Thursday, July 14, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 ለጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ


ee992-asee
አርበኞች ግንቦት 7 መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በምስልና ድምፅ ከኤርትራ ረቡዕ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት የአማራም ህዝብ ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።
የወልቃይት ህዝብ ማንነቱን በተመለከተ በህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያቀረበው ጥያቄ በህወሃት በኩል የሃይል ምላሽ መሰጠቱ የቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደግጭት ማምራቱን በጥሪያቸው ያስታወሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በጎንደር የታየው ህዝባዊ ዕምቢተኝነት በስርዓቱ ሰለባ ለሆኑትና ለውጥ ለሚሹ ሁሉ መነቃቃትን የፈጠረ እንደሆነ አመልክተዋል።
“ከተባበርን አንጸናለን፣ ከተከፋፈልን እንወድቃለን” በማለት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የአጋርነት ጥሪ ያቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ “ዛሬ በጎንደር ከተማ እና አካባቢዋ እየተዋደቁ ካሉ ወገኖቻችን ጎን ካልቆም በህወሃት የሚደርስብን አፈና ማለቂያ አይኖረውም በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለመከላከያና ለፌዴራል ፖሊስ አባላት ለብዓዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴን እንዲሁም ለህወሃት አባላት ጭምር በገዳዮችና ዘራፊዎች ላይ ተነሱ በማለት ጥሪ አቅርበዋል።
አገዛዙን በመቃወም የሚደረጉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች የትግራይን ህዝብ ለማጥቃት የተካሄደ በማስመሰል የሚቀርበውን አሳፋሪ ሴራ እንዲያጋልጥም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኦሮሚያና የአማራ ክልል የፖሊስና የሚሊሺያ አባላት ለነበራችውና አሁንም ላላችሁ በጎ ሚና ህዝቡ አክብሮቱን ይሰጣችኋል በማለት ከኤርትራ በምስልና በድምፅ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ውጭ በወንጀል ተባባሪ የሆኑና በግድያ ተሳታፊ የሆኑ የጸጥታ ሃይሎች በማናቸውም መንገድ ከተጠያቂነት ነጻ እንደማይሆኑ አሳስበዋል።
“በአንድነት ከተነሳት የነጻነት ቀን ቀርባለች” በማለት ወደንግግራቸው ማጠቃለያ የመሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች እንደሚገኙ አመልክተው፣ “ስትሞቱ እየሞትን ስትቆስሉ እየቆሰልን፣ ሊገድሏችሁ ያኮበኮቡትን እየታገልን እስከመጨረሻው የድል ምዕራፍ ከውስጣቸው እንደማንለይ ዕወቁት” ሲሉ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

ሰበር ዜና. . . . . የህወሃት ብሐራዊ መረጃ አጣብቂኝ ዉስጥ ገብቶአል።


በጎንደር ከተማ የሚገኙ የእስራኤል ከፍተኛ ባልስልጣኖችን ለማዉጣት ከእስራኤል ሔለኒክ አየር ሐይል የልዩ ሐይል ( SPECIAL FORCE ) አባላትን የያዘ የጦር ጀቶችና አፓቼ ሄሊኮፍተሮች ( Apache Helicopters ) ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የተጠየቀዉ የወያኔዉ ብሔራዊ ደህንነት አመጽ በተቀሰቀሰባቸዉ የጎንደር አካባቢዎች ሰላም ሰፍሮዋል የሚል የተዛባ ማስተባበያ እየሰጠ ይገኛል።
ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ መንስኤ የሆነዉ የብሔራዊ መረጃ ሌሎች የታጠቁ ተጨማሪ የደህንነት አፋኝ ሐይሎች ህዝቡን አመሳስሎ ሊያስገባ መሆኑን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆንበተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ የደህንነት ከፍተኛ አመራሮች አስተዳደሮችና ቁልፍ የስለላ ግለሰቦች ጎንደርን ለቀዉ እንዲወጡ ትእዛዝ ሲያስተላልፍ ህዝባቸዉ ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ለክክሉ የመከላከልና ዘመቻ ስምሪት ክፍል ትእዛዝ ቢተላለፍም የመከላከያ የጦር አባላትና፣ የአካባቢ ሚሊሻዎች እንዲሁም የክልሉ የፖሊስ አባላት አንዳች ጥይት እንደማይተኩሱና ህዝቡ ላይ ለሚወሰድ ማንኛዉንም አይነት እርምጃ የመከላከል ግዴታቸዉን እንደሚወጡ ለመረጃ ድርጅቱ በድፍረት ገልጸዋል።
በተያያዘ ሁኔታ አጋጣሚዉ የሰመረላቸዉ የዉስጥ አርበኞች በተጠናከረ መልኩ ህዝብን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የነበሩ አፋኝ ግለሰቦችን እያሳደዱ በማደን ላይ መሆናቸዉን የአርበኞቹ ምንጭ ጠቅሰዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
( ጉድሽ ወያኔ )
,
Aseged Tamene photo

Saturday, July 9, 2016

ሰበር ዜና.. በደቡብ አፍርካ ጆሐንስበርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን መድሐኒያለም ቤ/ክርስቲያን ዉስጥ የተነሳዉ አለመግባባት ወደ መጠፋፋት በመገስገስ ላይ ነዉ።


ደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መድሐኒያለም ቤ/ክርስቲያን ዉስጥ የተነሳዉ አለመግባባት ተባብሶ ወዳልተፈለገ የእርስ በእርስ ጸብ ተቀይሯ! መሐበር ምእመናን ይተባለዉ አካል ከከፍተኛ የፖሊስ አባላት ጋር በመመሳጠር ቤ/ክርስቲያኗን ከዘጋት ሰንበትበት ብሏል። ይህን ተንተርሶ በትናንትናዉ እለት ሐምሌ 08/2016 የሰበካ ጉባኤ አባላት የተባለዉ አካል በበኩሉ ቤ/ክርስቲያኗን በሔይል መነጠቁንና መወረሱን ጠቅሶ ለደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤ/ት በመክሰሱ. ፍርድ በቱ ቤ/ክርስቲያኗ የምትገኝበትን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ወይም ሂልብሮ ፖሊስ ስቴሽን ኮማንደር እና አንድ ከፍተኛ ሚኒስቴር እንዲሁም አባጾመ ልሳስንና አጋሮቻቸዉ በህግ ፊት እንዲቀርብቡ እና ቤ/ክርስቲያኗም ባስቸኳይ እንድትከፈት ወስኗል። ይህንኑ የፍርድ ቤት ዉሳኔ የማስፈጸም ስራን ለማከናወን ሲባል በተደረገ አለምግባባት በተንነሳ ጸብ አቶ ይልማ ሸዋ የተባለ ግለሰብ እና ሌሎችም አግባብ ያልሆነ ጥቃት መፈጸሙን ምንጮቻችን አሳዉቀዋል። በደቡብ አፍርካ የመድሐኒያለም ቤ/ክርስቲያን ላይ ዉስጥ ለዉስጥ በተጠና መልኩ እያደራጀና እያሰማራ ጸቡን በማካረር በኩል ትልቁን ሚና በመጫወት ላይ የሚገኘዉ የህወሃት ወያኔያዊ ተልእኮ ለመሆኑ የጠቆሙን ምንጮች በምስል የተደገፈ መረጃ አድርሰዉናል። በመሆኑም ከታች በፎቶ ላይ እንደምትመልከቱት ከደቡብ አፍሪካ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝና መረጃዎችን በማቀበል ከሲኖዶስ ጋር በተመሳጠረ ሁናቴ ከህዝብ የተሰበሰበን ሐብት ለምዝረፍ እንዲሁም ኢሃዲጋዊ አገልግሎትን ለማቀናበር የሚሰሩትን ግለሰቦች በተለይም ለዚህ አለምግባባት ዋነኛ ተዋናዮችን እንጠቁማለን። ከታች በፎቶ ላይ እንደምትመለከቱት ከሲኖዶሱ አዉራ አቡነ ማትያስ ጎን በስተቀኝ በኩል የተቀመጠዉ ግለሰብ ፍሰሐ ( ፊሽ ) የሚባል ሲሆን ወንድሙ የአዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት የጸጥታ ክፍል ሐላፊ ነዉ ፍሰሐ በደቡብ አፍሪካ ለረጅም ግዜ ነዋሪ የነበረ ሲሆን ለህወሃት የስለላ መረብ ቀኝ እጅ በመሆን ከደቡብ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ወገኖቻችንን በማስጠለፍ ለእስር እና ለእንግልት እንዲዳረጉ በማድረግ ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ፍሰሐ ከአዲስ አበባ ሆኖ ወደ ደቡብ አፍሪካ መመደብ የሚገባቸዉን ጳጳሳትና ቀሳዉስት በመምረጥና በመጠቆም ከሲኖዶሱ ጋር የሚሰራ ሲሆን ፍሰሐ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ቤ/ክርስቲያን እዚህ ደረጃ መድረስ የመጀመሪያ ተጠያቂ ነዉ። ከፍሰሐ አጠገብ የተቀመጠዉ ዘሚካኤል የተባለዉ ግለሰብ በተመሳሳዩ በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ሲሆን የቤ/ክርስቲያኗን መዘጋት በዉስጥ ተንቀሳቅሶ በመምራት ትልቅ ሚና ከመጫወት ባለፈ መልኩ በቤ/ክርስቲያንዋ ምክንያት በተፈጠረዉ አለምግባባት አግባብ ያልሆኑ የወንጀል ክሶች በተለያዩ ግለሰቦች ላይ እንዲከፈት በማድረግ ሰዎች እንዲታሰሩ ከፍተኛ ሚን ተጫዉቷል እየተጫወተም ይገኛል። ከህወሃቱ ሲኖዶስ አዉራ አቡነ ማትያስ አጠገብ ስተግራ በኩል የተቀመጠዉ ግለሰብ ደግሞ ከፍያለዉ የተባለዉ ግለሰብ የትዳር ጓዱ አበራሽ የተባለች የህወሃት የቀድሞ ወታደር እና የአሁኑ የብሐራዊ መረጃ የድህንነት ስርጭት አባል ናት ከፍያለዉ በሲቪክ መሐበራትና በተለያዩ ወያኔያዊ ኡደቶች ላይ በመንቀሳቀስ ህወሃትን ያገለግላል። ዉድ ወገኖቻችን ይህ በወያኔ የበላይ አቀናባሪነት መሐበረ ምእመናን በሚል እና ሰበካ ጉባኤ በተባለ የሐይል ስብሰብ የተከፋፈለዉ ቡድን በእንዲህ ያለ እርስ በእርስ የመጠፋፋት ሁኔታ ላይ በሚገኝበት ወቅት ላይ የማስታረቅ ስራ መስራት የነበረበት የአዲስ አበባዉ ሲኖዶስ የባሰዉን በደቡብ አፍሪካ በህዝብ ዘንድ ቂም የተቋጠረባቸዉን አቡነ ያእቆብን ለቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪነት ለመላክ ሽር ጉድ በማለት ላይ ይገኛል በመሆኑም ከሁለቱም ወገን ገለልተኛ የሆኑ አንድ አባት ነገ ይገባሉ የተባሉት አቡነ ያእቆብ ወደ ጆሐንስበርግ ከመንቀሳቀሳቸዉ ቀደም ብለዉ ሁለቴ ኢንዲያስቡ አሳስባለዉ ሲሉ ምክር ቢጤ ሰጥተዋል። ዉድ ኢትዮጵያዊያን ከታች የተቀመጠዉን ፎቶ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ አቡኑ ቢሮ ሲገቡ ክርስቶስ ኢየሱስ የተሰቀለበትን እርሱም መከራ የተቀበልከበትን መስቀል በምንጣፉ ላይ እንደሚረግጡ ያስታዉሱ!! ወያኔን ከሐገራችንና ከእመነት ቤታችን ይንቀልልን!! ጉድሽ ወያኔ

የአሜሪካ ሴናተሮች አገራቸው ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ እንድትመረምር ጠየቁ


የኢትዮጵያ መንግስት አክቲቪስቱን አንዳርጋቸው ጽጌን በማፈን በህገ ወጥ መንገድ በማሰሩና በአገሩ ውስጥ በሚፈጽማቸው ጥሰቶች የተነሳ የአሜሪካ ሴናተሮች ኮሚቴ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ እንድትመረምር ለማድረግ ጥሪ ለማቅረብ የሚያስችለውን ረቂቅ ለማጽደቅ የመነሻ ይሁንታን ከሰኔቱ ማግኘቱ ተሰምቷል፡፡ 
ረቂቁ ‹‹ድጋፍ ለሰብዓዊ መብት መከበርና መልካም አስተዳደርን በኢትዮጵያ ማበረታታት››የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በሰኔቱ የህግ አውጪዎች ስብሰባ ወቅት የመጀመሪያውን ደረጃ ለማለፍ የሚያስችለውን ማረጋገጫ በውጪ ግኑኝነት ኮሚቴ ውስጥ ከሚገኙ ሴናተሮች ማግኘቱ ተጠቅሷል፡፡
በረቂቁ የሰፈረው ጽሁፍ የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ ተቃዋሚዎቹን፣አክቲቪስቶችንና ጋዜጠኞችን እንዲለቅና መንግስትን የሚተቹ ሰዎችን ለማሰር እየተጠቀመበት የሚገኝን ህግ እንዲያርምና የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ለኢትዮጵያ በመሰጠት ላይ የሚገኘውን የደህንነት ድጋፍ እንዲገመግሙ ይጠይቃል ፡፡
ረቂቁ የቀረበው ከአሜሪካ ጋር ግኑኝነት ያለውና በእስር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚና አክቲቪስት የአንዳርጋቸው ጽጌ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በተነገረበት ወቅት ነው፡፡ባለቤቱና ልጆቹ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው እንግሊዛዊው አንዳርጋቸው በወርሃ ሰኔ 2006 ከየመን አየር መንገድ ታፍኖ ወደኢትዮጵያ ከተወሰደ በኋላ በ2002 በሌለበት የተላለፈበት የሞት ፍርድ ተግባራዊ ሊደረግበት እንደሚችል ተሰግቷል፡፡አንዳርጋቸው ላይ የሞት ፍርድ የተላለፈበትን ሂደት የተከታተሉት የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በጊዜው ውሳኔው ፖለቲካዊ ብቀላና ችሎቱም መሰረታዊ የሚባሉ የህግ ሂደቶችን ያልተከተለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአንዳርጋቸው ባለቤት ይኖሩባት የነበረችው ሜሪላንድ ከተማ ሴናተር የሆኑት ቤን ካርዲን ረቂቁን በዋናነት ለሰኔቱ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡ሴናተሩ ቤን ካርዲን የአንዳርጋቸው ጉዳይ በኢትዮጵያ የመንግስት ተቃዋሚዎችን እንደሚወክል ይናገራሉ፡፡
በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ዝነኛ የሆኑት አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ በ1998 ለአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት ንግግር አድርገው ነበር፡፡ለሴኔቱ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ‹‹በኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመ የሚገኘው የአፈና መጠን በአገሪቱ የጭለማ ወቅት ተደርጎ ይቆጠር በነበረው በወታደራዊው አገዛዝ ይፈጸም ከነበረው ልቋል››በማለት ተናግረው ነበር፡፡
አንዳርጋቸው ከታፈኑበት ቅጽበት ጀምሮ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቤተሰቦቻቸው ጨምሮ በማንም እንዳይጎበኙ አድርገዋል፡፡በምርመራ ላይ እንደነበሩ የሚያሳይ ቪዲዮም በብሄራዊው ቴሌቭዥን አማካኝነት ለእይታ አቅርበዋል፡፡ቶርቸር በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች የተለመደ በመሆኑም አንዳርጋቸውም ቶርቸር ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ ስጋቶች አሉ፡፡
ባለፈው ዓመት የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ታሪካዊ ጉብኝት በማድረግ ወደኢትዮጵያ ባመሩበት ወቅት የአገሪቱን ገዢ ፓርቲ የተቃዋሚዎቹን ድምጾች በማፈኑና ህጋዊነትን ባለመከተሉ ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር፡፡የአንዳርጋቸው ጽጌን ቤተሰቦች በመደገፍ ላይ የሚገኘው አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሪፕራይቭ ለኦባማ አስተዳደር በጻፈው ደብዳቤ ኦባማ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን ሲገናኙ የአንዳርጋቸውን ጉዳይ እንዲያነሱባቸው ተማጽንኦ የነበረ ቢሆንም ምላሽ አለማግኘቱ ታውቋል፡፡
በሪፕራይቭ የሞት ቅጣትን ከመላው አለም ለማስቀረት ንቅናቄ በማድረግ ላይ የሚገኘውን ቡድን በዳይሬክተርነት የሚመሩት ማያ ፎ ‹‹ላለፉት አመታት የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን፣ጦማርያንንና ተቃዋሚ አክቲቪስቶችን ለማፈን ያለተቃውሞ የሄደበትን የአፈና መንገድ ሴናተሮቹ ማውገዛቸው ትክክል ነው፡፡በመንግስት ጥቃት ከደረሰባቸው አንዱ አንዳርጋቸው ነው፡፡ አንዳርጋቸው በዛ ያሉ ጉዳቶች ደርሰውበታል፡፡ከአፈና ጀምሮ ቶርቸር ተፈጽሞበታል፡፡በሌለበት የሞት ፍርድ የተላለፈበትን አንዳርጋቸውን አሜሪካዊያኑ ቤተሰቦቹ አጠገባቸው ሊያገኙት በእጅጉ ይናፍቃሉ፡፡የኦባማ አስተዳደር በኢትዮጵያ የህግ የበላይነትንና ዴሞክራሲን ለማሻሻል ቆራጥ ከሆነም ዋይት ሐውስ ከሴኔቱ የሚቀርብለትን የማንቂያ ደወል በአስቸኳይ በማድመጥ እንደ አንዳርጋቸው ያሉ የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ መስራት ይኖርበታል››ብለዋል፡፡
የወሬው ምንጭ ሪፕራይቭ
 

Thursday, July 7, 2016

በአምቦ ዩኒቨርስቲ አንድ የጸጥታ አባል ሁለት የፌዴራል ፖሊሶችን ገደለ


በአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ዕርቀት ላይ በሚገኘው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ተመድቦ በማገልገል ላይ የነበረ አንድ የጸጥታ አባል ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ገድሎ ማምለጡን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ።
አዋሮ ተብሎ በሚጠራው የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሰኞ በጸጥታ ባልደርባው በተፈጸመው ጥቃት ሶስት ተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በጥይት ጉዳይ እንደደረሰባቸው ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የአምቦ ከተማ ነዋሪ ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል።
የአፋር ብሄር ተወላጅ መሆኑ የተነገረለት የጸጥታ ባልደርባ በሙስሊም የጾም ወቅት ከስራ ምደባ ጋር በተገናኘ ከሃላፊዎቹ ጋር በተደጋጋሚ አለመግባባት ውስጥ መቆየቱንና ድርጊቱ የዚሁ መነሻ እንደሆነ ከእማኞች ለመረዳት ተችሏል።
ስሙ ለጊዜው ያልተገለጸው የጸጥታ አባል ከሃላፊዎቹ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ምክንያት በማድረግ ሰኞ የዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ተኩስ መክፈቱንና ሁለት የጸጥታ ባልደርቦችን እንደገደለ ታውቋል።
ይሁንና ድርጊቱን የፈጸመው የጸጥታ ባልደባ እስከ ረቡዕ ድረስ አለመያዙን እማኞች አክለው አስረድተዋል።
ድርጊቱ የተፈጸመው የዩኒቨርስቲው የምረቃ ስነስርዓት ባካሄደ ማግስት በመሆኑ፣ አብዛኛው የዩኒቨርስቲው ተማሪ ከቅጥር ግቢው ወጥቶ እንደነበር እማኞች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል።
በተኩስ ዕርምጃው ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላት በጸጥታ ሃይሎች ለክህምና ከአምቦ ከተማ ውጭ መወሰዳቸውን እማኞች አክለው አስታውቀዋል።

ሁለት ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ የተደረገው ሙከራ የህዝብ ቁጣ ቀስቅሷል


ባለፈው ሳምንት በአዲስ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀጣና 01 መንደር 06 በተለምዶ አጠራር ቀርሳና ኮንቶማ በሚባለው አካባቢ የሚገኙ ሁለት ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ህዝቡ እየተቃወመ ነው።
ባለፈው ሳምንት ኡራኤል ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ሙከራ ሲደረግ ህዝቡ ባስነሳው ተቃውሞ ቤተክርስቲያኑ እስካሁን ሳይፈርስ ቆይቷል። ከሶስት ቀናት በሁዋላ ደግሞ የቤተክርስቲያኑ ቄስ በፌደራል ፖሊስ ተገድለዋል። አፍራሽ ግብረሃይሎች የጸበል ቦታውን ካፈረሱ በሁዋላ ፣ ሙሉውን ቤተከርስቲያን ለማፍረስ ህዝቡ ጽላት እንዲያወጣ ጠይቀዋል። ይሁን እንጅ ጽላቱን የሚያወጡ ቄሶችን ገድላችሁዋቸዋል በማለት ህዝቡ መልስ የሰጠ ሲሆን፣ ቤተክርስቲያኑም እስካሁን ከመፍረስ ድኗል። በተመሳሳይ ሁኔታም ኪዳነምረት ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ዛሬ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ካህናቱ ግን ጽላት አናነሳም እያሉ ናቸው።
ህዝቡም ተቃውሞውን በመግልጽ ላይ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ እናት ድርጊቱ የእግዚአብሄር ቁጣ ነው ይላሉ።
መስተዳድሩ በወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ከ30 ሺ በላይ ዜጎች ያለመጠለያ ቀርተዋል። ከ300 በላይ ወጣቶችም ተይዘው ታስረዋል። የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ታሪክ ፍቅሬን ጨምሮ ሁለት ፖሊሶችም ተገድለዋል።

የህወሃት ብሔራዊ መረጃ በመሐበራዊ የመገናኛ ዘርፎች ላይ የሚያደርገዉን አፈናና ክትትል በተመለከተ የጥቂት ወራቶችን ሪፖርት ለሚመለከተዉ

የህወሃት ብሔራዊ መረጃ በመሐበራዊ የመገናኛ ዘርፎች ላይ የሚያደርገዉን አፈናና ክትትል በተመለከተ የጥቂት ወራቶችን ሪፖርት ለሚመለከተዉ አካል አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት የብሔራዊ መረጃዉን መድብለ ሪፖርት አጠርና ጠቅለል ባለ መልኩ ለሚመለከታችሁ ሁሉ ለማድረስ እንሞክራለን…
ኢሳትን 24 ሰአት ከማሳደድ ይልቅ ቃናን 24 ሰአት ማንጎድጎድ ስኬታማ ዉጤት እያመጣ ነዉ። ያለዉ የብሔራዊ መረጃዉ በተያያዘ መልኩ የተለያዩ የመሐበራዊ የመገናኛ አዉታሮችን ማለትም እንደ ዘሐበሻ የመሳሰሉ አደገኛ የተባሉትን ድህረ ገጾች ለማዳከም እና ለማጥፋት ተጨማሪ የበጀት እቅዶችን ዘርግቷል።
የብሔራዊ መረጃ ወንበድዉ ክፍል የኢትዮጵያ ህዝብ በብዛት ትኩረቱን ወደ ቃና ቴሌቪዥን እያዘነበለ እንደሚገኝና ኢሳትን እና ተዛማጅ የመረጃ አዉታሮችን የማዳመጡ እና የመከታተሉ ሁናቴ እንዲባረድና እና እንድጠፋ የተደረገ ሲሆን ይህ እንቅስቃሴ ስኬታማ ዉጤት እያመጣ ነዉ ይላል::
ይህ ብሐራዊ መረጃ ቃናን የመሰለ አደገኛ ህዝባዊ ጠላት በሐገራችን ላይ ተክሏል። ከመረጃ ክፍሉ አስገራሚዉ ተዉኔተ ሪርት ዉስጥ ቃና በሐገራችን ላይ ሊያስከትል የሚችለዉ አሉታዊ ተጽእኖ በማላገጥ መልኩ ዳሶታል።
እንደ ሪፖርቱ ከሆንበ ለምሳሌ የሐሰት ቋት ስርጭት ክፍሉ ኢቢሲ ላይ ሊደርስ የሚችለዉ የዉድቀት አደጋ ሲሆን ይህዉም የማስታወቂያ እና የፕሮፓጋንዳ በተለይም ህወሃታዊ ድሰቶች ኪሳራ ላይ እንደሚወድቁ ሲብራራ አዉራ የማስታወቂያ ድርጅቶችም ፊታቸዉን ወደ ቃና እያዞሩ መሆኑ እንዲሁም የልማታዊ አርቲሶችን ቅሬታ በተመለከተ ጥቂት ተብሏል።
ነገር ግን የብሔራዊ መረጃዉ ኢቢሲን በተጭማሪ በጀት እና በድጎማ ማቆየትን እንደ መፍትሄ ሲያቀርበዉ ልማታዊ አርቲስቶቹን በተመለከተ ከቃና ጋር በመተባበር የትርጉም ድምጽ አገልሎት ላይ እንዲሳተፉ በሚል መልኩ ቀልዶባቸዉ ያልፋል የዚህ የብሔራዊ መረጃዉ እቅድ እንደሚያመልክተዉ ከሆነ በቅርቡ ከልማታዊ አር..ቲስቶቹ መካከል የሰራዊት ፍቅሬን እና የሙሏለምን ድምጽ በቃና ተከታታይ ድራማ ላይ እንደምናደምጠዉ ተስፋ አለን። የለቅሶ ዉጤት ነዉ!!!
ብሐራዊ መረጃዉ ተንኮለኛነቱን በማጉላት ረገድ ኢሳትንና መሰሎቹን በከፍተኛ ሁኔታ ለማዳከምና አዉራ ተወካዮችን በተለያየ መንገድ በማጥቃትና እና ከጨዋታዉ ለማውጣት . . . .ስም በማጥፋት፣ ቤተሰቦቻቸዉን በማነጋገርና በማሰር፣ እንዲሁም በድርድር፣ በማባበል፣ በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ኢኮኖሚያዉ ተጽኖ በመጣል የሚከወኑ የግፍ አፈጻጸሞች በዉስጡ ይገኙበታል።
የአፋኙ መደብ.. ብሔራዊ መረጃ በብዙ ሐገራት ተወዳጅ ያልሆነዉንና የስንፍና ቫይረስ ስርጭቱን ” የቃና ቴሌቭዥን “በኦሮምኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለህዝብ እንዲተላለፍ በማድረግ ኢሳት ላይ እየተተገበረ የሚገኘዉን የሚዲያ አፈና ዘዴ የነጃዋር መሐመድ የድካም ዉጤት በሆነዉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ላይ ለመፈጸም በጥብቅ እየሰራ ለመሆኑ ሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።
ዉድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ ይህ የወንጀለኛዉ የብሔራዊ መረጃ መዋቅር ከኢስት እስከ ፌስ ቡክ ድረስ የተዘረጋ የመጨረሻ መፍጨርጨር መሆኑን እንድትገነዘቡ እያሳሰብን አቀጣዩ በፌስ ቡክ ላይ የሚያካሐዱትን ተራ የአፈና እንቅስቃሴ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ድል ለኢቶጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )