Wednesday, May 11, 2016

በአርባ ምንጭ ያልታወቁ ሃይሎች የፖሊስ አባላትን ገደሉ


በአርባ ምንጭ ነጭ ሳር ፓርት አካባቢ ያልታወቁ ሃይሎች ከመንግስት ሃይሎች ጋር ባደረጉት ግጭት ቁጥራቸው ያልተገለጸ የፖሊስ አባላት ሲገደሉ፣ ከጣታቂዎች ወገን እንግዳ አበበ የተባለ ወጣት መገደሉን የአካባቢ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በርካታ የፌዴራል ፖሊሶች ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በከተማዋ የቤት ለቤት አሰሳ መቀጠሉም መረዳት ተችሏል።
ቅዳሜ ሚያዚያ 29 ፥ 2008 ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርት አካባቢ በፌዴራል ፖሊሶች ላይ ድንገተኛ ጥቃት የሰነዘሩት የታጠቁ ሃይሎች፣ የአካባቢውን የፌዴራል ፖሊስ አዛዥና ቁጥራቸው ያልታወቀ ሌሎች የፌዴራል ፖሊስ አባላትን መግደላቸውን የሚገልጹት የኢሳት ምንጮች ከጥቃቱ ቀደም ባሉት ቀናትም በከተማዋ አሰሳ ሲካሄድ መቆየቱን… አስታውሰዋል።
በተለይ ሚያዚያ 27 ፥ 2008 ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ በተካሄደው አሰሳ አንዲት አራስን ጨምሮ 13 የከተማዋ ነዋሪዎች የታሰሩ ሲሆን፣ ከአርባ ምንጭ ተወስደው አዲስ አበባ በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ ሉሉ መሰለ የ17 አመት ልጅም ከታሳሪዎቹ ውስጥ እንደሚገኝበትም የመጣው ዜና ያስረዳል።
በሳምንቱ መጨረሻ በነጭ ሳር ፓርክ አካባቢ ከፌዴራል ፖሊስ ሃይል ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት ታጣቂዎች ከየት የመጡና ዓላማቸው ምን እንደሆነ በግልፅ የተገለፀ ነገር ባይኖርም፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የአርበኞች ግንቦት 7 ናቸው እየተባሉ እንደሚጠቀሱም ተመልክቷል።

Saturday, May 7, 2016

ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንደገለጹት፣ ስዊድን እንደ ኖርዌይ ሁሉ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ያለገኙትን ከሰኔ ወር መግቢያ ጀምሮ ለማስወጣት ማቀዷን የኢትዮጵያን የስደተኞች ሊቀመንበር አቶ ኤፍሬም አክሊሉ ተናግረዋል።
ከአገር ተገፍቶ የወጣው ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ወረቀት ሳያገኝ፣ መንግስት ሁሉንም ሰነዶች አዘግጅቶ የሚልክላቸው እኛን ለመሰለል ሲመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በቀላሉ እንደሚያገኙ ተናግረዋል። ይህንን ለመቃወም በነገው እለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልጸዋል።

ሰበር ዜና . . በሰሜኑ ሱዳንና በወያኔ መከላከያ ሰራዊት የተደረገዉ አሰሳ አደጋ እንደገጠመዉ ጎነደር ከቋራ አካባቢ የደረሰን መረጃ ጠቁሟል።


የወያኔ ባለስልጣናቱ ሽፍታ ያሉት የጎንደር ጀግናና አርበኛ መሽጎበታል የተባለዉን ከቋራ ባሻገር የሚገኝ ስፍራ ለማሰስ ከሱዳንና ከኢትዮጵያ አቅጣጫ የተንቀሳቀሰ አሳሽ ቡድን አርበኞች አሉበት የተባለዉ ስፍራ ሲደርሱ ምንም በማጣታቸዉ ፊት ተለፊት ተገናኝተዉ ተስፋቸዉ በተመናመነበት ወቅት ድንገተኛ የመትረየስ ጥቃት ከየአቅጣጫዉ በመሰንዘሩ እርስ በእርስ እስከ መሞሻለቅ እንደደረሱ ምንጮች ከመካላከያ አሳዉቀዋል።
ከ15 ቀናት በፊት ይህን ሁኔታ ለመበቀል በንፋስ ገበያ በኩል የገቡ የሰሜን ሱዳን ወታደሮች አራት ገበሬዎችን ጠልፈዉ የወሰዱ ቢሆንም ገበሬዉ ከየአቅጣጫዉ በመነጋገር በመተናነቁ ተመልሰዉ ወደ መጡበት ፈርጥጠዋል።
የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን የጎንደርን ገበሬ ለማሸማቀቅ እና ለማስፈራራት ከባድ መሳሪያ የጫኑ ካሚዮኖች በየመንደሩ በማንቀሳቀስ ላይ ሲገኝ አፈናዉና ድንገተኛ የቤት ለቤት አሰሳዉ ቀጥሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
 

Etiopiska flyktingar i Sverige


Fredag den 6 maj kl. 13:00.
Etiopiska flyktingar i Sverige som flydde från diktaturen i Etiopien demonstrerade framför Migrationsverket i Solna. Synd att det är klämdag och ingen myndighetspersoner kom ut för att ta emot deras skrivelse och klagomål.








Thursday, May 5, 2016

ኢትዮጵያዊያንን በግፍ የገደለው አይሲስ ሶማሊያ ውስጥ አየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይፋ ሆነ


የዛሬ አንድ አመት በሊቢያ በርሃ እና የባህር ዳርቻው ላይ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻቸንን የኢ/ኦ /ተ/ ቤ/ክ እምነታቸውን እንዲ ቀየሩ አሊያም ሞት እንደሚ ጠብቃቸው ዛቻ ቢደርባሳቸውም “ ሃይማኖታችንን በጭራሽ እንቀይረም ” በማለታቸው “ አንገታቸውን ለአክራሪው ቡድን ሰይፍ ፣ ግንባራቸውን ደግሞ ያለ ፍርሃት ለጥይት በመሰጠት እጀግ ዘገናኝ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በማህበራዊ መገናናዎች መሰራጨቱን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኖች ከዳር እሰከዳር በተለይ ደግሞ የሟቾቹ ቤተሰቦች ልባቸውን የሰበረው ያ የክፈለ ዘመናቸን የሰማእትነት ጽዋን እንዲከፈሉ ያድረጋቸው እራሱን የእስላማዊ መንግስት (Islamic State) በማለት የሚጠራው ፣ነገር ግን ፍጹም ሃይማኖታዊ እና ሰብ አዊ አስተምሮት የማይከተለው ቡድን የመሰፋፋት አድማሱን በመቀጠል ሰላም እና መረጋጋት በራቃት በጎረቤታቸን በሶማሊያ ውስጥ የእኩይ ተግባሩን እንቅስቃሲ መጀመሩን የሚያሳይ መረጃ ሰሞኑን ይፋ ሆኗል ።
ዋርካድ የተባለውን ድህረ ገጽ ዋቢ ያድረገው የ ቻይናው የሲሲቲቪ የአፍሪካ ፕሮግራም ሰሞኑን ከሞቃደሾ/ሶማሊያ እንደዘገበው ምንም እንኳን የአገሪቱ /የማሊያ መንግስት ማረጋገጫ ባይሰጥበትም የአሲስ የመጀመሪያ በሆነው የፕሮፓጋንዳ የምስል መረጃው ላይ ቀደም ሲል የ ሶማሊያው የአልሸባብ አዋጊ/ኮማደር የነበረው እና ባለፈው አመት አይሲስን መቀላቀሉ በፑንትላንድ አካባቢ መኖሩ የሚነገረለት ሺክ አብዱቃድር ሙመን ለአይሲስ አባላት “እናንተ የተመረጣችሁ ናችሁ”የሚል የሙገሳ እና የእንኳን ደህና ምጣቸሁን አቀባበል ሲያድረግላቸው በምስሉ ላይ ያሳያል። ይህ መቼ ?እና የት ቦታ ?የሚለውን የጋዜጠኝነት መጠይቆችን ለጊዜው ያልመለሰው የ አይሲስ የፕሮፓጋንዳ መረጃ በሶማሊያ ባለሰልጣናት እይታ “ሁሉንም አሸባሪዎችን እናወቃቸዋለን ፣እንጨፈልቃቸዋለን ” የሚል ምላሽ ቢኖርም በርካታ የመቋደሾ ነዋሪዎችም በተለይ ወጣቱ ክፍል ልብ ለማማለል እና ወደ ሽብር ተግባር እንዲ ገቡ ለማድረግ የተወጠነ ተራ ፕሮፓንጋንዳ ነው”የሚል ትርጓሚ ቢኖረውም ይህ ስድስት ደቂቃዎች የማይበልጠው ቪዲዮ ለአካባቢው እና ለተጎራባች አገራት ሰጋት መፈጠሩ አይቀሬ ነው ሲል ሲሲቲቪ ከመቋደሾ ዘግቧል ።
በመካከለኛው ምስራው እና በሰሜን አፍሪካ /ሊቢያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሃይማኖት የለሹ የአይሲስ ቡድን በተመሳሳይ ወር እዚያው ሊቢያ ውስጥ 21 የግብጽ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በግፍ ማራዱን ተከትሎ ካይሮ በ አሸባሪው ቡደን ላይ ተከታታይ የአየር ላይ ድብደባ መፈጸሟ አይዘነጋም። በርካታ ኢትዮጵያዊያን በወቅቱ ምሬታቸውን እና ቁጭታቸውን በአገራቸው ውስጥ ወደ አደባባይ ወጥተው ለመግለጽ እንኳን የደረሰባቸው ወከባ ፣ግፍ እና መከራ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።
አይሲስ በሶማሊያ ውስጥ በሚገኙት የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ጦር ሃይል ላይ ሰሞኑን ጥቃት መፈጸሙን ቢናገረም የሰላም አሰከባሪው ባለሰልጣናት ግን ዘገባውን ያሰተባብላሉ። በጎርቤት ሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አፍቃሪ አልቅይዳ እንደሆነ የሚነገርለት የሶማሊያው አልሽባብ ም ቢሆን ከሰላም አስከባሪው ጦር የሚደርሰብት ብርቱ ጥቃትን መቁቋም ባለመቻሉ ከ ገጠራማዎች ቀበሌዎች ይልቅ ብዙ ህዝብ በሚኖርበት የመቁደሾ ከተማ እና በሰላም አስከባሪው የጦር ሰፈሮች ላይ የጥቃት ሙከራ ለማድረግ መሰናዳቱን መረጃዎች ይገልጻሉ። ከኢትዮጵያ ጨምሮ ወደ 22 ሺህ የሚጠጉ የሰላም አሰከባሪ ሃይል የሰፈረባት ሶማሊያ ሰላሟ እና ደህነነቷ የተነጠላጠለው በእነዙሁ የጎረቤ ት እና ባእዳን ሃይሎች ላይ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።
ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ ዜና በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ውስጥ እየተሰፋፋ የመጣው ሰወዲ አርቢያ ሰራሽ ( በሺክ በእብዱል ዋሃብ ትምህርት እና በስወዲ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች አማካኝነት ) አንደተቋቋ መ የሚነገርለት የ ወሃቢዘም አደገኛ አቅጣጫ እንዳለው በጉዳዩ ዙሪያ ሰፊ ጥናት ያድረጉት በቀድሞው መንግስት በእርዳታ ማስተባበሪያ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ (ኮሚሽነር የነበሩት ) ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ አሰጠነቀቁ ።”የወሃቢዝም በአፍሪካ የወረራ አቅጣጫ” (The Wehabi Invasion of Africa) የሚል ሰፊ ጥናት ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ማድረጋቸውን ለአሜሪካ ራዲዮ የአማሪኛ ው ከፍል ባለፈው ቅዳሜ የገለጹት ሻለቃ ዳዊት ሺያት፣ ሱኒያ የሚባሉት የ እልምና አመለካከቶች ከነብዩ መሃመድ መሞት በኋላ ተከታትለው የመጡ አንጋፋ እስተምረቶች መሆናቸውን እና የሙስሊሙ ማህበረሰብም ሊከተላቸው እንደሚገባ ጠቀሰው ፣በተቃራኒው ደግሞ የሙስሊም ወንድማማቾች Muslims Brothers Hoods)፣ሳላፊስት እና ወሃቢዛም የዘመናቸን እና የተለየ የአስተምሮት ወጤቶች መሆናቸውን ስይገልጹ አላለፉም ። አነዚህ ዘመን አመጣሻ አስተምረቶች በአብዛኛው ፖሊቲካ ዘመም መሆናቸውን ያወሱት ሻለቃ ዳዊት ለአክራሪዎቹ የእምነት አራማጆች አልቃይዳ፣ አይሲስ መሰረቾቹ ዋሃቢዝም እንደሆነ እስምረውበታል።
የሰውዲ አረቢያ የዋሂብዝም ፍልስፍና በኢትዮጵያ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሰፋፋቱን የጠቀሱት ሻለቃ ዳዊት የወቅቱ የአገሪቱ ገዢ መንግስት(ኢህ አዲግ) በማንኛውም ሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት የገለጹ ሲሆን ፣ይሁን እንጂ “ምናልባት አንድ የውጪ አገር በፖለቲካው ውስጥ ተጽእኖውን ለማሰረጸ ጥረት ካደረገ የመንግስት ጣልቃ ገብነት አሰፈላጊ ሊሆን ይችላል። ከዚያ ወጪ ግን ሙስሊሞች እንደ ሌሎቹ የእምነት ተከታዩች ያለ መንግስት ጥልቃ ገብነት ፣በነጻ ሊንቀሳቀሱ ፣ ያሽቸውንም ሊመርጡ ይገባል ” በማለት የግል አቋማቸውን ገልጸዋል ። በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ከሚባሉት የእምነት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የእሰልምና ሃይማኖት ተከታዮችን “ማንም ወገን ቢመጣ ሊያስተምራቸው አይችልም” ያሉት የደርግ ስር አትን እና ሰላጣናቸውን ጥለው ወደ አሜሪካ የተሰደዱት ሻለቃ ዳዊት “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከነቢዩ መሃመድ ጀምሮ ሲወረድ ሲዋረድ የመጣውን ሃይማኖታቸውን ላለፈው አንድ ሺህ አመት በላይ በሚገባ አጣጥመው የተማሩ በመሆናቸው ምንም አይነት አዲስ አስተምሮት እና ጫና አያሻቸውም፣እንግዳ ነገር ሲመጣ ሙስሊሞች እራሳቸው ለታገሉ ይገባል እንጂ መንግስት ጣልቃ ሊገባ አይገባውም” በማለት ምክራቸውንም ለግሰዋል ። የዋሂብዝም ተከታዮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሰለመኖራቸው ምን ማስረጃ አለ?” ለሚለው የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዋ ጥያቄ ሻለቃ ዳዊት ሲመልሱ “ ኢትዮጵያ ውስጥ በአይኔ ያየሁት ነገር ባይኖረም ከኢትዮጵያ ወደ ፓኪስታን /ማዳራስ እንዲሁም ወደ ሱዳን እና ወደ ሌሎች አገራት ለአስተምሮቱ በመጓዝ ጥናታቸውን ሲጨርሱ ወደ ኢትትዮጵያ ለመመለስ የሚፈልጉ መኖራቸውን ሲናገሩ ሰምቻለሁ “ብለዋል።ታዲያ ችግሮችን ለማቅለል ሲባል ምን መደረግ አለበት ይላሉ ? ለሚለው ተከታይ ጥያቄ”ሁል ጊዜ ውይይት እና መመካከር ቁልፉ ሚና ይጫውታል”ብለዋል።

በቬጋስ የትግራይ ተወላጆች ብቻ የተሰብሰቡበት ስብሰባ ተበጠበጠ።


ከቬጋስ አሁን የደረሰኝ መልእክት
ሰሞኑን የብአዴንና የአማራ ክልል ባለስልጣናት በአሜሪካና አውሮፖ ተሰማርተዋል። የትግራይ ተወላጆች የሚበዙባቸውን ስለአማራው ክልል የሚመክሩባቸው ስብሰባቸውን እያደረጉ ነው። በአብዛኛው በተቃውሞ ከሽፈዋል። ስለአማራው ትግራዩ ቢመለከተው አይገርምም። አማራዎች እንዳይሳተፉ መደረጉ ግን ግራ የሚያጋባ ነው።
ቬጋስ በዚህን ሰዓት ተመሳሳይ ስብሰባ ተጠርቶ እየተካሄደ ነው። የቬጋሱ የሚለየው በስብሰባው የተገኙት በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ሰብሳቢዎቹ የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣንና የአማራ ልማት ማህበር ሊቀመንበር ናቸው። ሌሎች እንዳይገቡ በር ላይ የተከለከለ ነው። በዚህም ግጭት ተፈጥሮ የቬጋስ ፖሊስ ደርሶ በአስለቃሽ ጢስ ለመበተን እየሞከረ ነው። አሁንም ፍጥጫው እንዳለ ነው

Wednesday, May 4, 2016

ሰበር መረጃ ወያኔ በሀገ ወጥ ሰዉ ዝዉዉር ሰንሰለት ዉስጥ !

የኢኳዶር ፖሊስ ( Ecuadorean police ) የኮሎምቢያ የጸረ አጋች ቡድን ወይም ኽዉላ ( Colombia’s elite anti-kidnapping squad, known as GAULA ) የአሜሪካዉ ሆም ላንድ ሴኪዉሪቲ ( us Home land security ) የብራዚል የህገ ወጥ ሰዉ ዝውውር ቁጥጥር ፖሊስ ( Brazilian migration police ) እና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ፖሊስ መረጃዎች እንዲሁም አለማቀፍ ፖሊስ ( Interpol ) በመተባበር የህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉርን ለማኮላሸት በጋራ መስራት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል!
እነዚህ መጠነ ሰፊ አሰሳ ላይ የሚገኙት ሐይሎችን ሆም ላንድ ሴኪዉሪቲ በበላይነት ሲመራቸዉ ከእነዚህ የትብብር ሀይሎች የወጡ መረጃዎች ጣታቸዉን ወደ ሐገራችን ኢትዮጵያ ቀስረዋል አዎ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሐገራት ባለስልጣናት፣ ኢሚግሬሽን እና ቦርደር ፖሊሶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እጃቸዉ በህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር ዉስጥ አሉበት ኢየተባለ ይገኛል።
ኢላይ ዳዊት ታደሰ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በ ( 05 May 2011 ) ኢኳዶር ላይ በእነዚህ ሐይሎች ቁጥጥር ስር ዉሏል ዳዊት ታደሰ አብዛኛዉን ንብረቱን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያስቀምጥና ከኢትዮጵያ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሐገራት ብዛት ያልቸዉ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ አሸጋግሯል ዳዊት 66 የሚጠጉ አጋሮቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የሆሳማ ቢን ላዲን ቀኝ እጅ የሆኑ ባልደረቦችም አብረዉት ተይዘዋል ዳዊትና ግብረ አባሮቹ ( 12 March 2011 ) ለሐያሏ አሜሪካ ተላልፈዉ ተሰጥቷል።
ሰብለ አማረ ትዉልደ ኢትይዮጵያዊ ስትሆን በኮሎምቢያና በብራዚል መካከል ሀገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር በማካሄድ ወንጀል በ 2014 በቁጥጥር ስር ዉላ በህግ ክትትል ላይ ትገኛለች በኮሎምቢያ በጥገኝነት የምትኖረዉ ሰብለ ኢትዮጵያዊ ስትሆን በህገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽኖች ጋር በመተባበር ሰዉ እንደምታሻግር እንዱሁም ከቦርደር ፖሊሶች ጋር አብራ እንደምትሰራ መረጃዉ ያመላከተ ሲሆን በሆምላንድ ሴኪዉሪቲ ክትትል ስር ትገኛለች።
ሳራ ሳህሌ በትዉልድ ኢትዮጵያዊ ስትሆን በ 2015 በኮሎምቢያ በህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዛ በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለሳልጣናት ጋር ትብብር እንዳላት መረጃዎች አመላክተዋል።
ሰለሞን . . በ 2013 በብራዚል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የተያዘበት ወንጀል ህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር ሲሆን ኢትዮጵያ ከሚገኙ ኢሚግሬሽን እና ቦርደር ፖሊሶች ጋር የተበቀ ግንኙነት እንዳለዉ መረጃዎች ሲያመላክቱ፡፤
በተያያዘ ሁኔታ ወደ እሩቅ ምስራቅ ሐገራት የሚደረጉ ተመሳሳይ ወንጀሎች በወያኔያዊያን የህግ ጥላ ተሰጥቷቸዉ ወንጀሉን በበላይነት የሚፈጽሙ አካላት ላይም ከፍተኛ ጥናት እየተደረገባቸዉ ይገኛሉ።
ባጠቃላይ ከአፍሪካ ከ18 በላይ ግለሰቦች በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ህጋዊ ማረጋገጫ እየተፈለገባቸዉ ሲሆን አብዛኞቹ ከትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን ጋር ትስስር እንዳላቸዉ ምንጮች ጠቁመዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያነ
Gudish Weyane's photo.