Thursday, January 14, 2016

የአውሮፓ ህብረት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ስላለው ተቃውሞ ማብራሪያን እንዲሰጡ ጠየቀ።


የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በህብረቱ ዋና መቀመጫ ብራሰልስ ከተማ ተገኘተው በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ስላለው ተቃውሞ ማብራሪያን እንዲሰጡ ጠየቀ። ሆኖም የተዘጋጀላቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተሰርዟል። የቀረበላቸውን ጥያቄ ተከትሎ በብራሰልስ የሚገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ በጉዳዩ ዙሪያ ከህብረቱ አባል ሃገራት በርካታ ጥያቄዎች ይቀርብላቸዋል ተብሎ በመጠበቅ ላይ መሆኑን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ኣየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ስጋት እንደደረሰበት የገለጸው ህብረቱ፣ የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለው እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል። መቀመጫቸውን በአውሮፓ ያደረጉ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በበኩላቸው ህብረቱ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ መልዕክት እንዲያስተላልፍ ዘመቻ መክፈታቸውም ታውቋል። በሂውማን ራይትስ ዎች የአውሮፓ ህብረት ተወካይ የሆኑት ሎቲ ሌችት ህብረቱ ዝምታውን በመስበር የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን የሃይል እርምጃ ማውገዝ እንደሚገባው ገልጸዋል። የአውሮፓ ህብረም የልማት ድጋፍ በሚያደርግላት ኢትዮጵያ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ የጥይት ምላሽ ሳይሆን ነገሮችን በድርድር እንዲፈቱ ግፊቱን ማጠናከር ይኖርበታል ሲሉ ተወካዩ አልክለው አስታውቀዋል። በአውሮፓ ማብራሪያ ለመስጠት የሚገኙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኦሮሚያ ክልል ስላለው ተቃውሞ ከሚሰጡት ማብራሪያ በተጨማሪ በሃገሪቱ እየተባባሰ ስላለው የድርቅ አደጋም ዝርዝር መረጃን ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል። ይኸው በኦሮሚያ ክልል ዳግም ተቀስቅሶ የሚገኘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ትኩረት ስቦ የሚገኝ ሲሆን በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን አመልክተዋል። ለኢትዮጵያ መንግስት የልማት ድጋፍን የሚያደርጉ ሃገራትም በሃገሪቱ ያለው ተቃውሞና የሰዎች ሞት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን በመረዳት መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጥ ማድረጋቸውንም ለመረዳት ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአውሮፓ ህብረት ጥሪ በቤልጂየም ብራሰልስ የሚገኙ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሲሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰርዟል። ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰረዘበት ምክንያት የታወቀ ነገር የለም።

የበጌ ምድር ሰው በላሰታ በኩል አድርጎ በየከዜ የጀግኖቹን ባንዲራ ከፍ አድርጎ ወደ ወልቃይት ጉዞው ጀምሮአል


የወልቃይትን ህዝብ ማሰር ማንገላታት ሰራየ ብሎ ከያዘው ድፍን 25አመት ሞላው ጀግናው ቆራጡ የቀልቃይት ህዝብም ወያኔን እምብኝ አትንካኝ አልነካህም ነገአ ግን እኔ እኔ ነኝ፡ በማለት ሲታገል ሲሟገት እምቢ ሲሉትም አርበኛን በመቀላቀል በእሰክብርቶም በመሳሪያም ሲፋጠጥ ድፍን 25 አመት ሞላው። በእርግጥ ወልቃይት ጸገዴን ጸለምትን ወያኔ በጉልበት ትግረኛ ተናገሩ ትግሪ ሁኑ ማንነታቹሁን ትታቹህ የእኔን ማንነት ተቀበሉ እያለ የራሱን ልቅ የሆነ የወሰን ማሰፋቱን ሰራ ሲያያዘው እምብኝ ያሉት ወልቃይት ብቻ አደሉም። ነገሩ እንዲህ ነው በወልቃይት በደል ልቡ ያልደማ ያላዘነ አንድም አማራ አይገኝም ሁሉም አዝኗል ልቡ በግኗል ነገር ግን ሁሉንም በትግሰት ነው ሲከታተለው የቆየው፡ ይህን የወልቃይትን መሪት ዘረፋ ተከትሎ ወንድሞቻችን ሲሞቱ ሲገረፉ ምውሪታቸን ሲቆረሰ ዝምታው እሰከመቸ ነው በማለት በባለፈው ወር በበጌምድር በሚሰጥር ታላቅ ውይይት ተካሄደ ጀግናው የበጌምድር ሰውም ቆራጥ አባቶችን ወደ አርማጭሆ በመላክ በጉዳዩ ተወያዩ አንድነት ፈጠሩ ወድድሮ ማንነታችን እንመለሰ ተኝተን ነበር ቀሰቀሱ ከዚህ በኋላ ማንም አይተኛም ጠላታችንን ሳናጋድም ብለው መሃላ ተማማሉ፡ ፡ትግሉም ቀጠለ ወያኔ በሁመራ በኩል የወልቃይትን ኮሚቴ አገተ ተባለ መልእክቱ ቀጥታ ማሰጠንቀቂያ ቢጢ ተነገረው የአማራ ትግሰቱ ማለቁን ሲነግሩት ወያኔም ተልካሻ ምክንያት በማቅረብ ታጋቾቹን ለቀቀ፡ አሁን ወደ ሰላሙ መንገስ እየገቡ ነብውር ወልቃይትንም የማንነት ጥያቄ መሪታችን፡መልሰ ሰትገሉን ኑራቹኋል አንድኛቹሁን ጭርሱን እና ውረሱት ቦታውን አልያም ልቀቁልን ሲሉ በብዙ ምክንያት ዳርዳርታው በዛ። አሁን ይህ አልዋጥለት ያለው ቀድሞ የተደራጀው የበጌምድር ሰው እንደትላንቱ ጠላትን ሊያርበደብድ የወያኔን ባንዲራ እሸቀንጥሪ ጥሎ ጉዞ ወደ ወልቃይት አድርጓል አሁን ጥያቄው ወልቃይት ይመለሰ ሳይሆን
ሁለት ነገር ይወልዳል ምክንያቱም ጀግኖች ሙተው ጀግኖች ተነሰተዋል ሲገሉን እልፍ ሆን ሲያስጨንቁን በረታን። እሰከዛሪ በወልቃይት ህዝብ ላይ ያደረሰውን በደል ባደባባይ ይቅርታ ይጠይቅ መሪቱን አሰረክቦ አንድም ትግሪ ከቦታው ላይታይ ቢታይም እንኳን ትምህርት ቤቶች በሙሉ በሃገራቸው በልልላቸው ቋንቋ በአማረኛ እንዲቀጥሉ
ህወሃት እና ብአዴን አማራን አይወክሉም የሚሉትን ወልዶ ትግሉ ቀጥሏል፡
የበጌ ምድር ሰው በላሰታ በኩል አድርጎ በየከዜ የጀግኖቹን ባንዲራ ከፍ አድርጎ ወደ ወልቃይት ጀምሮአል ጉዞው ለነጻነት ነው ወልቃይት በአሳሸ ቀኝ ትርሳኝ
ወልቃይት አማራ ነው በጌ ምድር ጎሸ አበጃቹህ በዛውም የተከዜን ግድብ ነጻ አውጡልን ብለናል
ታጋይ ገብርየ የጋይንቱ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት
Gebrye Yegaynt Anbesa's photo.Gebrye Yegaynt Anbesa's photo.

Wednesday, January 13, 2016

ሰብር ዜና የወያኔ ሰራዊት እርስ በእርሱ ተታኮሱ ከፍተኛም ጉዳት ደረሰ ተባለ


የመላዉ ኢትዮጵያ ህዝቦች ጠላት የሆነዉ እራሱን የትግራይ ነጻ አዉጭ ብሎ የሚጠራዉ የግፈኞች ስብስብ የሆነዉ ጎጠኛዉ ወያኔ በተለያዩ ከተሞች በዉትድርና ላይ ተሰማርተው የነበሩ የኦሮሞና የአማራ እንዲሁም የተለያየ ብሔር ያላቸዉን አባላት እና አርባ ምንጭ ላይ ከአሜሪካ ሰራዊት ጋር የነበረዉን መጠነኛ ብርጌድ በትግራይ ክልል ራማ ላይ በአንድነት አሰባስቦ! በካድሬዎቹ አማካኝነት፡
በኦሮሚያ ክልል ላይ የተነሳዉ ንቅናቄ የሚመራዉ በሽብርተኛ ሐይሎች በተለይም በኦነግና ! በርበኞች ግንቦት 7 ! ነዉ።
ዋነኛ አላማዉም ኢትዮጵያን አጥፍቶ ስልጣን በእጁ ማስገባት ብቻ ነዉ! 
ስለዚህም ይህን እንቅስቃሴ በማያዳግም እርምጃ መምታት አላማችን ነዉ!!
በሚል ዲስኩር ወር የዘለቀ ንትርክ እንደነበረ ምንጮች ሲገልጹ።
ከተለያዩ ክፍሎች የተዉጣጣዉ ሰራዊት በበኩሉ እኛ ከዚሁ ህዝብ ነዉ የወጣነዉ!
ለምን ወደዚህ ተነጥለንስ እንድንመጣ ተደረግን@!
ለምንስ ህዝባችን ላይ የማያዳግም እርምጃ እንድንወስድ ታግባቡናላችሁ!
በማለታቸዉ አለመግባባት የተፈጠረ ሲሆን በትናንትናው እለት በአንድ የአማራ ብሔር ተወላጅ ከፍተኛ መኮንን ትእዛዝ መሰረት 98 የሚደርሱ ልዩ ስልጡን ሐይሎች ከዚሁ ስብስብ ከሰራዊቱ በመነጠል እና ከራማ በመነሳት የወያኔን ወታደራዊ ቀለበት ቦርደር ጥበቃ ደምስሰዉ 23 ያህሉን በመግደል እና 13 በማቁሰል አስቸጋሪና ከባድ ዳገታማ ተራራ ወደ ሆነዉ አዲ በቕዩ በመገስገስ ላይ ሳሉ በድጋሚ ከተከታተላቸዉ የወያኔ ሐይል ጋር ተፋልመዉ ከ70 በላዩ በአዲቛላ ወደ ጎረቤት ሐገር በሰላም አልፈዉ መግባታቸዉ ከስፍራዉ እየተነገረ ነዉ።
ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት ከወያኔ በኩል በአጠቃላይ 54 ቅጥረኞች መደመሰሳቸዉን ከስፍራዉ የደረሰን ምንጭ የወታደራዊ መረጃዉን ተነርተርሶ የገለጸ ሲሆን ድንበር ዘለል የእርስ በእርሱ ዉጊያ የፈጠረዉ ድባብ ዛሬም በራማ አካባቢ የሰፈረዉን ሰራዊት እንዳስደነበረዉ ለመረዳት ተችሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ጉድሽ ወያኔ


ጸረ ሙስና ኮሚሽን በአባይ ጸሀዬ ሙስና ላይ መረጃ ቢደርሰውም ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ።


አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ።
በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት ወ/ሮ ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል።
ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም የተሰጣቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ሲነግዱ ስለነበር ነው።
የኮሚሽኑ የጎልጉል ምንጭ እንዳመለከቱት አቶ አባይ ጸሀዬ መሬት ሲነግዱ እንደ ነበር የታወቀው በክፍለ ከተማው በተካሄደ ምርመራ ነው። በክፍለ ከተማው በጠራራ ጸሃይ የግለሰቦችን መሬት ሳይቀር እየቸበቸበ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ በደረሰው ተደጋጋሚ ጥቆማ መሰረት የሚመለከተው መምሪያ መነሻ ጥናት ያዘጋጅና ምርመራው እንዲጀምር ይታዘዛል።
በዚሁ መሰረት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ስራቸውን ይጀምራሉ። የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ምርመራ እንደጀመሩ መሬት በህገወጥ መንገድ ሲቸበቸብ እንደነበር ይረዱና ከመሬት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያሽጋሉ። የመሬት ልኬትም ሆነ ከመሬት ጋር የተያያዘ ስራ እንዳይሰራ ያግዳሉ። በተጨማሪም መሬት እየለኩ ሲሰጡ የነበሩ መሃንዲሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራው በጥብቅ እንዲካሄድ ይደረጋል።
ክፍለ ከተማው ክልሉን ወደ ገጠር ቀበሌዎች እያሰፋ መሬት ይከልላል። መሬታቸው የተወሰደባቸው ደካማዎችን ቦሌ ክፍለ ከተማ ካሳ ለመውሰድ ሲንከራተቱ ማየት የተለመደ ነው። አራት ዓመት፣ አምስት ዓመት ከዚያም በላይ ካሳ ሳያገኙ የሚመላለሱ ደካሞች አሁን ድረስ አሉ። ባለንብረት ለንብረቱ ካሳ የሚከፍለው አጥቶ ይንከራተታል፤ መሬት የመንግስት እንደሆነ ያወጀው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣኖቹ አማካይነት መሬት አየር በአየር ይቸበችባል። ይህ የአሰራሩ ግድፈት ሲሆን ለአብነት የተጠቆመው ጉዳይ አስከፊነትና የወንጀሉ ርህራሄ አልባነት እዚህ ላይ ጎልቶ ይታያል።
አሳዛኝ የተባለው የምርመራ ውጤት ታሪክ የሚጀምርው እዚህ ላይ ነው። መሃንዲሶች በሙሉ ታስረው ተመረመሩ። ምርመራው በሙሉ ወደ አንድ ሰው ቢያመላክትም ያንን ሰው ደፍሮ የሚናገር ጠፋ። ይህን ጊዜ “ለምን” የሚል ጥያቄ ተነሳ። የመሬት አስተዳደር ሃላፊውና የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ተደርጎ መወሰዱ፤ መሬት በህገወጥ ስለመቸብቸቡ በቂ መረጃና ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ፣ መሬታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለሌላ ሰው የተሰጠባቸው እንዳሉ ተረጋግጦ ሳለ ካርታ ላይ የሚፈርሙትና ለመሃንዲሶች ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት የመሬት አስተዳደር እንዲታሰሩና እንዲመረመሩ አለመደረጉ በጓሮ ኮሚሽኑ የሚታማበት ጉዳይ ሆነ። “ጥርስ የሌለው አንበሳና የመለስ አሽከር” የሚለው የኮሚሽኑ ስም በስፋት ተነሳ!!
“ለፀረሙስና ኮሚሽን ሌላ ጸረ ሙስና ኮሚሽን” በሚል የክፍለ ከተማው ሰራተኛ የሆኑ ደብዳቤ በመጻፍ ወቀሳ ሰንዝረው ምርመራው በወጉ እንዲከናወን ጥቆማና አስተያየታቸውን ላኩ። አንዳንድ ስማቸውንና ማንነታቸውን የደበቁ ሰዎች ጉዳዩን ለግል ሚዲያና ለመንግስት መገናኛዎች እንደሚያቀብሉ ዛቱ። ማንም ምን ቢል የሚሰማም የሚደነግጥም ጠፋ።
ምርመራ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ለአብነት የተቀመጠው ዛሬ ህንጻ በብድር ተገነብቶበት ከፍተኛ ኪራይ የሚሰበሰብበት ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው አዲሱ ጎዳና ዳር ላይ ያለ አንድ ቦታ ጉዳይ ሲጎተት ሚስጥሩን ገለጠው። የመረጃው ምንጭ እንዳስረዱት ምርመራውን የያዘው ባልደረባቸው እንደነገራቸው ምስጢሩ ሲገለጽ ማመን አቅቶት ነበር።
ለክፍለከተማው የመሬት አስተዳደር ሃላፊ ቅርብ ተጠሪ የሆነው መሃንዲስ ምርመራ ሲካሄድበት “እንግዲያውስ እውነቱ ይህ ነው” በማለት አብራራ። በግፍ የተወሰደው ከላይ የተገለጸው ቦታ የተሰጠው ለአቶ አባይ ጸሃዬ ዘመድ መሆኑን ይፋ አደረገ። መሬቱ የቀድሞው ባለቤቶች ለመሆኑ የሚገልጽ በቂ ማስረጃ እንዳለው ቢታወቅም አለቃው አዲስ የባለቤትነት ማስረጃ ቀደም ሲል እንደነበር ተደርጎ እንዲያዘጋጅ ባዘዘው መሰረት የሰው ንብረት አሳልፎ መስጠቱን አስታወቀ። ይህን ጊዜ ምርመራው ባስቸኳይ ወደ ሌላ መርማሪ እንዲዛወር ተደረገ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ መሠረት የአቶ አባይ ጸሃዬ የቅርብ የስጋ ዘመድ ሲሆኑ፣ በእርሳቸው ትዕዛዝና አጽዳቂነት በክፍለ ከተማው በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ለዘመድ አዝማድ በሽርክና፣ ለባለ ገንዘብ በሽያጭ እንዲዘዋወሩ መደረጉ በምርመራ እንደታወቀ አስቸኳይ መመሪያ ተላለፈ።
መመሪያው እስረኛው መሃንዲስ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ፣ ምርመራውም እንዲቋረጥ የሚል ነበር። ከፍተኛ የሙስና ወንጀልና የስነምግበር ጉድለት መከሰቱን፣ በግፍ ንብረታቸውን ተቀምተው ባዶ እጃቸውን የቀሩ እንዳሉና፣ በማስፋፊያ ስም ቁልፍ ቦታዎች ከህግ ውጪ መተላለፋቸውን ይፋ ለማድረግ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሰራው ስራ ሙሉ በሙሉ ይፋ ሳይሆን ተዳፈነ። የተልከሰከሰ የስራ ሪፖርት እንዲቀርብ ተደርጎ ፋይሉ ተዘጋ። ከእስር የተፈታው መሃንዲስም ደብዛ ጠፋ። የአገር ደህንነት ከበርካታ ተመሳሳይ ወንጀሎች ጋር ጉዳዩን እንደያዘው የጎልጉል ዘጋቢ አረጋግጧል።
የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የአቶ አባይ ዘመድ እንኳንስ ሊታሰሩ በእድገት የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አማካሪ ሆነው አዲስ አበባ አስተዳደር ተመደቡ። ዋና ስራ አሰፈጻሚው የፌደራል ስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው። በአሁኑ ወቅት የከንቲባው አማካሪ የሆኑት የአባይ ጸሃዬ ዘመድ መሬትን አስመልክተው ኪራይ ሰብሳቢነት ስለመስፋፋቱ ክፍለ ከተሞችን ሰብስበው ይሰብካሉ። ስለ ሙስና አደገኛነት በየመድረኩ እንዲያስተምሩ ተደረገ። ድርጊቱ በርካቶችን አስቆጣ። በርካታ የወቀሳ ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ጎረፈለት። በአካል ቀርበው ምስክርነት የሰጡና ኮሚሽኑ ሊመሰርት አቅዶት ለነበረው ክስ ምስክር ለመሆን የተስማሙ ደነገጡ።
ጉዳዩ እንዲዳፈን ስለተደረገበት ምክንያት ሲያስረዱ “በየትኛውም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በደህንነት ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና መካከለኛ ደረጃ ሃላፊዎች በግልጽ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው በመረጃ ቢቀርብም ኮሚሽኑ እርምጃ የማይወስደው ሙስና አንዱ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ መንገድ በመሆኑ ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
“ኢህአዴግን እያገለገሉ ያሉ ባለስልጣኖች ህወሃትን በሚገባ መከራከር የማይችሉትና በታዛዥነት እያጎበደዱ ለመኖር የሚገደዱት የገቡበትን የሙስና ማጥ ስለሚያውቁት ከተቃወምን እንታሰራለን” በሚል ፍርሃቻ መሆኑን የኮሚሽኑ ባልደረባ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጭ ተናግረዋል። ባለሙያው አያይዘውም “በአገሪቱ የተንሰራፋው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ከላይ እስከታች ተበለሻሽቷል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
“ባለሥልጣናትን በሙስና ማበስበስ” የስርዓቱ ዋንኛ የማኮሰሻና የማዋረጃ ስልት እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጣቀስ “አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ ባቀረብነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል። ኢህአዴግ ለትምህርት ውጪ አገር የላከቸውና ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉት ተናጋሪ “ስርዓቱ በስብሷል” ባይ ናቸው።
“ባለኝ መረጃ መሰረት የኔ ስጋት እነዚህ ያለቀረጥ የሚነግዱ፣ ገንዘብ የሚያቀባብሉ፣ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተሰማሩ፣ ድርጅት ያላቸው፣ በቅጽበት ተመንጥቀው ባለሚሊዮኖች የሆኑ፣ የባንክ ብቸኛ ተጠቃሚዎች፣ ሸቃጮችና አወራራጆች ከትንሽ እስከ ትልቅ ስራውን የሚሰሩት ከባለስልጣናት ጋር ነው። ከመከላከያ አመራሮች ጋር ነው። ከደህንነትና ከዋናው የስልጣን እርከን ጋር በመመሳጠርም ነው” በማለት ቃለ ምልልስ አድራጊው በውል የሚያውቁትን ተናግረዋል። አያይዘውም “ስርዓት ሲበሰብስ ልዩ ምልክቱ ትናንሽ መንግስታት ማቆጥቆጣቸው ነው። በኢህአዴግ መበስበስ አቶ መለስን ጨምሮ በርካቶች ይስማማሉ። ኢህአዴግ መዓዛውን አልቀየረም የሚሉት በአገሪቱ ድፍን ቆዳ ላይ የራሳቸውን መንግስት የተከሉ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። እነሱ ክሬሙን እየላሱ ስለሆነ የመበስበስ አደጋ አይታያቸውም። ስለመበስበስ ለማሰብም ጊዜ የላቸውም። የበሰበሰው ነገር ሲናድ የሚበላው ግን አስቀድሞ እነሱን ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ በጣም ትልቅ ነው” በማለት ፍርሃቻቸውን ይገልጻሉ።
የፌዴራል መንግስት የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና በገለልተኛ ወገን አስጠንቶ ያገኘውና ይፋ የተደረገው ውጤት አስደንጋጭ መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ ጥናት መሰረት ፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች፣ አጠቃላይ የፍትህ ተቋማትና ራሱ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀዳሚ ሙስና የተንሰራፋባቸው ተቋማት መሆናቸውን ማረጋገጡ፣ ተቋማቱም በጥናቱ ቅር መሰኘታቸውን በመግለጻቸው በዝርዝር ይቀርባል የተባለው ጥናት እስካሁን ይፋ ሊሆን አለመቻሉም ታውቋል፡፡
የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ አቶ መለስ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለእርቸው ስለሆነ አዲስ በሚያቋቁሙት ካቢኔ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን የነቀዙ ባለስልጣናት ለመለየት ፋይላቸውን ከኮሚሽኑ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
(በጎልጉል ሪፖርተር)

በኦሮሚያ እና በሰሜን ጎንደር የተከሰተው የተቃውሞ እየተጋጋለ መሄድ እንጂ የመቀዛቀዝ ባህሪ አላሳየ


ሰሞኑን በኦሮሚያ እና በሰሜን ጎንደር የተከሰተው የተቃውሞ ንቅናቄ ሀገሪቱን ውጥረት ውስጥ ከትቷታል፡፡ አመጹ እየተጋጋለ መሄድ እንጂ የመቀዛቀዝ ባህሪ አላሳይ ብሏል፡፡ አሁንም በልዩ ልዩ አካባቢዎች ቀጥሏል፡፡ በአራቱም አቅጣጫዎች ውጥረት ሰፍኗል፡፡ በህይወት ዘመኔ ይህንን ያህል ዘላቂ ሆኖ የቆየ አመጽ አይቼ አላውቅም፡፡ በዚህ አመጽ ለጠፋው ህይወትና ንብረት እናዝናለን፡፡ በየትኛውም ወገን ሆኖ በትርኢቱ ውስጥ የተሳተፈው የኛው ዜጋ በመሆኑ ነፍሱና አካሉ ታሳዝነናለች፡፡
ታዲያ አመጹ የተከተሰው በመንግሥት ሚዲያ እንደሚነገረው “ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ግንቦት ሰባቶችና ኦነጎች በወጠኑት ሴራ ነው” የሚለው ምክንያት መሰረት የለውም፡፡ እንደዚህ ማለት “ህዝቡ አያገናዝብም፤ በማንም ይታለላል” የማለትን ያህል ነው፡፡ በኤርትራ የመሸጉት ድርጅቶችም ሆኑ “ኪራይ ሰብሳቢ” የሚባሉት የማይታወቁ ሃይሎች በዚህ አመጽ ላይ የተለየ ሚና የላቸውም፡፡ ድርጅቶቹ አመጹን ደግፈው መግለጫ መስጠታቸው የአመጹ ቀስቃሽም ሆነ መሪ ሃይል የሚያስብላቸው አይደለም፡፡
አመጹ የተወለደው የህዝብ ብሶቶች እንደ ኩሬ ውሃ እየተጠራቀሙ ከግድባቸው አልፈው መፍሰስ በመጀመራቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዚህ የህዝብ ብሶቶች ተጨባጭና ወቅታዊ ምላሽ እየሰጠ ኩሬውን ማድረቅ ነበረበት፡፡ ነገር ግን ከህዝብ ከሚነሳው ቅሬታ ይልቅ ካድሬዎቹ በሚጽፉት አማላይ ሪፖርት ስለሚታለል ስለብሶቶቹ የሚያወሳውን ሁሉ እንደ ተቃዋሚ ያይ ነበር፡፡ ትክክለኛ ተቃዋሚዎችን ደግሞ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ የቋመጡ ተስፈኞችና ሁከት ፈጣሪዎች ብሎ ከመፈረጅ ውጪ እንደ ተቃዋሚ የማየት ችግር አለበት፡፡ ተቃዋሚዎች ከሚያነሱት የተቃውሞ ሃሳብ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አይገነዘብም፡፡ የነዚህ ሁሉ ግድፈቶች ድምር ነው እንግዲህ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት እያሰለሱ ሲፈነዱ የነበሩትን አመጾች ሲቀሰቅሱ የነበሩት፡፡
የኢፌዴሪ መንግሥት አሁን አመጹን (በርሱ አገላለጽ “ሁከቱ”ን) ተቆጣጥሬአለሁ እያለ ነው፡፡ ነገር ግን ከሁኔታው ትምህርት ቀስሞ ለህዝብ ጥያቄዎች ተጨባጭ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አሁንም ተመሳሳይ ስህተት ወደ መስራቱ ነው ያዘነበለው፡፡ ለምሳሌ በብዙ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል አካባቢዎች ሰዎች በገፍ እየታሰሩ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንትም ሁለት የኦፌኮ አመራር አባላት እና የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ታስረዋል (አንደኛው በቅርቡ የተለቀቁት አቶ በቀለ ገርባ ናቸው)፡፡ አንዳንድ ሰዎችም ከስራ ገበታቸው እየተወገዱ ስለመሆናቸውም እየተነገረ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራንም ከትምህርታቸውና ከስራቸው መባረራቸውና መታሰራቸው ተዘግቧል፡፡ ይህ ሁሉ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ሲደረግ ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ይህንን ፈርቶ ለተቃውሞ እና ለአመጽ ከመውጣት አልታቀበም፡፡ ብሶቱ ሲያንገሸገሽው ለተቃውሞ ይወጣል፡፡ መንግሥት ለወደፊቱ ተመሳሳይ አመጽ እንዳይከሰት ከፈለገ የህዝቡን የልብ ትርታ ነው ማዳመጥ ያለበት፡፡ ዘወትር የሚወቀስበትን ተቃውሞን በጸጥታ ሃይል የመቆጣጠር ስልትን ተከትሎ በውጥረት ላይ ውጥረት መጨመር አይገባውም፡፡
—-
መንግሥት ራሱን አንቅቶ ሀገሪቱን መምራት የሚሻ ከሆነ በሶስት ደረጃዎች የሚተገበሩ እርምጃዎችን መውሰድ ያለበት ይመስለኛል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ከሚፈጸሙት ተግባራት መካከል የመጀመሪያው በቅርቡ የተካሄደው ንቅናቄ “የህዝብ አመጽ” መሆኑን ማመን እና ይህንኑ በየደረጃው ላሉት አባላትና ደጋፊዎቹ የማሳመን ስራ ነው፡፡ በምዕራብ ኦሮሚያ ጫፍ ከምትገኘው መንዲ ጀምሮ እስከ ምስራቅ ሀረርጌዋ የኮምቦልቻ ከተማ የሚኖረው ህዝብ የተሳተፈበትን ተቃውሞ “የጥቂት ነውጠኞች” ተቃውሞ እያሉ ማጥላላት አይቻልም፡፡
ንቅናቄው የኢህአዴግ መሪዎች በአድናቆት ከሚያወድሷቸው የራያ (ቀዳማይ ወያነ)፣ የጎጃም እና የባሌ ገበሬዎች አመጽ ጋር እንጂ አይተናነስም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚለው ንቅናቄው የተለኮሰው “ሽብርተኞች፣ ኒዮ-ሊበራሎች፣ ጋኔሎች እና ጋንግስተሮች” ባደረጉት ቅስቀሳም አይደለም፡፡ ስለዚህ ተቃውሞው የህዝብ እንደሆነ ማመን ይገባል፡፡
ከመንግሥት የሚጠበቀው ሁለተኛው ተግባር ደግሞ ተቃውሞው የህገ-መንግሥት ይከበር ጥያቄ መሆኑን ማመንና ማሳመን ነው፡፡ ለምሳሌ በአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ጉዳይ ላይ የቀረበው ጥያቄ የህገ-መንግሥት ይከበር ጥያቄ ነው፡፡ ህገ-መንግሥቱ “የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ልዩ መብት አለው” በማለት ደንግጎ ሳለ ከዚህ ድንጋጌ ጋር በቀጥታ የሚጋጭ ማስተር ፕላን መንደፍ ምን ማለት ነው…? አዲስ አበባ ለኦሮሚያ መስጠት የሚገባውን ልዩ ጥቅም ሳይሰጥ ሃያ ዘጠኝ የኦሮሚያ ከተሞችንና ከሚሊዮን የበለጠ ደሃ ገበሬ የሚኖርበትን መሬት ደረጃ በደረጃ በአዲስ አበባ ውስጥ ለማካለል መሞከር በየትኛው የህገ-መንግሥቱ አንቀጽ ነው የሚፈቀደው? በዚያ ላይ ማስተር ፕላኑ ከሁለት ዓመታት በፊት ደም ያፋሰሰ መሆኑ እየታወቀ እና ለወደፊቱ ይቀራል ተብሎ ለህዝቡ ተነግሮ ሳለ ዘንድሮ ላይ ለተፈጻሚነቱ መንቀሳቀስ ጥቅሙ ለማን ነው….?. ህዝቡ ከህግ አግባብ አልወጣም፡፡ የየማስተር ፕላኑን ጥያቄ ጨምሮ ህዝቡ የተንቀሳቀሰላቸው ሌሎች ታላላቅ ጥያቄዎች ሁሉ ህገ-መንግሥቱን የማስከበር ጥያቄ እንደሆነ ማመንና ለተፈጻሚነታቸው መንቀሳቀስ ተገቢ ይመስለኛል፡፡
ሶስተኛው ታላቅ ተግባር ደግሞ በመንግሥት የሚሰነዘሩ ሃሳቦችንም ሆነ ፖሊሲዎችን የማይቀበለውን ዜጋና ድርጅት እንደ ሀገር ጠላት አድርጎ የሚፈርጀውን ኮሚኒስታዊ እሳቤ ማቆም ነው፡፡ በተግባር እንደሚታወቀው ኮሚኒስቶች እነርሱን የሚቃወመውን ሁሉ እንደጠላት ነበር የሚፈርጁት፡፡ ይህ ኮሚኒስታዊ አረዳድ በሀገራችን ውስጥ ምን አይነት ጥፋት እንዳስከተለ እናውቃለን፡፡ ለቀይ ሽብር መከሰት ዋነኛው ምክንያት የነበረው በ1966 ዓብዮት ማግስት ባበቡት ድርጅቶች መካከል የነበረው የአቋም ልዩነት ሳይሆን ድርጅቶቹ ከነርሱ የተለየ ርዕዮት ያለውን ዜጋና ቡድን በጅምላ እንደ ጠላት የሚያዩበት ኮሚኒስታዊ (ግራ-ዘመም) ዘይቤአቸው ነው፡፡ ኢህአዴግም የኮሚኒዝም አቀንቃኝ በነበረበት ዘመን ከርሱ የሚለዩትን ሁሉ በጠላትነት ይፈርጅ ነበር፡፡ ታዲያ ዛሬ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ተከታይ ነኝ በሚልበት ዘመን እንኳ ከዚያ የጥንት ልማዱ ሙሉ በሙሉ አልተላቀቀም፡፡ ይህ ልማድ ካልቀረ ደግሞ ለሀገር በትክክል የሚያስበውን ዜጋ ለይቶ ማወቅ አይቻልም፡፡ ለሀገር ተቆርቁሮ በመንግሥት ፖሊሲዎችና የልማት ፕሮግራሞች ላይ ትችት የሚሰነዝረው በሙሉ እንደ ጠላት ስለሚፈረጅ የርሱ ሃሳብ አይደመጥም፡፡ የሚገርመው ደግሞ መንግሥት ብዙ ከተጓዘ በኋላ ከነዚህ ተቆርቋሪ ዜጎች የተሰነዘሩትን ሃሳቦች አምኖ የሚቀበል መሆኑ ነው፡፡ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡
በ1994/95 ሀገራችን ልክ እንደ አሁኑ በከፍተኛ ድርቅ ተመትታ ነበር፡፡ በዚያ ዘመን የገበሬውን ህይወት ለመለወጥ በሚል መንግሥት በተግባር ላይ ካዋላቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ “ውሃ ማቆር” የሚባለው ነው፡፡ ሃሳቡ በአጭሩ “ገበሬው በክረምትና በበልግ ወራት የሚዘንበውን ዝናብ በጉድጓድ አጠራቅሞ ዝናብ በጠፋበት ወቅት ይጠቀምበት” የሚል ነው፡፡ ይሁንና የተለያዩ የውሃ ኤክስፐርቶች ይህ አሰራር ሀገር አጥፊ መሆኑን ማስረጃ እየጠቀሱ ሞገቱ፡፡ ለምሳሌ “በኩሬ የተጠራቀመው ውሃ ቀስ በቀስ ወደ መሬት እየሰረጎደ ስለሚገባ የገበሬው ልፋት ከንቱ ሆኖ ይቀራል፤ በተጨማሪም በጉድጓዱ ውስጥ ደለል ስለሚገባበት ገበሬው የሚፈልገውን ያህል ውሃ ማጠራቀም አይቻልም” ተብሎ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ውሃው ለወባ መራቢያ አመቺ በመሆኑ በገበሬው ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል” የሚል ስጋት ከውሃ እና ከጤና ኤክስፐርቶች ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዚህ ሃሳቦች ዋጋ በመስጠት ፈንታ “ጠላቶቻችን ልማታችንን ለማደናቀፍ የሰነዘሩት ሃሳብ ነው” እያለ ማጥላላትን ነው የመረጠው፡፡
ይሁንና በሂደት ሁሉም ችግሮች ቀስ በቀስ እየታዩ መከሰት ጀመሩ፡፡ ውሃው ወደ ኩሬ ውስጥ ከገባ በኋላ በኩሬው ውስጥ ከመቆየት ይልቅ ወደ መሬት ውስጥ እየሰረጎደ እንደሚገባ ታወቀ፡፡ መንግሥት ይህንን ለማስቀረት በሚል በኩሬው ውስጥ ፕላስቲክ ይነጠፍ ማለት ጀመረ፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ግን ታላቅ አደጋ ተከሰተ! በዚያ የውሃ ማቆር ዘመቻ ሳቢያ ሀገሪቱ በታሪክ ያላየችው የወባ በሽታ ተጠቂ ሆነች!! መንግሥቱ በድርቅና በወባ ተወጠረ፡፡ አንደኛውን ችግር በአስቸኳይ ማስወገድ ስለነበረበት እንደዚያ የተለፋበትና የፕሮፓጋንዳ ጥሩምባ የተነፋለት የውሃ ማቆር ዘመቻ በ1997 አጋማሽ ላይ ለማንም ሳይነገር ተሰረዘ፡፡ ከዚያ በኋላ ስለርሱ ያወራ የለም፡፡ በቃ “የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ” ሆኖ ቀረ!!!
የኢትዮጵያ መንግሥት ከያኔው ስህተቱ ተምሮ ከምሁራን የሚሰነዘሩ ሃሳቦችን መስማት ነበረበት፡፡ ነገር ግን አሁንም ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ጆሮውን ለምሁራን ውትወታ ሲከፍት አይታይም፡፡ በዚህ አያያዝ መቀጠል የህዝብ ብሶትን ማጠራቀም ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ሃሳብ የሰነዘረን ግለሰብ እና ቡድን አክብሮ ለሃሳቡ ዋጋ መስጠትና መመርመር፣ እንደዚሁም ሃሳቦቹን ጠቅልሎ ከመዘነ በኋላ ለተግባራዊነታቸው መንቀሳቀስ ይገባል፡፡
—–
በሁለተኛው ደረጃ ላይ የሚከናወኑት ተግባራት ከህዝቡ ህይወት ጋር በቀጥታ ለሚገናኙ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡባቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገበሬው ብሶት የሚያሰማበትን በግዴታ ላይ የተመሰረተ ማዳበሪያ የመጠቀም አሰራር እና ከተሜው ለሚማረርባቸው የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት አፋጣኝ መፍትሄዎችን መሻትን ይጨምራል፡፡ ሁሉም ዜጋ የሚንገሸገሽባቸው የመልካም አስተዳደር እጦትና የሙስና አሰራርም የመንግሥትን ፈጣን እርምጃ ይሻሉ፡፡ ከመደበኛ ነጋዴዎች የተለየ ድጋፍ የሚደረግላቸው ኢንዶውመንት ፈንድስ የሚባሉት ድርጅቶች (ኤፈርት፣ ጥረት፣ አምባሰል፣ ዲንሾ፣ ቱምሳ፣) ትክክለኛውን ህጋዊ መስመር ይዘው እንዲሰሩ መደረግ አለባቸው፡፡
ብዙዎች “የጆሮ ጠቢ ስርዓት” እያሉ የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን ማስወገድና የወጣቶችና የሴቶች ሊግ አባላት ብቻ እየተመረጡ ተጠቃሚ የሚሆኑበት የጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ፈጠራ ፕሮጀክት ለብዙሃኑ ህዝብ ክፍት ማድረግ ይገባል ፡፡ በዚህ ረገድ የሚሰሙት ብሶቶች ከህዝቡ ህይወት ጋር በቀጥታ የተገናኙ በመሆናቸው ሌላ የህዝብ ቁጣ እንዲነሳ የማድረግ አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ብሶቶቹን በጊዜ ለመቅረፍ መንቀሳቀስ ይገባል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ የሚፈጸሙት ስትራቴጂያዊ እቅድ ወጥቶላቸው የሚተገበሩ ስራዎች ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል አንዱ አዲስ የከተሞች ልማት ስትራቴጂ መቅረጽ ነው፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት እስከ አሁን ድረስ የሚሰራበት የከተሞች ልማት ስትራቴጂ አዲስ አበባን ወደ ጎን ከመለጠጥ እና አስከፊውን የመሬት ቅርምት ዘመቻ ከማባባስ ውጪ በከተሞቻችን እድገት ላይ ያመጣው ተጨባጭ ለውጥ አነስተኛ ነው፡፡ በአንዳንድ ከተሞች የተወሰኑ ፎቆችንና መለስተኛ ፋብሪካዎችን ለማየት ቢቻልም በከተሞቻችን መካከል ተመጣጣኝ እድገት ማምጣት አልተቻለውም፡፡ የመንግሥቱ ትኩረት በአዲስ አበባ ላይ ብቻ በመሆኑ የክልል ከተሞች ከእንፉቅቅ ጉዞ ሊወጡ አልቻሉም፡፡ አዲስ አበባ እየተለጠጠች በማስተር ፕላን ስም የኦሮሚያ መሬቶችን ለመዋጥ ያሰፈሰፈችው የፌዴራል መንግሥቱ ለከተማዋ የሰጠው ገደብ የለሽ አትኩሮት በርካታ ፍላጎቶችን ስለቀሰቀሰ ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱ ወልጋዳ የከተሞች እድገት ስትራቴጂ ተወግዶ ሁሉም ከተሞቻችን ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አዲስ የከተማ ልማት ስትራቴጂ መቀረጽ ይኖርበታል፡፡
ሌላው ደግሞ ዲሞክራሲን በትክክል የማስፈን ስራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ቢታወጅም ሀገሪቱ በተጨባጭ የምትመራበት ስርዓት ስያሜ በየትኛውም መዝገበ-ቃላት ተፈልጎ የሚገኝ አይመስለኝም፡፡ ህገ መንግሥቱ ከአንዳንድ አንቀጾቹ በስተቀር በምዕራቡ ዓለም ያሉትን ህገ-መንግሥቶች ይመስላል (አብዛኛው ክፍሉ ከፈረንሳይ ህገ-መንግሥት የተገለበጠ ነው ይባላል)፡፡ በመሆኑም “ተራማጅ” ሊባል የሚችል ጤናማ ህገ-መንግሥት ነው፡፡ በአንዳንድ አንቀጾቹ ላይ (አንቀጽ 39፤ የመሬት አዋጅ ወዘተ…) የሚሰነዘሩት ጥያቄዎች ሀገሪቷ ወደ እውነተኛ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ኑሮ እድገት ውስጥ በምትገባበት ጊዜ በሚፈጠረው ብሄራዊ መግባባት ሊመለሱ ይችላሉ፡፡ ችግሩ ግን ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነቱን ተራማጅ ህገ-መንግሥት አጽድቆ ለርሱ ተገቢውን አትኩሮት የማይሰጥ መሆኑ ነው፡፡ ድርጅቱ ከህገ-መንግሥቱ ይልቅ በፓርቲ ደረጃ ለሚመራባቸውና ለሚያምንባቸው መርሖዎች ከፍተኛ ስፍራ ይሰጣል፡፡ እነዚህ መርሖዎች በአብዛኛው ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የተገለበጡ ነው የሚመስሉት፡፡ እነዚህ የፓርቲው መርሖዎችና ህገ-መንግሥቱ ሰማይና መሬት ናቸው፡፡ ሁለቱ ባልተጣጣሙበት ሁኔታ ትክክለኛ ዲሞክራሲን ማስፈን አይቻልም፡፡ ስለዚህ ፓርቲው መርሖዎቹን እንደገና በህገ-መንግሥቱ አቅጣጫ አስተካክሎ ራሱን ለፉክክር ማዘጋጀትና ሀገሪቱ ከጭምብል ዲሞክራሲ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የምትሸጋገርበትን ስርዓት ለመገንባት ሌት ከቀን መጣር አለበት፡፡
——
ከላይ በግሌ የሰነዘርኳቸው የመፍትሔ ሃሳቦች ሙሉእ አይደሉም፡፡ የህዝብን ብሶት ለማሻርና እምባውን ለማበስ የሚሰሩት ስራዎች በጣም በርካታ ናቸው፡፡ እኔ እነኝህን የመፍትሄ ሃሳቦች የጠቀስኳቸው ችግሮችን ዘርዝሬ መፍትሔዎችን ካልጠቆምኩ “ችግር ዘምዛሚ” የሚል ስም እንዳይሰጠኝ በመፍራቴ ብቻ ነው፡፡ ይሁንና መንግሥት መፍትሔ ሰጪ መሆንን የሚሻ ከሆነ እኔ የጻፍኩትን ባይሆን እንኳ ጉዳዩን ይበልጥ መዘርዘር ከሚችሉ ምሁራንና ተቋማት የሚሰነዘሩትን የምክር ሃሳቦች ይስማ እላለሁ፡፡ በልዩ ልዩ ከተሞች አመጹን ለማስቆም በሚል በጸጥታ ሃይሎች የሚካሄደው ግድያ፣ እስራትና ከስራ መፈናቀል በውጥረት ላይ ውጥረትን እየደራረበ ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ከመውሰድ ውጪ ወደ መፍትሔ አያመሩንም፡፡ ስለዚህ እነርሱን በአስቸኳይ ማቆምና ለህዝብ ጥያቄዎች መፍትሔ የመሻት ስራዎች ላይ መረባረብ ይገባል፡፡ “ህዝቡ መቶ ፐርሰንት መርጦኛል” የሚለው የኢትዮጵያ መንግሥት በእውነትም ለህዝብ ጥቅም የቆመ ህዝባዊ መንግሥት ከሆነ ጆሮውን ከፍቶ ህዝቡን ማዳመጥ አለበት፡፡
—–
አፈንዲ ሙተቂ

በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሁለት ወራት ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች የዘር ፍጅት በመቀስቀስ የተቃውሞውን አቅጣጫ ለመቀየር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ታማኝ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።
የዘር ፍጅት እቅዱ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች በተለይም በአማሮች ላይ የተነጣጠረና የተቀነባበረ ጥቃት በመሰንዘር፣ የሌላ አካባቢ ተወላጆች በስጋት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ በማድረግ ሁኔታውን ወደ እርስ-በእርስ ግጭት በመውሰድ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚሰራጩት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) በኢትዮጵያ ስርጭታቸው መታወኩ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች የታቀደውን ጥፋት በቀላሉ ለማስፈጸም ይቻላቸዋል የሚል ግንዛቤ መያዙንም ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያብራራል።
በመንግስት የደህንነት ሃይሎች የተቀነባበረው ጥቃት፣ በህዝቦች መካከል ግጭት ከመጋበዝ ባሻገር፣ በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የተቀነባበሩ የቦንብ ፍንዳታዎች ጭምር ለማከናወን መታቀዱንና የቀደሙ ዕርምጃዎች የዚህ ውጤት መሆናቸው ተመልክቷል።
ድርጊቱን ለማስፈጸም የተመለመሉ የኦህዴድና የብአዴን ሰዎች ጭምር መዘጋጀታቸውንም ለመረዳት ተችሏል።
ለኢሳት መረጃውን ያደረሱት ወገኖች ህዝብን ለፍጅት ለመዳረግ በመንግስት የደህንነት ተቋም እየታቀደና እየተወሰደ ያለውን እርምጃ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ በትኩረት እንዲከታተሉና መረጃውን በማድረስ እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል።

Tuesday, January 12, 2016

በጅማ ዩኒቨርስቲ የእጅ ቦንብ ተወርውሮ 35 ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል


በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትናንት ምሽት በግቢያቸው ውስጥ ተቃውሞ በማሰማት ላይ እያሉ በተወረወረባቸው የእጅ ቦንብ 35 ተማሪዎች ከፍተኛና ቀለል ያለ ጉዳት በማስተናገዳቸው ወደ ከተማይቱ ሆስፒታል ተወስደዋል ።ሶስት ተማሪዎች ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸው በመሆኑም ወደ አዲስ አበባ መላካቸውን በጅማ ሆስፒታል እሰራለሁ ያለ አንድ ባለሞያ ባደረሰኝ መልእክት ገልጿል ።
በፍንዳታው የተጎዱ ተማሪዎች አብዛኛዎቹ የተለያዩ የአካል ክፍሎቻቸውን ማጣታቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ ።