Tuesday, May 31, 2016

እነ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ያለቀጠሮአቸው ተገደው ፍርድ ቤት ቀረቡ


ፍርድ ቤቱ የተክሳሽኦችን የመክላክያ ምስክሮች በምን ጭብጥ ላይ እንደሚያስመሰክሩ ከምስክሮቹ ቀጠሮ አስቀድሞ እንዲገለፅ ጠይቃል።
–ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ እና ማረሚያ ቤት ህገወጥ ጫናና ወከባ እየፈጠሩብን ነው ብለዋል የክስ መዝገባቸው በከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት
በመታየት ላይ የሚገኘው 4 ተከሳሾች ብርሀኑ ተ/ያሬድ ፤እየሩሳሌም ተስፋው፤ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ
ብይን በሰጠባቸው ጉዳአዮእ ላይ የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ ከግንቦት 30-ሰኔ 8 ክትሮ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግንቦት 23 ቀን ያለቀጠሮዋቸው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጋል ተከሳሾቹ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሌላቸው ለማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች የገለፁ ቢሆንም በማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ሃላፊዎች
ወከባና ግፍተራ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችላል። ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ከቀረቡም በኃላም ለፍርድ ቤቱ ይህንን ያስረዱ ሲሆን የፍርድ ቤቱም ዳኛም “ዛሬ ቀጠሮ ባይኖራችሁም ፍርድ ቤቱ ማጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ነው የጠራናችሁ”በማለት የተከሳሾቹ መከላከያ ምስክሮች የሚመሰክሩበትን ጭብጥ ተከሳሾቹ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ
እንዲያስረዱ ጠይቀዋል ተከሳሾቹም ምስክሮቻቸው የሚመሰክሩበት ጭብጥ ምስክርነት በሚሰጥበት እለት እንጂ ምስክሮቹ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ለፍርድ ቤቱ የማሳወቅ ህጋዊ ግዴታ የሌለባቸው መሆኑን የገለፀ ሲሆን ዛሬ በፍርድ ቤቱ እየተጠየቁ ያለው ቅድመ ሁኔታ ግን ህጋዊ መሰረት የሌለው እና ፍርድ ቤቱም የሌሎች የገዢው ፓርቲ የአፈና መዋቅርት ተፅእኖ እንዳረፈበት የሚያሳይ ነው ብለዋል. ተከሳሾቹ አያይዘው እንደገለፁትም ለምስክሮች የተዘጋጀው መጥሪያ በፍርድ ቤቱ ዳኛ ተፈርሞ ለምስክሮቻቸው እንዲሰጥ ማረሚያ በት ለሚገኙ ተከሳሾች ከደረሳቸው በሀላ በድጋሚ“በፍርድ ቤት ትእዛዝ ነው” በሚል ምክንያት መጥሪያዎቹን
የተነጠቁ ሲሆን በማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች በኩልም መከላከያ ምስክሮቻቸውን በተመለከተ በተለይም የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለምስክርነት ማስጠራታቸውን ተከትሎ ማስፈራርያና ወከባ እየደረሰባቸው ነው በመጨረሻም ተከሳሾቹ የምስክሮቻቸውን ጭብጥ ለፍርድ ቤቱ እንደማያሳውቁ በአፅንኦት የገለፁ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ዳኛ “ከአነጋገራችሁ የምስክሮቹን ጭብጥ ለመረዳት ጭለናል በመሆኑም ይህኑኑ ጉዳይ መርምረን ለግንቦት 30-2008 ብይን እንሰጥበታለነረ “ በማለት ተከሳሾቹን በተጠቀሰው ቀን እንዲርቡ ትእዛዝ ሰጥተዋል።

28/05/2016 Ethiopian in Stockholm was to attend a fundraising gathering...

Monday, May 30, 2016

ዜና መረጃ… በረከት ስሞን አርበኞች ግንቦት 7 ያለዉ ዉስጣችን ነዉ ይላሉ!!


ወሎን ሰፈር ተሻግሮ ሩዋንዳ ሙልሙል ዳቦ አካባቢ ወደ ቦሌ በሚወስደዉ መንገድ በስተቀኝ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ይገኛል ከዩኒቨርሲቲዉ በተጓዳኙ በስተግራ ካለዉ ነጭ ህንጻ ላይ በደረጃ ቀስ እያልን ወደ 5ተና ፎቅ አመራን ከቢሮዉ በተያያዘ ቱሪዝም ኤጀንሲ ባጎራባች ሲኖር ከስሩ ደግሞ ሱፐር ማርኬት አለ በዋናነት ወደዛ የሄድንበት ምክንያት የበረከት ስሟን ቢሮ እዚያ እንደሚገኝ በደረሰን መረጃ መሰረት ነዉ።
ቢሮዉ እነደደረስን ጸሐፊዉን ለማግኘት ትንሽ ብንጠብቅም አግኝተን አናገርናት የበረከት ስሞን ቢሮ መሆኑን ካረጋገጥን በኍላ ትንሽ ጠብቁ ተብለን ተቀመጥን ከጥቂት ቆይታ ወዲህ በረከት በሁለት ሰዎች መካከል ሆኖ ከተፍ ሲል ተመለከትነዉ የመሰብሰቢያ ቢሮ በመሰለዉ ቢሮ ዉስጥ በአይኑ ሁላችንንም ገርበብ አድርጎን በአንገቱ ሰላምታ ሰጥቶን ወደ ዉስጥ ዘለቀ!
እኛም እዚያዉ መጠበቅ ጀመርን ከጥቂት ቆይታዎች በኍላ እቃ እንደረሳንና በሌላ ቀን እንደምንመለስ ለጸሐፊዋ ነግረን ተመልሰን ወጣን።
መኪናችን ዉስጥ ገብተን ወደተቀመጥንበት ሆቴል ገሰገስን ክፍላችን ዉስጥ እንደገባን መቀረጸ ድምጻችንን በቢሮዉ ዉስት ንደምን ለጥፈነዉ እንደወጣን እየተወያየን ተዝናናን!
ክትትላችንንም በመጠኑ በተለያዩ አካሎቻችን በማከናወን መግቢያ መዉጫቸዉን አጠናን ከ3 ቀናት በኍላ የተቀረጸዉን ድምጽ በእጃችን አስገባን መቅረጻችንም በጥቂቱ ይህን ይዟል።
_አቶ በረከት… አርበኞች ግንቦት 7 በየሐገሩ በየቦታዉ የተደራጀ ሐይል አለዉ ከእንግዲህ አ/ግንቦት 7 ልግባ መንገድ ልቀቁልኝ ወይም አሳልፉኝ አይልም ከእንግዲህ አ/ግንቦት 7 ገፍትሮንም አይገባም አ/ግንቦት 7 ያለዉ ዉስጣችን ነዉ! ከባዱ ስራ የሚሆነዉም ይህዉ ነዉ! የሚጠረጠሩ ግለሰቦች በሙሉ የመኖሪያና የመስሪያ ቦታቸዉ ድረስ እየተዞረ የፎቶና የተለያዩ ተጨባጭ መረጃዎች ይያዝ! ያለበለዚያ ምን እንደምንሰራ አይገባንም።
_አቶ ሳህረ የሚባል የብሄራዊ መረጃ ተወካይ…. በትክክል ብለዋል አቶ በረከት አባሎቻችን መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ነዉ የመጣነዉ እንዲሁም ከማህበራዊና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ የመጣነዉ እያሉ ቤት ለቤት ሁሉ እየዞሩ ነዉ። ግን መረጃዎችን ለማግነት ይህ ብቻ በቂ ነዉ ብለን አናስብም።
በሌላኛዉ እለት እዚያዉ ቢሮ ተገኘንና አቶ በረከትን አነጋግረን ድምጸ መቅረጻችንን ካስቀመጥንበት አንስተን ወጣን እንግዲህ በአሁኑ ወቅት ወያኔ ይህዉ ነዉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )

Saturday, May 28, 2016

Ethiopian in Stockholm was to attend a fundraising gathering about the Esat day

  • Ethiopian Satellit Television ESAT sixth year anniversary of service started date colorfully honored in Sweden the capital of Stockholm may 282016. From Amsterdam ESAT journalist Gelila Mekonen and Afework Agdaw top guest inattandance.
  • Program which was started by the religious father talk next come discussion about the day was and also stating the love and respect song for ESAT, Traditional dance and poetry competition was also near.
  • The main reason establish enthusiat ESAT is there is no any free media in Ethiopia. As a result , the society can not get any information. The dectator and racists Government purpusely preventing infomation from society. To eliminat this problem ESAT last 6 years work hard  vital information access to society this has high contributed  build democratic country, human right and low honored, based on race and corruption rule to become end so ESAT founded six year ago too fight at this level. http://video.ethsat.com/?p=25689
                                                                                                 

Friday, May 27, 2016

ሰበር መረጃ በኢቲዮ_ኤርትራ ድንበር ከፍተኛ ጦርነት በነፃነት ዓሎችና በወያኔ ወታደሮች ተካሄደ


74 ከአ/አ ከጎንደር ከሀረር ደቡብ ወዘተ የተሰባሰቡ ነፃነት የጠማቸዉ በምህንድስናና በጤና ድግሪ ያላቸዉ ወጣቶች በኢቲዮ_ኤርትራ ድንበር ከተማ ከትመዋል ወጣቶቹ ከመላዉ ኢ/ያ የተሰባሰቡት ቀጭን ቀጠሮ ይዘዉ ነዉ:: ማእከላዊነት ፈጥረዉ ሁሉም ሌሎች የተቀጣጠሯቸዉን ይጠባበቃሉ:: ከወጣቶች መሀል አንደኛዉ ስልኩ ቢዚ ሆኗል:: ቶሎ ቶሎ ያናግራል:: የሚያወራዉ ስልክ Unknown number ይላል:: ስልኩ ከኢትዮጵያ ዉጭ ነዉ::
”ሃሎ ሃሎ” ይላል ልጁም ተመሳሳይ መልስ ይመልሳል::
”ከርቀት እየተጠባበቃችሁ ተንቀሳቀሱ መንገድ ጀምሩ ስላችሁ ብቻ ወደተከዜ ሰሜን አቅጣጫ ኑ:: የሚመራችሁ ከጀርባዉ የኢትዮጵያ ባንዲራ የተለጠፈበት ወጣት ይመጣል:: እሱ ወደሚሄድበት ተከፋፍላችሁ ከ7 በማይበልጥ ስብስብ ተከተሉት:: አሁን ልጁ ይታያችሁዋል አደል? ጀምሩ!”
አለ የማይታወቀዉ ስልክ ይመጣል የተባለዉ መጣ:: 7 ሰባት እየሆኑ መከተል ጀመሩ:: ጫፍ ላይ ደርሰዋል:: በአካባቢዉ ዝር የሚል የለም:: የሚመራዉ ጠንከር ፈርጠም ያለዉ ወጣት ጃኬቱ ስር ታጥቋል:: ከመቅፅበት ቁም የሚል ከሁለት አቅጣጫ ከአንድ ጥይት ጋር ተሰማ:: የኢ/ያ መከላከያ 24ኛ ክ/ጦር ሻለቃ አባል ነበር:: ወዲያዉ ቁም ያለዉ ወታደር ተመቶ ወደቀ:: ማን እንደመታዉ አልታወቀም:: ወጣቶቹ ግራ ገባቸዉ:: ተኩስ ከየአቅጣጫዉ ይፈነዳል:: የኢ/ያ ወታደሮች በየቦታዉ ሲወዳድቁ ይታያል:: ጥይት ወደወጣቶቹ አልተተኮሰም::
”ማን ከማን ጋር ነዉ?” ሲል ከፊት የሚመራዉን ፈርጣማ ወጣት ከወጣቶቹ ሲደዋወል የነበረዉ ጠየቀ::
”አይዟችሁ ደርሰዋል:: እኛን የሚመሩን የነፃነት ሀይላችን ሰራዊት ሊያጠቁን ከመጣ ከወያኔ ወታደር ጋር ነዉ የገጠሙ:: ደርሰናል:: ቅርብ ናት የ5 ደቂቃ መንገድ ነዉ የቀረን ጀግኖቹ እየተፋለሙ ነዉ:: እኛ ሰላም ነን… ”…
(የቀጠለ) በርቱ ደርሰናል:: አሀን ያለንበት የኤርትራ ምድር ነዉ:: ቅድም ወንዙን ከመሻገራችን በፊት ያለዉ መሬት ነዉ የኢትዮጵያ:: ዉጊያዉ ያለዉ ከኢትዮጵያ መሬት ነዉ:: አንዱን ሻለቃ የ24ኛ ክፍለ ጦር እያርበደበዱት ያሉት ከ30 የማይበልጡ የነፃነት ጉዋዶቻችን ናቸዉ:: የዉስጥ አርበኞችም እያገዟቸዉ ነዉ:: ገዥ መሬት ስለያዙ ለማጥቃት አይቸገሩም:: ትርርርር ያለ ተኩስ የሚተኩሱት ወያኔወች ናቸዉ እዉር ድንብሱን ተስፋ በቆረጠ መልኩና እየተብከነከኑ ስለሚተኩሱ ድምፁ እንደዛ ነዉ በአንድ ቃታ ነዉ 30 ጥይት የሚጨርሱት:: በፍርሀት ሳያስቡት እኛን ለመብላት ብቻ ስለመጡ ሳያስቡት በገጠማቸዉ ጠንካራ ጡጫ ተደናብረዋል:: ብዙዉን ማጥቃትም መከላከልም አያደርጉም በተለይ እንደዛሬዉ ካላሰቡት:: ወደሀዋላ ነፋስ እየደበደቡ እየተኮሱ ነዉ እግሬ አዉጭኝ የሚሮጡት:: በመትረየስ ሽፋን ጣ….ጣ…ጣ…ጣጣጣ…ጣጣ የሚለዉ ተኩስ ድምፅ ደሞ የኛወቹ የነፃነት ሀይሎች ናቸዉ:: እያዩ ነዉ የሚሮጠዉን የሚቀልሙት:: የወያኔ ወታደር ነፃነት ሀይሎች መጡ ከተባለ ላብ በላብ ነዉ የሚሆኑ:: በፍርሀት ነዉ ቀድመዉ ነዉ የሚሞቱት:: የተማረኩ ወታደሮች የሚሉትም ይሄኑ ነዉ:: በነፃነት ሀይል ባህል ተኩሶ አደለም መሳት ያሰቡት ነጥብ ላይ አለማሳረፍ ያሳፍራል:: ታያላችሁ ማንም ሳይሰዋ ነዉ የሚመለሱት… ለማንኛዉም እኛ ወደካምፕ ተጠግተናል:: በሁለት ተሰለፉ 27 ሀያ ሰባት ሁኑ::” አለ መሪያቸዉ:: የነፃነት ታጋይ አባል:: ወዲያዉኑ የነፃነት ሀይሎች ከርቀት በተረጋጋ መንፈስ ሲመጡ ይታያሉ:: ፈርጣማዉ የነፃነት ሀይሎች አባል አጨበጨበ:: ”ይሄዉ ታጋዮቻችን ሁለት ሶስት ክላሽና መትረየስ እየተሸከሙ ከሄዱት 30 ተራብተዉ 55 ሆነዉ እየመጡ ነዉ:: የነፃነት ሀይል መሸነፍ አያዉቅም:: በተለይ እጅ መስጠት
ጠት አይታሰብም:: (የቀጠለ)…ብም:: ሁሉም በድል ተመልሰዋል:: እዛዉ ስለምንገናኝ እንድረስና አረፍ እንበል:: እንግዲህ ሀያ አምስቱ ተጨማሪወቹ የወያኔ የተማረኩትና የዉስጥ አርበኞች ናቸዉ ማለት ነዉ:: ቃኘዎችና የዉስጥ አርበኞቻችን ነበሩ:: የመሩት እነሱዉ ናቸዉ:: የዉጊያዉን ሁኔታ እስቲ ልጠይቅ…” ብሎ መገናኛዉን አወጣና ነካ:: ”ሀሎ ኦ7 ሃሎ ይሰማል ኦ7 ይሰማል:: ኦ74 ነኝ!” አለ:: ”ከዛኛዉ ማዶም ሀሎ ኦ74 ይሰማል ኦ7 ነኝ በሰላም ገባችሁ? እያየናችሁ
ነዉ:: እኛ በሰላም ተመልሰናል:: የተወሰነ ማርከናል ከ171 በላይ ሙትና ቁስለኛ ተመዝግቧል ከኛ 2 ጉዋዶች በመጠኑ ቆስለዋል:: ሁላችንም ጠመንጃወችና
ትጥቆችን ማርከናል:: የዛሬዉ በተለይ ከንጋጋቱ ያገኘነዉ ድል ልክ የለዉም:: ከባድ ጉዳት ነዉ ያደረስነዉ:: የዉስጥ አርበኞቻችንም ይዘናል:: የተሳካ ነዉ:: በቀን
16/09/2008 ቀንቶናል::” በሉ እዛዉ እንገናኝ ቻዉ ኦ74 ቻዉ ሞርኮ የሚቀበለን ደጀን ሀይል ደርሶልናል:: ሰላም ግቡ ደርሰናል::” ብለዉ ተሰነባበቱ::
በ16/09/2008 ሌሊት ጀምሮ ከመላዉ ኢትዮጵያ ተጠራርተዉ የመጡ ወጣቶችን ወደ ነፃነት ሀይሎች ለመቀላቀል የተደረገ ፍልሚያ በነፃነት ሀይሎች አሸናፊነት ከ171 በላይ የወያኔ ወታደር በመግደልና በማቁሰል የጦር መሳሪያም በመማረክ ነፃነት የጠማቸዉን ወጣቶች በሰላም እንዲቀላቀሉ በማስቻል ተጠናቀቀ::
ህሊና ፀረወያኔዋ
 

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ስላለው የዴሞክራሲ ችግር ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እየተወያየሁ ነው

በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲ ችግሮች ላይ ዝምታን መርጧል የሚል ትችል እየቀረበበት ያለው የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ ያለውን ችግር በተለያዩ መድረኮችና ከባለስልጣናት ጭምር በመግለጽ ላይ መሆኑን አስታወቀ።
በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደረጉና ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩት የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት “ትክክለኛ የሆነ አመራር በአፈና ላይ የተመሰረተ መሆን የለበትም” ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካል ቅሬታቸውን መግለጻቸውንም ይፋ አድርገዋል።
በአውሮፓ ፓርላማ ካሉ የፖለቲካ ተወካዮች መካከል ዋነኛ የሆነው የሶሻሊስትና የዴሞክራቲክ ጥምር ፕሬዚደንት የሆኑት ጅያኔ ቲፔላ ህብረቱ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ዝምታን አለመምረጡና ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እየተከታተለው እንደሆነ አዲስ ስታንዳርድ ከተሰኘ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል።
እንደሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ሁሉ በኢትዮጵያ ያለውም የልማት እንቅስቃሴ ከዴሞክራሲ ተለይቶ የሚታይ ጉዳይ አለመሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል።
የአውሮፓ ህብረት ሽብርተናነትን ለመዋጋት በሚል በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ችላ ብሎታል ተብሎ ስለሚቀርቡ ቅሬታዎች የተጠየቁት ጂያኒ ቲፔላ በሃገሪቱ በመገናኛ ብዙሃን የፖለቲካ አመራሮች ላይ የተወሰዱ የእስር ድርጊቶችን በአደባባይ በማውገዝና ስጋታቸውን በመገለጽ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በተወያዩ ጊዜ ይሁንኑ ጉዳይ በአግባቡ ማስረዳታቸውንና ህብረቱ ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ይልቅ ለዴሞራሲ መከበር ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
የአውሮፓ ፓርላማ ቡድን በቅርቡ በኢትዮጵያ ላይ ሊወሰዱ ስለሚገቡ ጉዳዮች የተጠየቁት የፓርላማ አባሉ፣ ህብረቱ ውሳኔውን ካስተላለፉ በኋላ የሚወሰዱ ለውጦችንንና እርምጃዎችን እየተከታተለ መሆኑን አክለው አስረድተዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመውን ግድያና የጅምላ እስራት ተከትሎ የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ጉባኤን በመጥራት የተለያዩ ውሳኔዎችን ማፅደቁ ይታወሳል።
በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎች ድርጊት እንዲጣራ ጥያቄን ሲያቀርብ የቆየው ህብረቱ ከተቃውሞው ጋር በተገናኘ ለእስር የተዳረጉ የፖለቲካ አመራሮችና ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁም በማሳሰብ ላይ ነው።

Thursday, May 26, 2016

ጋዜጠኛ ጌታቸውን ከከሰሱበት ፍሬከርስኪ ክሶች መካከል የተወሰደ


“ተከሳሽ በሚጠቀምበት ማሀበራዊ ድህረ ገጽ በተለይም ፌስ ቡክ አድራሻዉን ተጠቅሞ በዉጭ አገር ከሚገኝ የሽብር ቡድኑ ግንቦት ሰባት አመራር እና አባል የሆነው ግርማ ካሳ ተብሎ የሚጠራ ግንኙነት በመፍጠር በሽብር ቡድኑ የተሰጠዉን ተልእኮ በማስፈጸም በቀን 27/2/2007 ዓ/ም፣ በ28/2/2007 ዓ/ም፣ በ10/6/2007 ዓ/ም፣ በ11/06/2007 ዓ/ም፣ በ18/06/2007 ዓ/ም፣ በ01/07/2007 ዓ/ም እየተገናኙ ስለ ግንቦት ሰባት እና አሸባሪ ተብለው የተከሰሱትን ቤተሰቦቻቸው እንዴት ሊደገፉ እንደሚችሉ የሚገልጽ የተለያዩ ይዘት ያላቸው መረጃዎች የተለዋወጡ በመሆኑ በዝርዝር ያደረጉት ንግግር በክሳችን በተጠቀሰው ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ”…
ጋዜጠኛ ጌታቸውን ከከሰሱበት ፍሬከርስኪ ክሶች መካከል የተወሰደ ነው። የአንድነት ፓርቲ እውቅናዉን ከተነፈገ በኋላ የአንድነት ደጋፊዎችና ለሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ የእስረኞች ኮሚቴ አቋቁመን፣ መጠነኛም ቢሆን የሕሊና እስረኞች ቤተሰቦችን (ኢኮኖሚካሊ ችግር ላይ ያሉትን) ለመደገፍ ጥረት ስናደርግ ነበር። በቂ ነበር? በቂ አልነበረም። ካደረገነው የበለጠ ማድረግ እንችል ነበር ? በሚገባ። ግን ትንሽም ብትሆን ከምንም ይሻላል።
አሁንም ያ ጥረት እየቀጠለ ነው። የአንድነት እስረኞችን ብቻ ሳይሆን፣ የመድረክ፣ የሰማያዊ፣ የመኢአድ፣ ጋዜጠኞና በዉሸት ክስ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው የተፈረደባቸውንም ሳይቀር። የትም ድርጅት ይሁኑ ሁሉም የታሰሩት ለአገርና ለሕዝብ ነውና የሕሊና እስረኞች ናቸው። ጀግኖቻችን ናቸው።
በዚህ ረገድ የምናደርገው እንቅስቃሴን ነው እንግዲህ “ሽብርተኝነት” ተደርጎ ለክስ እያቀረበ ያለው። በዉሸት ክስ መከሰሳቸው ሳያንሳቸው፣ እስረኞችን ኢሰብዓዊ ጭካኔ እየፈጸሙ መደብደባቸው ሳያንሳቸው፣ የነርሱን ልጆች ለመዝናናት በፓሪስና በዱባይ እየላኩ የሌሎች እስረኞችን ልጆች ያስራቡት ሳያንሳቸው ፣ አሁን ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ለእስረኞች ቤተሰቦች ድጋፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ “ሽብርተኝነት ነው” ይላሉ። ከዚህ የበለጠ ጭካኔ፣ ከዚህ የበለጠ አሪዮስነት ምን አለ ?
በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ አይምሮ አለን የምትሉ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች እንድትጽፉና የምትደግፉት ድርጅት አመራሮች ላይ ግፊት እንድታደርጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ይኸው 25 አመት ደፈናችሁ። ምንድን ነው እየሆናችሁ ያላችሁት። በጫካ ከነበረችሁበት ጊዜ ሁሉ የባሰ አዉሬዎች እየሆናችሁ ነው ? እንዴት ነው ሳንወድ በግዳችን፣ የምንቃወመዉን ደርጅት እንድነቀላቀል ነው እንዴ የምትፈልጉት? እኛ የግንቦት ሰባት አካሄድ አያዋጣም እያልን እየተከራከርን፣ መልሳችሁ እኛን ” የግንቦት ሰባት አመራር አባል” ብላችሁ ስትሰይሙን እንደው አታፍሩም?
ለማጠቃለል ትንሽ ስለ ጌቾ ልጻፍ። ጌታቸው ሽፈራው ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆን ለተቸገሩ የሚራራ፣ በተለይም ለእስረኞችና ለቤተሰቦቻቸው ትልቅ ሸክም የነበረው ትልቅ ሰው መሆኑን ነው በቀረበበት ክስ ከሳሾቹ ለአለም ሁሉ የነገሩለት። እኛ በፊት እናውቀዋለን። አሁን ግን ማንን እንዳሰሩ ሁሉም አወቋል። ጌታቸው የእስረኞች ጉዳይ በጣም ይከነክንው የነበረ ነው። የእስረኞች ወዳጅ ነው።
አሁንም እኛ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጋርነታችንን ለጌታቸውና ለሌሎች አሁንም በወህኒ እየተሰቃዩ ላሉ የበለጠ ማሳየት ይጠበቅብናል። በተለይም የእስረኞች ልጆች ፣ አረጋዊያን እናቶቻቸውና አባቶቻቸው ዳቦ ማጣት የለባቸውም።
ግርማ ካሳNegere-Ethiopia-edtor-Getachew-Assefa-300x200.jpg