን የገለጹት ወ/ሮ አዚዛ፣ በፈተናው ላይ የተገኙት 4,000 እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡ የመጀመርያውን ፈተና ያለፉት ተማሪዎች 1,080 መሆናቸውንም አክለዋል፡፡
በአየር መንገዱ አሠራር ሠራተኛ ሲቀጠር ማንኛውም ቅጥር የሚፈጸመው በሰው ሀብት መምርያ አማካይነት እንደነበር የገለጹት ወ/ሮ አዚዛ፣ የተማሪዎቹ ቅጥር ትኩረት ስለተሰጠው የተፈጸመው በከፍተኛ የማኔጅመንት ኃላፊዎች መሆኑን፣ በቃለ መጠይቅ ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር በመብዛቱ ውጤታቸው ከሦስት ነጥብ በላይ የሆኑት ተደምሮ እንዲያልፉ መደረጉን አስረድተዋል፡፡
በተቀመጠው የመጨረሻ ማለፊያ መሥፈርት 557 ተማሪዎች ማለፋቸውንም ወ/ሮ አዚዛ ተናግረዋል፡፡ የተቀጠሩት ተማሪዎች በአየር መንገዱ በሚሰጣቸው ሥልጠና እየታዩ ለአብራሪነት፣ ለቴክኒሻንነትና ለሌሎች የአየር መንገዱ የሥራ ክፍሎች የሚሆኑት ተለይተውና በደንብ ሠልጥነው ወደ ሥራ እንደሚሰማሩ ምክትል ፕሬዚዳንቷ ገልጸዋል፡፡  557ቱ ተማሪዎች ከሁሉም ዩኒቨርሲቲ የተመረጡ በመሆናቸው፣ ሁሉንም ዩኒቨርሲቲዎች ያማከለ ቅጥር መሆኑንና የዚህ ዓይነት ቅጥርም ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ቀደም ብሎ አየር መንገዱ ባወጣው የሥራ ማስታወቂያ መሠረት ቅጥር ፈጽመውና የሥልጠና ጊዜያዊ መታወቂያ ከወሰዱ በኋላ ያልተጠሩትን በሚመለከት ወ/ሮ ኢዚዛ በሰጡት ምላሽ፣ የአየር መንገዱ አንድ መምርያ ሠራተኛ ሲፈልግ እንዲቀጠርለት ይጠይቃል፡፡ የሰው ሀብት መምርያ በጥያቄው መሠረት የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቶ ከቀጠረ በኋላ፣ እንዲቀጠሩለት የፈለገው መምርያ በበጀት እጥረት ምክንያት ቅጥሩ እንዲቆይለት ይጠይቃል፡፡ በዚህ መሠረት ቅጥሩ ባለበት ይቆምና በጀት ሲለቀቅ እንደሚፈጸም ተናግረው፣ በዚህ ጊዜ አሠራሩ እንደ ስህተት ገልጸዋል፡፡ረፖርተር

Thursday, February 19, 2015

የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።
g 7ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል  ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም።  በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ  ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።
ያም ሆኖ ግን በምርጫ ላይ ያላቸው ተስፋ ፈጽሞ ያልተሟጠጠ ፓርቲዎችን በማክበርና ሥራቸውንም አስቸጋሪ ላለማድረግ ሲባል ከምርጫ 97 ወዲህ የነበሩ ብሄራዊም ሆነ ክልላዊ ምርጫዎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምርጫ ዉጭ ያሉ ሌሎች አማራጮችን ብቻ እንዲመለከት አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አድርጎ አያውቅም ነበር። አሁን ግን የአገራችን ኢትዮጵያ የፓለቲካ ሁኔታዎች  ይህንን የቆየ አቋም በሚያስቀይር መንገድ፤ የአገራችንን የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ያካባቢውን ሰላም በሚጎዳ መልኩ ተቀይሯል። የሰሞኑ የወያኔ እርምጃዎች ትንሽ ተስፋ ያደርግ የነበረውን የዴሞክራሲ ወገንተኛ ተስፋም እምሽክ አድርጎ በልቶታል:: እየተቃረበ ያለው ዓይነት የፌዝ ምርጫ ወያኔ እንደ እንጄራ የራበውን የተቀባይነት እጦት ለአጭር ጊዜ ያስታግስለት ይሆናል እንጂ የሀገሪቱን እያደር እየተወሳሰበ የመጣ ችግር ለጊዜውም እንኳን የሚያስታግስ አይሆንም፤ ይልቁንም ጊዜው በገፋ ቁጥር ችግሩ መቋጠሪያ የጠፋው እየሆነ ይሄዳል::
የሁኔታውን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር የወቅቱን የአገራችን የፓለቲካ ሁኔታ በጥንቃቄ መርምሮ የሚከተሉት ግንዛቤዎች ላይ ደርሷል።
1. ህወሓት ብዙዎች እትዮጵያዊያን የተሰውላቸውን አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በመበተን የድርጅቶቹን ስምና ንብረት ለአገልጋዮቹ መስጠቱ፤ ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው የመራጭን ድምጽ መስረቅ ሳይበቃው የምርጫ ተወዳዳሪንም መዝረፍ መጀመሩን አመላካች ነው። ይህ ተግባር ህወሓት የምርጫ ውጤትን ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪዎችንም እሱ ራሱ ለመምረጥ መወሰኑን ያሳያል፤ ከዚህ በተጨማሪ የሴራ ምርጫውን ከጅምሩ ጀምሮ አስቀድሞ እስከተወሰነለት መዳረሻው ድረስ ለምንም ዓይነት ያልተጠበቀ አጋጣሚ (በምርጫው ወቅት የሚደረጉትን ክርክር ተብዬዎች ጨምሮ) እድል ላለመስጠት ወስኖ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፤
2. ይህ እኩይ ውሳኔ በምርጫ ቦርድ ፊርማና አንደበት ቢነገርም ምንጩ የህወሓት ፓሊት ቢሮ  መሆኑን የሚከተሉት ተግባራት ይጠቁማሉ፤
2.1.         በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲገለጽ የተወሰነው እርምጃ ለማስመሰል ያክልም ቢሆን የህጋዊነት ሽፋን እንዲኖረው አለመደረጉ ውሳኔው ፍጹም እብሪተኛ በሆነ አካል መወሰኑን ያመለክታል። እንዲህ                   ዓይነቱ እብሪተኛ አካል ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ነው። ውሳኔውን ለማስፈፀም የነበረው ጥድፊያም ይህንኑ ያጠናክራል።
2.2.        ለማስመሰያ ያክል እንኳን ምንም አይነት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖር ፓሊስ የአንድነትና የመኢአድ ቢሮዎችን መውረሩ፤ ህወሓት አንድነትንና መኢአድን አጥፍቶ የድርጅቶቹን ስሞችና ንብረቶች                   ለሚፈልጋቸው ሰዎች ሰጥቶ በአስቸኳይ ለምርጫ ድራማው በፊት መስመር ሊያሰልፋቸው መወሰኑን አመላካች ነው። እንዲህ ዓይነት ከባድ ውሳኔ የሚሰጠው ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ብቻ                    ነው።
2.3.        ወደ ፈቃድ መንጠቅ ከመደረሱ በፊትም በሰማያዊ ፓርቲ፣ በአንድነትና በመኢአድ አባላት የደረሰው አረመኔያዊ ድብደባ፤ ንቁ የፓለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉ ዜጎች ላይ የሚደርሰው እስር፣ መሰወርና                 እና ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መገኘት መብዛት እነዚህን አገራዊ ፓርቲዎች የመበተን የፓለቲካ ውሳኔ መሰጠቱን አመላካቾች ናቸው።
1. ለጊዜው የፈቃድ ነጠቃና የንብረት ዘረፋ የተፈፀመው በአንድነትና በመኢአድ ላይ ቢሆንም በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በየእለቱ እየጠነከረ የመጣው የአፈና እርምጃም በተመሳሳይ ፓርቲውን ወደማገድ አለዚያም ፈጽሞ መንቀሳቀስ ወደማይችልበት ደረጃ ሊያደርሰው ይችላል የሚል እምነት አሳድሯል። ሌሎች ፓርቲዎችም ከዚህ ህወሓት ካሰመረው የውሸት ጫወታ መስመር የመውጣት ዝንባሌ ቢያሳዩ ተመሳሳይ እርምጃ አይቀርላቸውም።
2. የህወሓት የወቅቱ የጥፋት ዒላማ ያነጣጠረው አንፃራዊ በሆነ መንገድ የተሻለ መዋቅርና ማኅበራዊ መሠረት ባላቸው እና በአገራዊ አጀንዳዎቻቸው በሚታወቁ ፓርቲዎች ላይ መሆኑ፤ የወቅቱ የጥፋት ዘመቻ የኢትዮጵያ አንድነትን የማዳከምና ከፋፍሎ የመግዛት የህወሓት ትልቁ አጀንዳ አካል መሆኑን ያሳያል።
3. እራሱን በዘር ያደራጀዉና ኢትዮጰያ ዉስጥ ያለዉ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አደረጃጀት ከዚሁ እሱ ከተደራጀበት የዘር አደረጃጀት ዉጭ እንዲሆን በፍጹም የማይፈቅደዉ የወያኔ አገዛዝ፤ መጣፊያው ሲያጥረውና ወደ ማይቀረው ውድቀቱ ሲያመራ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አገራችን ኢትዮጵያን በቀላሉ ወደማትወጣዉ የዘዉግ ግጭት ዉስጥ አስገብቶ ዘመናት ያስቆጠረዉ አንድነቷ እንዲፈረስ በትጋት እየሠራ መሆኑን ያሳያል።
4. ከመለስ ዜናዊ ሞት ወዲህ ህወሓት ከሁሉን ጠቅላይ (totalitarian) አገዛዝ ወደ ፋሽስታዊ ቡድንነት ያሽቆለቆለ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ህወሓት ዘረኛ፣ ጠቅላይና ፈላጭ ቆራጭ ጨቌኝ በመሆኑ ፋሽስት ብለነዋል።  ሆኖም በታሪክ የሚታወቁ ፋሺስታዊ አገዛዞች ከፍተኛ ብሄራዊ ስሜት የነበራቸው ሲሆን የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ግን ብሔራው ስሜት አልባ መሆኑ ልዩ እና የበለጠ አደገኛ ያደርገዋል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን የህወሓት መሪዎችንና ጥቂት ሌሎች አጫፋሪዎቻቸውን የያዘ ለጊዜው አስተባባሪ መሪ የሌለው ሆኖም ግን የጦር ሠራዊትን፣ የስለላ መዋቅሩንና ፓሊስን ተቆጣጥሮ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ይህ አስኳል የለሽ ፋሽስታዊ ቡድን መሆኑ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን ተደላድሎ መሪ እንዲፈጥር ከተፈቀደለት አገራችንን የከፋ መከራ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል።

ከላይ በአጭሩ ከተራ ቁጥ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን በማገናዘብ በግንቦት 2007 ሊደረግ የታቀደውን አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሴራ ምርጫን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ውሳኔዎችን አስተላልፎ ከዚህ የሚከተሉት ጥሪዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቅርቧል።
1. በምርጫ 2007 መሳተፍ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ ፋሽስታዊውን ቡድን የሚያጠናክርና የኢትዮጵያን ሕዝብ የወደፊት ዕድል የሚገድል በመሆኑ፣ ለፍትህ፣ ለነፃነት፤ ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት ግድ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ከአሁኑ ከዚህ የይስሙላ ምርጫ ዉጭ ዓይኖቻቸውንና ሙሉ ጉልበታቸዉን በሌሎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃነት በሚያፋጥኑ አማራጮች ላይ እንዲያሳርፉ ጥሪ ያደርጋል። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ዓይን ያወጣ የሴራ ምርጫ ይልቅ መብቱን፤ ነፃነቱንና እኩልነቱን በሚያፋጥኑለት በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመፅ የትግል አመራጮች ላይ እንዲሳትፍ ለመላው ያገሪቱ ሕዝብ ጥሪ ያስተላልፋል።  ህወሓት ማኅበረሰባችንን ለመከፋፈልና ለማባላት የሚያደርገውን እኩይ ሴራ በጋራ እንድናከሽፈው ወገናዊ ጥሪ ያስተላልፋል፤ “አንከፋፈልም፤ ተከፋፍለንም አንጠቃም“ እንበል ይላል::
2. ህወሓትን ማስወገድ የሚቻለው በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ በመሆኑ፤  ከሁለቱ አንዱንም አለመያዝ ሌላ ሰው ታግሎ ነፃነቴን ያቀዳጀኝ እንደማለት የሚቆጠር በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአፋጣኝ ከእነዚህ ሁለት የትግል ዘርፎች ዉስጥ የተሻለ አስተዋጽኦ አበረክታለሁ በሚለው የትግል ዘርፍ ውስጥ ተሳትፎ  እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል።
3. አርበኞች ግንቦት 7፣ በሁለቱም የትግል ዘርፎች ድርጅታዊ መዋቅሩን እያሰፋና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በስፋት እንዲቀላቀሉት፤ በኅብረት እንድንቆም እና የህወሓትን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንድናፋጥን ጥሪ ያደርጋል::
4. ያለንን አቅም በሙሉ ህወሓትን በማስወገድ ላይ ካዋልነው አንድ ጠንክር ያለ ሕዝባዊ አመጽ አገዛዙን ሊያፍረክርክው የሚችል በመሆኑ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ከምርጫ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች ሊውል ታስቦ የነበረው የሰው ኃይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብና እውቀት ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀሻነት እንዲውል ጥሪ ያደርጋል።
5. በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም በ2007 ምርጫ ላይ ጊዜና ንብረት ከማባከን ይልቅ በአንድ ልብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ያደርጋል።   ከሁሉም ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የተውጣጣ አካል የዚህን ጥሪ ተፈፃሚነት እንዲከታተል ቢደረግ ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል ብሎ ያምናል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቤተመንግስት ተገመገሙ

ኢሳት ዜና
ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ በማድረግ ነው።
በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ ከ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተገመገሙት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣”የሀሰት የስራ አፈጻጽመ ታቀርቢያለሽ” የተባሉት የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር ዘነቡ ታደሰ፣”ሳሞራን ትፈራዋለህ”ተብለው የተገመገሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣”ኮምፒዩተርና ሞባይል ላይ ጥብቅ ትላለህ” የተባሉት አቶ ሬድዋን ሁሴን፣”ከባልደረቦችሽ ጋር ትጋጫለሽ”የተባሉት ወይዘሮ አስቴር ማሞ ፣”ፈሪ ነህ” የተባሉት ዶፐክተር ካሱ ይላላ፣ “ከደባል ሱስ የጸዳህ አይደለህም”የተባሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ ሶፊያን አህመድ እና ሌሎች በርካታ ባለስልጣናት ” ሲ” አግኝተዋል።
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ፣ የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ጸጋይ በርሄ፣ የ አማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዓለምነው መኮንን፣አቶ ስዩም መስፍን፣አቶ አርከበ እቁባይ እና ሌሎች በርካታ ሹመኞች “ቢ” ውጤት ተሰጥቷቸዋል።
እስካሁን ለ ኢሳት በደረሰው ሰነድ በግምገማው “ኤ”ውጤት የተሰጣቸው የ ኢህአዴግ አመራር የህወሀቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ብቻ ናቸው። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም “በሶሻል ሚዲያ የግለሰቦችን ታሪክ ለራስህ ገፅታ ግንባታ አውለሀል፣ ስራ ታዘገያለህ” የሚሉና ሌሎችም ደከማ ነጥቦች የተነሱባቸው ቢሆንም፤ ከሌሎቹ አመራሮች በተለየ ሁኔታ “የቀረበብኝን ድክመት”አልቀበልም በማለት ነው ውድቅ ያደረጉት። ሌሎቹ አመራሮች በሙሉ፤ ከግምገማቸው በሁዋላ፦ “ድክመታችንን ተቀብለናል፤እናሻሽላለን”
ማለታቸውን ተከትሎ ነው “ቢ” እና “ሲ” የተሰጣቸው። “ሲ”ከተሰጣቸው የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ” ኢህአዴግ ገለልተኛ ነው” እያለ የሚናገርለትን ምርጫ ቦርድን በሰብሳቢነት የሚመሩት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ይገኙበታል።
በኢህአዴግ ውስጥ ቀደም ሲል አንድን ነገር “ድርጅቱ ነው ያለው” ሲባል፤ “መለስ ነው ያለው”ማለት እንደሆነ የቀድሞው የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ ገሠሰ “የመለስ ትሩፋቶች” በተሰኘው መጽሐፋቸው መግለጻቸው ይታወቃል። ኢሳት እጅ የገባው የግምገማ ሰነድ እንደሚያመለክተው፤ የመለስን ቦታ-አቶ በረከት ስምኦን መያዛቸውን ነው።
አቶ ሬድዋን፤”የሀገሪቱን ገጽታ ለውጪ ሚዲያ ዝግ አድርገኸዋል” ተብለው ሲገመገሙ <<ዝግ ያደረኩት እኔ ሳልሆን ድርጅቱ ነው” ብለው መልስ የሰጡ ሲሆን ፤ <<ድርጅቱ ማን ነው?>>ተብለው በአቶ ሀይለማርያም ሲጠየቅ፦<<በረከት>> በማለት መልሰዋል።

ሰበር ዜና ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡
ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ለመጋቢት 21-23 ሠጥቶ ተበትኗል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን ተከሳሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡
በተያያዘ ዜና የመሀል ዳኛው የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ ይቀየሩልን ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት ከችሎቱ ያገለሉ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር በፍርድ ቤት ጉዳዩን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አቤቱታ ላይ ቀጠሮ ሰጠ

የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘው ክስ መዝገብ የተከሰሱት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡ በዛሬው ችሎት የተከሳሾቹ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ‹‹ህዳር 12 ለ 13/2007 ዓ.ም አጥቢያ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የተጠርጣሪዎቹ ንብረት ተወስዶባቸዋል፣ የሰብአዊ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል፣ ድንገተኛ ፍተሻው ህገ ወጥ ነው›› በሚል በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ ላቀረቡት አቤቱታዎች ማረሚያ ቤቱ የሰጠውን መልስ ሰምቷል፡፡
የማረሚያ ቤቱ መልስ በጽሁፍ ከቀረበ በኋላ በቃልም እንዲቀርብ በታዘዘው መሰረት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቀጠሮ ማረፊያ አስተዳደር አስተዳዳሪ ዋና ሱፐር ኢንተንደንት አምባዬ ክቡር ፍተሻው መካሄዱን አምነው ነገር ግን፤ ‹‹ፍተሻው የተከናወነው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከጠዋቱ 12 ሰዓት በኋላ ነው፡፡ ፍተሸውም በአቤቱታው ላይ እንደቀረበው ባልታወቁ ሰዎች ሳይሆን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ጥበቃዎች ነው የተከናወነው›› ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡ የፍተሻውን አላማም ‹‹የታራሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የተከለከሉ ነገሮችን ፈትሾ ለማስወገድ ነው፡፡ በፍተሸውም ሚስማር፣ ስለት ነገሮች፣ እንዲሁም ብጥብጥ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎች ተገኝተዋል፡፡›› ብለዋል፡፡
ባለፈው የአብዛኛዎቹ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሲደረግ የ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን፣ እንዲሁም 8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ የተወሰኑ የክስ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት በሁለቱ ተከሳሾች ላይ አሻሽየዋለሁ ያለውን ክስ አቃቤ ህግ ይዞ ቀርቦ በንባብ አሰምቷል፡፡
በመጨረሻም በፍተሻው ወቅት ተፈጽሟል በሚል በተከሳሾቹ ጠበቃ የቀረበውን አቤቱታና ማረሚያ ቤቱ የሰጠውን መልስ አገናዝቦ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም፤ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ የቀረበው ማሻሻያ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ‹‹ተሸሽለዋል ወይንም አልተሸሻሉም›› የሚለውን ለመወሰን ለየካቲት 25/2007 ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Wednesday, February 18, 2015

በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ የኢህአዴግ ዲፕሎማቶች መረጃ የላቸውም

ሳውዲ አረቢያ ቢሻ እየተባለ የሚጠራ አነስተኛ ከተማ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በሳውዲያዊ አሰሪዋ ከተተኮሰባት ጥይት ከሞት መትረፏን ምንጮች አረጋገጡ። በዚህች ኢትዮጵያዊት ላይ ስለደረሰው የነፍስ ማጥፋት ጥቃት በኢህአዴግ ተመልምለው የተሰየሙት ዲፕሎማቶች ምንም ዓይነት መረጃ የላቸውም፡፡
አደጋው የደረሰባት ወጣት በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኗን የሚናገሩ የዜናው አቀባዮች ወጣቷ  እንደተራራ የገዘፈውን ህይወት በመጋፈጥ ቤተስቦቿን ከችግር ለመታደግ በወቅቱ ከነበሩ የኤጀንሲ ደላላዎች ጋር ተዋውላ ሳውዲ አረቢያ ለስራ መምጣቷን ይናገራሉ።
በተጠቀሰው ውል መስረት ወጣቷ አሰሪዋ የወር ደሞዝዋን በየወቅቱ እንዲከፍላት ለማስረዳት ብትሞክረም ከኢትዮጵያ ከመጣች ጀምሮ ላለፉት ሁለት አመት ያለደሞዝ ለመቆየት መገደዷን ለመረዳት ተችሏል። ሰሞኑን ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የሁለት አመት ኮንትራት ውሏን መጨረሷን ተከትሎ አሰሪዋ ደሞዝዋን በአግባቡ አስቦ እንዲከፍላት ጥያቄ ብታቀርብም በንግግሯ የተበሳጨው ሳዑዲያዊ ከመሳቢያ ሽጉጥ በማውጣት ኢትዮጵያዊቷን የቤት ሰራተኛ ለመግደል አከታትሎ እንደተኮሰባት  የሚናገሩ እማኞች ወጣቷ በሁለት ጥይት ተመታ እንደወደቀችና  በአካባቢው ሰዎች ትብብር በተለምዶ መሊክ አብደላ እየተባለ ወደሚጠራ  ሆስፒታል በመውሰድ ህይወቷን ለማትረፍ ተችሏል ብለዋል።
eth woman in saudi1ጅማ ውስጥ ተወልዳ እንዳደገች የሚነገርላት ይህች ወጣት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ጉዳዩን የሚከታተልላት ዘመድና ቀባሪ የሌላት በአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ደላሎች እምነት ጥላ የሳውዲ አረቢያን ምድር ከረገጠች ወዲህ ከማንም ጋር በቴሌፎንም ሆነ በአካል እንዳትገናኝ በአሰሪዎችዋ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግባት ስለነበር ወጣቷ ከሃገር ይዛ የመጣቸው የቤተሰቦችዋ የስልክ አድራሻ በአሰሪዎቿ በመነጠቁ ረዳት የሌላቸውን እህት ወንድሞቿን መርዳት ቀርቶ በህይወት መኖራቸውን እንኳን በትክክል እንደማታውቅ ይነገራል።
በአሰሪዋ ጥይት ህይወቷ ከመነጠቅ ተርፋ ሆስፒታል የገባችው ኢትዮጵያዊት ወጣት በአሁኑ ሰአት ያለችበትን የጤንነት ሁኔታ የሆስፒታሉ የምርመራ ውጤት በትክክል ባይገልጽም የጥይት አረሩ ከሰውነቷ መውጣቱን ማረጋጋጥ ተችሏል። ወንጀሉን የፈፀመው ሳዑዲያዊ አሰሪ ላይ ምንም አይነት እርምጃ ባለመወሰዱ ወጣቷ ሊገለኝ ይችላል በሚል ስጋት በጭንቀት እንቅልፍ  በማጣት ላይ መሆኗን እና “ከሆስፒታል አውጡኝ፤ ሃገሬ ውስዱኝ” እያለች በኦሮምኛ ቋንቋ ስትማጽን ተሰምታለች።
የኢትዮያዊቷን ትክክለኛ የሃገር አድራሻ ለማወቅ አስሪዋ ፓስፖርቷን እንዲሰጥ ቢጠየቅም እስካሁን ፈቃደኛ አለመሆኑ ከአካባቢው የመጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ለዜጎች ህይወት ደንታ የሌላቸው ሪያድ እና ጅዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች አደጋ ስለደረሰባት ወጣት ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
ቀደም ሲል በኤጀንሲ ደላሎች  ወደ ሳውዲ አረቢያ ከገቡ በመቶ ሺህ ከሚቆጠሩ እህቶች ውስጥ ገሚሱ የወር ደሞዛቸው በአሰሪዎቻቸው ተነጥቆ ግፍ እና በድልን ተሸክመው ለአገራቸው ሲበቁ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ሳውዲ ውስጥ ያሉበትን ሁኔታ በትክክል መግለጽ እንደማይቻል ይነገራል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ከወራት በፊት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት መጥተው እንደነበር የሚነገርላቸው አፈጉባዔ አባዱላ በኮንትራት ሰራተኞች ዙሪያ ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካ የሚገልጹ ታዛቢዎች የዜጎችን መብት የሚያስክብር ሁለትዮሽ «ኦፊሴላዊ» የጋራ ውል በሌለበት የኮንትራት ሰራተኞችን ወደ አረብ ሃገራት ለመላክ ለተወካዮች ምክርቤት እንደሚቀርብ የሚጠበቀው የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ረቂቅ ህግ ሃላፊነት የጎደለው ከዜጎች መብትና ጥቅም ይልቅ ቱባ ባለስልጣናትንና ተላላኪዎቻቸውን ኪስ ክቡር በሆነው የዜጎቻች ህይወት ለማደለብ የሚደረግ ሩጫ መሆኑን በጉዳዩ ላይ ቅርበት ያላቸው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።eth woman in saudi1

በሰማያዊ ፓርቲ ምልክት መወዳደር አለብኝ የሚለው ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ጋር ተወዛገበ

semayawi-partyከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመዋሀድ የሚያስችለውን ቅድመ ስምምነት ማድረጉንና በአንድ የምርጫ ምልክት ለመወዳደር መወሰኑን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁን የገለጸው የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦሕዴኅ)፣ ከቦርዱ ጋር መግባባት ባለመቻሉ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡
ኦሕዴኅ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ መሥፈርቶችን አሟልቼ ካስገባሁ በኋላ ቦርዱ አፅድቆልኛል ቢልም፣ ምርጫ ቦርድ ግን የደረሰው ሪፖርት እንደሌለ በመግለጽ፣ ፓርቲው በወሰደው ሕጋዊ ሠርቲፊኬት ላይ ለውጥ ማድረጉን እንዳላፀደቀ አስታውቋል፡፡
የኦሕዴኅ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ በቀለ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በሰማያዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በሰጡት መግለጫ፣ ፓርቲያቸው በሰማያዊ ፓርቲ ምልክት ለመወዳደር ወስኗል ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ አባሎቼ በምርጫ እንዳይወዳደሩ ጫና እየተደረገባቸውና እየተሰረዙ ነው ለሚለው ወቀሳ፣ ምርጫ ቦርድ የታገዱት ግለሰቦች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሳይሆኑ የኦሕዴኅ አባላት ናቸው ማለቱን እንዴት ይታያል ለሚለው የሪፖርተር ጥያቄ በሰጡበት ማብራሪያ ነው አቶ ግርማ ይህንን የተናገሩት፡፡
ኦሕዴኅ ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለምርጫ ቦርድ ሪፖርት ማድረጉን የጠቆሙት አቶ ግርማ፣ በተለይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የተናጠል ስምምነት እንዳለውና የስምምነቱ አንዱ መንፈስ ደግሞ የዚህ ስምምነት ፈራሚዎች ለ2007 ጠቅላላ ምርጫ አባላትን በአንድ መወዳደሪያ ምልክት ማቅረብ እንደሆነ መግለጻቸውን አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሠረት የአንዱ ፓርቲ አባልና አመራር በሌላው ፓርቲ ስምና ምልክት የሚወዳደርበትን ጉዳይ ማመቻቸትና ስምምነት ሲደረስም ተግባራዊ ለማድረግ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር መስማማታቸውን አስረድተዋል፡፡ ‹‹ዕጩዎችን እንዴት ማቅረብ እንዳለብን ምርጫ ቦርድ አይወስንም፤›› ሲሉም ምርጫ ቦርድ የወሰደው የዕግድ ዕርምጃ ሕገወጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ወንድሙ ጎላ ግን፣ ‹‹አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ከሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ውህደት፣ ቅንጅትና ግንባር መፍጠር ይችላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች በጠቅላላ ጉባዔ ፀድቀው ለቦርዱ ሲቀርቡና ቦርዱ ሲያፀድቀው ነው ተፈጻሚነት የሚኖራቸው፤›› በማለት ለሪፖርተር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
‹‹በሰማያዊ ፓርቲ በኩል እየቀረበ ያለው ውንጀላ ግን ሕጉን መሠረት ያላደረገና ተገቢዎቹን የሕግ መሥፈርቶች ያላሟላ ነው፤›› በማለት የሰማያዊ ፓርቲን ክስ አጣጥለውታል፡፡
‹‹የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት የተባለው ድርጅት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ምልክት ወስዷል፡፡ በመሆኑም ውህደት፣ ግንባር አልያም ቅንጅት መፈጠሩን ቦርዱ ሳያውቀው የፓርቲው ዕጩዎች በሌላ ፓርቲ ምልክት ተመዝገበዋል ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ሕገወጥ ነው፤›› በማለት የተፈጠረውን ውዝግብ አብራርተዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ከኦሕዴኅ ጋር ስለተደረሰው ስምምነት ምንም ነገር ያልተናገሩ ሲሆን፣ ‹‹በተናጠል ሌላ ፓርቲ ውስጥ የነበረ ሰው ያኛውን ፓርቲ ትቶ ሰማያዊን ወክሎ የመወዳደር መብት አለው፤›› በማለት ይሞግታሉ፡፡
የቦርዱ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ ግን፣ ማንኛውም ግለሰብ በፈለገው ፓርቲ ውስጥ የመወዳደር መብት እንዳለው ገልጸው፣ ‹‹ነገር ግን እንዲህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች ሕዝቡን ውዥንብር ውስጥ የሚከቱ መሆን የለባቸውም፤›› ይላሉ፡፡
ለዚህም እንደ መከራከሪያነት የሚያቀርቡት ደግሞ፣ ‹‹አሁን የታገዱት የኦሕዴኅ አባላት ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ በኦሕዴኅ የተመዘገቡ አባላት ናቸው፡፡ ከዚህ ባለፈም የኦሕዴኅ ፕሬዚዳንት እንኳን ለመወዳደር የተመዘገቡት አዲስ አበባ ውስጥ ነው፤›› በማለት ዕገዳው የመነጨው አባላቱ ከፓርቲው ባለመልቀቃቸው እንጂ፣ ሌላ የተለየ ዓላማም ሆነ ዕቅድ ስላለ አይደለም በማለት መልሰዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የዘጠኝ ፓርቲዎች ትብብር የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በተመረጡ 15 የአገሪቱ ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ለማድረግ ይዞት የነበረውን ዕቅድ ለአንድ ሳምንት ወደፊት በመግፋት፣ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁን በዕለቱ በተሰጠው መግለጫ ይፋ ተደርጓል፡፡

‹‹የአገር መከላከያ ሠራዊት ተዋጽኦ እንደ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የሚከፋፈል አይደለም›› ጄኔራል ሳሞራ የኑስ

የማነ ናግሽ
የአገር መከላከያ ሠራዊት ብሔራዊ ተዋጽኦ የጠበቀና የተመጣጠነ መሆን ያለበት ቢሆንም እንደ የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የሚከፋፈል እንዳልሆነ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላላ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ተናገሩ፡፡
17e9ea1bbb4afb9cc8160d9171516192_L (1)በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ በሆነችው በባህር ዳር ከተማ የተከበረውን ሦስተኛውን የሠራዊት ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ (ሲምፖዝየም)፣ ‹‹የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ከየት ወዴት?›› በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት ጄኔራል ሳሞራ የመከላከያ ሠራዊት አመጣጥ፣ ዕድገትና አሁን የሚገኝበትን ደረጃ ተንትነዋል፡፡
ቀደም ሲል ደርግን ያሸነፈው የኢሕአዴግ ሠራዊት የአሁኑ መከላከያ ሠራዊት መሠረት እንደሆነ አስታውሰው፣ ለማመጣጠን ሲባል ከ30 ሺሕ በላይ ነባር ታጋዮች እንዲቀነሱ የተደረገበት ምክንያት ብሔራዊ አስተዋጽኦን ለማጠናከር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ለታጋዮችም ሆነ ለአመራሮች ፈታኝና ከባድ ውሳኔ የነበረ ቢሆንም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ወስነናል፤›› በማለት የገለጹት ጄኔራል ሳሞራ፣ በመከላከያ ሠራዊት አነስተኛ ተሳትፎ ከነበራቸው ብሔር ብሔረሰቦች አዲስ አባላት በመመልመል፣ ከወንጀል ነፃ የሆኑ ተፈላጊ ችሎታና ሙያ የነበራቸው የደርግ ሠራዊት አባላትም ታክለውበት ሠራዊቱ እንደ አዲስ መደራጀቱን አብራርተዋል፡፡ በወቅቱ ካልተቀነሱት የሕወሓት ታጋዮች ላይ ሁለት ማዕረግ እንደተቀነሰ፣ በአንፃሩ ደግሞ ለሌሎች ብሔር ተወላጆች ላይ ሁለት ማዕረግ እንዲጨመር መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ ኢሕአዴግ ውስጥ ከተፈጠረው መከፋፈል በኋላ በተደረገው የተሃድሶ እንቅስቃሴ መሠረት የሠራዊቱ ማነቆ የነበሩ ችግሮችና አስተሳሰቦች መወገዳቸውንም አውስተዋል፡፡ አዲሱ የሠራዊት ግንባታ ሕገ መንግሥታዊ ተልዕኮዎችን የሚያሳካ፣ የመከላከል ቁመናው የማይደፈር ሆኖ በዋናነት የሻዕቢያ ተላላኪዎችን ጨምሮ ማናቸውም የደኅንነት ሥጋት መቆጣጠር የሚችልና የጦርነት አደጋን ከሩቁ የሚገታ ስትራቴጂ የተከተለ እንደነበርም ጄኔራሉ አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የኤርትራ ጦርነትን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት ጄኔራል ሳሞራ፣ ‹‹ጦርነቱን ባንፈልገውም በውጊያ የተፈተነና ብቃት ያለው የተመጣጠነ ሠራዊት ለመገንባት አስተዋጽኦ አድርጎልናል፤›› ብለዋል፡፡
ብሔራዊ ተዋጽኦን በተመለከተ እንደ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ያነሱት ጄኔራል ሳሞራ ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎችን መሠረት ያደረገ፣ ለመስዋዕትነት ዝግጁ የሆነና ለውትድርና የሚያስፈልጉ ሙያ፣ ዕውቀት፣ ችሎታና ልምድን መሠረት ባደረገ ምልመላና ዕድገት ሠራዊቱ መደራጀቱን አስረድተዋል፡፡
‹‹የሠራዊታችን ግንባታ ብሔራዊ ተዋጽኦን ያረጋገጠ መሆን አለበት ሲባልም፣ ይህን ሙያና መሠረታዊ መሥፈርቶችን መነሻ ያደረገውን መርህ በአግባቡ በመረዳት መሆን አለበት፤›› ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከመሠረቱ የታጋዮች ሕዝባዊ ባህርያትን የተላበሰ፣ የሰላምና የልማት ኃይል በመሆኑ ከሌሎች አገሮች እንደሚለይ ገልጸው፣ ‹‹ብሔራዊ አስተዋጽኦ ግን በዋናነት በብቃትና በሙያ የሚለካ እንጂ እንደ የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የሚከፋፈል አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ በዚህም የተደረገው ምልመላ ብሔር ብሔረሰቦችን ያሳተፈ ቢሆንም፣ ለአገር ጥቅም ሲባል ብቃትና ችሎታን መሠረት ባደረገና ግልጽነት በሰፈነበት የተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
እንዲሁም መከላከያ ሠራዊት ፕሮፌሽናል (ዘመናዊ) ለማድረግ በርካታ የጥናትና የትምህርት ተቋማት ተመሥርተው አባሉ ራሱን እንዲያሳድግና እንዲያድግ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በዚህም ብቃትና አቅም ያለው ሠራዊት በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ጄኔራሉ አክለዋል፡፡ የአመራር መተካካት ሠራዊቱንም የሚመለከተው ሲሆን፣ በዚህ ተቋም መተካካት የተሻለ አመራርን ለመቀየርና ሠራዊቱን በከፍተኛ ደረጃ ያገለገሉ ታጋዮችንም በክብር እንዲተኩ ለማድረግ ጥቅም ላይ እንደሚውል ገልጸዋል፡፡
ከፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ አኳያ፣ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርገው አንዳንድ አዳዲስ መመርያዎች፣ ደንቦችና ማኑዋሎች በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡
በሲምፖዝየሙ ‹‹የኢትዮጵያ ህዳሴና መከላከያ ሠራዊታችን›› በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት የኢፌዲሪ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ቀደምት ሥርዓቶች ሠራዊት በሕገ መንግሥቱም ሳይቀር የንጉሠ ነገሥቱ ተገዢ ነበረ ብለዋል፡፡ የአሁኑ የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ለገዢው ፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገዢ የሆነ ሕዝባዊ ሠራዊት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለመከላከያ ሠራዊት የሚመደበው በጀት ከሌሎች የዓለም አገሮች ጋር ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የተናገሩት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አብቃቅቶ በመጠቀም ከራሱ ተርፎ በልማት ሠራዊት ላይም በማዋል ውጤታማ ለመሆን ችለዋል ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሪፖርታቸውን ለፓርላማ ሲያቀርቡ የሠራዊቱ ተዋጽኦ ላይ ለውጥ እየታየ ቢሆንም፣ የሌላው የማመጣጠን ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ ገልጸው ነበር፡፡ በሠራዊት አባላት ብዛት ቅድሚያ የሚይዘው ክልል አማራ እንደሆነ፣ በመቀጠልም ደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች እንደሚከተሉ አመልክተው ነበር፡፡ ትግራይ ከሁለተኛነት ወደ አራተኛ መውረዱም ተገልጾ ነበር፡፡ ታዳጊ ክልሎችም የማሠልጠኛ ሥራቸውን በማጠናከር ለምልመላ ጥሪዎች ምላሽ እንዲሰጡ ሪፖርቱ መጠቆሙ ይታወሳል፡፡

(አሳዛኝ ዜና) ሲኖ ትራክ እና ሚኒባስ በመጋጨታቸው በተፈጠረ እሳት የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

kataelo
በቡራዩ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋና ተከትሎት በተነሳው የ እሳት ቃጠሎ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘገበ:: በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ ቀርሳ በተባለ ስፈራ ትላንት ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲሉ መንግስታዊው ሚዲያዎች ዘግበዋል:: እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ አደጋው የደረሰው ትላንት ምሽት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ሲሆን፥ ወደ አዲስ አበባ ይመጣ የነበረ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው። በዚህ አደጋ የተነሳም የ11ዱ ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት ሲሆን ሲኖ ትራኩ ላይ የነበሩት ሹፌር እና ረዳት ከአደጋው መትረፍ ቢችሉም በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ከ11 የሚበልጡ ሰዎች በተነሳው እሳት ተቃጥለው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ ለመንግስት ሚዲያዎች አስታውቋል::

ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎችን በይፋ በማገድ ጀመረ።

እኛ የታዘዝነውን ነው የፈፀምነው›› አቶ ታደሰ ሻረው/ የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ፡፡
ዛሬ በቀን 10/06/2007 ዓ.ም በደቡብ ወሎ የሰማያዊ እጩዎን የማፅዳት ዘመቻ አንዱ አካል የሆኑት የኮምቦልቻ ሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች በይፋ ታግደው ያስገቡት ዶክሜንት ተመላሽ ተደርጎላቸዋል፡፡ በትናንትናው እለት በአቶ ትግስቱ አወሉ ተወክያለሁ የምትለው ወ/ሮ ሰብል ይመር የተባለች የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ በተሰጣት ተልእኮ መሰረት ተወስኖ የመጣላትን ውሳኔ በደቡብ ወሎ በሚገኙ ከ20 በላይ የምርጫ ወረዳዎች በመሄድ ህጋዊ ደብዳቤ እንኳ ሳትይዝ የእጩዎችን ስም ዝርዝር ብቻ በመያዝ ለምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች ትእዛዝ ስታስተላልፍ እንደነበርና ትእዛዙን ተከትሎ የምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች የማስፈፀም ተልእኳቸውን እንደጀመሩ መግለፄ ይታወቃል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለትየኮምልቻ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ትናንት ክሊራንስ አላቀረባችሁምበሚል ክስ እንደቀረበባቸውና ክሊራንስ እንዲያመጡ በተጠየቁት መሰረት ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን አስቀድመው የሚገነዘቡት ቢሆንም በታጋሽነት ከኮምቦልቻ አንድነት ሰብሳቢ አቶ ሰይድ መሀመድ ክሊራንስና መልቀቂያ ይዘው ቢቀርቡም፤ ቦርዱ ‹‹ግለሰቡን እውቅና አልሰጠነውም›› በሚልምላሽ መመለሱን ተከትሎ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ በኮምቦልቻ ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ተከትሎ የሚጠየቅ ሰው ባለመኖሩ፤ ጉዳዩን ወደዞኑ አንድነት ፅ/ቤትበመሄድ በወቅቱ በእጃቸው ማህተም ከያዙ የዞኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ህጋዊ ክሊራንስና የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው ቢመጡም በድጋሜ ቦርዱ ‹‹ህጋዊ ደብዳቤ ብታመጡም አንቀበልም››ሲል ምላሽ የሰጠ ሲሆን ይህን ተከትሎ እጩዎቹ ጋር ከፍተኛ እሰጣ ገባ ውስጥበመግባት ለረዥም ሰዓት ቢከራከሩም እልባት እንደሌለውና በ24 ሰዓት ክልል ምርጫ ቦርድ ይግባኝ አቅርባችሁ ውሳኔው ተሸሮ ካልመጣ በቀር የወሰነው ውሳኔ አይሻርም ብለዋል፡፡ እጩዎቹ በበኩላቸው የእናንተ ውሳኔ ያላስረከቡትን ንብረት ያስረክቡ፤ክሊራንስ ያምጡ የሚል ነው፤ እኛም ምንም እንኳ ከፓርቲው መታወቂያን ጨምሮ ቁራጭ ወረቀት እንኳ ያልተሰጠንና ለትግሉ ከቤት ኪራይ አንስቶ ሌሎች ወጭዎችን ከግላችን አዋጥተን፤ከገንዘብ እስከ ውድ ጊዜያችን ሰውተን የለፋንለት ሰላማዊ ትግልና ፓርቲያችን በዚህ ሁኔታ ወድቆ በመፈራረስ የሆነው ነገር ቢያሳዝነንም ዙራችሁ ባለእዳ ካደረጋችሁን በማለት ከዞን ህጋዊ ክሊራንስና ህጋዊነቱ በደብዳቤ ካልተሻረ ሀላፊ ክሊራንስ አምጥተን አንቀበልም መባሉ አስቀድሞ የተወሰነ ውሳኔና ምርጫ ቦርድም የአጥቂውን ሚና እየተጫወተ እንደሆነ አረጋግጠናል›› …..በማለት ተናግረዋል፡፡
የምርጫ ቦርዱ ሀላፊ አቶ ታደሰ ሻረው የተባሉ ግለሰብ ከእጩዎቹ ጋር ባደረጉት ንግግር ውስጥ፤……‹‹እኛ ስሜታችሁንና እውነታውን እናውቃለን፤ነገር ግን ከበላይ ታዘን በመሆኑ የምናደርጋችሁ ነገር የለም አትልፉ፤ …..ከየትም ደብዳቤ ብታመጡ በአቶ ትግስቱ የተፈረመ ካልሆነ በስተቀር እንዳንቀበል ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቶናል ስለዚህ ያላችሁን መረጃ ውሰዱ በማለት ለእጩዎች የመለሱላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በቃሉና በሌሎች የደቡብ ወሎ ወረዳዎች የሚገኙ የሰማያዊ እጩዎች ተመሰሳይ እጣ እንደገጠማቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Monday, February 16, 2015

ETHIOPIAN Revolution : •“ሠማያዊ ፓርቲ የኔን መዋቅር ተጠቅሞ ነው እጩ ያስመዘገበው” አቶ ትዕግስቱ አ...

ETHIOPIAN Revolution : •“ሠማያዊ ፓርቲ የኔን መዋቅር ተጠቅሞ ነው እጩ ያስመዘገበው” አቶ ትዕግስቱ አ...: -“እጩዎቻችንን ለማስመዝገብ ከቦርዱ አስፈፃሚዎች ተግዳሮት ገጥሞናል” ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ ብሔራዊ በርጫ ቦርድ ወያኔ ሰራሹ አንድነት በአቶ ትዕግስቱ አወሉ እየተመራ ወደ ምርጫ እንዲገባ የወሰነለት እና በአቶ ...

•“ሠማያዊ ፓርቲ የኔን መዋቅር ተጠቅሞ ነው እጩ ያስመዘገበው” አቶ ትዕግስቱ አወሉ

• -“እጩዎቻችንን ለማስመዝገብ ከቦርዱ አስፈፃሚዎች ተግዳሮት ገጥሞናል” ሰማያዊ ፓርቲ
በቅርቡ ብሔራዊ በርጫ ቦርድ ወያኔ ሰራሹ አንድነት በአቶ ትዕግስቱ አወሉ እየተመራ ወደ ምርጫ እንዲገባ የወሰነለት እና በአቶ አበባው መሃሪ እንዲመራ የተወሰነው መኢአድ በምርጫው ለመወዳደር እጩዎቻቸውን ማስመዝገባቸውን ከብሔራዊ በርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል፡፡
ወያኔ ሰራሹ አንድነት ፓርቲ ከ200 በላይ እጩዎች ማስመዝገቡን ያስታወቀ ሲሆን መኢአድ በበኩሉ፤ መረጃዎቹ ተጠናቅረው አልደረሱኝም ብሏል፡፡ ከብሄራዊ በርጫ ቦርድም ፓርቲዎቹ ያስመዘገቧቸው እጩዎችን ብዛትን በተመለከተ ማረጋገጫ ማግኘት አልተቻለም ምክንያቱም ወያኔ ገና ስሌቱን አልጨረሰም፡፡
ወያኔ ሰራሹ የአንድነት ፕሬዚዳንት አቶ ትዕግስቱ አወሉ፤ ወያኔ  ፓርቲውን እንዲመሩ ከወሰነ ጊዜ አንስቶ ከቢሮ መረካከብ ጋር በተፈጠረው የጊዜ መጓተት ምክንያት በ5 ቀናት ውስጥ ብቻ በአዲስ አበባ ሃያ ሶስቱም የምርጫ ክልሎች ጨምሮ ከሱማሌ፣ ጋምቤላና ትግራይ በስተቀር በሌሎች ክልሎች 201 እጩዎችን ማስመዝገብ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡
ለሌሎች ፓርቲዎች የተሠጠው 49 ቀን ሲሆን ለእነሱ 7 ቀን ብቻ እንደተሰጠና ፓርቲው በ5 ቀን ብቻ እጩዎቹን ለማስመዝገብ መገደዱ የፈለገውን ያህል እጩ ማቅረብ እንዳላስቻለው የጠቀሱት አቶ ትዕግስቱ፤ በማስመዝገብ ሂደቱ ፓርቲው በውዝግብ ውስጥ ማለፉ ተግዳሮት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡
የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎም አባላት ወደ ሠማያዊ ፓርቲ መቀላቀላቸው፣ ሠማያዊ ፓርቲ የኛን መዋቅር ተጠቅሞ እጩዎቹን ለማበራከት አስችሎታል ያሉት አቶ ትዕግስቱ፤ የአንድነትን አባላት ማስመዝገቡ የተገቢነት ጥያቄ ያስነሳል  ብለዋል፡፡ “ሠማያዊ ፓርቲ በተለይ በደቡብ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የአንድነት አባላትን አስመዝግቧል” ያሉት የአንድነት ሊ/መንበር፤ ይህም ፓርቲው ቀደም ሲል በአካባቢዎቹ መዋቅር እንዳልነበረውና አጋጣሚውን እንደተጠቀመ ያመለክታል ብለዋል፡፡ “የኛ ሰዎች ባይኖሩ ሠማያዊ ፓርቲ ምን ያስመዘግብ ነበር?” ሲሉ ወያኔው  ትዕግስቱ ጠይቀዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሠጡን የሠማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በበኩላቸው፤ እንኳን ከአንድነት ወደ ሠማያዊ የተቀላቀሉትን ቀርቶ የፓርቲውን ነባር አባላት እንኳ ለማስመዝገብ ችግር ገጥማቸው እንደነበር ጠቅሰው በተለይ ጐጃም ውስጥ ለፓርላማ 10 እጩዎችን እንዳናስመዘግብ ተደርገናል ብለዋል፡፡ ደቡብ እና ኦሮሚያ ላይ በግልጽ ሠማያዊ ፓርቲን የተቀላቀሉ የአንድነት አባላት መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ ዮናታን፤ አዲስ አበባ ላይም ከ23 ቦታዎች በ4ቱ የአንድነት አባላት የነበሩት ይወዳደራሉ ብለዋል፡፡
ሠማያዊ ፓርቲ ከመነሻው 380 መቀመጫ ለማሸነፍ አልሞ 400 እጩዎችን እንደሚያቀርብ አረጋግጦ ወደ ምርጫው እንቅስቃሴ መግባቱን የጠቆሙት አቶ ዮናታን፤ የአንድነት አባላት የነበሩት በፖለቲካ ትግሉ ያበረከቱት አስተዋጽኦ እየተመዘነ ለቦታዎቹ ታጭተው የነበሩ የሠማያዊ ፓርቲ አባላትን በመተካት እንዲገቡ ተደርጓል እንጂ ሠማያዊ የእጩ ችግር የለበትም ብለዋል፡፡ ለአንድነት የተመዘገቡ እጩዎች ሣይቀሩ ከአንድነት ለቀው ለሠማያዊ የመመዝገብ መብትም እንዳላቸው ሊታወቅ ይገባል ብለዋል አቶ ዮናታን፤ የመኢአድ የምርጫ አስተባባሪ በበኩላቸው፤ ፓርቲው በተሰጠው አጭር ጊዜ ውስጥ እጩዎቹን ለማስመዝገብ መሞከሩን ጠቅሰው ምን ያህል እጩዎች ተቀባይነት አግኝተው ተመዘገቡ የሚለውን ለማወቅ ገና ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ETHIOPIAN Revolution : 12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር በኩዌት ታሰሩ

ETHIOPIAN Revolution : 12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር በኩዌት ታሰሩ:          የኩዌት መንግስት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በህገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ በማስገባት በቤት ሰራተኝነት ያስቀጥራሉ የተባሉ  12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝ...

12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር በኩዌት ታሰሩ

የኩዌት መንግስት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በህገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ በማስገባት በቤት ሰራተኝነት ያስቀጥራሉ የተባሉ  12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እንዳስታወቀ አረብ ታይምስ ዘገበ፡፡
የሚኒስቴሩን መግለጫ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፤ 12 ሴቶችንና አንድ አሽከርካሪን በአባልነት ይዞ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ስራ ላይ እንደተሰማራ የተገለጸው ይህ ቡድን፣ በአንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት መሪነት በህገወጥ መንገድ ወደ ኩዌት የሚያስገባቸውን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለአገሪቱ ዜጎችና ለሌሎች አገራት በቤት ሰራተኝነት ሲያስቀጥር ቆይቷል፡፡
የኩዌት የነዋሪዎች ጉዳይ ምርመራ ክፍል ባለስልጣናት፤ በድኑ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ላይ እንደተሰማራ ከታማኝ ምንጭ ያገኙትን መረጃ መሰረት በማድረግ ባካሄዱት ክትትል፣ የቡድኑን አባላት የህገወጥ የሰዎች ዝውውር በሚያከናውንበት ጀሊብ አል ሹዮክ የተባለ የአገሪቱ ክፍል በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
የቡድኑ አባላት ከአገሪቱ የሰራተኞች ቢሮ ጋር የስራ ግንኙነት ያላቸውና በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ በማስመሰል በበርካታ የኩዌት ነዋሪዎች ላይ የማጭበርበር ድርጊት ሲፈጽሙ ነበር ብሏል፤ ዘገባው፡፡
በቁጥጥር ስር በዋሉት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እየሰሩ እንደሚገኙም ዘገባው አመልክቷል፡፡

እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ከፖለቲካ ፣ ሲቪክ ፣ የሃይማኖት ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ፤

«ለውጥ በማይቆም ተሽከርካሪ የሚጓዝ አይደለም፤ የተከታታይ ትግል ውጤት ነው። ነጻነት የምንፈልግ ሁሉ ጀርባችንን ቀና አድርገን መታገል አለብን። ራሳችን ካልፈቀድንለትና ካልተሸማቀቅን፤ ማንም ሰው እንደ ከብት ሊጋልበን ከቶ አይችልም» ነበር ያሉት ዶር ማርቲን ሉዘር ኪንግ ጁኔር ። በማንኛውም አገር ቢሆን፣ ነጻ የሆነ የዜና አገልግሎት የማያገኝ፤ ተቆርቋሪ የፖለቲካ ወይንም የማህበረሰብ ወይንም የሲቪክ ድርጅት እና በነጻነት የሚንቀሳቀስ የመገናኛ ብዙሃን አገልግሎች የሌለው ሕዝብ መብት የለውም። መብቱ በመንግሥት የተከለከለ ግለሰብ ሆነ ቡድን፤ ማህበረሰብ ሆነ ሕብረተሰብ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት አይጎናፀፍም።
ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለሃያ አራት ዓመታት በበላይነት ሲገዛት የቆየችዋ ኢትዮጵያችን ፍትህ፤ ነጻነት፤ ሰብአዊ መብት፤ የሕግ የበላይነት የማይታይባትና አምባገነናዊ ስርዓት የሰፈነባት ሃገር ሆናለች። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ የመድበል ፓርቲ ስርዓት የምትከተል መሆኗ በሕገ መንግስቱ ቢደነገግም፣ በተግባር የታየው ግን ከገዝው ሕወሃት/ኢሕአዴግ ነጻ የሆኑ ድርጅቶችን ሁሉ የማጥፋት ሂደት ነው። የአገሪቷን ሕግ ሆነ የምርጫ ቦርድን አሰራር በጣሰ መልኩ፣ በቅርቡ በአገሪቷ ጠንካራ የሚባለውን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አመራርን በማገድ ራሱ ያቋቋማቸዉን ተለጣፊ መሪዎች መሾሙ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በምርጫ የማያምንና፣ ብቻውን ለሚቀጥሉት ሃያ፤ ሰላሳ አመታት በጉልበት ለመግዛት እንደወሰነ አመላካች ነው። የዜጎችን የመደራጅትና የመሰባሰብ ሰባአዊ መብትም የረገጠ ነው። በአንድነት ፓርቲ ላይ ከታየው የሕወሃት/ኢሕአዴግ ያገጠጠ ኢፍትሃዊ እርምጃ በተጨማሪ፣ በሌሎች የፖለቲካና የሲቪክ ማህብራት ላይ አፈናዉና የመብት ረገጣው ተባብሷል። በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ ድርጀቶች ሁሉ ህልውናቸው አደጋ ላይ ነው። ዜጎችን ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ ይደበደባሉ። ጋዜጠኞች የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት መሪዎች ይታሰራሉ።
ሕወሃት/ኢሕአዴግ በሚያራምዳቸው የተሳሳቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ዜጎች ባስከፊ በድህነት እና የኑሮ ዉድነት ስቃይ ዉስጥ እንዲዘፈቁ አድርጓቸዋል። የስራ እድል ማጣት፤ የተፈጥሮ ሃብት ከኢትዮጵያዊያን ተነጥቆ ለጥቂቶች ሃብት ማካበቻ መሆን፣ የጎሳ አድልዎ፣ ጉቦ፣ ሙስና፣ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከሕግ ውጭ ማሸሽ፣ በኢትዮጵያዉያን መካከል ስርዓት ወለድ የሆነ የጎሳና የኃይማኖት መለያየት በአገራችን ትልቅ ቀዉስን እና ዉስጣዊ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ከመቼዉም ጊዜ በላይ አገራችን ትልቅ አደጋ ላይ ትገኛለች። መንግስት የሕዝብ አገልጋይ ሊሆን ይገባዋል። ህወሃት/ኢሕአዴጎች ግን በመንግስት ወንበር ላይ ተቀምጠው ህዝብን ማገለገል ሳይሆን ህዝቡን እየከፋፈሉትና እያሰቃዩት ነው። ለሃያ አራት አመታት በህዝብ እና በሀገር ላይ እጅግ ብዙ በደል ፈጽመዋል። ይህን ለማስቆም ኢትዮጵያዉያን ቆርጠንና ደፍረን፣ አገር አቀፍ በሆነ ደረጃ መነሳት ይኖርብናል። በውጭና በውስጥ የምንገኘው ለውጥ እና ፍትህ ፈላጊ ኃይላት፣ አብረን ተባብረን መስራት ግዴታችን ሆኗል። ሕወሃት የሚፈልገው በየተራ ለማጥቃት እንዲያመቸው በተናጥል የሚደረግን ትግል ነው። ትግሉ የመኖር ያለመኖር፤ የህልውና ጉዳይ ስለሆነ አብሮ ተያይዞ መነሳት የወቅቱ መሪ ጥያቄ ነው።
እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው ስብስቦች እንደዚህ ያለ ተከታታይ ግፍ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲካሄድ በአንድ ላይ ድምፃችን ማሰማት ግዴታችን ነው እንላለን። ስለሆነም፤ በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትን ህገወጥ በሆነ መንገድ የገዝው ቡድን መሳሪያ በሆነው የምርጫ ቦርድ አማካይነት ከሀላፊነታቸው በግዳጅ አባሮ በአባላት ያልተመረጠ ግለስብ በመሪነት መሾሙን አጥብቀን እናወግዛለን። ለዚህ በስርአቱ ለተሾመ ግለሰብም፣ እውቅና የማንሰጥ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብር እንዲነፍገው እንጠይቃለን። የተለጣፊው ቡድንም፣ ሊወድቅ የተቃረበን የግፍ አገዛዝ ለማገለገል በወሰዳቸው አሳፋሪ ተግባራትም ተጠያቂ እንደሚሆን ለማሳሰብ እንወዳለን። ስርአቱ በመኢአድ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና በቀጣይ የከፋፋይነት ስራ ድርጅቱን ለማዳከም የሚያካሂደውን ሁሉ ተገንዝበናል። ይህ የገዥው እኩይ ተግባር እውን የሚሆነው በከፊል በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን ችግሮች በመመካከር ማስወገድ ሳይቻል ሲቀርና ለገዥው ቡድንም ጣልቃ መግባት መንገድ ሲከፍት እንደሆነ በመገንዘብ፣ ሁሉም የድርጅቱ መሪዎችና አባላት ውስጠ ድርጅት ቅራኔዎችን በውስጥ አሰራር፣ በመቻቻል፣ በሆደሰፊነትና በተለመደ ሀገራዊ ጨዋነት በመፍታት ሁሉም የድርጅቱ አባላት እንዲሰባሰቡና ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን በጋራ እንዲወጡ እናበረታታለን።
ገዥው ቡድን በአንድነት ፓርቲ ላይ የማፈራረስ እርምጃ ሲወስድ የድርጅቱ አባላት ፣ ተስፋ ቆርጠው፣ ትግሉን እርግፍ አድርገው እንዲያቆሙ ወይም ሀገር ጥለው እንዲሰደዱ ለማድረግ ነው። ይህን በማድረግም አላንዳች ተቀናቃኝ ሁሉንም ተቆጣጥሮ በህዝባችን እና በሀገራችን ላይ የጀመረውን የግፍ አገዛዝ ለመቀጠል ነው። ሆኖም ሁላችንም እንደተመለከትነው አፍራሹን ህወሀት/ኢህአዴግን በሚያሳፍር ለውጥ ፈላጊውን ደግሞ በሚያኮራ መልክ በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ያሉ በዛ አሉ የአንድነት አባላት አሁንም ትግሉን ለመቀጠል ወደ ሰማያዊ ፓርቲ እየተቀላቀሉ መሆናቸውን እንገነዘባለን። በዚህ እጅግ ፈታኝ በሆነ ሰዓት ከድርጅት በላይ ሀገርንና ነጻነትን በማስቀደም በወሰዱት ቆራጥ እርምጃ ያለንን አድናቆት እየገለጥን ወደ ሰማያዊ ያልተቀላቀሉ ጥቂት የአንድነት አባላትም የአንድነትና የዴሞክራሲ ሀይሎችን በመቀላቀል ትግላቻውን እንዲቀጥሉ እናበረታታለን።
ሁሉም የአንድነትና የዴሞክራሲ ሀይሎች የህወሀት/ኢህአዴግን ቀጣይ አፈና መቋቋም የሚቻለው ተነጣጥሎ ሳይሆን በጋራ በመቆም እንደሆነ በመገንዘብ አሁንም ትብብራቸውን አጠናክርው ትግላቸውን እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። በአፋኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ስርአት ስር ለሀገር አንድነት፣ ለህዝብ መብት መከበርና ግፈኛውና ከፋፋይ ስርአት ተደምስሶ በምትኩ ለህዝብ ሙሉ መብት መከበር፣ ለሀገር እንድነትና፣ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስታዊ ስርአትን ለመመስረት ለሚደረገው ትግል ያለንን አጋርነት በጋራ እናረጋግጣለን። ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። ነጻነት ስለተመኘናት አትመጣም። የኛ እጅ ለእጅ መያያዝና መተባበር የአምባገነኖች ፍጻሜ መጀመርያ ነው። በመሆኑም በተጨበጡ ሥራዎች ዙሪያ ትብብራችንን እያጠናከረን፣ አገር ቤት ለሚደረገው ትግል ሙሉ ድጋፍ እያሳየን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል እንደመሆናችን የህዝባችን ነጻነት እስኪያረጋግጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሳንታክት በጽናት የምንታገል ስለመሆናችን ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን።
የሴቶች የሰብዓዊ መብት ድርጅት
የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት
የሰማያዊ ድጋፍ ማህበራት
የአንድነት የስዊዱን ድጋፍ ማህበር
የአንድነት የለንደን ድጋፍ ማህብር
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ
ሞዓ አንበሳ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ድርጅት በካናዳ (ሶሴፕ ካናዳ)
ጋሻ ለኢትዮጰያ የሲቪክ ድርጅት
ኢትዮጰያዊነት የሲቪክ ድርጅት
ኢትዮ ሶሊዳሪቲ ሚኔሶታ
የአንድነት የሰሜን አሜሪካ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ኮሚቴ
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (በስሩ የሚገኙት አባል ድርጅቶች ሁሉ
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ዴሞክራሲያዊ)
የኢትዮጵያ መድህን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)
ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት)
መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መ.ኢ.ሶ.ን)
የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ስብስብ በእንግሊዝ ሀገር
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ኢፓእአኮ)
ኢትዮጵያ ሲቪል ኅብረተሰብ ደጋፊዎች በለንደን ኦንታሪዮ